ቀሬ አላምረው ቢሻው Kerie Alamrew Beshaw

ቀሬ አላምረው ቢሻው Kerie Alamrew Beshaw Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቀሬ አላምረው ቢሻው Kerie Alamrew Beshaw, Landmark & historical place, Arat Mekeraker/Four Mountain/, Amanu'el.

በመላው ዓለም የምትኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቼ፡-እንኳን ለቡኄ/ደብረታቦር/ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!! መልካም በዓል !!!13/12/2012 ዓ.ም
19/08/2020

በመላው ዓለም የምትኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቼ፡-እንኳን ለቡኄ/ደብረታቦር/ በዓል በሰላም አደረሰን፤ አደረሳችሁ !!! መልካም በዓል !!!
13/12/2012 ዓ.ም

እንኳንም ተወለዳችሁልኝ !
18/08/2020

እንኳንም ተወለዳችሁልኝ !

Kerie Alamirewየአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ National Movement of Amharaከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የተሰጠ መግለጫ፤*****የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ብሔራዊ ሥራ አ...
18/08/2020

Kerie Alamirew
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ National Movement of Amhara
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የተሰጠ መግለጫ፤
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከነሐሴ 9-11
ቀን 2012 ዓ.ም ለሦስት ቀናት የቆየ አመታዊ 4ኛ ዙር መደበኛ ስብሰባዉን
በአዲስ አበባ ከተማ በድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት አካሂዶ አጠናቋል፡፡
ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴዉ በፓርቲዉ ዉስጥ ባሉት የአመራር እና የመዋቅር
ጉዳዮች ዙሪያ የተወያየ ሲሆን በወቅታዊ የሀገራችን ሁኔታዎችና በሕዝባችን ላይ
እየተፈጸሙ ባሉ ዘር እና እምነት ተኮር ጥቃቶች እንዲሁም ባንዣበቡ አደጋዎች
ዙሪያ ሰፊ ዉይይቶችን አድርጎ በቀጣይ መደረግ ያለባቸዉን ጥናቶች ብሎም
ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች በመለየት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
በአጠቃላይ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ለዉይይት ተቀርጸዉ በነበሩ መሠረታዊ
አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ዉይይት አድርጓል፡፡
በአጀንዳነት ተመዝግበዉና ዉይይት ተደርጎባቸዉ ዉሳኔ ከተሰጠባቸዉ ጉዳዮች
መካከል ድርጅታችን ከምስረታው ጀምሮ አጽንኦት ሰጥቶ ከሚታገልላቸዉ እና
በፖለቲካ ፕሮግራሙ ዉስጥ በግልጽ ከሰፈሩ መሠረታዊ አጀንዳዎች አንዱ
የሆነዉን በሴራ የተቃኘ እና ጊዜያዊ የኃይል ብልጫ አግኝቻሁ በሚል ከአማራ
ሕዝብ በመንጠቅና በመነጠል በተለያዩ ክልሎች እንዲካተቱ የተደረጉትን
በማንነት፤ በሥነልቦና እና በታሪክ (የ)አማራ አካል የሆኑትን ሕዝቦች እና
አካባቢዎች ከሚመስላቸዉ እና አብረዉ መሆን ከሚፈልጉት የአማራ ሕዝብ ጋር
ተቀላቅለዉ በአንድ ክልላዊ አስተዳደር ስር መሆን አለባቸዉ የሚለዉ ነዉ።
የሽብር ቡድን ሆኖ ተመስርቶ እና የሽብር መንግስት ሆኖ አሳልፎ በመጨረሻ
ወደነበረበት አርከን ተገፍቶ የወረደዉ የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር
(ትሕነግ) በታሪክ ክፍተት አልፎ ሀገራዊ ስልጣን መቆጣጠር መቻሉን ተከትሎ
ካነገባቸዉ ዓላማዎቹ እና ከማደረጃ መርኾዎቹ መካከል አንዱ የአማራን ሕዝብ
ዘላቂ የሆነ የማኅበራዊ እረፍት መንሳት ነዉ፡፡ የዚህ እኩይ ዓላማ አካል አድርጎ
ተፈጻሚ ያደረገዉ የአማራን ሕዝብ እና አካባቢዎች ወደ ተለያዩ ክልሎች ማካለል
ሲሆን ከእነዚህ መካከል የወልቃይት፤ የፀገዴ፤ የፀለምት እና የራያ አማራ ሕዝቦች
ተጠቃሽ ናቸዉ።
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ግንባር (ትሕነግ) የማዕከላዊውን መንግስት
ስልጣን ከተቆጣጠረ ጀምሮ በመላው ኢትዮጵያ በሚኖረው የአማራ ሕዝብ ላይ
የተቀነባበሩ የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት እና ማንነትን መሰረት ያደረጉ የተለያዩ
ጥቃቶችን ሲፈጽም እና ሲያስፈጽም ቆይቷል፡፡ በተለይም ትሕነግ በቀጥታ
በሚያስተዳድረዉ የትግራይ ክልል ስር በጉልበት ባካለላቸው አካባቢዎች
የሚኖሩ አማራዎች ላይ እስከአሁን ድረስ የዘለቁ ዘግናኝ ግፎችን ሲፈጽም
ቆይቷል።
የአማራ ሕዝብ ከባድ መስዋዕትነትን በመክፈል ባደረገዉ ትጋድሎ በትሕነግ
ይመራ የነበረዉን የማእከላዊ መንግስት አገዛዝ እስትንፋሱን በማቋረጥ አማራ
ጠል ራዕዩን ከትቦ ወደተነሳት ሰፈር አሽቀንጥሮ መልሶታል፡፡ በዚህ ረገድ
በመላው ሀገራችን ዉስጥ በተለይም በአማራ ሕዝብ በኩል ሲደረግ የነበረዉን
የእኩልነት እና የነጻነት ትግል ወደ ልዩ የከፍታ ምእራፍ በማሸጋገር የትሕነግን
አገዛዝ ወደ መቃብር ለማውረድ ወሳኝ ድርሻ ያበረከተዉና በኃይል በተካተቱት
አካባቢዎች ያሉ አማራዎችን መብቶች ለማስከበር እና የማንነት ጥያቄዎችን
ለማስመለስ በግንባር ቀደምነት የተሰለፉ የአማራ ልጀች የፈጸሙት የአርበኝነት
ተጋድሎ መሆኑን ግራቀኙ የማይስተው ሃቅ ነዉ፡፡
ሆኖም የአማራ ሕዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያዉያን ወገኖቹ ጋር በትብብር ባደረገዉ
ተጋድሎ ግፈኛውን፣ ከፋፋዩን እና ዘረኛውን የትሕነግ አገዛዝ ከማዕከላዊ
መንግስት መንበር አሽቀንጥሮ መጣል እና ማባረር ቢችልም ወደ ትግራይ
በኃይል የተካለሉት አሁንም በትሕነግ አገዛዝ በከፍተኛ ጭቆና ስር የሚገኙት
የአማራ ሕዝብ ነጻ ያልወጣበት እንቆቅልሽ የግድ መፈታት አለበት፡፡ የትሕነግን
የጭቆና ስርዓት በመቋቋም እየተፈጸሙ ያሉትን ዘር-ተኮር ጥቃቶች ቀሪ
ለማድረግ በሚል መሪ ምክንያት የመጣዉ አንጻራዊ ሀገራዊ ለዉጥ እና ተከትሎ
የተመሰረተዉ “የለዉጥ ስርአት" ለወልቃይት፤ ለፀገዴ፤ ለፀለምት እና ለራያ
የአማራ ሕዝብ እስካሁን አንዳች የተሻለ ነገር ማበርከት አልቻለም። ይባስ
ብሎም በሀገር ደረጃ ተንሰራፍቶ የነበረዉ የትሕነግ የጭቆና ስርዓት ከማዕከል
ተገፍቶ የሄደዉን ኃይሉን ጭምር በአንድ ቀጣና እንዲያሰባስብ መፈቀዱ በተለይ
በአካባቢዎቹ የአማራ ወገኖቻችን ላይ የሚፈጸመዉ ግፉ እና ጭቆና እንዲበረታ
አድርጓል፡፡
በሀገራችን በተከሰተው የሳንባ ቆልፍ (COVID-19) ወረርሽኝ ምክንያት
ክልላዊና ሀገር አቀፉ ምርጫ እንዲሸጋገር የተወሰነ ቢሆንም ትሕነግ ራሱ ቀርጾ
ስራ ላይ ያዋለዉን "ሕገ-መንግስት" በግልጽ በሚጥስ መልኩ በትግራይ ክልል
ምርጫ ለማድረግ ወስኖ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ውስጥ መግባቱ ይታወቃል።
አብን ትሕነግ የቀረጸዉን ሕገ-መንግስት በተመለከተ ያለዉ አቋም ግልጽ እና
ያደረ ነዉ፡፡ በርግጥ በትሕነግ ዘመን በተለይ መብቶችን በሚመለከት ያሉት
የሕገ-መንግስቱ ድንጋጌዎች ባለማከበር ሲከበሩ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ትሕነግ
ለማድረግ ያወሰነዉን ምርጫ በሕገ-መንግስቱ የሚደገፍ ለማስመሰል የሄደበት
ርቀት እና ፍጹም ለማያዉቀዉ የቅቡል ምርጫ ጉዳይ ጠበቃ ሆኖ መቅረቡ ራሱን
ብቸኛ የሕግ ትርጉም እና የፍትኅ ምንጭ አድርጎ ከመዉሰድ ባኅሉ የተቀዳ ሲሆን
ድርጅቱ ከእዉቀት፣ ከሞራል እና ከሕግ በቋሚነት የተፋታ ስለመሆኑ ዓብይ ማሳያ
ነዉ፡፡
በትሕነግ በኩል ያለዉ የምርጫ አካሂዳለሁ ዉሳኔ በወቅታዊ እና ተጨባጭ
የሀገራችን ሁኔታዎች ክህደት ላይ የተመሰረተ፣ አጠቃላይ ግጭት ለመጥራት እና
ሀገራችንን ለማፍረስ ያለመ፤ የፌዴራሊዝምን ጽንሰ-ኃሳብ ገሸሽ በማድረግ
የተቃኘ እና ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ሲሆን ከመነሻ እሳቤዉ ጭምር ፉርሽ(Void)
ነዉ::
ትሕነግ ምርጫውን ለማከናወን መወሰኑን ተከትሎ ከመቸውም ጊዜ በላይ
በወልቃይት እና አካባቢዎቹ እንዲሁም በራያ ሕዝብ ላይ ጥቃት እና ጭቆናውን
አጠናክሮ በመቀጠል ሕዝቡን ለጅምላ እስር፣ መፈናቀል እና ስደት እየዳረገ
ይገኛል። ሕዝቡ ትሕነግ ሊያከናወን ባቀደው የይምሰል ምርጫ ላለመሳተፍ
ቢወስኑም የአካባቢዎቹን የአማራ ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በዘላቂነት ለመድፈቅ
እንደ ምቹ አጋጣሚ በመቁጠር ምርጫውን በኃይል ለማስፈጸም እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም፦
1. ይህ የትሕነግ እሳቤ፣ ተያያዥ እንቅስቃሴዎች እና በልዩ ሁኔታ የአማራ
ማንነትን መሰረት አድርጎ እየፈጸማቸዉ ያሉ ዘርፈብዙ ጥቃቶች ለድርጅታችን
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) እና ለመላው የአማራ ሕዝብ እጅግ አሳሳቢ
ሆነዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የአማራ
ሕዝብ፤ ለሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን፣ ለአማራ ብሔራዊ ክልል መንግስት እና
ለፌዴራል መንግስቱ ሕዝቡ እያደረገ ካለው ትግል ጎን በመቆም ድጋፋቸዉን
እንዲሰጡ፤ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስትና የአማራ ሕዝብ ትሕነግ
በየዕለቱ የሚፈጽመቻዉን የፀብ አጫሪነት ድርጊቶ እና ትንኮሳ በመመከት
አካባቢዉን በንቃት እንዲጠብቁ፡፡
2. በትሕነግ ጥቃትና አፈና ምክንያት ከቀያቸዉ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችንም የክልሉ
መንግሰትና ሕዝብ ተገቢዉን ድጋፍ እንዲያደርጉ፤
3. የአማራ ሕዝብ ያሉትን የድንበር እና ወሰን ጉዳዮች በተለይም የወልቃይት እና
የራያ ሕዝብ የማንነት ጥያቄዎች በሕግ አግባብ መፍትኄ እስኪያገኙ ድረስ
የማንነት ጥያቄዎቹ ቀርበዉለት ጉዳዮቹን በይደር የያዘው የፌዴሬሽን ምክር ቤት
የእግድ ትዕዛዝ/Injunction/ እንዲሰጥ፤
4. በሕገ-መንግቱ አንቀጽ 13(1)፤ 55 (16)፤ 62(9) ድጋጌዎች እንዲሁም
በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 77(10) እና 93 ድንጋጌዎች መሰረት የፌዴራሉ
መንግስት፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት
በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለዉን ዘግናኝ እና መጠነሰፊ የሰብዓዊ መብቶች
ጥሰት የማስቆም ኃላፊነታቸዉን እንዲወጡ እና ትሕነግ ሕገ-መንግሥታዊ
ሥርዓቱን አደጋ ላይ ለመጣል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ወደከፋ እና ተመልሶ
ሊካካስ ወደማይችል ደረጃ ከመድረሱ በፊት በአፋጣኝ እንዲያስቆሙ ጥሪያችንን
እስተላልፋለን፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ አማራዎችን በሚመለከት ቀደም ሲል
ባወጣነዉ መግለጫ የጠየቅናቸዉ ጥያቄዎች እንደተጠበቁ ሆነዉ ከጥቃቱ
በሕይወት የተረፉ ወገኖቻችን አሁንም በከፍተኛ ችግር ዉስጥ መሆናቸዉ
ይታወቃል፡፡ ስለዚህ እነዚህ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም አስፈላጊዉን ድጋፍ
እንዲያደርግ በድጋሚ እየጠየቅን አሁንም ንጹሀንን በመያዥያነት የሚጠቀሙ
ጽንፈኛ የጥላቻ ኃይል በቀጣይ ጥቃቶችን ለመፈጸም ፍላጎት እንዳላቸዉ እና
እንደሚዘጋጁ በመገንዘብ በመንግስት በኩል አስተማማኝ የሆነ የደኅንነት ጥበቃ
እና የሕግ የበላይነት የማስፈን ተግባራት እንዲያከናዉን የአማራ ብሔራዊ
ንቅናቄ(አብን) ይጠይቃል፡፡
በሌላ በኩል በአብን በ2012 ዓ.ም 4ኛ ዙር የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ
ስብሰባ ወቅት የተወሰኑ ዉሳኔዎችን አፈጻጸም እንደዚሁም የስራ ክንዉኖችን
በተመለከተ በአዎንታዊነት የገመገመ ሲሆን ከተደረገዉ የድርጅቱ ሪፎርም አንፃር
የፓርቲዉን አደረጃጀት እስከ ታችኛዉ እርከን ድረስ የማደራጀት ስራ ተጠናክሮ
እንዲቀጥል አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብሰባዉን አጠናቋል፡፡
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!
ነሐሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም
አዲስ አበባ፥ ሸዋ፥ ኢትዮጵያ

