Aleta Wondo General Hospital

Aleta Wondo General Hospital This is the official page of Aleta Wondo General Hospital. This page delivers News, Health-

03/06/2026





29/05/2026


       #አስደሳች ዜና!👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከፍተኛ የአጥንት ቀዶ ህክምና (Orthopedic Surgery) እየተሰጠ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።👉ሆስፒታላችን የተሟ...
19/05/2026




#አስደሳች ዜና!

👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከፍተኛ የአጥንት ቀዶ ህክምና (Orthopedic Surgery) እየተሰጠ መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

👉ሆስፒታላችን የተሟላ የአጥንት ቀዶ ህክምና እና የመገጣጠሚያ ህመሞች ህክምና በተሟላ ሁኔታ ልምድ ባላቸዉ የአጥንት ስፔሻሊስት እየሰጠ ይገኛል::

👉በዚህም ከዚህ ቀደም ወደ ሌላ ተቋም ይላኩ የነበሩ ታካሚዎቻችን አገልግሎቱ በሆስፒታላችን እየተሰጠ የሚገኝ በመሆኑ በመሰል ህክምናዎች መላኩ ቀርቶ በሆስፒታላችን መሰጠት መጀመሩን እንገልጻለን፡፡

💧አገልግሎቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ

👉የዳሌ መገጣጠሚያ ህክምና (Hip Dislocation)
👉የእጅ አንጓ ስብራት ህክምና (Wrist Fracture)
👉የታችኛው እግር/ቅልጥም አጥንት ስብራት ህክምና (Open Tibia-Fibula Fracture) እና ሌሎችም ህክምናዎች የተሰጡ ሲሆን፣

💧በሆስፒታላችን:-
👉የአጥንት ስብራት እና ዉልቃት ህክምና
👉የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ኢንፌክሽን ህክምና
👉የመገጣጠሚያ እና የአጥንት ጥመት ማስተካከል
👉የልጆች የጡንቻ እና የአጥንት ህክምና
👉የመገጣጠሚያ ጅማቶች ሕክምና
👉የአጥንት መሳሳት ሕክምና
👉የአርተራይተስ ሕመም ሕክምና
👉የመገጣጠሚያ እና የአጥንት መልሶ ጥገና
👉የጀርባ ሕመም እና መሰል ህክምናዎች መሰጠት እንደሚችሉ ለማሳዎቅ እንወዳለን፡፡

💧ያስታውሱ በሆስፒታላችን በልዩ ልዩ የህክምና ስፔሻሊስቶች በርካታ የቀዶ ህክምናዎች እየተሰጡ የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

👉የድንገተኛ ቀዶ ህክምና (Emergency surgery)
👉በቀጠሮ የሚሰሩ ቀዶ ህክምና(Elective surgery)
👉ከባድ ቀዶ ሀክምና (major surgery)
👉ቀላል ቀዶ ህክምና (minor surgery)

💧በቀጠሮ የሚሰሩ ከባድ ቀዶ ህክምና
👉የእንቅርት ቀዶ ህክምና
👉የሀሞት ከረጢት
👉የሽንት መስመር እጢ
👉የኩላሊት ጠጠር
👉የሰውነት ላይ እባጭ
👉ሄርንያ(ቡአ) እና ሌሎችም

💧ቀላል ቀዶ ህክምናዎች
👉ግርዛት
👉የሰውነት ለይ እባጭ
👉hydrocele(የዘር ፍሬ ውሀ መቋጠር
👉dermoid cysts
👉lipoma
👉የመገጣጠሚያ ውልቃት
👉ቀላል የአጥንት ስብራት

💧 ከማህፀንና ፅንስ ጋር የተያያዙ ቀላል እና ከባድ ህክምናዎች
👉Emergency Gynecological Care (ድንገተኛ የማህፀን ህክምና)
👉Cesarean Section (በቀዶ ጥገና መውለድ )
👉Pelvic prolapse surgery (ለዳሌው ብልት መራቅ ወይም መውጣት ቀዶ ህክምና)
👉surgical treatment for cancers of the cervix, o***y, uterus, v***a, and va**na.
👉የማህጸን በር ጫፍ፣ ኦቫሪ እና ሌሎች የማህጸን ክፍሎች የካንሰር ምርመራ እና የቀዶ ጥገና ሕክምና)
👉Mayoma (የማህፀን ውስጥ እባጭ)
👉ድንገተኛ እንዲሁም በቀጠሮ የሚሰጥ በቀዶ ህክምና ማዋለድ አገልግሎቶች ይሰጣሉ።

🎯ሆስፒታላችን በማንኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙና ቀዶ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዮች በሙሉ ህክምናውን እየሰጠን መሆኑን እንገልጻለን።

        👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡ 👉 የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ...
09/05/2026



👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ቦርድ የ2018 በጀት ዓመት የ3ኛ ሩብ ዓመት ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል፡፡

👉 የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ክቡር መድረኩን የመሩት ሲሆን የሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሌሎች የቦርድ አባላት ስብሰባውን ተካፍለዋል፡፡

👉የቦርዱ ሰብሳቢ የሆኑት ክቡር የመክፈቻ ንግግር በማድረግና የመወያያ አጀንዳዎችን በማስተዋወቅ ስብሰባውን ያስጀመሩት ሲሆን ዋና ዋና የስብሰባ አጀንዳዎችም

1. የ2019 በጀት ዓመት የ9 ዕቅድ አፈጻጸም
2. የሰው ሀይል ማሟላት በሚመለከት
3. እንዲሁም የሆስፒታሉን ቅጥር ግቢ ማስፋፊያ በሚመለከት ናቸው፡፡

👉በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል መሰረት የ2018 በጀት ዓመት የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም በሆስፒታላችን ስራ-አስኪያጅ ቀርቧል፡፡

👉የሰው ሀብት ስብጥሩን ጨምሮ አጠቃላይ ተቋማዊ ዳሰሳ
👉በበጀት ዓመቱ የተሠጡ የጤና አገልግሎቶች ( )
👉ፋይናንሻል ሪፖርት ( )
👉ሪፎርሞችና ዋና ዋና ኢኒሼቲቭስ ( )
👉ያጋጠሙ ተግዳሮቶች (challenges)
👉ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ (Ways Forward) በሪፖርቱ ላይ ተካተው ተብራርተው ቀርበዋል፡፡

👉የተሰሩ ስራዎችንና የቀረቡ ሪፖርቶችን ማዕከል በማድረግ በተሳታፊያን መካከል ፍሬያማ ውይይት ተካሂዷል፡፡

👉የሆስፒታሉ የ9 ወራቶች ዕቅድ አፈጻጸም ሲዳሰስ ከብዙ በጥቂቱ በሚከተሉት አገልግሎቶች ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል፡፡

1. የቅድመ ወሊድ አገልግሎት ያገኙ እናቶች ቁጥር ( -1, -4, and -8 coverage)
2. ለ1997 (106%) እናቶች የወሊድ አገልግሎት መሰጠት መቻሉ ( and )
3. ለ244 (116%) የጽኑ ጨቅላ ህጻናት የህክምና አገልግሎት መሰጠት መቻሉ ( and_Outcome)
4. ለ126,600 (115%) የተመላላሽ ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ተችሏል ( )
5. ለ52 ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ተጋላጭ የማህበረሰባችን ክፍሎች የአንድ መስኮት አገልግሎት ማቅረብ ተችሏል፡፡ ( )
6. 8135 (101%) ታካሚዎች የድንገተኛ ህክምና ማግኘት ችለዋል ( )
7. ለ3686 (107%) ታካሚዎች የአስተኝቶ ህክምና መስጠት ተችሏል፡፡ ( ) ከዚህ ጋር በተያያዘ 85% የአልጋ መያዝ ምጣኔ ተመዝግቧል፡፡
8. ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ያገኙ ታካሚዎች 634 ሲሆኑ ይህም ከዕቅድ አንጻር 101% ሆኗል፡፡ ( )
9. በስፔሻሊቲ ክሊኒኮች ማለትም በአይን ፣ በስነ-አዕምሮ ፣ በቆዳ እና አባላዘር፣ በጥርስ፣ በፊዝዮቴራፒ የህክምና ክፍሎች እና በስነ-ደዌ የምርመራ ክፍል ለበርካቶች አገልግሎት ማቅረብ መቻሉ (Eye_Clinic, , , , , , )

10. እንዲሁም የአዋቂዎች ጽኑ ህክምናም በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል፡፡(Adult ICU)

👉ከነዚህ በተጨማሪ ከወረቀት ነጻ አገልግሎት አሰጣጥ ስራው ከተጀመረበት የበጀት ዓመቱ ጀምሮ ያለመቆራረጥ እና በየጊዜ እየዘመነ መምጣቱ እንዲሁም ሌሎች ዲጂታላይዜሽን ላይ የተሰሩ ስራዎች የምርጥ ተሞክሮ ማዕከል በሚል ቀርቧል፡፡

💧የውስጥ ገቢን ከማሳደግ አንጻር ከዕቅድ አንጻር ጥር አፈጻጸም ላይ መገኘቱ ( )

