በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት time is technology

በለዉጡ መንግስት የንፁህ መጠጥ ዉሃን ተደራሽነትን ለማስፋትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ ግንቦት 12/2018 በሀላባ ዞ...
21/05/2026

በለዉጡ መንግስት የንፁህ መጠጥ ዉሃን ተደራሽነትን ለማስፋትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ገለፁ

ግንቦት 12/2018 በሀላባ ዞን ዌራ ወረዳ በለዉጡ መንግስት የንፁህ መጠጥ የዉሃን ተደራሽነትን ለማስፋትና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ ገልፀዋል ።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ ይህንን የገለፁት በዛሬው ዕለት በመንግሥት ትብብርና በመካና የሱስ ድርጅት ድጋፍ የሀቢቦ ፉራና ቀበሌ የንፁህ መጠጥ ዉሃ ቁፋሮ በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው ።

ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በአከባቢ የንፁህ መጠጥ ውሃ በአቅራቢያው ባለመኖሩ ለዘመናት ማህበረሰቡ ስቸገሩ የነበሩበት በዛሬው ዕለት መፈታት መቻሉን ገልጸዋል።

አያይዘው መንግስት በጊዜ ሂደት የማህበረሰቡን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት እየፈታ መሆኑን ጠቁመው አሁንም ቢሆን የህዝቡን አዳጊ የልማት ጥያቄ በየደረጃው ለመመለስ በልዩ ትኩረት እየሠራም ነው ብሏል ።

ስለዚህ ህዝቡ በለውጡ መንግስት እየተከናወነ ያለውን ልማት ሥራ በመንከባከብ ቀጣይም በዕቅድ ለመሥራት የተያዙ መሠረተ ልማትን ጨምሮ ሌሎች የልማት ሥራዎችን በትዕግሥት በመጠባበቅ ከመንግስት ጎን መሆን እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

የሀላባ ዞን ውሃ ማዕዲን ኢነርጂ መምሪያ ሀላፊ አቶ አ/አዚዝ ከይራዲን በበኩላቸው ይህንን ሃብት የአካባቢው ህብረተሰብ በእንክብካቤ መጠበቅ እንዳለበት ገልፀዋል ።

የአከባቢዉ ማህበረሰብ በመንግስት ትብብርና በመካናየሱስ ድርጅት የንፁህ መጠጥ ውሃ በቅርበት አገልግሎት እንዲያገኝ ላደረገዉ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል ።

የዌራ ወረዳ ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መ/ሻፊ አሳሞ በበኩላቸው እንደገለፁት ለህብረተሰቡ አስፈላጊና መሠረታዊ ከሆኑ ልማቶች አንዱ የሆነውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር እንደ ወረዳ በዘላቂነት ለመፍታት በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በትኩረትና በቅንጅት ይሰራል ብለዋል።

በተለይ ከመሠረታዊ ፍላጎቶች እጅግ አስፈላጊ የሆነው ፍትሀዊ የንፁሁ የመጠጥ ውሃ ሽፋን በወረዳው ተደራሽነትን በማስፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል ።

በመርሃግብሩ ላይ የፕሮጀክቱ አስተባባሪዎች የቀበሌው አመራሮች እና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

ከበርካታ ከዓለም ሀገሮች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነየሱስ ልማት ድርጅት አስተባባሪዎች ባለፉት ዓመታት በዌራ ወረዳ የተሰሩ የዉሃ ልማት ስራዎችን አካላዊ ምልከታና ግ...
02/05/2026

ከበርካታ ከዓለም ሀገሮች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነየሱስ ልማት ድርጅት አስተባባሪዎች ባለፉት ዓመታት በዌራ ወረዳ የተሰሩ የዉሃ ልማት ስራዎችን አካላዊ ምልከታና ግምገማ አደረገ።

ሚያዚያ 24/2018 ከበርካታ ከዓለም ሀገሮች የተውጣጡ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነየሱስ ልማት ድርጅት አስተባባሪዎች ባለፉት ዓመታት በሀላባ ዞ በዌራ ወረዳ የተሰሩ የዉሃ ልማት ስራዎችን አካላዊ ምልከታና ግምገማ አድርገዋል ።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስትያን መካነየሱስ ልማት ድርጅት የተሰሩ ስራዎችን በቦታዉ በአካል በመገኘት የፕሮጀክቱን ዉጤታማነት ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

