የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ

የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ, Government Official, Alaba K'ulito.
(1)

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላምና ደኅንነት አፈፃፀም ገመገመ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27 ቀን...
04/06/2026

የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላምና ደኅንነት አፈፃፀም ገመገመ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢ.ፌ.ፖ.ሚ)፦የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፀጥታና ደኅንነት አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት ተገምግሟል።

በመድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የጋራ ግብረ ኃይሉ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫው ወቅትና ከምርጫ በኋላ ያሉ ስራዎችን እንደ ሀገር ዕቅድ አውጥቶ በቅንጅት በመመራቱ፤ በተግባር የተፈተሸ፣ የተናበበና ሰላምን ለማፅናት ጀግንነት የታየበት ተግባር በመፈፀሙ ምርጫው በሰላም ሊጠናቀቅ ችሏል ብለዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አያይዘውም ባለፉት የለውጥ ዓመታት በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶት በፀጥታና ደህንነት ተቋማት ላይ በተሰራው ሪፎርም አሁን ላይ በተጨባጭ ትላልቅ ተልዕኮዎችን መሸከም የሚችሉ የፀጥታ ተቋማት መፈጠራቸውን በምርጫው ላይ የተመዘገበው ውጤት ማሳያ ነው ብለዋል። የጋራ ግብረ-ኃይሉ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለማደናቀፍ በሀገር ውስጥና በውጭ ጠላቶች የተቀናጀውን ከፍተኛ ሴራ ያከሸፈ፣ ያመከነና የሀገርን ሉዓላዊነት ያረጋገጠ፤ የሪፎርሙ ውጤት በተግባር የተለካበትና የታየበት መሆኑንም ገልፀዋል።

እንደ ፀጥታ ተቋም መኩራትና መመካት ያለብን በኢትዮጵያ ህዝብ ነው ያሉት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል በሀገራችን ላይ እየሆነ ያለውን ተረድቶ፣ ሁሉንም በሚዛን አስቀምጦ፣ የምርጫው ቀን ሲደርስ ለሁላችንም ትምህርት ያስተላለፈ የሀገር አንድነት እና ሉአላዊነትን ያጸና የኢትዮጵያ ህዝብ ታላቅ ህዝብ መሆኑን ያረጋገጠበት እንዲሁም ከዚህ በኋላ መንግስት በካርድ እንጂ በጥይት አይሆንም የሚል መልዕክት ያስተላለፈበት ምርጫ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይም በሽብርተኞችና በፅንፈኞች ላይ የተጀመረው የተቀናጀ ኦፕሬሽን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የገለፀው የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ-ኃይሉ የምርጫው ውጤት ታውቆ አዲስ የመንግስት ምስረታ እስከሚከናወን እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ያሉ ሕዝባዊና መንግስታዊ ሁነቶች በስኬት እንዲጠናቀቁ የፀጥታ ሥራውን ይበልጥ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አቅጣጫ አስቀምጧል።

Ethiopian Federal Police

በሀላባ ዞን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን ተገለፀ ************ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ሀላባ ቁሊቶ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን 7ኛው...
02/06/2026

በሀላባ ዞን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጡ ሂደት በሠላም መጠናቀቁን ተገለፀ

************
ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ/ም ሀላባ ቁሊቶ፦

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጫ ሂደቱ ከሰኞ ማለደ 12:00 ጀምሮ በዞኑ በሦስቱም ወረዳዎችና በቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች ድምጽ የመስጠት ሂደት ፍጹም ሠላማዊ በሆነ መልኩ መጠናቀቁን የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ገልፀዋል።

ዛሬ ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ ከሁሉም ምርጫ ጣቢየዎች መራጩ ህዝብ የሰጠውን ድምጽ በፖሊስና ከየምርጫ ጣቢያ ከሉ አስፈፃሚዎች አማካይነት ወደ ማዕከላዊ የገባ መሆኑን ኮማንደሩ ገልፀዋል።

በድምፅ መስጠት ሂደት ስነስርዓት ወቅት በዞኑ በሁሉም በምርጫ ጣበቢያዎች አከባቢ ህዝቡ ፍፁም ጨዋነት በተላበሰ መልኩ በሰልፍ ቆመው ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዱሁም ከትራፊክ አደጋ ነፃ ሆኖ እንደተጠናቀቀ ኮማንደሩ ገልፀዋል ።