👉በውይይቱ ወቅትም ከላይ የተዘረዘሩት አፈጻጸሞች በጥሩ ጎን የተነሱና ወደፊትም ሊቀጥሉ ይገባቸዋል የተባሉ ሲሆኑ ይህ በእንዲህ እንዳለ በተደጋጋሚ ለውይይት የቀረበው የህንጻ ግንባታ አለመጀመር በሚመለከት፣ የጤና መድኃን ተጠቃሚዎችን ቁጥር እና እርካታ መጨመር፣ የመድኃኒት አቅርቦት በቀጣይ ትኩረት የሚያሻቸው ናቸው በሚል ሀሳብ ተሰንዝሮባቸዋል፡፡

👉በዚህም መሰረት የህንጻ ግንባታ ከሚመለከተው ባለድርሻ አካል ጋር በመቀናጀት በቶሎ ወደ ግንባታ መግባት

👉የቅጥር ግቢውን ለማስፋት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያሻው

👉ከወቅታዊው የነዳጅ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ሆስፒታሉን በሚመጥን መልኩ አቅርቦቱን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ

👉የመድህኒት በአጠቃላይ የህክምና ግብዓቶችን በሚመለከት የአቅርቦት ሰንሰለቱን በማጠናከር በበቂ ለማቅረብ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ በቀጣይ ሊሰራባቸው ይገባል በሚል ተነስተዋል።

🎯በማጠቃለያውም ክቡር ለተገኙ ስኬቶች የሆስፒታሉን ሠራተኞች ጨምሮ መላውን ባለድርሻ አካላት በማመስገን በአውንታዊ የተነሱ ጉዳዮች ማስቀጠል እንደሚገባ አሳስበው በቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን ስራዎች በዝርዝር አንስተው የስራ አቅጣጫዎችንና መመሪያዎች አስቀምጠው ስብሰባው ተጠናቋል፡፡

      👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተከታታይ 2 ቀናት ሲሰጥ የቆየው እና Hospital Accreditation ፣ Patient safety እና ልዩ ልዩ የሆስፒታል ኢኒሼቲቭስ ላይ ያ...
07/05/2026





👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ለተከታታይ 2 ቀናት ሲሰጥ የቆየው እና Hospital Accreditation ፣ Patient safety እና ልዩ ልዩ የሆስፒታል ኢኒሼቲቭስ ላይ ያተኮረው ኦረንቴሽን በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።

👉ሆስፒታላችን በያዝነው የበጀት ዓመት በልዩ ልዩ የሆስፒታል ኢኒሼቲቮች አመርቂ ውጤት እያስመዘገ እንደሚገኝ ይታወቃል።

👉በመሆኑም ከጤና ሚኒስቴር በመጡ ባለሙያዎች በቀጣይ ሆስፒታላችን በሚመዘንበት Hospital Accreditation program ዙሪያ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል።

👉በስልጠናው ላይ የሆስፒታላችን ስራ-አስኪያጅ በሀገር ደረጃ Hospital Accreditation program ላይ መመረጣችንን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመውሰድ ዛሬ የተሰጠው ኦረንቴሽን መነሻ በማድረግ ሁሉም በየዘርፉ የሚጠበቅበትን እንዲወጣ አሳስበዋል።

👉ከሲዳማ ክልል ጤና ቢሮ የጥራት ቁጥጥር ስራ ሂደት አስተባባሪ በልዩ ልዩ የሆስፒታል ኢኒሼቲቮች ላይ ኦረንቴሽን የሠጡ ሲሆን በኦረንታሽኑም clinical audit፣ Death Audit፣ SBFR እንዲሁም patient safety ተካተውበታል።

👉በኦረንቴሽኑ ላይ ከሆስፒታሉ ልዩ ልዩ ክፍሎች የተውጣጡ በርካታ ባለሙያዎች እና የአስተዳደር ሠራተኞች ተካፍለዋል።

👉በማጠቃለያውም ለ2 ቀናት ሲሰጥ በቆየው ኦረንቴሽን የተካፈሉት የሆስፒታላችን የልዩ ልዩ ክፍሎች ባለሙያዎች በየዘርፎቻቸው እና በየስራ ክፍላቸው ሊከውናቸው ስለሚገባቸው ተግባራት እና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ገለጻ ተደርጎ ፕሮግራሙ ተገባዷል።

    እናመሰግናለን! 👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከይርጋለም ደም ባንክ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት የ2018 ዓ.ም የሶስተኛ ሩብ ዓመት የደም ልገሳ መርሀ-ግብር አከናውኗል...
30/04/2026



እናመሰግናለን!

👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከይርጋለም ደም ባንክ ቅርንጫፍ ጋር በመተባበር በዛሬው ዕለት የ2018 ዓ.ም የሶስተኛ ሩብ ዓመት የደም ልገሳ መርሀ-ግብር አከናውኗል።

👉በመርሀ-ግብሩ ላይ ለተግባር ልምምድ በሆስፒታላችን የሚገኙ የሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች፣ የሆስፒታላችን ሰራተኞች እንዲሁም ሌሎች በጎ ፈቃደኞች ተሳትፈዋል።

👉የሆስፒታላችን ስራ-አስኪያጅ በሩብ ዓመቱ የተካሄደውን መርሀ-ግብር ያስተባበረውን የሆስፒታሉን የደም ልገሳ ኮሚቴ በማመስገን ይህን መሰል የበጎ ስራ እንቅስቃሴዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

👉የቀረበውን የሕይወት አድን ጥሪ ተቀብላችሁ ደም የለገሳችሁና ፕሮግራሙን ያስተባበራችሁ ክቡር የሆነውን የሠውን ልጅ ሕይወት ታድጋቸኋልና ምስጋና ይድረሳችሁ፡፡

በድጋሜ እናመሰግናለን።

     👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከይርጋለም ደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል። 👉ከሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተግባር ልምምድ በሆስ...
30/04/2026




👉የአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከይርጋለም ደም ባንክ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የደም ልገሳ መርሃ-ግብር በመካሄድ ላይ ይገኛል።

👉ከሀዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተግባር ልምምድ በሆስፒታላችን የሚገኙ ተማሪዎችን ጨምሮ ሌሎች በጎ አድራጊዎች የልገሳ ፕሮግራሙ ላይ እየተካፈሉ ይገኛሉ።

👉እርስዎም በሆስፒታላችን በመገኜት በዚህ የሕይወት ጥሪ ላይ በመሳተፍ እንዲለግሱ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

    ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታልየሰብዓዊነት ጥሪ!ደም ይለግሱ – ህይወት ይታደጉ! ለክቡራን የሆስፒታላችን ማህበረሰብ በሙሉ፡፡ ሆስፒታላችን በመጪው ሀሙስ ማለት ሚያዝያ 22/2018 ዓ....
28/04/2026



ከአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል
የሰብዓዊነት ጥሪ!
ደም ይለግሱ – ህይወት ይታደጉ!

ለክቡራን የሆስፒታላችን ማህበረሰብ በሙሉ፡፡

ሆስፒታላችን በመጪው ሀሙስ ማለት ሚያዝያ 22/2018 ዓ.ም የደም ልገሳ መርሀ-ግብር ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል፡፡ በመሆኑም እርስዎም ከጧቱ 2፡30 ጀምሮ በሆስፒታላችን በመገኘት ውድ የሆነውን ስጦታ ይለግሱ ዘንድ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

ደም ይለግሱ። ህይወት ይታደጉ።

በጎነትን እንስፋፋ!

    👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከተገልጋይ ላይ የስርቆት ወንጀል በፈጸመው ግለሰብ ዛሬ በዋለው ችሎት የእስራት ውሳኔ ተላልፏል።  👉የአለታ ወንዶ ከተማ አቃቢ ህግ ባደራጀው የክስ ዝ...
23/04/2026



👉በአለታ ወንዶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከተገልጋይ ላይ የስርቆት ወንጀል በፈጸመው ግለሰብ ዛሬ በዋለው ችሎት የእስራት ውሳኔ ተላልፏል።

👉የአለታ ወንዶ ከተማ አቃቢ ህግ ባደራጀው የክስ ዝርዝር መሰረት መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በሆስፒታላችን ቅጥር ግቢ ከታካሚ ጋር ተመሳስሎ በመግባት ከአገልግሎት ፈላጊ ታካሚን የተንቀሳቃሽ ስልክ ዘረፋ መፈጸሙን የክሱ ዝርዝር ያስረዳል።

👉በዚሀም መሰረት በዛሬው በዋለው ችሎት እሱንም ሌሎች በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰቦችን ያስተምራል በሚል የ 1 ዓመት ከ 6 ወር የእስራት ውሳኔ ተላልፎበታል፡፡

👉የህግ አካላትን እንዲሁም ጉዳዩን ሲከታተሉ የቆዩትን በሙሉ እያመሰገንን መሰል የስርቆት ወንጀሎችን ለመከላከል አሁንም ከህግ አካላትና ከማህበረሰባችን ጋር ተቀናጅተን የምንሰራ ይሆናል፡፡

Address

Aleta

Telephone

+251462240112

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Aleta Wondo General Hospital posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Aleta Wondo General Hospital:

Share