Zemedkun Bekeleዓድዋ - የሚኒልክ እጅ ሥራ።[ በ Isho Berhan ]*~★★~*• NB~ “ ሊነስራችሁ ስለሚችል የእንቁላል ቀቃይ የመንገድ መሪ የባንዳ የልጅልጆችና የዐረብ ቅጥረኞች...
18/08/2020

Zemedkun Bekele
ዓድዋ - የሚኒልክ እጅ ሥራ።
[ በ Isho Berhan ]
*~★★~*
• NB~ “ ሊነስራችሁ ስለሚችል የእንቁላል ቀቃይ የመንገድ መሪ የባንዳ የልጅ
ልጆችና የዐረብ ቅጥረኞች ይህን ጦማር ባታነቡት ይመከራል።” ይኸው ነው።
# ETHIOPIA | ~ የባንዳ የልጅ ልጆችንና የፀረ ኢትዮጵያ አረብ ናፋቂ
ዲቃላዎችን ጫጫታ ታግሳችሁ ይህቺን ጦማር በጥሞና አንብቧት።
ትጠቀማላችሁ።
•••
ሚኒልክን ልትጠላው ትችላለህ፤ ደግሞም ልትወደው ትችላለህ። ነገር ግን
ሚኒልክ ተራ ስብዕና እንዳልነበረ ለመረዳት አይከብድም። ሚኒልክ ውስብስብ
ሰው ነው። ረቂቅ ነው። ደግሞ አድማጭ ነው። ሚኒልክ እንደ ገሞራ እሳት
የሚፋጅ ነው። ደግሞ እንደ ምንጭ ውኃ ገር ነው። ሚኒልክ ሀገር መመስረት፣
ግዛት ማስተዳደር ያውቃል። ተራ የታሪክ ሰው አይደለም። ጉልህ ነው።
የሚኒልክን ነገር ለማጉላት ብዬ ከሌሎች ማወዳደር አልፈልግም። ዳግሞም
ማሳነስ ሊሆን ይችላል።
•••
የውጫሌ ውል የዓድዋ ጦርነት መነሻ ነው ይላሉ። ፈፅሞ ስህተት ነው። የዓድዋ
ጦርነት መነሻ የበርሊን የቅኝ ገዢዎች ውል ነው። አውሮጳ አፍሪካን ለመቀራመት
የተስማማው በበርሊን ስምምነት ነው። ያን ለማስፈፀም አውሮጳውያን በውድም፣
በውልም፣ በግድም አድርገውታል። በውል ወደ ቅኝ ግዛት የገቡ ብዙ ናቸው።
•••
ጣሊያን ለሚኒልክ የውጫሌን ውል ስታቀርብለት፣ ሚኒልክ ሳይገባው ቀርቶ፣
ተሸውዶ፣ ወይ ገር ሆኖ ነው ማለት ደካማ የታሪክ ተማሪ ከመሆን የመጣ ነው።
የውጫሌ ውል የተፈረመው አፄ ዮሐንስ በሞቱ በ 10 ቀናት ውስጥ ነው።
የዓድዋ ጦርነት የተካሄደው አፄ ዮሐንስ ከሞቱ ከ 5 ዓመት በኋላ ነው።
•••
ሚኒልክ የውጫሌን ውል በመፈረም የራሱን ጉልበት እስኪያጠናክር ግዜ መግዣ
ነው ያደረገው። ሚኒልክ ከፍ ለማለት ዝቅ ማለትን ያውቃል። እንደ ጣይቱ
የሚፋጅ እሳት፣ እንደ ልብ ወዳጁ ራስ መኮንን የረጋ ውኃ ብቻ ቢሆን፣ ሀገርም
አይሠራም፣ መንግሥቱንም አያፀናም ነበር።
•••
ውጫሌ በተፈረመበት ወቅት ሚኒልክ፣ ብዙ ጠላቶች ነበሩት። ተጨማሪ ጠላት
ጣሊያንን ማድረግ ስላልወደደ የፈረመው ነው። የውጫሌ ውል ኖረ አልኖረ፣
ጣሊያን ኢትዮጵያን መውረሯ እንደማይቀር የሚታወቀውማ የትግራይና የኤርትራን
መኳንንት ጥሩ አድርጋ ስትክድ በማየት ነው። ሚኒልክ ግን ጦርነቱን ቢያንስ እሱ
በመረጠ ግዜ እንዲሆን ማድረግ ችሏል።
•••
ሚኒልክ ሁሉን ያዳምጣል። በቅንም ይረዳል። ዓላማውን አይስትም። ብልሃተኛ
ነው። የአምባላጄ ጦርነት፣ የመቀሌን ከበባ በአሸናፊነት ሲያልፍ፣ በሚኒልክ
ውሳኔ የሚቆጡ ብዙ ነበሩ። ጣሊያኖችን ቢማርክም መልሶ እንደውም ከመጋዣ
(ፈረስና በቅሎ ) ጋር ላካቸው እያሉ የሚወቅሱት ነበሩ። ሚኒልክ ግን ጦርነት
የሚገጥምበትን ቦታ እየመረጠ ነበር። የእሱ መኳንንት የሚያውቁትን ሚኒልክ
ጠፍቶት አይደለም። ከባድ ስትራቴጂስት ስለነበረ ነው።
•••
ሚኒሊክ ያሰለፈውን ኃይል ያውቀዋል። ከቴዎድሮስ እስከ ራስ ውቤ፣ ወርቂትና
ተዋበች፣ እስከ ዮሐንስና ጎበና የነበሩ ጦርነቶችን፣ በአይኑ ያየና የሰለጠነም
ንጉሥ ነው። ጦርነት አዋቂ ነው።
•••
የቻይናው ታዋቂ የጦር ጀነራል - ሱን ሱ " ኃይል እንዳለህ ስታውቅ፣ ደካማ
ምሰል " ያለውን ሚኒልክ ፈፅሞታል። ጥሊያን ዓደዋ ላይ የዘላለም ውርደት
እስክትከናነብ፣ በዚህ የሚኒልክ ብልጠት ተሸውዳለች። ሚኒልክም ዓድዋ
እስኪደርስ ድረስ የሚፋጅ ነብር መሆኑን ደብቆ ቆይቷል።
•••
አምስት ወር የተደረገ ጉዞ፣ የስምንት ሰዓት አጭር ጦርነት የሆነው በዚህች
አስደናቂ የሚኒልክ ብልሃት ነው። ሚኒልክ ያደረጋቸዉ ነገሮች፣ የፈፀማቸው
ታሪኮች፣ የሰበሰባቸው ሸንጎዎች፣ የወሰናቸው ውሳኔዎች በእርግጠኝነት
የሚልክን ልህቀት የሚያገኑ ናቸው።
•••
ዓድዋ - በሚኒሊክ ተመርጦ፣ በሚኒልክ ታቅዶ፣ በሚኒልክ ተመርቶ፣ የተፈፀመ
ጀብዱ ነዉ። ለዚያም ነው ሚኒልክ የሀገር መሪ ብቻ ሳይሆን ሀገር መስራችም
ነው የሚባለው። ከዚህ መለስ ስላለው የታሪክ ፋይዳ፣ ውጤት፣ ጥቅምና ጉዳት
እንነጋገር እንጂ ሁነቱ ዳግም ላይመለስ፣ በሚኒልክ ተፈፅሟል። በማለት እጅ
የምታስቆረጥም ጦማሩን ጀባ ብሎናል። ቁርጥማት አይንካህ።
•••
ቤተ ዐማራ ፔጅ ደግሞ የአጼ ምኒልክን ይቅር የማያስብሉ ስህተቶችን ነቅሶ
ባማውጣት እንዲህ አድርጎ ይገልጸዋል።
1ኛ. ምኒልክ ከተከዜ ማዶ ሄደው ከጣልያን ጋር ጦርነት ማድረጋቸው፣
2ኛ. እርስ በርሱ በጎሳ ጦርነት ሲመዣረጥ የነበረውን የምሥራቅ፤ ደቡብ እና
ምዕራብ ጎሳ ሁሉ ጦርነቱን አስቁመው በአንድነት በሰላም እንዲኖር
ማድረጋቸው፣
3ኛ. ከጣልያን ጋር ቀጥታ ጦርነት፤ ከእንግሊዝና ከፈረንሳይ ጋር ደግሞ
የዲፕሎማሲ ጦርነት በማካሄድ ዛሬ እንደ ጠላት የተነሳባቸውን አፈር በታኝ ጎሳ
ሁሉ ከቅኝ ግዛት ማስጣላቸው፣
4ኛ. ቅኝ ቢገዛ ኖሮ ይጠፋ የነበረውን የየብሔረሰቡን ቋንቋ፤ ባህልና ማንነት
ጠብቀው ለትውልድ ማስተላለፋቸው፣
5ኛ. እርስ በእርስ በባርነት ሲሻሻጥ የነበረውን ብሔረሰብ ሁሉ እንዳይሻሻጥ
በአዋጅ ከልክለው እኩል ሰው ማድረጋቸው፣
6ኛ. የባርያ ንግድን በመንግሥት ደረጃ በዐዋጅ ማስቆማቸው
7ኛ. ሁሉም የፈለገውን እምነት እንዲከተል መፍቀዳቸው፣
8ኛ. በክፉ ቀን ጊዜ መኳንንቱ ሁሉ ለመንግሥት ግብር እንዳያገባ እና ለተራበው
ብቻ እንዲያበላ ማድረጋቸው፣
