Halaba Zone Health Department - የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ

Halaba Zone Health Department - የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ This is the official Halaba Zonal Health Dept page you can get all the latest information’s.

Detail contact information to follow us:
https://halaba.gov.et/

የ28ኛው ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ግምገማ ጉባኤ (ARM)​የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር አመታዊ የጤና ጉባኤ ከጥቅምት 11 እስከ 13 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 21–23, 2026) በማዕከላዊ ...
19/09/2026

የ28ኛው ዓመታዊ የጤና ዘርፍ ግምገማ ጉባኤ (ARM)

​የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር አመታዊ የጤና ጉባኤ ከጥቅምት 11 እስከ 13 ቀን 2019 ዓ.ም. (October 21–23, 2026) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሆሳዕና ከተማ ይካሄዳል።

በክልሉ የጤና ተደራሽነት እና አገልግሎት ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ ፡በክልሉ ጤና ቢሮ ኃለፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የተመራ የቢሮ ማኔጅመንት ለተከ...
19/09/2026

በክልሉ የጤና ተደራሽነት እና አገልግሎት ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ ፡

በክልሉ ጤና ቢሮ ኃለፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የተመራ የቢሮ ማኔጅመንት ለተከታታይ አራት ቀናት በጤና ተቋማት ያካሄደውን ጉብኝት አጠናቋል ፡፡

በጉብኝቱ የመጀመሪያ ደረጃ ጤና ክብካቤ አሃድ ማጠናከር በበሽታ መከላከል በጤና ተቋማት ተደራሽነት ፣ የህክምና አገልግሎት አሰጣጥ እና ጥራት ማሻሻል ፣ የጽዱ ኢትዮጵያ ኢንሼቲቭ በእናቶች እና ህጻናት ጤና ማሻሻል ፣ በወረርሽኝ ቁጥጥር ላይ የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የግል ጤና ተቋማት አገልግሎቶችን የቢሮ ማኔጅመንት በመዘዋወር ጉብኝት አካሂዷል ፡፡

በጉብኝቱ መንግስት ህብረተሰቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ህብረተሰቡ በጤናው ዘርፍ ተጠቃሚ እንዲሆን የተከናወኑ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን በጉብኝቱ ተገልጿል ፡፡

የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ በጉብኝቱ ማጠቃለያ እንደገለጹት ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኝ በየደረጃው ካለ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት አጠቃላይ እና መሰረታዊ ጤና ኬላዎች ፣ ጤና ጣቢያዎች ማስፋፊያ ግንባታዎች በማጠናቀቅ አገልግሎት ማስጀመር እንዲሁም የመድሃኒት እና የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦት ማሻሻል ላይ ትላልቅ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡

ነባር ጤና ተቋማትም የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እንዲያሻሽሉ ተደራሽ እንዲሆን ህብረተሰቡን አጋር አካላትን በማስተባበር በግብዓት ፣ በህክምና ቁሳቁስ በሰው ሀይል ስልጠና እና አቅም ግንባታ ተከታታይ በተሰሩ ስራዎች አገልግሎታቸው መሻሻል ማሳየቱን ኃላፊው ገልጸዋል ፡፡

በጉብኝቱ የታዩ ውጤታማ ስራዎችን በክልሉ በሌሎች አካባቢዎች የማስፋት እንዲሁም በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች በመለየት እንደሚፈቱ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ ጠቅሰዋል ፡፡

በክልሉ የጤና አገልግሎት አሰጣጥ እና ተደራሽነት ላይ ለመጣው ለውጥ አመራሩ ፣ ህብረተሰቡ ፣ ባለሙያው እና ባለድርሻ አካላት ላበረከተቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል ፡፡

‼️ አስደሳች_ዜና!ለዓይን ህሙማን በሙሉ!""ነፃ የዓይን ምርመራ እና  የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና!!!ዘንባባ ጄኔራል ሆስፒታል ከዳይረክት ኤይድ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ...
18/09/2026

‼️ አስደሳች_ዜና!
ለዓይን ህሙማን በሙሉ!""

ነፃ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና!!!

ዘንባባ ጄኔራል ሆስፒታል ከዳይረክት ኤይድ ኢትዮጵያ የተሰኘዉ ግብረ-ሰናይ ድርጅት ከሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ጋር በመተባበር በበሸኖ የመጀመሪያ ደረጀ ሆስፒታልና በቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ከመስከረም 09/2019 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ነፃ የዓይን ምርመራ እና የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ይሰጣል።

በመሆኑም ማንኛዉም የአይን ጤና ችግር ያለባችሁ በሙሉ በተጠቀሱት ቀናት በቁሊቶና በበሸኖ ሆስፒታሎች በመገኘት ነፃ የአይን ምርመራ እና የአይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን።

የማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በሀላባ ዞን የጤና ልማት ስራዎችን ምልከታ አደረገ፡፡(ሀላባ ቲቪ፣ መስከረም 6/2019) በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የተመራ የቢሮ ማኔጅመን...
16/09/2026

የማዕከላዊ አትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ በሀላባ ዞን የጤና ልማት ስራዎችን ምልከታ አደረገ፡፡

(ሀላባ ቲቪ፣ መስከረም 6/2019) በክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የተመራ የቢሮ ማኔጅመንት በዞኑ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ በሚገኙ የጤና ተቋማት ምልከታ አድርገዋል ፡፡

በምልከታው የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታልና የሀላባ ቁሊቶ ጤና ጣቢያ የመሠረታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥ ያለበትን ደረጃ አመራሮቹ ምልከታ አድርገዋል።

በምልከታው እየተሰሩ ያሉ የጤና ልማት ስራዎች ፣ የጤና አገልግሎት ማሻሻል ፣ የማህበረሰብ መረጃ ስርዓት ማጠናከር ፣ ከወረቀት ነፃ አገልግሎት አሰጣጥ፣ የጤና ተቋማትን በህክምና መሳሪያዎች ማደራጀትና በአገልግሎት ለማዘመን የተሰሩ ስራዎች ምልከታ ተካሂዷል ፡፡

በምልከታው ወቅት የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ዳርጌ የጤና አገልግሎቱን ቀልጣፋ ለማድረግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል።

ሀላባ ቲቪ

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2019 የሁለት ወረት እቅድ አፈጸጸም የ PMT እና 36ኛ ሳምንት RRT ግምገማ መድረክ ተካሄደ ****************(መስከረም 06/2019 ዓ/ም) የአ...
16/09/2026

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2019 የሁለት ወረት እቅድ አፈጸጸም የ PMT እና 36ኛ ሳምንት RRT ግምገማ መድረክ ተካሄደ
****************
(መስከረም 06/2019 ዓ/ም) የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት የ2019 የ2 ወረት እቅድ አፈጸጸም (PMT) አና የ RRT የግምገማ መድረክ ተካሂዷል።

የግምገማ መድረኩን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ሀላፊ አቶ ሙፍቲ አወል እና የጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ ከአቶ ሸሪፎ ከዲር ጋር በጋራ የመሩ ስሆን
ለዉይይት መድረክ የተዘገጀዉን ሰነድ የጽ/ቤት ልማት እቅድ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ሙሉብርሃን ፓስካል አማከይነት ቀረቡዋል

በዚህ ወቅት የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ዋና ሀለፊ አቶ ሙፍቲ አወል እንዳገለጹት በሽታ መከለከል ተግባራት በተለይ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ላይ ማህበረሰብን በመሳተፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጹዋል። የእናቶችና ህፃናት ጤና በተመለከተ የክትባት አገለግሎት ሁሉንም አይነት ክትባት መውሰድ የሚገባቸው ህፃናት እንዲየገኙ በትኩረት መስረት ያስፈልጋል ብሉዋል።

በማጠቃለያው አፈጻጸም ዝቅተኛ ሆነው የተለዩ ተግባራት ላይ በሁሉም ስራ ህደቶች የድርጊት መርሃ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባት እንዳለብን የጽ/ቤቱ ዋና ሀላፊ አቶ ሙፍቲ አወል አሳስቧል።

በመድረኩ ለይ የ የጽ/ቤት ማናጅሜንት አባለቶችና ባለሞያዎች የጤና ጣብያ ሀላፊዎች እና ሱፐርቫይዘሮች ተገኝተዋል።

14/09/2026
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የወባ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል የቤት ለቤት ፀረ-ወባ ኬሚካል ርጭት ስልጠና ተጀመረ፦ መስከረም 4/2019​የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት የወባ በሽ...
14/09/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የወባ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል የቤት ለቤት ፀረ-ወባ ኬሚካል ርጭት ስልጠና ተጀመረ፦ መስከረም 4/2019

​የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ጤና ጽሕፈት ቤት የወባ በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል የቤት ለቤት ፀረ-ወባ ኬሚካል ርጭት ቅድመ-ዝግጅት ስልጠና ለባለድርሻ አካላት በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል።

​ለተከታታይ ሶስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን በክረምት ወቅት ሊከሰት የሚችለውን የወባ በሽታ ስርጭትና ጫና አስቀድሞ መከላከልና መቆጣጠርን ታላሚ ያደረገ ነው።

​የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰይፈድን ቱሊሳ በስልጠናው መክፈቻ ላይ እንደገለጹት፣ የበሽታውን ስርጭት ለመግታት የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑን ገልፀው ሰልጣኞችም ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ለሚከናወነው የቤት ለቤት እርጭት ስራ ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