በመጨረሻም ድምጽ የመስጠት ስርዓቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ መራጩ ህዝብ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ዕጩዎች እና ታዛቢዎች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ኃላፊነታቸውን በተገቢው ለተወጡ ለዞንና ለ3ቱም ወረዳዎች ፖሊስ ጽ/ቤቶች ፖሊስ አመራርና አባላት የዞንና የሁሉም መዋቅር ሠላምና የፀጥታ አመራርና አባለት ኮማንደሩ ላቅ የለ ምስጋና አቅርቧል።

የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ የህ/ግ/ገ/ግ/ድቨዥን!!

ፌዴራል ፖሊስ የታጣቀቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለምርጫው ውጤታማነት…አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የታጣቀቸው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የ7ኛውን ...
02/06/2026

ፌዴራል ፖሊስ የታጣቀቸው የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለምርጫው ውጤታማነት…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የታጣቀቸው ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ውጤታማነት በማስጠበቅ ረገድ ገንቢ ሚና ተጫውቷል።

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት በትናንትናው ዕለት የተካሄደ ሲሆን÷ በተለያዩ የምርጫ ክልሎች ስር የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው ዕለት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶችን በመለጠፍ ዜጎች እየተመለከቱ ይገኛል።

የድምጽ አሰጣጥ ሂደትም ፍጹም ሰላማዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና ገለልተኝነቱን ጠብቆ እንዲካሄድ የፌዴራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመተባበር ከፍተኛ ስራ ሰርቷል።

የፌዴራል ፖሊስ የቴክኖሎጂ ማስፋፊያ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደምሴ ይልማ እንደገለጹት÷ ተቋሙ በምርጫው ወቅት ዜጎች በነጻነት ድምጻቸውን የሚሰጡበትን ሂደት ለማገዝ ሰፊ ዝግጅት አድርጓል።

በተለይም በአዳዲስና ፈጣን እድገት ላይ ያሉ ቴክኖሎጂዎችን ከነባሮቹ የቴክኖሎጂ መሰረተልማቶች ጋር በማቀናጀት፣ የፖሊስ ሰራዊት ስምሪት እና የምርጫ ጣቢያዎችን እንቅስቃሴ እያንዳንዱን በቀጥታ ለመከታተል መቻሉን ገልጸዋል።

በዚህም በየአካባቢው የሚታየውን የፀጥታ ሁኔታና የምርጫ ድባብ አመራሩ ከኮማንድ ኮንትሮል ማዕከል ሲከታተል መቆየቱን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ከሁሉም የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በሰራው ስራ የምርጫው ሂደት ሰላማዊ እና ውጤታማ በሆነ መንገድ መከናወኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ሆሳዕና፣ግንቦት 25/2018) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን  የሰባተኛው ጠቅላላ...
02/06/2026

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም መጠናቀቁን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

ሆሳዕና፣ግንቦት 25/2018) የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት በሰላም ተጠናቋል ብለዋል።

በክልሉ እስከ ታችኛው መዋቅር የጸጥታ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ወደ ተግባር መገባቱን ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

ማህበረሰቡን በጸጥታ ስራ ማሳተፍ አብይ አጀንዳ እንደነበር ያስታወሱት ኮሚሽነሩ ይህም አስቀድሞ ወንጀልን በመከላከል ረገድ የላቀ አበርክቶ ነበረው ሲሉም ጠቁመዋል።

ወጣቶችን፣ሴቶችን፣የሀይማኖት አባቶችን እና የሀገር ሽማግሌዎችን ያሳተፈ ውይይት ማካሔድ በመቻሉ የወንጀል መከላከል ስራው ስኬታማ መሆኑን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

የክልሉን ዘላቂ ሰላም ለማረጋገጥ ከተከናወኑ ተግባራት ውስጥ የገለልተኛ አማካሪ ምክር ቤት እና የጸጠሰታ ምክር ቤት ማጠናከር ተጠቃሽ መሆኑን ኮሚሽነር ሽመልስ በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።

ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመቀናጀት በህግ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎችን በማቅረብ እና ምርመራ በማካሔድ ህግ የማስከበር ስራ ማከናወን ስለመቻሉም ተናግረዋል።

የክልሉ አጠቃላይ የጸጥታ ሁኔታ በክቡር ርዕሰ መስተዳድሩ በየጊዜው እየተገመገመ መሆኑን የተናገሩት ኮሚሽነሩ በዚህም አስተማማኝ እና ዘላቂ ሰላም በመገንባት ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አስረድተዋል።

ከምርጫ በፊት የጸጥታ ሀይሉን የማጠናከር ስራ ልዩ ትኩረት እንደተሰጠው የጠቆሙት ኮሚሽነሩ በዘርፉ ተጨማሪ የሰው ሀይል በማሰልጠን ወደ ስራ መግባቱን ጠቅሰዋል።

የጸጥታ ሀይሉን በምርጫ ስነ ምግባር ላይ አስቀድሞ ግንዛቤ እንዲጨብጥ በማድረግ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ወደ ተግባር መገባቱን ኮሚሽነሩ አስረድተዋል።

በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ 35 የምርጫ ክልሎች እና 2ሺ 998 የምርጫ ጣቢያዎች እንደነበሩ ኮሚሽነሩ በመግለጫቸው አውስተዋል።

በክልሉ በሁሉም የየምርጫ ጣቢያዎች የጸጥታ ሀይል በመመደብ ወደ ተግባር መግባት መቻሉን የገለጹት ኮሚሽነር ሽመልስ ተጨማሪ እገዛ በሚያስፈልጋቸው አካባቢዎች የክልሉ አድማ ብተና ፖሊስ፣የፌደራል ፖሊስ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ባላት ስምሪት ወስደው ድጋፍ ሲያደርጉ እንደነበርም አብራርተዋል።

በምርጫ በሂደቱ ያጋጠሙ ቀላል ጉዳዮች ከምርጫ አስተባባሪዎች ጋር በመነጋገር መፍታት መቻሉን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል ።

በክልሉ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያጋጠመ የጸጥታ ችግር አለመኖሩን የገለጹት ኮሚሽነሩ በዚህም ህብረተሰቡ በነጻነት ድምጽ በመስጠት ወደ መደበኛ ስራው መሰማራቱን በመግለጫቸው አብራርተዋል።

አብዛኛው የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ክልል የማጓጓዝ ስራ መከናወኑን ተናግረዋል።

የዘንድሮው ምርጫ ስኬታማ እንዲሆን የክልሉ ህዝብ፣ፖሊስ፣የድማ ብተና ኃይል፣ቪአይፒና ተቋማት ጥበቃ ሻለቃ፣ማረሚያ ቤቶች፣የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፌደራል ፖሊስ፣የሚሊሻ አባላት፣የክልል፣የዞን ፣የልዩ ወረዳ፣የወረዳ፣የከተማ አስተዳደር እስከ ቀበሌ ያለው አመራር ለጸጥታ ስራው የላቀ ድጋፍ በማድረጋቸው ኮሚሽነሩ ምስጋና አቅርበዋል።

ፍቅረኛዬን ለሌላ ሰው ደልለሃታል በሚል ቂም ተነሳስቶ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተከሳሽ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ፍቅረኛዬን ለሌላ ሰው አማክረሃል...
02/06/2026

ፍቅረኛዬን ለሌላ ሰው ደልለሃታል በሚል ቂም ተነሳስቶ ግለሰብን በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ተከሳሽ እስራት እንዲቀጣ ተወሰነ።

በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳደር ፍቅረኛዬን ለሌላ ሰው አማክረሃል በሚል ቂም ተነሳስቶ አንድን ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ የገደለው ግለሰብ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የኮንታ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ መስጠጡን ያመለከተው የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

ተከሳሽ ስንታየሁ ዶሳ የተባለው ግለሰብ ሟች ታደሰ ዙላን መጋቢት 13/2018 ዓ.ም አሳቻ ሰዓት ጠብቆ በመኖሪያ ቤቱ በመግባት በተለያዩ የአካል ክፍሎች ላይ በስለት በመውጋት ከባድ የነፍስ ግድያ መፈፀሙን ፍ/ቤቱ ከጽሁፍና ከቃል ማስረጃዎች ማረጋገጡን በችሎቱ አቅርቧል።

