በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት አቶቲ ኡሎ ህ/ስ/ል/ጽ/ቤት

Permanently closed.
የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የልማት ትሩፋት ስራዎችን ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን- የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ ገለጹ!***********...
03/06/2026

የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የልማት ትሩፋት ስራዎችን ማስፋፋት ወሳኝ መሆኑን- የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ ገለጹ!
*************
(ግንቦት፤26/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ ስርዐት ምግብን ክፍታትን ለማሟላት (በHCO)ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት በቁንጩ የዬና በ2ኛ ጡቃ ቀበሌ በመንደር የዶሮ ስርጭት ተደርገዋል።

በዛሬው ዕለት በወረዳው ከ1200 በላይ የ45 ቀን የዶሮ ጨጩት ስራጭት ለማድረግ መቻሉን ግብርና ጽ/ቤት አስታወቋል።

የህብረተሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥና የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም የሚያስችሉ የልማት ትሩፋት ስራዎች በመንደር መሰራጨት ተጠናክሮ መቀጠሉን ተገልጸዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ እንደገለጹት የልማት ትሩፋት ስራዎችን ማስፋፋት ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ እንደሆነ አስረድተዋል።

የልማት ትሩፋት ስራዎች ዝቅተኛ ገቢ ያለውን የህብረተሰብ ክፍል በቀጥታ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በመሆናቸው እነዚህን ተሞክሮዎች ለመስፋፋት በልዩ ትኩረት ልሰራ ይገባል ብለዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ምክትል ሀላፊና እንስሳትና ዓሳ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሉሉ ከድር በበኩላቸው የዶሮ እርባታ አነስተኛ ቦታና ቀላል ጉልበትን በመጠቀም ምርታማነትን በማሳደግ የቤት ፍጆታን ማሟላትና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ትልቅ ፈይዳ እንዳለው ገልጸዋል።

የተሰራጩት ዶሮዎች በጥሩ ጤንነት አድገው ለታለመላቸው ውጤት እንዲበቁ የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ተከታታይ የሙያ ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ ገልጸዋል።

ግብርናን በማዘመንና በየቤቱ የልማት ስራዎችን በመተግበር ዜጎች ራሳቸውን እንዲችሉና የአካባቢያቸውን እንዲያነቃቁ የሚሆን ተግባር መሆኑን አመልክቷል።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት የልማት ዕቅድ ባለሙያ የሆኑት አቶ አ/ቃድር ኑርዬ በበኩላቸው በወረዳው በስርዓተ ምግብ ላይ የሚከሰቱ ተስተውሎትን ለመቅረፍ የHCO ፕሮጀክት ለህዝብ የሚበጅ መፍትሔ ይዞ መምጣቱን ተናገረዋል

በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች የዶር ስርጭት በመንደር ማድረጉ ገልጸው፦በዛሬው ዕለት አርሶአደሩ በአንድ ቦታ ሁሉንም ነገር አግኝታው እራስንና ተደግ የሆኑ ልጆች ብቁ ሆኖ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ በምግብ እራሳቸውን መገንባት ወሳኝ መሆኑን አመልክቷል።

በፕሮግራሙ ላይ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀሰን አብደላ፣እንዲሁ የቀበሌው አመራሮች ተጠቃሚ ማህበረሰብ ክፍል ሌሎችም ተገኝተዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

ዓለም አቀፍ ተቋማት የመሰከሩለት የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ***************** በሰላማዊነቱ እና በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎው ደማቅ ታሪክ ያስመዘገበው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ም...
03/06/2026

ዓለም አቀፍ ተቋማት የመሰከሩለት የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ
*****************

በሰላማዊነቱ እና በከፍተኛ የሕዝብ ተሳትፎው ደማቅ ታሪክ ያስመዘገበው የኢትዮጵያ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ፥ ከአፍሪካ ኅብረት እና ከኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች እንዲሁም ከአውሮፓ ኅብረት እና ከአጋር ሀገራት ጠንካራ ዕውቅና እና አድናቆት አግኝቷል።

የአፍሪካ ኅብረት ታዛቢ ቡድን መሪ የሆኑት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣ ሕዝቡ ከማለዳው ጀምሮ በከፍተኛ ፅናት እና እርጋታ ድምፁን መስጠቱን አድንቀዋል።