9ኛ. በጣም ርህሩህ እና አዛኝ መሆናቸው፣
10ኛ. ወደር የለሽ ጀግና መሆናቸው፣
11ኛ. የጥቁርን ዘር ሰው መሆኑን በጠብመንጃ ተፋልመው ነጭን አንበርክከው
ማሳመናቸው፣
12ኛ. ብልህ እና አስተዋይ መሆናቸው።
•••
በል እንግዲህ ይሄን ጦማር አንብበህ ስታበቃ ኢትዮጵያዊ ስም የሌለህ ባንዳ
የባንዳ ልጅ መጤ ወራሪና ሰፋሪ ሁላ፣ ሃይማኖት የሌለህ፣ የዐረብም የፋሽስትም
ዲቃላ ሁላ እንደልብህ ተንበጫበጭ።
ደስ የሚለው እኔ ሚንልካዊ ነኝ። እናንተስ?
•••
ሻሎም ! ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ነሐሴ 11/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

ጮቄ የጎጃም ምንጮች ጋን የወንዞች ሁሉ እናት እና አናት!==================================== # share ይደረግ!1. "ብርቅየነቱና ግርማ ሞገሱ ይማርካል፤ ብርዱ ግን ...
16/08/2020

ጮቄ የጎጃም ምንጮች ጋን የወንዞች ሁሉ እናት እና አናት!
====================================
# share ይደረግ!
1. "ብርቅየነቱና ግርማ ሞገሱ ይማርካል፤ ብርዱ ግን አይጣል ነው፡፡ ቅዝቃዜው
ከበጋ እስከ ክረምት አንድ በመሆኑ ደጋ መባል ያንሰዋል፡፡ በደቂቃዎች ልይነት
አንዳንዴ ደመናማ ቆየት ብሎም ብራ እየመሰለ የተፈጥሮ መቅበጥበጥ
በሚታይበት ይህ ተራራ አናት ላይ ወጥቶ አካባቢውን መቃኘት ልዩ ስሜትንና
መደነቅን ይፈጥራል። በተራራው ላይ ያለው በረዶው ብዙዎቻችን ከምናውቀው
ጠጣር በረዶ ይለያል፡፡ ጉም ይመስላል፡፡ የበረዶ ካፊያ እንደተነደፈ ጥጥ
በጸጉርና በሰውነት ላይ ብትን ብሎ ሲታይ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ የበረዶው
ካፊያ ግን አያረጥብም፣ ምክንያቱም ቶሎ አይሟሟም፤ አይቀልጥም፡፡ "ስትል
ትናገራለች ባንድ ወቅት ይህን ቦታ ጎብኝታ የተመለሰችው የአዲስ አድማስ
ጋዜጣ ጸሀፊ አበባየሁ ገበያሁ።
2. "ጮቄ" የሚለው ቃል በጥሬ ትርጓሜው የሚይዘው ፍቺ ከቅዝቃዜ መጠንከር
የተነሳ እርጥቡ ወደ ግግር በረዶነት የተለወጠና እጅግ የቀዘቀዘ፣ ማናቸውንም
በህይወት ዙሪያ የሚገኙ አካል በመንካት የምንለይበት የስሜታዊ ህዋስ መለያ
ባህሪ ነው። ከዚም ተነስተው ቀደምት አባቶች በጎጃም መሀል ምድር በተፈጥሮ
እንደ ሰቀላ ቤት ውቅር ተሰድረው የተሰሙትን የተራሮች ሰንሰለት ጮቄ በሚል
ሞክሼ ስም ሰተውታል።
3. የነዋሪው የአመጋገብና የአለበበስ ባህል ብርድን እና ውርጭን ያገናዘበ ነው፡፡
በጥጥ የተሰራ ኮፍያ፣ ሙቀት ሰጪ ካፖርት፣ ጓንት፣ ከክር የተሰራ ኮፍያ፣
ስካርፕ፤ ጎጃም አዘነ የተሰኘው ፎጣ መልበስ ያዘወትሩሉ - ‹‹ደገኞቹ›› የጮቄ
ነዋሪዎች።
4. የተራራው ከፍታ ዝቅተኛው ከ 1600ሜትር ያላሰ ከፍተኛው 4400 ሜትር
እንደማይበልጥ ይገመታል።
5. የጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ አቀማመጥ በምስራቅ ወደ ደብረማርቆስና ብቸና
አውራጃዎች ዘንበል ያለ፣ በሰሜን የሞጣን አውራጃ ተንተርሶ፣ በምእራብና
በደቡብ ምዕራብ ቀጥ ባሉ አቀበቶችና እንደ አራት መከራክር ባሉ ድንጋዮችና
ቋጥኞች የዳሞትን ወረዳዎች አቅፎ ቆሟል።
6. የጮቄ የከፍታ ማማ ግዛት በ150 ካሬ ኪሎ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን
ከነዚህ የተራራ ሰንሰለት ስር በርካታ ምንጮችና ወንዞች እየፈለቁ የአባይ ገባር
ወንዞች ይፈጥራሉ። የጮቄ ተራራና አካባቢው የ273 ምንጮችና የ59 ወንዞች
መፍለቂያ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ 23ቱ የአባይ ገባር ወንዞች እንደሆኑ
ይነገራል። ከጠቅላላው የአባይ ውሃ 9.5% ያህል ከጮቄ እንደሚመነጭ ጮቄን
ያጠኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ከነዚህ ወስጥ በጉብኝቶ ጊዜ ሊያይዋቸው
የሚችሉት ጨሞጋ፣የዳ፣ ሺገዝ፣በጨት፣ቦገና፣ሙጋ፣
ሶሀ፣ይበርት፣ዛት፣ዐበያ፣ጨየ፣ጌደብ፣ጉድላ፣ተምጫ፣ ቀጨም፣ብር፣ ቁሌች
ይገኙበታል።
7. የጮቄ ተራራ ለጎጃም ህዝብ በአደራ የተሰጠ ትሩፋትና ጸጋው ነው። ከነዚህ
በረከቶች ውስጥ በአይነትና በብዛት የማይቆጠሩና የማይወሰኑ የዱር አራዊትና
እንስሳት፣ አእዋፋትና እጽዋት(እንደ አስታ፣ጅብራ፣ግብይ፣አሻንግድዬ)
ይገኙበታል።
የጮቄ ተራራን ፓርክ በኢኮቱሪዝም የማስተዋወቅ መስክ መንቀሳቀስ
ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት በፍጥነት ሊያስብበትና ሊሰራዉ የሚገባዉ
ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው። ካወቀበት በዚህ ወቅት ክልሉ ከፍተኛ የሆነ
የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፍሰት እድል አለዉ። አመቺ የሆነ የመኪና መንገድ
የመዝናኛ ስፍራዎች በአካባቢው ቢሰሩና በሰፊው ስራ ቢሰራ የቱሪስት
መስህብነቱ ከአገር አልፎ በአለማቀፍ ጎብኝዎች ትኩረት የሚስብ ተፈጥሮዊ
ቦታ ነው።
የ 74 ወንዞች መነሻ
የ 254 ምንጮች መፍለቂያ ጮቄ ተራራ
Mount Choke, at 4,400 meters, is one of the highest
mountains in Ethiopia. 273 springs and 59 rivers flowing from
the heights make up to 10% of the Blue Nile river.
ማጣቀሻ
አዲስ አድማስ ጋዜጣ