ፍ/ቤቱም ከቀረቡ ማስረጃዎች መነሻ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ 39/1/ሀ መሠረት ተከሳሹ የወንጀል ሪከርድ የሌለበት መሆኑን ማቅለያ በመያዝ እርከን መነሻ 43 መሠረት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሽ ስንታየሁ ዶሳ በ21 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ፍርድ ቤቱ ወስኗል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንድንጠነቀቅ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አባለት በተጠንቀቅ ቆመው በስራ ለይ መገኘታቸው...
01/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን 7ኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ በሠላም እንድንጠነቀቅ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ማህበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል አባለት በተጠንቀቅ ቆመው በስራ ለይ መገኘታቸውን በምስል!!

ሀገሪቱን  ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ ...
31/05/2026

ሀገሪቱን ማስቀጠል እንዲቻል ምርጫ ወሳኝ በመሆኑ በክልሉ ያለውን ሰላም በማረጋገጥ ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥል ተጠየቀ።

ሆሳዕና ግንቦት 23 ቀን 2018 (ማ.ኢ.ፖ.ኮ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ፖሊስ ኮሚሽን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በአጠቃላይ የፀጥታ ስራ ዙሪያ መግለጫ ሰጥቷል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ም/ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ለደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሰጡት መግለጫ ክልሉ በሰባት ዞኖችና በሶስት ልዩ ወረዳዎች የተደራጀ ሲሆን አዲስ ክልል እንደመሆኑ የምርጫ ሁነትን ሲያስተናገድ የመጀመሪያው መሆኑን ገልፀዋል።

በክልሉ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በማስመልከት በቅድመ ምርጫ ወቅት በርካታ የፀጥታ ስራዎች መሰራታቸውንም ገልጸዋል።

በየደረጃው የፀጥታ ግብረ ሃይል በማቋቋም እና ምርጫው ያለምንም የጸጥታ ስጋት በሰላማዊ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ስራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል።

በየአካባቢው ወንጀልን በመከላከልና አጥፊውን በማጋለጥ ሂደት ማህበረሰቡ ከፀጥታ አካላት ጎን መቆም እንዲችልና ምርጫው በሰላምና በስኬት እንዲካሄድ በሁሉም አካባቢዎች በጸጥታ ዙሪያ ሰፊ ውይይት መደረጉንም ም/ኮሚሽነሩ አብራርተዋል።

ከዚህ ጎን ለጎን አጥፊዎችን የመያዝና ከክልሉ ፍትህ ቢሮ ጋር በመሆን ወንጀልን በምርመራ የማጣራትና በህግ እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም በመግለጫቸው አክለዋል።

ይህ ሁሉ ስራ ሲሰራ መላው የፀጥታ ኃይል በጋራ እና በቅንጀት በመስራታቸው እንዲሁም አጠቃላይ የፀጥታ ስራዎችን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር በጋራ በመገምገም አቅጣጫ እየሰጡ በመሄዳቸው በቅድመ ምርጫ ወቅት በተሰሩ የጸጥታ ስራዎች በክልሉ የተሻለ ሰላም መኖሩንም አስረድተዋል።

በክልሉ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚካሄድባቸው 35 ምርጫ ክልሎችና 2ሺ 9መቶ98 ምርጫ ጣቢያዎች መኖራቸውን የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ በሁሉም ቦታዎች የጸጥታ ኃይል ተሰማርቶ ስራላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከስምሪት በፊት በቂ የምርጫ ስነምግባር ስልጠና በመስጠት የጸጥታ ኃይሉ ነጻና ገለልተኛ ሆኖ እንዲሰራ መደረጉንም ም/ ኮሚሽነር ሽመልስ ካሳ ገልጸዋል።

ለስኬቱ የፌዴራል ፖሊስና የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተገቢውን ድጋፍ እያደረጉ መቆየታቸውን ገልጸው ለዚህም ምስጋና አቅርበዋል።

ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ ሰላም ወዳድ የሆነው የክልሉ ህዝብና የጸጥታ ኃይሉ የተለመደውን ቅንጅታዊ ስራ አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል።