የፕሮጀክቱን ጥራት፣በወቅቱ ከማጠናቀቅ እና የህዝቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የተሰራዉን ስራ በማድነቅ ቀጣይ በወረዳዉ ያለዉን የዉሃ ችግር በዘላቅነት መፍታት በምቻልበት ጉዳዮች ዉይይት ተደርጓል።

ፕሮጀክቱ ባለፋት ዓመታት በተሰሩ ስራዎች ዉጤት መመዝገቡንና ለሌሎች ፕሮጀክቶች ተሞክሮ መሆን የምችል እንዲሁም ስኬታማነቱ የላቀ መሆኑንም አንስተው ለስኬታመነቱ የመንግስት ና የህዝቡ ትብብር አቅም መሆኑንም ገልፀዋል ።

ፕሮጀክቱ በወረዳው የነበረበትን የውሃ ችግሮችን በመፍታት ለነዋሪዎቹ ምቹ እና ቀጣይነት ያለው አገልግሎት ለመስጠት እየሰራ ያለውን ስራ ተመልክተው አድንቀዋል ።

የንጹህ መጠጥ ውሃ ችግር መፍታት የህብረተሰቡን በርካታ ማህበራዊ ችግር መፍታት ነው ያሉት የፕሮጄክቱ አስተባባሪዎች በወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽነትን በማሻሻልና የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሰራ ያለው ስራ በቀጣይም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብሏል ።

ሁሉም ተባብሮ ተቀናጅቶ ከሰራ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚቻል የገለፁት የዌራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከድር የሴ በወረዳው በንፁህ መጣጥ ውሃ ላይ በርካታ ስራዎችን እየሰራ የሚገኘውን የመካና የሱስ ድርጅትን አመስግነው በቀጣይም በፕሮጀክቱ ጎን ሆነው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል ።

በመስክ ምልከታ ላይ ኤመንዳ የምስራቅ አፍርካ የፕሮጀክቱ ዳይራክተርአቶ ብቅላ አባያ: የእ/ዌ/ቤ/ክ/መ/የሱስ ልማትና ማህበራዊ አገልግሎት ኮሚሺን የፕሮግራሞች ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ቢቂላ አበያ EECMY DASSC ፕሮግራሞች ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ተርፋሳ መኮ EECMY DASSC CNE AO ስራ አስኪያጅ የዌራ ወረዳ ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መ/ሻፊ አሳሞና ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል ።

✍️በአስራሩ ጀማል

በጤናው ዘርፍ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።  #የአሚን ሆስፒታል ደረጃ በጠበቀ መመልኩ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ለመገንባት መሠረተ-ድንጋይ ተቀምጧል። ሚያ...
02/05/2026

በጤናው ዘርፍ የግሉ ዘርፍ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለፀ።
#የአሚን ሆስፒታል ደረጃ በጠበቀ መመልኩ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ለመገንባት መሠረተ-ድንጋይ ተቀምጧል።
ሚያዚያ 22/2018 ሀላባ ቲቪ
------------
በመርሐግብሩ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መሐመድ ኑርዬ የአሚን ሆስፒታል መስራች ዶ/ር መሐመድ ሽኩር የጤናውን ዘርፍ ለመደገፍ እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።

አክለውም መንግስት በጤናው ዘርፍ የጤና ፖሊሲን ሪፎርም በማድረግ በሽታን ከመከላከል ወደ አክሞ ማዳን በማሳደግ ከፍተኛ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል።

የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ሳሙዔል ዳርጌ በበኩላቸው የሀገራችንንና የክልላችን መንግስት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በግሉ ዘርፍ የሚንቀሳቀሱ ሆስፒታሎች የመንግስት ሆስፒታሎችን ለማገዝ አቅም ስላላቸው የሚበረታታ ነው ብለዋል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ለመገንባት መሠረተ ድንጋይ የተጣለው ይህ አሚን ሆስፒታል የመንግስት ሆስፒታሎችን የስራ ጫና ለመቀነስ የሚያግዝ መሆኑን ተናግረዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው የአሚን ሆስፒታል መስራች ዶ/ር መሐመድ ሸኩር ከአዲስ አበባ ውጪ ሆስፒታል ለመገንባት ሀላባን ስለመረጡ በሀላባ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የሀላባ ህዝብ የጀመረውን ፕሮጀክት ገንብቶ በመጨረስ የሚታወቅና በራሱ ጥረት በርካታ ልማቶችን ገንብቶ በማጠናቀቅ የሚታወቅ አርበኛ ህዝብ መሆኑን አቶ ሙህዲን ጠቁመዋል።