16/08/2020

ጮቄ የጎጃም ምንጮች ጋን የወንዞች ሁሉ እናት እና አናት!
====================================
# share ይደረግ!
1. "ብርቅየነቱና ግርማ ሞገሱ ይማርካል፤ ብርዱ ግን አይጣል ነው፡፡ ቅዝቃዜው
ከበጋ እስከ ክረምት አንድ በመሆኑ ደጋ መባል ያንሰዋል፡፡ በደቂቃዎች ልይነት
አንዳንዴ ደመናማ ቆየት ብሎም ብራ እየመሰለ የተፈጥሮ መቅበጥበጥ
በሚታይበት ይህ ተራራ አናት ላይ ወጥቶ አካባቢውን መቃኘት ልዩ ስሜትንና
መደነቅን ይፈጥራል። በተራራው ላይ ያለው በረዶው ብዙዎቻችን ከምናውቀው
ጠጣር በረዶ ይለያል፡፡ ጉም ይመስላል፡፡ የበረዶ ካፊያ እንደተነደፈ ጥጥ
በጸጉርና በሰውነት ላይ ብትን ብሎ ሲታይ ልዩ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ የበረዶው
ካፊያ ግን አያረጥብም፣ ምክንያቱም ቶሎ አይሟሟም፤ አይቀልጥም፡፡ "ስትል
ትናገራለች ባንድ ወቅት ይህን ቦታ ጎብኝታ የተመለሰችው የአዲስ አድማስ
ጋዜጣ ጸሀፊ አበባየሁ ገበያሁ።
2. "ጮቄ" የሚለው ቃል በጥሬ ትርጓሜው የሚይዘው ፍቺ ከቅዝቃዜ መጠንከር
የተነሳ እርጥቡ ወደ ግግር በረዶነት የተለወጠና እጅግ የቀዘቀዘ፣ ማናቸውንም
በህይወት ዙሪያ የሚገኙ አካል በመንካት የምንለይበት የስሜታዊ ህዋስ መለያ
ባህሪ ነው። ከዚም ተነስተው ቀደምት አባቶች በጎጃም መሀል ምድር በተፈጥሮ
እንደ ሰቀላ ቤት ውቅር ተሰድረው የተሰሙትን የተራሮች ሰንሰለት ጮቄ በሚል
ሞክሼ ስም ሰተውታል።
3. የነዋሪው የአመጋገብና የአለበበስ ባህል ብርድን እና ውርጭን ያገናዘበ ነው፡፡
በጥጥ የተሰራ ኮፍያ፣ ሙቀት ሰጪ ካፖርት፣ ጓንት፣ ከክር የተሰራ ኮፍያ፣
ስካርፕ፤ ጎጃም አዘነ የተሰኘው ፎጣ መልበስ ያዘወትሩሉ - ‹‹ደገኞቹ›› የጮቄ
ነዋሪዎች።
4. የተራራው ከፍታ ዝቅተኛው ከ 1600ሜትር ያላሰ ከፍተኛው 4400 ሜትር
እንደማይበልጥ ይገመታል።
5. የጮቄ ሰንሰለታማ ተራራ አቀማመጥ በምስራቅ ወደ ደብረማርቆስና ብቸና
አውራጃዎች ዘንበል ያለ፣ በሰሜን የሞጣን አውራጃ ተንተርሶ፣ በምእራብና
በደቡብ ምዕራብ ቀጥ ባሉ አቀበቶችና እንደ አራት መከራክር ባሉ ድንጋዮችና
ቋጥኞች የዳሞትን ወረዳዎች አቅፎ ቆሟል።
6. የጮቄ የከፍታ ማማ ግዛት በ150 ካሬ ኪሎ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲሆን
ከነዚህ የተራራ ሰንሰለት ስር በርካታ ምንጮችና ወንዞች እየፈለቁ የአባይ ገባር
ወንዞች ይፈጥራሉ። የጮቄ ተራራና አካባቢው የ273 ምንጮችና የ59 ወንዞች
መፍለቂያ ነው፡፡ ከነዚህም ውስጥ 23ቱ የአባይ ገባር ወንዞች እንደሆኑ
ይነገራል። ከጠቅላላው የአባይ ውሃ 9.5% ያህል ከጮቄ እንደሚመነጭ ጮቄን
ያጠኑ ተመራማሪዎች ይናገራሉ፡፡ከነዚህ ወስጥ በጉብኝቶ ጊዜ ሊያይዋቸው
የሚችሉት ጨሞጋ፣የዳ፣ ሺገዝ፣በጨት፣ቦገና፣ሙጋ፣
ሶሀ፣ይበርት፣ዛት፣ዐበያ፣ጨየ፣ጌደብ፣ጉድላ፣ተምጫ፣ ቀጨም፣ብር፣ ቁሌች
ይገኙበታል።
7. የጮቄ ተራራ ለጎጃም ህዝብ በአደራ የተሰጠ ትሩፋትና ጸጋው ነው። ከነዚህ
በረከቶች ውስጥ በአይነትና በብዛት የማይቆጠሩና የማይወሰኑ የዱር አራዊትና
እንስሳት፣ አእዋፋትና እጽዋት(እንደ አስታ፣ጅብራ፣ግብይ፣አሻንግድዬ)
ይገኙበታል።
የጮቄ ተራራን ፓርክ በኢኮቱሪዝም የማስተዋወቅ መስክ መንቀሳቀስ
ያስፈልጋል፡፡ የአማራ ክልል መንግስት በፍጥነት ሊያስብበትና ሊሰራዉ የሚገባዉ
ጉዳይ የልማት ጉዳይ ነው። ካወቀበት በዚህ ወቅት ክልሉ ከፍተኛ የሆነ
የኢንቨስትመንትና ቱሪዝም ፍሰት እድል አለዉ። አመቺ የሆነ የመኪና መንገድ
የመዝናኛ ስፍራዎች በአካባቢው ቢሰሩና በሰፊው ስራ ቢሰራ የቱሪስት
መስህብነቱ ከአገር አልፎ በአለማቀፍ ጎብኝዎች ትኩረት የሚስብ ተፈጥሮዊ
ቦታ ነው።
የ 74 ወንዞች መነሻ
የ 254 ምንጮች መፍለቂያ ጮቄ ተራራ
Mount Choke, at 4,400 meters, is one of the highest
mountains in Ethiopia. 273 springs and 59 rivers flowing from
the heights make up to 10% of the Blue Nile river.
ማጣቀሻ
አዲስ አድማስ ጋዜጣ