በዞኑ በ36ኛው ሳምንት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ፣ የወባና የስርዓተ ምግብ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት፣ መደበኛ የጤና እንዲሁም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ተገመገመ...
14/09/2026

በዞኑ በ36ኛው ሳምንት የሕብረተሰብ ጤና ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ፣ የወባና የስርዓተ ምግብ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት፣ መደበኛ የጤና እንዲሁም የክረምት በጎ ፈቃድ ተግባራት ተገመገመ።

በሳምንቱ የወባ በሽታ ልጨምርባቸው በሚችሉ አከባቢዎች ላይ ልዩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶክተር ሸምሱ ረሽድ ተጠቁሟል።

መስከረም /2019 የሀላባ ጤና መምሪያ | ቁሊቶ
____

በዞኑ የወባና የስርዓተ ምግብ ክስተት አስተዳደር ሥርዓት ተዘርግቶ በተሰሩ የተቀናጁ ሥራዎች የወባ ስርጭት ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ስነፃፀር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገልጿል።

የወባ ስርጭቱ አሁንም ከወረርሽኝ ማስጠንቀቂያ ወሰን (epidemic threshold) አንጻር ቀሪ ሥራዎች እንዳሉ ማዕከሉ አስታውቋል።

የወባ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የበሽታ ቅኝት፣ ቅድመ ልየታ፣ የላቦራቶሪ ምርመራ፣ ተገቢ የሕክምና አገልግሎት፣ የትንኝ መራቢያ አከባቢ ቁጥጥርና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል እንዳለባቸው ተገልጿል።

የስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ችግርን ለመቀነስ የተከናወኑ የቅኝት፣ የቅድመ ልየታና የምላሽ ሥራዎች አበረታች ውጤት እያሳዩ መሆናቸውም ተጠቁሟል።

የዞኑ ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶክተር ሸምሱ ረሽድ እንደገለጹት፣ ከአየር ፀባይ ለውጥና መዛባት ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ ኮሌራ፣ ወባ፣ ኩፍኝ እና እከክ (scabies ) በሽታን የመሳሰሉ በሽታዎችን ቀድሞ ለመለየት የቅኝትና የአሰሳ ሥራዎች መጠናከር አለባቸው ብለዋል።

በወባና በስርዓተ ምግብ አለመመጣጠን ላይ የተመዘገበውን ውጤት ማስቀጠል እና አዳዲስ የጤና ስጋቶችን በቅድሚያ መለየት ይገባልም ብለዋል።

በሳምንት የተመዘገቡ አበረታች የጤና ውጤቶችን ማስቀጠል፣ እንዲሁም ከአየር ፀባይ ለውጥ ጋር ተያይዘው ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና ስጋቶችን ለመከላከል ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ልሠራ እንደሚገባ ተገልጿል።

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ 2019 አዲሱን አመት አስመልክቶ በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝቶ ለሚታከሙ ህሙማን ማዕድ አጋራ=====መስከረም 1/2019 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ 2019 አ...
11/09/2026

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ 2019 አዲሱን አመት አስመልክቶ በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝቶ ለሚታከሙ ህሙማን ማዕድ አጋራ
=====

መስከረም 1/2019 የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ 2019 አዲሱን አመት አስመልክቶ በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ተኝቶ ለሚታከሙ ህሙማን ማዕድ አጋርተዋል።

የአዱሱን አመት ማስመልከት ማዕድ ያጋሩት በሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ውስጥ ተኝቶ ታካሚ የህብረተሰብ ክፍሎች ነው።

በራስ ተነሳሽነትና በመልካምነት የሚመነጨው ይህ በጎ ተግባር ዘርና ቀለም፣ ብሔርና ሀይማኖት የማይለይ በመሆኑ የመረዳዳትና የመደጋገፍ በጎ እሴት ይበልጥ እየጎለበተ እንዲሄድ ማስቻሉን ተመልክቷል።

የተቸገሩ ወገኖችን የመርዳትና የመደገፍ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል።

ዛሬ በሆስፒታሉ የተካሄደው ሰው ተኮር በጎ ስራዎች የዚሁ ማሳያ ናቸው ተብለዋል፡፡

በዚህም የዞኑ ጤና መምሪያ ማኔጅመንት አባላትና የሆስፒታሉ ስራአስኪያጅ ዶክተር ከይረዲን ሀቢብ፣ የሆስፒሉ ማኔጅመንት የህክምና ባለሙያዎች የአዱሱን አመት ማስመልከት ተኝቶ ታካሚዎችን በማጠየቅ ማዕድ መጋራት ችለዋል።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

አመራሩ የህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የሚጠበቅበትን ድጋፍ በብቃት ሊሠጥ ይገባል!፦አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊየሀላባ ዞን ...
11/09/2026