እንዲሁም ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ታዛቢዎች ምርጫ አስፈጻሚዎች እና በምርጫው ስራ ላይ የተሰማሩ ሁሉም አካላት የምርጫ ስነምግባር ደንብ በመከተል የምርጫ ስራውን በመስራት ለስኬት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ችግሮች ሲከሰቱም ወዲያው ለፀጥታ ኃይል ማሳወቅ እንደሚገባ ም/ኮሚሽነሩ አስገንዝበዋል።

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል" – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠...
30/05/2026

"7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል እያደረገ ያለውን ተግባር አጠናክሮ ይቀጥላል" – ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠
‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22 ቀን 2018 ዓ.ም (ኢፌፖሚ)፦ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና በቴክኖሎጂ ያደረገውን ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ በዋና መስሪያ ቤቱ በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ለጋራ ግብረ-ኃይሉ ማብራሪያ ሰጥቷል።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንደገለጹት፣ የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይሉ ለምርጫው ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ ነው። ምርጫውን ለማደናቀፍ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች የተለያዩ ሙከራዎችን እያደረጉ ቢሆንም፣ መከላከያ ሠራዊት ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ኃይሎች እነዚህን የጥፋት ዕቅዶች ማክሸፉን አረጋግጠዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ አክለውም፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሪፎርሙ በኋላ በሰለጠነ የሰው ኃይል፣ በዘመናዊ ትጥቅና በቴክኖሎጂ መደራጀቱ የዜጎችን ደህንነት ለመጠበቅና በተለይም 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ አዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በበኩላቸው፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ የተቋቋመው የፀጥታና ደህንነት የጋራ ግብረ ኃይል ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር መረጃዎችን በመለዋወጥ እና ከህዝቡ ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በቅድመ-ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ሂደት፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች እና የምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ደህንነት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።

ክቡር ኮሚሽነር ጀነራሉ አያይዘውም፣ ቀሪውን የምርጫ ሂደት ሰላማዊነት ለማረጋገጥ አስፈላጊ የሆኑ ሎጀስቲክስ እና ትጥቆች መሟላታቸውን እንዲሁም ለተልዕኮው የሚመጥን በቂ ስልጠና እና ኦሪንቴሽን የወሰደ የሰው ኃይል በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች መሰማራቱን ገልጸዋል።

በቀጣይም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በቴክኖሎጂ የታገዘ የፀጥታና ደህንነት የማስከበር ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከምርጫው በኋላ የሚከናወኑ ሂደቶችም በስኬት እንዲጠናቀቁ ግብረ-ኃይሉ ሙሉ ዝግጅት ማድረጉን ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል አረጋግጠዋል።

28/05/2026
በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶ በሠላም ተከብራ =====ግንቦት 19/2018ዓም ሀላባ ቁሊቶ ፦በሀላባ ዞን በቁሊቶ...
27/05/2026

በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1ሺህ 447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶ በሠላም ተከብራ
=====
ግንቦት 19/2018ዓም ሀላባ ቁሊቶ ፦

በሀላባ ዞን በቁሊቶ ከተማ 1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በተለያዩ ሀይማኖታዊ ስነ-ስርዓቶች በሠላም መከበሩን የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ኑርዬ ከድር ገልፀዋል

በኢድ ሰለት ስነ-ስርዓት ወቅት የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ጨምሮ ሌሎች የክልል እና የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የእስልምና እምነት ተከታዮች በተገኙበት በታላቅ ሀይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን መከናወናቸውን ኮማንደሩ ገልፀዋል ።

በዓሉ በሚያከበሩበት ወቅት የተቸገሩ ወገኖች የሚረዱበት ፈጣሪን የሚለመንበት፣ አንድነትን ወንድማማችነትን የሚሰበክበት በዓል እንድሆን መልካም ምኞቱን ገልፀዋል

በመጨረሻም የኢድ ሶለት ስነስርዓት ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ድረስ የለምንም መሠላቸት በተጠንቀቅ በሁሉም አቅጣጫ ቆመው የሰገዱ የ3ቱም ወረዳዎች ፖሊስ አመራርና አባለትን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አመራርና አባለት ለሁሉም ባለድርሻ አካለት የለ ምስጋና አቅርበዋል።

በድጋሚ እንኳን የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል ።

Address

Alaba K'ulito

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ፖሊስ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share