15/08/2020

አጀንዳዬንማ አልቀይርም።
*~★★~*
• ፌስቡክ ላይ ብለጥፈው ፌስቡክ ሄጵ ስለሚልብኝ እዚሁ ቴሌግራም ላይ ብቻ
ለጥፌዋለሁ። ይነበብ !!
# ETHIOPIA | ~ መልካሙን ሥራ ለማድነቅ ቅሽሽ እንደማይለኝ ሁላ ከፉውን፣
አረመኔያዊውን፣ መጥፎውን ተግባርም ለመቃወም ቅሽሽ አይለኝም። ከኑመ ጋ
ዱቢን።
•••
በ1988 ዓም መሠረቱ ተጥሎ የተጀመረውን እንጦጦን የማስዋብ ፕሮጀክት
በሚገባ በሥነ ሥርዓት እያስፈጸመ በመሆኑ ለዐቢቹ ምስጋና ማቅረብ ንፉግነት
ነው የሚሆነው። ያምራል። ደስስም ይላል። ለዚህም ገለቶሚም እላለሁ።
ቆሜም አጨበጭባለሁ። ደግሞም ዛሬ 44 ተኛ ነው 45 ተኛ የልደት በዓልህ
ነው ተብሏልና እንኳን አደረሰህ ለማለትም እወዳለሁ። ነገር ግን አባው ከዚሁ
ጎን ለጎን በእጅህ፣ በአስተዳደር ዘመንህ ኦርቶዶክሳውያን ላይ እየፈጸምከው፣
እያስፈጸምከው ያለውን የዘር ማጥፋት ልረሳልህ አልችልም። ምስጋናውን
ለመውሰድ እንደምትንሰፈሰፈው ሁሉ ወቀሳውንም ለመቀበል አትንቀጥቀጥ።
የጊዜ ጉዳይ እንጂ የፍትህ ዘመን ሲመጣ በዘር ማጥፋት መጠየቅህ አይቀርም።
ዛሬ ሽመልስን በግልጽ በሥልጣን ያስቀጠልከው፣ ጊዜው፣ ገንዘቡና ሥልጣኑ
በእጅህ ስላለ ነው። እናም ለወቀሳውም ተዘጋጅ።
•••
አውቃለሁ የዶር ዐብይ አሕመድ ተራሮችን ችግኝ በመትከል ማስዋብ የሚለው
አጀንዳ ከየት የተቀዳ እንደሆነ ማየት አይቸግርም። ችግኝ እየተከሉ ሰው መንቀል
ግን ኃጢአትም ነውርም፣ ወንጀልም ነው። የችግኝ መትከሉን ያህል ሃገር
ለማዳን፣ ሕግም ለማስከበር ለምን አትለፋም? ከንግግህ ውስጥ በአብዛኛው
የኢትዮጵያ ከፍታ በሚቀጥሉት አስር ዓመታት ነው የሚል ነገር ትጠቀማለህ።
ይህን ቃል ከየት እንዳመጣኸውም እኮ ይታወቃል። ከፓስተርህ ከቀሲስ በሊና
ሳርካ “የከፍታው ዘመን በኢትዮጵያ” ከሚለውና ከ18 ዓመት በፊት ከተጻፈ
መፅሐፋቸው ቃል በቃል የተቀዳ መሆኑንም እናውቃለን። በዚህ መጽሐፍ ገፅ 60
ላይ “… በኢትዮጵያ የከፍታ ዘመን ላይ ሲደርስ ተራራዎች ከረብቶች ሁሉ ዛፍ
ይተከልባቸዋል። ኢትዮጵያ ትበለጽጋለች። የሚለውን በመያዝ የብልጽግና
ወንጌልን በብልጽግና ፓርቲ ቀይረህ ልክ እንደ አውሮጳና አሜሪካ ምድርን በአበባ
በመሸፈን ኦርቶዶክሳውያንን በማጽዳት ኢትዮጵያን አሳድጋለሁ ብለህ
እንደተነሣህ አይጠፋንም። ለዚሁም ከምድሪቱም፣ ከሥልጣኑም ሥፍራ ሁሉ
የተዋሕዶ ልጆች እንዲጸዱ መደረጋቸውንም እንታዘባለን። የበሊናን ትንቢት
መፈጸምህ መልካም ቢሆንም ግን ዛፍ ተክለህ ሰው ንቀል በሚለው ሰይጣናዊ
ድርጊትህ ግን ነቃፊህ ነኝ።
•••
አሁን እንዲህ ያማረችዋ ከተማ እንደ ሻሸመኔ ሶሪያ ለመምሰል ሰከንድ
አይፈጅባትም። በኦሮሚያ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል፣ ሆቴሎች፣ የመዝናኛ
ስፍራዎች፣ አብያተ ክርስቲያናት፣ መኖሪያ ቤቶች፣ ፋርማሲ፣ ጤናጣቢያ፣
ክሊኒኮች፣ የትራንስፖርት መኪኖች፣ ሱቆች፣ ህንጻዎች፣ ፋብሪካዎችን
የኦርቶዶክሳዊያን ብቻ ስለሆኑ አውድመህ፣ አስወድመህ ስታበቃ አሁን አዲስ
አበባን እንዲህ አደረኩላት ምናምን ብትል ያው ሚሞሪ ሾርቱን መንጋ ትሸውድ
ቢሆን እንጂ ልባሞችን ለመሸወድ አይመችም። መልካም አስተዳደር ከሌለ፣
ፍትህ ከሌለ፣ መከላከያ ሠራዊቱ፣ ፌደራል ፖሊስና የከተማ ፖሊሱ በአክራሪ ፀረ
ኢትዮጵያ ኃይሎች የሚመራ ከሆነ ያየነውን ለማውደም ሰከንድ
አይፈጅባቸውም። ደግሞም አዲስ አበባም በሀጫሉ ሞት ምክንያት ልክ እንደ
ሻሸመኔ ኢሪሊቫንት ለመደረግ ተሞክሮ እድሜ ለእስክንድር ነጋና ለሸገር ልጆች
ቢታሰሩም ማማሰያ፣ መወልወያና መጥረጊያ ይዘው ታድገዋታል። እናም ብዙ
ባይዘለል ሸጋ ነው።
•••
እኔ ዘመዴ አጀንዳዬን አልለውጥም። 11 ሺ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች
ከእነ ቤተሰቦቻቸው በራሱ በአቢቹ አስተዳደር ተፈናቅለው በዝናብና በብርድ
በውርጭም፣ በረሀብም እየተሰቃዩ እያየሁ አጀንዳዬንማ አልቀይርም። መከላከያ
ሠራዊቱ እያያቸው፣ ፖሊስ እየተመለከታቸው፣ ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች
እንደከብት ተጋድመው በሚስት፣ በልጅ፣ በባል ፊት “አላህ ወአክበር” በሚል
አክራሪ በአሩሲና በባሌ፣ በሀረርጌና በጅማ አራጆች እጅ ከታረዱ እኮ 40 ቀን
አልሞላቸውም። እናም አጀንዳዬን አልቀይርም።
•••
የባለማዕተቦች ቤት ተመርጦ የተቃጠለው፣ የወደመው፣ የነደደው፣ ወደ
ዐመድነት የተለወጠው እኮ የዛሬ 40 ቀን አካባቢ ነው። ካህናቱ የተደበደቡት፣
ቤት ንብረታቸው የተቃጠለው እኮ አሁን በቅርቡ ነው። እናም እኔ ሞኝ
አይደለሁም። እኔ ፋራም አይደለሁም። ንክር ሁላ። በአንድ ጀንበር በብልጭልጭ
ነገር የምሸወድም ጀዝባ አይደለሁም። አጀንዳዬን በፍጹም አልቀይርም።
በፍጹም። ፍትህ እጠይቃለሁ። የተጠቁትን እደግፋለሁ። እጮህላቸዋለሁ።
ብረሳቸው ቀኜ ትርሳኝ። ባላስባቸው ምላሴ ከጉረሮዬ ይጣበቅ።
•••
መንጋው መኖህለል መብቱ ነው። እኔ ግን በመናፈሻ አበባ፣ በብልጭልጭ ቁስ
የሰማዕታቱን ደም አላረክስም። ከሞት፣ ከአሩሲ አክራሪ የወሀቢይ እስላሞች
የተረፉትን የተዋሕዶ ልጆች እኮ ኮሮና እያሰጋቸው ነው። ይሄው የመናፈሻ ገንቢ
መንግሥት እኮ ነው ተቀምጦ ያሳረዳቸው። ሽመልስ አብዲሳ እኮ አሁንም
ደንታው አይደለም። እናም በመናፈሻማ ማዕተቤን አልበጥስም። በዚህና
በሌሎች መሰል አጀንዳዎች ላይ ወደ በኋላ፣ በተለመደው ሰዓት በተለመደው
የዩቲዩብ ቻናሌ ብቅ እላለሁ። አቋሜንም እገልጻለሁ። ቃሌንም አስመዘግባለሁ።
በሚመሰገነው አመስግኜ በሚወቀሰው እወቅሳለሁ። እንጂ እንዳንተ
እንደመንጋው በመናፈሻ አበባ የሰማዕታቱን ደም አልለውጥም። አጀንዳዬንም
አልቀይርም።
• # ማስታወሻ | # ማስጠንቀቂያም ፦ “ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን ክብርና
መብት አስጠባቂ ኅብረት” የሚል ስም ይዛችሁ፣ በካድሬ ቆዳ ተጠቅልላችሁ
መልካችሁን በሜካፕ ወደ ተዋሕዶነት ቀይራችሁ፣ የጭቃ ውስጥ እሾህ
ሆናችሁ፣ በታከለ ኡማ ቀለብ ሰፋሪነት፣ የይሁዳን ካራክተር ይዛችሁ፣ በቅድስት
ቤተ ክርስቲያን ልጆች ደም ለመነገድ የተነሣችሁ ወፍራም አርዮሶች ብትጠነቀቁ
ይሻላችኋል። ተናግሬአለሁ።
•••
በተለይ አቶ ሙሉቀን የተባልክ አስብቶ አራጅ፣ የመስከረም 4ቱን ሰልፍ
አስቀርተህ አሁን እንዲህ እንድንታረድ፣ እንድንቃጠል ያስደረከን ከንቱ የሆንክ
ሰው ተጠንቀቅ። ከዚህ ነውረኛና ጴጥሮሳውያን ብሎ በጠላት ካርታ
ከሚንቀሳቀስ ዘጥዛጣ ጋር አብራችሁ የምታዘጠዝጡ የራሳችን የምንላችሁ
ሰዎችም ሁሉ ተጠንቀቁ። ዲን ዳንኤል ክብረትም በስምህ እየነገዱ ነውና መላ
በላቸው። ተናግሬአለሁ። ደላሎች ተፋቱን።
•••
እናንት የካርታ ደላሎች ተጠንቀቁ፣ እናንት የታከለ ቡችሎች ተጠንቀቁ። እናንት
አስመሳዮች ተጠንቀቁ። ዝም ስንል ሞኝ አንምሰላችሁ። እስስቶች። ማኅበረ
ቅዱሳን ከእነዚህ ኮተቶች ጋር ያለህን ጉዳይ አቁም። ይዘውህ ገደል ይገባሉና
ተጠንቀቅ። ለተፈናቀሉት የሰማዕታት ቤተሰቦች ተብሎ የተሰበሰበው ገንዘብ ላይ
ለመከመር ያሰፈሰፋችሁ ጆፌ አሞሮች ሥነሥርዓት ያዙ። እናንት የሙዳይ
ምጽዋት አይጦች ተጠንቀቁ። ይሄ የደም ገንዘብ ነው። ነቀርሳ ነው የሚሆንባችሁ
ተጠንቀቁ። እናንት ነፍሰ በላዎች፣ ከአራጅ እኩል የምትቆጠሩ አውሬዎች
ተጠንቀቁ። ስማችሁን ሳልጠራው አስቡበት። በተለይ ጴጥሮሳውያን የተባልክ
ጆከራም አደብ ግዛ።
•••
ይሄንንም በሰፊው እመጣበታለሁና ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ። እነዚህ ከሃዲዎች፣
በታከለ ኡማ ኮንዲሚንየም ሃይማኖታቸውን አሳልፈው የሰጡ ይሁዳዎች እነማን
እንደሆኑ በስም ዝርዝር ከእነ ፎቶአቸው አስቀምጣለሁ። ቀልድ የለም።
ጠላትማ ጠላት ምንጊዜም ጠላት ነው፣
አስቀድሞ …… አሾክሻኪውን ነው። አከተመ።
•••
ሻሎም !ሰላም !
ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ነሐሴ 9/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።

ፍቱት ዋ !
15/08/2020

ፍቱት ዋ !