አመራሩ የህዝቡ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ወደላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር የሚጠበቅበትን ድጋፍ በብቃት ሊሠጥ ይገባል!፦አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ

የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የዞኑን አመራር ታችኛውን መዋቅር ቀበሌ ወርዶ የህዝብን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ማህበራዊ፣ የመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ አስመልክቶ ድጋፍ እንዲሰጥ አረንቴሽን ሰጥቶ አሰማርተዋል።

ኦረንቴሽኑን የሰጡት ​አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ በዞኑ በየደረጃው የሚገኘው አመራር በፓርቲ መሪነት፣በጠንካራ የመንግሥት አፈጻጸም በየዘርፉ የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን ብርቱ ጥረት ይበልጥ ማለቅ ከአመራሩ ይጠበቃል ብለዋል።

በዚህም በዞኑ በየመዋቅሩ ከነገ ጀምሮ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚሠማራው ይህ የአመራር የሱፐርቪዥን ቲም እስከታችኛው ቀበሌ ድረስ በመውረድ በጥብቅ የፓርቲ ዲስፕሊን በቼክሊስት የተደገፈ የተደራጀ የክትትል እና ድጋፍ ስራ እንደሚያደርግ ሀላፊው ገልፀዋል።

​የሱፐርቪዥን ቡድኑ በዋናነት ትኩረት አድርጎ በጥልቀት እንዲመለከት፣የሚከታተላቸው እና የሚያጠናቅቃቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች አቶ መሀመድከማል በዝርዝር አብራርተዋል።

በዚህም የ2019 በጀት አመት ፈጻሚ ማዘጋጃ አተገባበር ያለበትን ደረጀ የ2019 የትምህርት ዘመን አጀማመር እና ምዝገባ በተለይም ​የትምህርት ዘመኑን አስመልክቶ ይፋ በተደረገው አቅጣጫ መሰረት መስከረም 2 ቀን ትምህርት በይፋ እንደሚጀመር ተገልጿል።​

​ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ክፍት መሆናቸውን እና የመዝገብ ሂደት ዝግጅት መጠናቀቁን በሱፐርቪዥኑ ማረጋገጥ ይከናወናል።

​የክረምት የበጎ አድራጎት እና የልማት ስራዎች ማጠቃለያ ያለበትን ሁኔታ የሱፐርቪዥን ቡድኑ በትኩረት እንድመለከት ያሳሰቡት ሀላፊው​ በክረምት የበጎ አድራጎት መርሃ ግብር የተጀመሩ የአርሶ አደሮች ማሳ እንክብካቤ፣ የቤት እድሳት እና የአረንጓዴ አሻራ ስራዎች በላቀ ሁኔታ መከናወናቸው ገልጿል።

​የቀሩ አላስፈላጊ አካላዊ እና ቴክኒካዊ ክፍተቶችን በመለየት ስራዎቹ ሙሉ በሙሉ እንዲጠናቀቁ እንደሚደረግም አንስተዋል።

​የመልካም አስተዳደር እና የፖለቲካ ኢኮኖሚ አጀንዳዎችን በዝርዝር እንዲመለከት ኦረንተሼን የሰጡት አቶ መሀመድከማል ​ከተረጅነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የታቀዱ የልማት ስራዎች እና የአርሶ አደሩን ምርታማነት ይበልጥ ለማሳደግ ላይ ትኩረት እንዲያደርግ ድጋፍ ማደረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

​ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን፣ የአሰራር ክፍተቶችን እና የአመራር ድክመቶችን በግልጽነት በመገምገም የመፍትሄ አቅጣጫ በማስቀመጥ የሱፐርቪዥን ቡድኑ የራሱን ሀላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባም ሀላፊው አስምረውበታል።

​የሱፐርቪዥን ቡድኑ በየቀበሌው የሚገኙ የመዋቅር አመራሮች፣ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች እና የሙያ ባለቤቶች ጤና ኤክስቴንሽን እና የግብርና ባለሙያዎች በተሳተፉበት መድረክ ተጨባጭ መረጃዎችን በመሰብሰብ እና ሰነዶችን በመመርመር አንገብጋቢ ክፍተቶች ሲያጋጥሙም ፈጣን ግብረ-መልስ እየሰጠ ተገቢውን እርምት መውሰድ እንዳለባትም
አስታውቋል።

​ሱፐርቪዥን ቡድኑ የሚያከናውነው የተደራጀ የክትትል እና ድጋፍ ስራ ለቀጣይ ወሳኝ ሥራዎች በግብአትነት እንደሚጠቅም የገለፁት ሀላፊው እስከ መስከረም ቀን 30 ድረስ በሚደረጉ ሰፊ የህዝብ እና የፓርቲ መድረኮች የወደፊት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ለማቃናት ትልቅ መነሻ እንደሚሆን አመላክቷል።

Address

Halaba
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Halaba Zone Health Department - የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share