የሀላባ ዞን ከለውጡ ወዲህ የጤና ተደራሽነትን ለማስፋፋት በርካታ የጤና ተገንብተው መጠናቀቃቸውን ጠቁመው በግሉ ዘርፍ ያሉ የጤና ተቋማትም እያበረከቱት ያለው አስተዋፅዖ ከፍተኛ መሆኑን አብራርተዋል።

የአሚን ሆስፒታል መሥራች ዶ/ር መሐመድ ሹኩር በበኩላቸው በሀላባ ውስጥ ሆስፒታል ለመገንባት ያነሳሳቸው የሀላባ ህዝብ ፍቅር የሆነ ህዝብ በመሆኑ እንደሆነ ገልፀዋል።

በቀጣይ በሀላባ ዞን ያሉ የጤናውን ዘርፍ ስራዎችን ሁሉ በመተጋጋዝ እንደሚሰሩ ዶ/ር መሐመድ ሹኩር አብራርተዋል።

በመድረኩ ላይ በቅርቡ ወደ ፕርሚየር ሊግ የተቀላቀለውን የሀላባ ከነማን ለመደገፍ 2 ሚሊዮን ብር ለመስጠት ቃል ገብተዋል ።
ምንጭ Halaba Tv

በመሐመድ ሞክሼ

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ  ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመቀናጀት የተዘጋጅ ወረዳ አቀፍ የትምህርት ቤቶች ፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን በዛር ...
24/04/2026

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከወረዳው አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመቀናጀት የተዘጋጅ ወረዳ አቀፍ የትምህርት ቤቶች ፈጠራ ስራ ኤግዚቢሽን በዛር የፓናል ዉይይት መድረክ ተካሄደ!!!
***************
‎(ሚያዝያ፣ 16/2018 ዐዓ.ም) የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከወረዳው ከትምህርት ጽ/ቤት በጋራ በመሆን የሳይንስና ሂሳብ የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽንና ውድድር በዌራ ወረዳ በቆጮጬ በመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት ተካሄዷል።

‎"ሰይንስ ይመራናል ቴክኖሎጂ ያስቀድመናል" በሚል መሪ ሀሳብ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተሳተፉበት የፈጠራ ስራዎች ኤግዚቢሽን እና ውድድር ተካሄዷል ።

‎የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኑረዲን ሽፋ፣የዌራ ወረዳ የት/ት ጽ/ቤት ም/ሃላፊ አቶ አ/ሰመድ ሽፋ፣ ከወረዳዉ ዉስጥ ከሉት ከተለያዩ ት/ቤት የተሰተፉ የፈጠራ በለቤቶች ሪ/መምህራን ፣ መምህራን ፣የጽ/ቤት መነጅመንት አከለት እና የቆጮጬ ት/ቤት ተማርዎችና መምህራን በተገኙበት መድረኩ ተካሄዷል ።

‎በዘርፉ የተሻለ ጥረት ማድረግና ስራውን ይበልጥ ማሳደግ ያስፈልጋልም ተብሏል።

‎የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንቴክኖሎጂ ቴክኖሎጃ ጽ/ቤት ኃላፊ እንዳሉት የበለፀጉ ሀገራት ሚስጥር ለሳይንስና ፈጠራ ስራዎች ውጤትና ለዘርፉ የሰጡት ልዩ ትኩረት መሆኑን ገልፀው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ቁልፍ ሚና እንዳለው አስረድተዋል።

‎በወረዳ ደረጃ የፈጠራ ስራዎችን የሚያበረታቱ ጅምር ስራዎች የበለጠ በማጠናከር በተለያዩ የትምህርትና ስልጠና ማዕከላት እየተሠራ የሚገኝ ቢሆንም አሁን የበለጠ ወረዳዊ የፈጠራ አቅማችንን በሚያጎለብትና ቀጣይነቱ የሚያረጋግጥ ቅንጅታዊ ስርዓት ከትምህርት ማዋቅር ጋር በጋራ እየተመራ ይገኛል፡፡