15/08/2020

Christian Tadele Tsegaye
ግብረ ንስር
*****
1. ንስሮች በከፍታ ለብቻቸው ይበራሉ፦ ንስር ፈፅሞ ከጥንብ አንሳ፣ ቁራና
መሰል ትናንሽ አእዋፍት ጋር አብሮ አይበርም።
አንድምታ፦ አንሰው ከሚያሳንሱን፤በስሁት መንገድ ከሚነጉዱ፤ የአስተሳሰብ
አድማሳቸውም ውስን ከሆኑ ሰዎች ራሳችንን እናርቅ። ንስር ከቁራ ጋር ማኅበር
የለውም። ወዳጃችሁን አስምሩ፤ አዋዋላችሁን መርምሩ።
2. የንስር እይታ እንከን የለሽ ነው፦ ንስር እስከ 5 ኪ·ሜ ድረስ ጥርት አድርጎ፤
ዒላማውን አነጣጥሮ የማየት ፀጋን የታደለ ነው። ምንም ዓይነት አስቸጋሪ
ሁኔታዎች ቢያጋጥሙት እንኳን ታዳኙን እስኪይዝ ድረስ ካነጣጠረበት ዒላማው
ላይ ዓይኖቹን ላፍታ ዘወር አያደርግም። .
አንድምታ፦ የፈለገ ያህል መሰናክል ቢያጋጥማችሁ እንኳን የታወቀ መዳረሻ
ግባችሁን በውል አውቃችሁ እዚያ ላይ ትኩረት አድርጋችሁ እስከተንቀሳቀሳችሁ
ድረስ ኅልማችሁን መኖራችሁ የተረጋገጠ ጉዳይ ነው። አስር ያባረረ አንድ
አይዝም ነው ነገሩ።
3. ንስሮች ጥምብ አይበሉም፦ ንስር የበከተ ነገር አይመገብም፣ ራሱ ያደነውን
ነገር ይበላል።
አንድምታ፦ በትናንት ስኬታችን ከመዘናጋት ይልቅ ወቅታዊና ስትራቴጂካዊ
አዳዲስ አውዶች ጋር ለመጋፈጥና ሁሉንም እንደየአውዱ በድል ለመሻገር
ወትሮዝግጁ መሆን ያሻል። ትናንትን ለትናንት በመተው ልምድ ቀስሞ መሻገሩ
ተመራጭ ይሆናል።
4. ወጀብ ለንስሮች ፍስኃ ነው፦ ደመናት መሰባሰብ ሲጀምሩ ንስር ልቡ ሐሴትን
ታደርጋለች። ንስሩ ወጀቡን ለክንፎቹ መንሳፈፊያና ወደ ከፍታ መመንደጊያ
ይጠቀምበታል። ንስር ወደ ወጀቡ የሚወስደውን አውሎ ሲያገኝ በአውሎው
ኃይል ከደመናው በላይ ከፍ ብሎ ለመውጣት ይጠቀምበታል። ይኼ ደግሞ
ለንስሩ ክንፎቹን ያለ ድካም ዘርግቶ እንዲበር ምቹ ሁኔታን ይፈጥርለታል። ንስር
ከደመና በላይ፤ ከወጀቡ በላይ በክብር ሲንፈላሰስ ሌሎች አእዋፋት በአንፃሩ
የዛፍ ቅርንጫፎችን ከወጀቡ መጠጊያ መሸሸጊያ ለማድረግ ይራኮታሉ።
አንድምታ፦ ችግር በእዬዬና ዋይታ አይፈታም። ይልቅ ችግርህን ፊት ለፊት
ተጋፈጠው። ችግርህን መጋፈጥ ቢያበረታህ እንጂ አይሰብርህም።ችግር
የብልኃት መምህር ነው። እንዲያውም ያጋጠመህ ችግር ከገባህበት የትናንት
አርንቋ ተመንጭቀህ እንድትወጣ ኃይልና ብርታት ይሆንሃል። ችግር ወደ ከፍታው
መውጫ መንገድ ነው። የአሸናፊዎች ቦታቸው ከፍታ ነው። አሸናፊዎች
በሚያጋጥማቸው ፈተናና ችግር ከመነፋረቅና መቆዘም ይልቅ ወደ ምቹ አጋጣሚ
በመቀየር ነጋቸውን በአስተማማኝ መደላድል ለማቆም ለሚያደርጉት ጉዞ
እንደመስፈንጠሪያ ይጠቀሙበታል።
5. ንስሮች ራሳቸውን ለልምምድና ሥልጠና ያዘጋጃሉ፦ ንስሮች በጎጇቸው
የጎዘጎዙትን ለስላሳ የላባ ስጋጃና የሳር ዳውጃ አስወግደው ጫጩቶቻቸው
ጎርባጣውን እንዲያውቁት፤ ሲጎርብጣቸውም ከጎረበጠው ጎጆ በመውጣት
መብረር እንዲለማመዱ ያደርጋሉ። በእርግጥም በእሾሃማ ጎጆ ከመቀመጥ
ወጥቶ መብረር ለጫጩት ንስሮች አማራጭ የሌለው ምርጫቸው ስለሚሆን
በረራን መላመድ ግድ ይሆንባቸዋል። በዚያውም በረራን እንዲህ ይለምዳሉ።
አንድምታ፦ ከለመድኸው የምቾት አንቀልባ ውረድና በእግርህ ተጓዝ።
ተንቀሳቀስ፤ እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል!
6. ንስር ራሱን ያድሳል፦ ንስር ዘመኑ በሄደና ባረጄ ጊዜ ወጀቡን የሰንጠቁ፤
ከደመና በላይ ያስቧረቁ አክናፋቱ መዛል ይጀምራሉ። ክንፎቹ ልቡ ባሰበበት ቦታ፥
በተመኘውም ጊዜ ማክነፍ ይሳናቸዋል። እንደልቡ ወደ ሰማይ ልብ ሰንጥቆ
በመብረር ከፍታው ላይ ለመገማሸርም አያስችሉትም። በዚህ የተነሳም ንስሩ
አቅመቢስነት እየተሰማው ሄዶ ሄዶ ለሞትም ይቃረባል። በዚህ ጊዜ ወትሮ
ለአደንና ፈንጠዝያ ከሚፏልልበት ቦታ ሁሉ በመቅረት ወደ ረጅም አምባ፤ ማንም
ወደ ማይደርስበት ተራራ ይመንናል። ያረጁና የበሰበሱ ላባዎችንም ነቃቅሎ
ያራግፋል። ከቋጥኝ ጋር በማጋጨትም የተቆለመመ መንቆሩንና የዶለዶሙ
ጥፍሮቹን ጨርሶ ያወላልቃል። ይኽም የሚቆጠቁጥ ቁስልና ከፍተኛ መድማትን
ያስከትልበታል። አዲስ ላባ፣ የሾለ መንቆርና ስለታም ጥፍሮች እስኪበቅሉለት
ድረስም ራሱን በነጠለበት የምናኔ ተራራው ደብቆ ያቆያል። እንዳዲስ
ሲበቅልሉትም ራሱን አድሶ ከዚህ በፊት ይበርበት ከነበረው ከፍታ በላይ መብረር
የሚያስችል አቅም ገንብቶ ይወጣል።
አንድምታ፦ ከተለመደው አሰስ ገሰስ ልምድ መላቀቅ ያስፈልጋል። ለዛሬያችንም
ሆነ ለወደፊት መዳረሻችን እሴት የማይጨምሩ አስካሁን ይዘናቸው የነበሩ
ልምዶች፣ አሰራሮችና አስተሳሰቦች ካሉ ለመተው ዝግጁ ልንሆን ይገባል።

14/08/2020

What's on your mind?
*የሽመልስ ንግግር ብልጽግናን አይወክልም ለምትሉ +
-በመቶ የሚቆጠሩ ፈፃሚዎችን ሰብስቦ ቢያንስ 3 ከፍተኛ ባለስልጣን በመሩት
መደበኛ ስብሰባ የተደረገ ንግግር የግለሰብ ሀሳብ ነው ለማለት ሞራሉን ከየት
አመጣችሁት?
-ሽመልስ ከተናገረው ቋንቋን የተመለከተው በሚኒስትሮች ም/ቤት የተወሰነ
ጉዳይ ነው፣የአድስ አበባን ጉዳይ አብይ እራሱ የሚያውቀው፣ህግ ጥሶ በሾመው
ታከ ዑማ መሪነት የሚፈፀም በእነ # ሰናይት ደግፌ ሲጋለጥ ለመሸፋፈን ብዙ
የደከመለት ጉዳይ ነው፡፡የአብይን የመሸፋፈን መግለጫ ተከትሎ ወ/ሮ ሰናይት
መረጃ አጥሮት ከሆነ የሰነድም የቪዲዮም መረጃ እኔ እሰጠዎታለሁ ይጠይቁኝ
ብላ በሚድያ ተናግራለች፡፡ድርጅቱም በመግለጫ አድስ አበባ የኦሮሞ ናት ብሎ
ተናግሯል፡፡አድሲቷ ኢትዮጵያ የሚሏት በኦሮሙማ የተዋጠችዋን መሆኑን እኮ
በይፋ እያየን ነው፡፡እስኪ የሰሞኑን እስር ልብ ብላችሁ ተመልከቱ?ኦሮማይዝድ
ኢትዮጵያን ለማንበር እንቅፋት ይሆናሉ ያሏቸውን ነው ከዘር አጥፊዎች ጋር
አጃምለው ያሰሩት፡፡በነገራችን ላይ የአስራት ጋዜጠኞች የታሰሩት በ #አዴፓ
የይታሰሩልኝ ጥያቄ መሆኑን መረጃ ደርሶኛል በቅርቡ ይረጋገጣል፡፡ታዳ እንደ
ድርጅት እየፈፀሙት ያለን ጉዳይ በስብሰባ ሽመልስ ተወክሎ ስላቀረበው የግል
ሀሳቡ ነው እንደት ይባላል?
የድርጅት አቋም እኮ # በአባላቱ ሙሉ በመዝሙር መልክ አይቀርብም በተመረጠ
አንድ ሰው እንጂ፡፡
እናንተ አምናችሁ እና ግራ ተጋብታችሁ ሌሎችንም ለማሳመን እና ግራ ለማጋባት
አትድከሙ እዚያው እራሳችሁ Convinced ወይም confused ሆናችሁ
ቀጥሉ።ሽመልስ ለእኛ ለማላላክ የተሰለፉ ብዙ አሉ ያለው ለካስ እውነቱን ነው