‎አቶ ኑረዲን ሺፈ አያይዘውም ቴክኖሎጂ ለአዲሱ ትውልድ ቋንቋ በመሆኑ የፈጠራ ስራዎችን ለውጤት ማብቃት እና የማህበረሰቡን ችግር የሚያቃልል አድርጎ ወደ ውጤት መቀየር ያስፈልጋል በማለት የፈጠራ ተሰጥኦ ላላቸው ተማሪዎች ልዩ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል።

‎የዌራ ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊ አቶ አብድልሳመድ ሽፋ ለማህበረሰቡ የኑሮ ሁኔታ የሚያቀል እና ግዜን የሚቆጥብ ዘርፍ በመሆኑ ተማሪዎች ለሳይንስና ፈጠራ ስራ ልዩ ትኩረት መስጠት አላባቸው ብለዋል።

በመጨረሻም በዕለቱ በፈጠራ ስራቸው ተወዳዳሪ ለሆኑ አካለት የገንዘብና የሰርተፊኬት ሽልማት በመበርከት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል ።

የዌራ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

 #በኢኮቴ መሰረት ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ፡፡ ወራቤ፣ ሚያዚያ 1...
23/04/2026

#በኢኮቴ መሰረት ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ክህሎት ማጎልበት ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ገለፀ፡፡

ወራቤ፣ ሚያዚያ 15/2018ዓም፡-ስልጤ ዞን ኮሙኒኬሽን

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዞንና ለልዩ ወረዳ ለተውጣጡ የኢኮቴ ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት በወራቤ ከተማ እየሰጠ ያለው ስልጠና ዛሬም እንደቀጠለ ነው…

የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምክትል ቢሮ ኃላፊና የኢኮቴ ልማት አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ተወካይ አቶ እስጢፋኖስ ጡራሞ የአቅም ግንባታ ስልጠናው በኢኮቴ መሰረተ ልማት ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲመጣ ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል፡፡
ቢሮው ከተጣለበት ኃላፊነት በመነሳት መጠነ ሰፊ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ያሉት አቶ እስጢፋኖስ የዘርፉን ባለሙያዎች ክህሎት መገንባት ተቀዳሚ ተግባሩ አድርጎ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡

በተለይ በበጀት ዓመቱ ተከታታይነት ያላቸው የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ሲሰጡ መቆየቱን ጠቅሰው ለክልሉ ዜጎች የሚሰጣቸው አገልግሎቶች ዘመኑን የዋጀ በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ በዕቅድ ተይዞ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝም አብራርተዋል፡፡

በዚህም በክልሉ የተቋማት አገልግሎቶች በኢኮቴ መሰረት ልማት እንዲታገዙ በማድረግ ረገድ አበረታች ውጤቶች ማስመዝገብ ተችሏል ብለዋል፡፡

በዘርፉ እየተመዘገቡ ያሉ ውጤታማ ስራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የዘርፉን ባለሙያና ባለድርሻ አካላት አቅም መገንባት ወሳኝ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በትላንትናው ዕለት በህዋዌ ኦፕሬትንግ ኔትወርኪንግ ርዕሰ ላይ ያተኮረ ስልጠና በITSC ካምፓኒ ከፍተኛ የኔትወርክ ባለሙያ አቶ ሐብታሙ አሳይቶ መሰጠቱ ይታወሳል፡፡
ዛሬም ልክ እንደትናንቱ በተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያነጣጠረ የክህሎት ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል፡፡

20/04/2026
👉👉በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የ2018 የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ!!!መጋቢት 09/2018 የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የጽ/ቤቱ ማ...
17/04/2026

👉👉በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የ2018 የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ!!!

መጋቢት 09/2018 የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አከላት በተገኙበት የ2018 የ9 ወር ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ገምግሞ ቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጧል ።

በሁሉም ዛርፍ እያተከነዎኑ የሉ ተግባራትን ትኩረት በመስጠት ስራዎች ዓላማ ተኮር ሆነው በተቀደዉ እቅድ መሰረት እንዲከናወኑ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባም የጽ/ቤቱ ሃለፊ አቶ ኑረዲን ሺፈ አስገንዝበዋል፡፡

# #በአጠቃላይ በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥና በዕቅድ ትግበራ፣ በ2018 በጀት አመት የ9ወር ዕቅድ ተግባር፣ በታቀደለት ጌዜ እያተከነዎና እያሄዳ ነዉ የሚለዉን በስፈት በመገምገም ቀር ተግበራት በቀጠይ እቅድ ተቅደዉ መሰራት እንዳለባቸው በሰፊው ተመልክተዋል።

ከጽ/ቤቱ ማኔጅመንት አካላት ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የጽ/ቤቱ ሀላፊ አቶ ኑረዲን ሺፈ ምላሽና ማብራሪያ በመስጠት በቀጣይ የነበሩ ጥንካሬዎችን ይበልጥ ማስቀጠልና ጉድለትችን ማረም በሚቻልበት ሂደት የጋራ መግባባት በመፍጠርና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማስቀመጥ መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጨወታ ውድድር ሀላባ ከተማ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በሆነው ውጤት በመሸነፍ ወደ ከፍተኛ ፕሪሚየርሊግ ተቀላቅለዋል። እንኳን ደስ አላችሁ!!!!
15/04/2026

የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ጨወታ ውድድር ሀላባ ከተማ ደሴ ከተማን 1 ለ 0 በሆነው ውጤት በመሸነፍ ወደ ከፍተኛ ፕሪሚየርሊግ ተቀላቅለዋል። እንኳን ደስ አላችሁ!!!!

11/04/2026
በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት  አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት በቁፌ ክለስተር በቁፌ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ሳምንት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ።የዌራ ወረ...
08/04/2026

በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት አዘጋጅነት በዛሬው ዕለት በቁፌ ክለስተር በቁፌ በመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ሳምንት በደማቅ ሁኔታ ተከበረ ።

የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ከወረዳዉ ት/ት ጽ/ቤት ጋር በመሆን ሳይንስና ቴክኖሎጂን መተግበር ለትውልድ ተስፋን መመገብ ነው ፤ የሚሞክሩት ይበረታታሉ የሚችሉት ይፈጥራሉ በሚል መሪ ቃል በቁፌ ክለስተር በቁፌ በመጀመርያ ደረጃ ት/ቤት የሳይንስ ሳምንት በደማቅ ሁኔታ አክብሯል ።

የዕለቱን የሳይንስ ሳምንት ክብረ በአል በንግግር የከፈቱት የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት ኃላፊ ኑረዲን ሺፋ የሳይንስ ሳምንትን ማክበር የተማሪዎችን የሳይንስ ትምህርትና የፈጠራ ፍላጎት ያነሳሳል ያሉ ሲሆን በቀጣይም ተማሪዎች በሳይንስ ክበብ ጠንካራ ተሳትፎ በማድረግ በርካታ የማህበረሰባችንን ችግር ፈቺ የሆኑ በግብርና ፣በጤና ፣በትምህርት በተለያዩ ዘርፎች የፈጠራ ሥራዎችን መስራት እንደሚችሉ በማስገንዘብ ለዚህም ጽ/ቤቱ በቅንጅት የሚሠራ መሆኑን አስታውቋዋል።

በመቀጠልም የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት የሳይንስ ዘርፍ አስተበበር የሆኑት አቶ ከይሩ አበብያ እንደሉት ተማርዎች ለሳይንስ ትምህርት እና ለሳይንስ ክበብ ትኩራት በመስጠት የአከበብዉን ችግር ጥነት በመድረግ ሀሳብ በመፍላቅ በወደደቁ ነገርች ሙካራ በመድረግ የፈጠራ በለቤት በመሆን የማህበራሳቡን ችግር መፍተት ትችለለችሁ በማለት ሁሉም በለድርሻ አከለት በቅንጅት መስራት አለብን ብሏል።

በመጨረሸም በተማርዎችና በመምህራን የተሞከሩ ሙካራዎችን ተጠነክራዉ መሰራት እንደለበቸዉና የተሸሉ ፈጠራዎች ተለይተዉ ለወረዳ ኤግዝብሽን መቅረብ እንደለበቸዉ በመወያያት የጋራ በመድረግ ተጠቀሏል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to በሀላባ ዞን የዌራ ወረዳ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት:

Share