12/08/2020

ASRAT MEDIA HOUSE
በሕገወጥ መንገድ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉ የአሥራት ሚድያ
ባለሙያዎችንና የቀድሞ ባለሙያን አስመልክቶ ከአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ
የተሰጠ የተቃውሞ መግለጫ
---------------------------------------------
የአማራ ሕዝብ ለዘመናት በተካሄዱበት የተጠኑና የተቀናጁ ሴራዎች፤ እነዚህም
ፍሬ አፍርተው አማራ በገዛ ሀገሩ መንግሥትና ሀገር አልባ እንዲሆንና የሕግ
ጥበቃ እንዳይኖረው መዋቅራዊና ሕገመንግሥታዊ ማዕቀፍ ከተበጀለት ከሁለት
አሠርት ዓመታት በላይ ሆኖታል። በዚህም መሠረት፤ የአማራን ሕዝብ ክብር
መንካት፣ የፈጠራ ክስ መክሰስ፣ ታሪኩን መካድና ገልብጦ መጻፍ፣ እንዲሁም
በፈጠራ ድርሰት ላይ ተመርኩዞ የጥላቻ ሐውልት ማቆምና እንደቅዱስ ስፍራ
ሕዝብን ማስጎብኘት በሙሉ የተፈቀዱ ናቸው። እንዲያውም የሚመስለው፤
የአማራን መልካም ታሪክ ማንሳት እንደወንጀል የተቆጠረ ሆኗል። በዚህ ሰበብ
የሚጠቁ ንጹሃን አማራዎችና ወንድም/እህት ዜጎችን ታይቶና ተሰምቶ
በማይታወቅ ጭካኔ መግደል፤ እንዲሁም ንብረታቸውን መዝረፍና ማቃጠል
የተለመደ ተግባር ሆኗል። ላለፉት ፴ (30) ዓመታትም በዚህ መልክ ለደረሱ
ወንጀሎች ተጠያቂዎች ለፍርድ ሲቀርቡ አልታየም። እንዲያውም፤ ከወንጀለኞች
የወገኑ የብዙኃን መገናኛዎች ጥቃቶችን በተደጋጋሚ ካለመዘገብ ጀምሮ፤
በአንዳንዶቹ ጥቃቶች የሟቾችን ስም በማጥፋት የገዳዮችን ስም ሲያነጹ
ኖረዋል። በዚህም ምክንያት የአማራ ሳተላይት ራዲዮና ቴሌቪዥን (አሥራት)
በተቆርቋሪ ዜጎች እንዲመሰረት ግድ ብሏል።
አሥራት የአማራን ሕዝብ፤ ሀገሩ ኢትዮጵያ ከሌሎች ወንድሞቹ ኢትዮጵያውያን
ጋር በእኩልነትና በሰላም የሚኖርባት እንድትሆን ከአንድ ነጻ የብዙኃን መገናኛ
ተቋም የሚጠበቀውን ድርሻ ለመወጣት አቅሙ በፈቀደው ሁሉ ሲሰራ ቆይቷል።
በአጭር ጊዜ የአገልግሎት ዘመኑ፤ አድሎአዊ አሠራሮችን፣ የንጹኃን
ጭፍጨፋዎችን፣ የንጹሃን የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ኢ-ሰብአዊ ግድያዎችና
ማሰቃየቶችን፣ ሕገወጥ መፈናቀሎችን፣ ጠለፋዎችን፣ በስልጣን አላግባብ
መጠቀምን፣ በአጠቃላይ ብልሹ አስተዳደርን ሲዘግብ፣ ሲያጋልጥና ገንቢ
ትችቶችንና ጥቆማዎችን ሲሰጥ ቆይቷል። በዚህም በሀገራችን እየደረሱ ካሉ
የባሱ ችግሮች እንዳይከሰቱ መከላከሉን እንረዳለን። በዚህም በሀገር ላይ
ሊደርሱ የሚችሉ አደጋዎችን በመከላከል ኃላፊነት ከሚሰማው አንድ የብዙኃን
መገናኛ የሚጠበቀውን ድርሻ መወጣቱን እናምናለን። ተቋሙ እነዚህን ተግባራት
ለመፈጸም ይበቃ ዘንድ፤ በበጎ ፈቃድና በቂ ባልሆነ ክፍያ ላገለገሉና እያገለገሉ
ላሉ የተቋሙ አስተባባሪዎችና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም በሀገር ውስጥና ከሀገር
ውጭ ላሉ ደጋፊዎቻችን በዚህ አጋጣሚ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
መዋቅራዊና ሕገመንግሥታዊ ሥርዓት አበጅታ የአማራ ሕዝብን ካለተከላካይ
ለምትገድል፣ ለምታፈናቅልና ለምታሳድድ ሀገረ-መንግሥት፤ ምናልባት
ስለአማራው መበደል መዘገብ እንደወንጀል የተቆጠረ ይመስል፤ ከምሥረታው
ጀምሮ በተቋሙ ላይ የተለያዩ አፈናዎች ሲካሄዱበት ቆይተዋል። አንድ የበጎ
ፈቃድ ባለሙያ፣ የአሥራት የበጎ ፈቃድ አስተባባሪና አንድ በቃለ-ምልልስ ላይ
የተሳተፈ የገቢዎች ሚኒስቴር ባለሙያ፣ ካለምንም ጥፋት ለወራት በጨለማ
ክፍል ታስረው ተንገላተዋል። የአሥራት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፤ በአርቲስት ሀጫሉ
ሁንዴሳ ግድያ ማግስት፤ አሥራት ቴሌቪዥን በአየር ላይ ባልነበረበት ሁኔታ፤
"ብሔርን ከብሔር በማጋጨት" እና በተለያዩ ጥፋቶች በሐሰት መወንጀሉ፣
ተቋሙ እየደረሰበት ላለው ስም ማጥፋትና የማፈን ተግባራት የሚከተሉት
ጉዳዮች መነሻ ሊሆኑ እንደሚችሉ ያምናል።
ሀ) በአጣዬ፣ በማጀቴ፣ በከሚሴና በአቅራቢያዎቻቸው በሚገኙ ቀበሌዎች
በንጹሐን ዜጎች ላይ የደረሱ ግድያዎችንና ዝርፊያዎችን መዘገቡ፣
ለ) በኦሮሞ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በአማራ ተወላጆች ላይ የደረሱ
በደሎችን መዘገቡ፤
ሐ) በኦሮሞ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ በነበሩ የአማራ ተወላጅ
ተማሪዎች ይደርሱ የነበሩትን ዘርፈ-ብዙ ጥቃቶችን፣ ግድያዎችንና ሌሎች
በደሎችን መዘገቡ፤
መ) ከላይ የተጠቀሱትን በደሎች ሸሽተው ወደቤተሰቦቻቸው ሲጓዙ የነበሩ ፲፯
(17) ተማሪዎች ደምቢዶሎ አካባቢ መጠለፋቸውን ያየችና በመልካም ዕድል
ያመለጠች ተማሪ በማነጋገር ማጋለጡ፣ የተጠለፉት ተማሪዎች የደረሱበት
እንዲታወቅ የሚመለከታቸውን አካላት መጠየቁ፣ የተጠለፉ ተማሪዎችን
ቤተሰቦች ማነጋገሩ፣ አሳዛኝ በሆነ ሁኔታ "ተጠለፉ ከተባሉት ተማሪዎች መካከል
እኛ እንገኝበታለን" ካላላችሁ ተብለው የታሰሩ ንጹሓን እንስት ዜጎችን በማናገር
ለሕዝብ ይፋ ማድረጉ፤
ሠ) በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የሚፈጸሙ ሥልጣንን አላግባብ
የመጠቀም ድርጊቶች መዘገቡ፤ እንዲሁም
ረ) በአዲስ አበባና በአካባቢው የሚደረጉ ሥልጣንን አላግባብ የመጠቀም
ድርጊቶችን መዘገቡ ናቸው።
በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ሐምሌ ፳፱ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት ከሰዓት
በኋላ አሥራት ቴሌቪዥንን በዝግጅቶች አርታኢነት የሚያገለግለው ጋዜጠኛ
በላይ ማናዬና ጋዜጠኛ ሙሉጌታ አንበርብር፤ ሐምሌ ፴ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት
ደግሞ የአሥራት ቴሌቪዥን የካሜራ ባለሙያ የሆነው አቶ ምስጋናው ከፈለኝና
እስከኅዳር ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት ድረስ የአሥራት ቴሌቪዥን የካሜራ ባለሙያ
የነበረው አቶ ዮናታን ሙሉጌታ ካለጠያቂ በቁጥጥር ሥር እንዲዉሉ ተደርገዋል።
ካለምግብና ካለመድኃኒት፣ እንዲሁም ካለልብስ ከቤተሰብ ዕውቅና ውጭ
ለቀናት በእስር እንዲቆዩ ተደርገዋል። አቶ በላይ ማናዬም የሳይነሳይት ሕመም
እንዳለበት እየታወቀ ከመጸዳጃ ቤት አጠገብ እንዲታሰር ተደርጓል።
በተጨማሪም፤ ዓለምንና ሀገራችንን የኮሮና ቫይረስ ክፉኛ እየተፈታተናት ባለበት
በዚህ ወቅት ሰብአዊነት በጎደለው ሁኔታ ከሌሎች ታሳሪዎች ጋር ካለምንም
መከላከያ ተደርበው እንዲታሰሩ ተደርገዋል።
ከላይ የተጠቀሱት የአሥራት ቴሌቪዥን ባልደረቦችና ከተቋሙ ከለቀቀ ብዙ
ወራት ያስቆጠረው አቶ ዮናታን ሙሉጌታ ነሐሴ ፩ ቀን ፳፻፲፪ (2012) ዓመተ
ምህረት ፍርድ ቤት ቀርበው "በደምቢዶሎና በኦዳ ቡልቱ (በኦሮሞ ክልል) አመፅ
በማነሳሳት፣ አማራው ተበደለ በማለትና መንግስት የአማራን ሕዝብ ከጥቃት
መከላከል አልቻለም" ብለዋል በሚል "ጥርጣሬ" ለ፲፫ (13)ቀናት ተጨማሪ
እስር ተዳርገዋል።
መንግስት "አማራ ተበደለ" ብሎ መናገርን ወንጀል ማድረጉ በኢትዮጵያ ውስጥ
ላለፉት ብዙ ዘመናት በአማራ ሕዝብ ላይ የተፈጸሙ ቁጥር ስፍር የሌላቸው
ወንጀሎችን የመካድ ሙከራ ብቻ ሳይሆን፤ በሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናት
ስለመኖሩ የሚነገርለትን ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት የሚጻረር ነው።
የአማራ ህዝብ በሕገ-መንግስት በተደገፈ ፓሊሲ ስልታዊ የግድያ (በበደኖ፤ አርባ
ጉጉ፤ ሙጊ፤ ቤኒሻንጉል ወዘተ) እና የማፈናቀል (ከ 70,000 በላይ አማራ ከጉራ
ፈርዳ፤ ከ13,000 በላይ አማራ ከምስራቅ ወለጋ፤ ከቤኒሻንጉል፤ ከወልቃይት
ከጠገዴ፤ ከጠለምት፤ ከራያ ወዘተ) ወንጀል ተካሂዶበታል። በዚህ ሰሞን ደግሞ
በኦህዴድ ባለሥልጣኖች ትብብርና ዝምታ የአክራሪ የኦሮሞ ብሄረተኖች ዘግናኝ
ጥቃት ሰለባ ሆኗል። ተፈናቅለው በጊዜያዊነት በተጠለሉባቸው አብያተ-
ክርስቲያን የሚገኙትን የአማራ ተወላጆችና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ምዕመናን የሆኑ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ድረስ እንኳ ሄዶ ያያቸው
የመንግስት አካል የለም። በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት እነዚህን ዜጎች
በነገድ ማንነታቸውና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ክርስቲያናዊ እምነታቸው
ምክንያት የአሰቃቂ ሞትና መፈናቀል ሰለባ ሲሆኑ፤ ይህ እንዲሆን ያስቻሉና
የተሳተፉ የኦሮሞ ክልል መንግስት ተሿሚዎች ላጠፉት ጥፋት ይቅርታን
አልጠየቀም። ከጥቃቱ የተረፉትን አልደገፋቸውም፤ አላጽናናቸውም፤ ለሃዘናቸው
እውቅና ሰጥቶ ብሄራዊ የሃዘን ቀን አላወጀም፤ ለሞቱት መታሰቢያ የማቆም
ፍላጎት አላሳየም። ታዲያ እነዚህን ከመሳሰሉ ግልጽ ኹነቶችና ድርጊቶች ተነስቶ፤
መንግሥት የመናገር ነጻነት አለ በሚልበት ሀገር፤ አንድ ጋዜጠኛም ሆነ ሌላ
ለኅሊናው ተገዥ የሆነ ሰው "ይህ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት በኦሮሚያ
ክልል የሚኖሩ የአማራ ተወላጆችንም ሆነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ
ቤተክርስቲያን ምዕመናንን መብትና ጥቅም አላስከበረም" ቢል ይህ ሃሳብ
ወንጀል የሚሆንበት ምክንያት ምንድነው? ለመሆኑ ሃሳብን መግለጽ ወንጀል
በሆነባት ኢትዮጵያ እንዴት ስለዲሞክራሲ ማውራት ይቻላል? ጥያቄውን
ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት እናቀርባለን።
ሕዝብን ከሕዝብ ጋር ሲያጋጩ የሚዉሉና የሚያድሩ ሚድያዎች በሞሉባት ሀገር፤
የጥላቻ ሐውልት ገንብታ ትውልዶችን በምታስጎበኝ ሀገር፤ ለሀገሪቱ ሰላምና
ለሕዝቧ በዕኩልነት የመኖር ራዕይ አስተዋጽዖ የሚያደርግን አንድ ተቋም
ለማፍረስ ማሴር "አህያውን ፈርቶ፤ ዳውላውን!" የሚለውን ብሂል ያስታውሰናል።
የአሥራት ጋዜጠኞች ሕዝብን ከሕዝብ ወይም ኃይማኖት ከኃይማኖት ጋር
የሚያጋጩ ቅስቀሳዎች አካሂደው አያውቁም፤ በተቃራኒው የሐሰት ትርክቶችን
በማስረጃ በመሞገት የዜጎችን እኩልነትና ሰላም ለማረጋገጥ የተቻላቸውን
ሰርተዋል። በቅን ልቦና ለሙያቸው ስነ-ምግባር ተገዥ የሆኑ ባለሙያዎችን
ማሰርና ማንገላታት ኢሰብዓዊ ከመሆኑ በላይ ለሀገርና ለመንግስት ጎጂ ተግባር
እንደሆነ እናምናለን። ስለሆነም፤ የዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት አሥራት
ቴሌቪዥንም ሆነ ባልደረቦቹ የሰሯቸው ዕውነተኛ ዘገባዎች፤ በሙያዊ ስነምግባር
የተገሩና ለመልካም አስተዳደር መስፈን እንደግብዓት ሊቆጠሩ እንጂ፤
እንደተባለው ሊተረጎሙ የማይገባቸው መሆናቸውን በመገንዘብ፤ ያቀረባቸውን
ውንጀላዎች አንስቶ በነጻ ያሰናብታቸው ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
በተጨማሪም፤ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ
መብቶች ጉባዔ፣ ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶች፣ የጋዜጠኞች
መብቶች ተከራካሪ ድርጅቶችና በተቋሙ ላይ ያንዣበበው የጥፋት ደመና
የሚያሳስባችሁ ወገኖች ሁሉ እነዚህ ንጹሓን ባለሙያዎች ካለተጨማሪ እንግልት
በነጻ ይለቀቁ ዘንድ የበኩላችሁን ድጋፍ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።
የአሥራት ሚድያ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ፤
ነሐሴ ፫ ቀን ፳፻፲፪ ዓመተ ምህረት።

10/08/2020

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ National Movement of Amhara
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈፀመውን የዘር
ማጥፋት በዘላቂነት ለመመከት በሚያደረገው ትግል የአመራሩ ሚና የጎላ
መሆኑን ገለፀ፤
*****
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ለአዲስ አበባ ከተማ እና በከተማው ከሚገኙ
አስሩም ክፍለ ከተሞች ለተውጣጡ አመራሮቹ ነሐሴ 2 እና 3 ቀን 2012 ዓ.ም
የኮሮና ቫይረስን መከላከል ታሳቢ ባደረገ መልኩ በድርጅቱ ርእዮተዓለማዊ ፅንሰ
ኃሳብ፣ በሀገራችን ወቅታዊ ፖለቲካና የወቅቱ የኃይል አሰላለፍ ትንተና እንዲሁም
በትግል ስትራቴጂው ዙሪያ በንቅናቄው ዋና ጽ/ቤት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ በየደረጃው የሚገኙ የንቅናቄው አመራሮች በድርጅታዊ
ርዕዮተዓለም፣ በወቅታዊ ፖለቲካና የትግል ስትራቴጂ ረገድ መሠረታዊ ግንዛቤ፣
ክህሎትና መረጃ በማስጨበጥ በአመራሩ ውስጥ የአመለካከትና የተግባር
አንድነት ለመፍጠር እና አመራሩ የድርጅቱን ተልእኮ ወጥና መዋቅራዊ በሆነ
መንገድ እንዲፈፅም ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
አብን ውጤትንና የትግል መርኅን ሚዛናዊነት ጠብቆ የሚንቀሳቀስና ስልጡን
ፖለቲካ የሚያራምድ በመሆኑ መሰል ስልጠናዎች በየደረጃው የሚገኝ አመራር
ይኼን ሚዛን በመጠበቅና የአብን ትክክለኛ ገፅታ ለሕዝቡ በማሳየት መላ
ሕዝቡን በማንቀሳቀስ ከድርጅቱ ጎን ለማሰለፍ ሚናው የጎላ መሆኑም
ተጠቅሷል፡፡
በሥልጠናው የተካፈሉ አመራሮችም ስልጠናው የሀገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታና
የኃይል አሰላለፍ በሚገባ ተረድቶ ወጥ የተግባርና የአመለካከት አንድነት ይዞ
ወደ ሕብረተሰቡ ወርዶ ለመስራት ግንዛቤ በመፍጠር በኩል ከፍተኛ ጠቀሜታ
እንዳለው ገልፀዋል፡፡
መሰል ስልጠናዎች በየደረጃው የሚገኙ የንቅናቄውን አመራርና አባላት አቅም
በመገንባት በኩል አይተኬ ሚና ስላለው በቀጣይም በሌሎች ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
እስከታች ላለው መዋቅር በስፋት ሊሰጥ እንደሚገባ ያነሱት የስልጠናው
ተሳታፊዎች በቀረቡት ጉዳዮች ላይም ኃሳቦች አንስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) ከአሁን ቀደም በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ደቡብ፣
ሐረሪ፣ ቤንሻንጉል፣ ጋምቤላ ክልሎችና ከድሬድዋ ከተማ አስተዳደር ለተውጣጡ
የዞን አመራሮች ተመሳሳይ ስልጠና መስጠቱ ይታወሳል።
አንድ አማራ ለሁሉም አማራ፥ ሁሉም አማራ ለአንድ አማራ!

Address

Arat Mekeraker/Four Mountain/
Amanu'el
034

Telephone

+251968408022

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቀሬ አላምረው ቢሻው Kerie Alamrew Beshaw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share