የአፍሪካ የነፃነት ምልክት የሆነችው ኢትዮጵያ ባሳየችው ዴሞክራሲያዊ አፈጻጸም ሕዝቧ እና መንግሥቷ በራሳቸው ሊኮሩ እንደሚገባ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ፣ የኢጋድ ታዛቢ ቡድን መሪ ስፔሲዮዛ ዋንዲራ ካዚብዌ (ዶ/ር) በሰጡት ምስክርነት፣ በሂደቱ የታየው አካታችነት፣ የመራጩ ሕዝብ የላቀ ትዕግሥት እና ሰላማዊ ድባብ ከዚህ ቀደም በየትኛውም ሀገር እንዳላጋጠማቸው ገልጸዋል።

ከምርጫው ጋር ተያይዘው የሚነሡ ማናቸውም ቅሬታዎች በሕጋዊ መንገድ ብቻ መፍታት እንዳለባቸው አሳስበው፣ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም "ለአፍሪካ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ" በሚለው መርሕ መሠረት ኢትዮጵያውያን የውስጥ ጉዳያቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ ዕድል እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበዋል።

የአውሮፓ ኅብረት ከካናዳ፣ ኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ጋር በጋራ ባወጣው መግለጫ የምርጫውን ስኬታማ ሂደት በደስታ ተቀብሏል።

ተቋማቱ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለልተኝነት፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለእጩዎች ለሲቪል ማኅበራት እና ለፀጥታ ተቋማት አዎንታዊ አስተዋፅኦ ሙሉ ዕውቅና ሰጥተዋል።

እነዚህ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ምስክርነቶች፣ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ዴሞክራሲያዊ ሽግግር በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን በጉልህ ያሳዩ ናቸው።

በዮናስ በድሉ

ቀኑ ደረሰ! የታሪክ ባለቤት ለመሆን ተዘጋጅታችኋል?‎‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!‎‎የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ለመወሰንና የልማታችንን ቀጣይነት በአለት ላይ ለመቅረጽ ቀጠሮ የተያዘለ...
29/05/2026

ቀኑ ደረሰ! የታሪክ ባለቤት ለመሆን ተዘጋጅታችኋል?

‎መላው የሀገራችን ሴቶችና ወጣቶች!

‎የነገዋን ኢትዮጵያ እጣ ፈንታ ለመወሰንና የልማታችንን ቀጣይነት በአለት ላይ ለመቅረጽ ቀጠሮ የተያዘለት ያ ታላቅ ቀን እነሆ ደረሰ!

‎የሀገራችን ደም-ስሮች የሆናችሁ ሴቶችና ወጣቶች፤ እንደ ሁልጊዜው ሁሉ በአስተዋይነት፣ በሰለጠነና ጨዋነትን በተላበሰ መልኩ፣ ነገን በጥንቃቄ በማሰላሰል "ይበጀኛል" የምትሉትን ለመምረጥ ዝግጁ ናችሁ?

‎🗳️ ውሳኔዎ፡ የነገው ሰላምዎ ነው!
‎🗳️ ምርጫዎ፡ የልጆችዎ መጻኢ ዕድል ነው!
‎🗳️ አሻራዎ፡ የጸናች ሀገር መሠረት ነው!

‎ስሜታዊነትን አውጥተን በዕውቀትና በብስለት፣ ለሀገራችን አንድነትና ብልጽግና ስንል ድምፃችንን እንስጥ። ጨዋነትንና ሰላምን አስቀድመን የዜግነት አሻራችንን በኩራት እናኑር!

‎በ7ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ድምፅዎ የነገ ተስፋዎ ነው!

29/05/2026
የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒደል አድሃ (ዐረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል!!ዒድ...
26/05/2026

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ኅብረት ሥራ ልማት ጽ/ቤት ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የዒደል አድሃ (ዐረፋ) በዓል በሠላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል!!

ዒድ ሙባረክ!

በሀላባ ዞን የአቶቲ  ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ብልጽግና ቤተሰብ አባላት ለ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ዉይይት መድረግ ተችሏል!...
26/05/2026

በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ብልጽግና ቤተሰብ አባላት ለ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ዉይይት መድረግ ተችሏል!

ግንቦት 18/09/2018 ዓ/ም አቶቲ ኡሎ

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት ብልጽግና ቤተሰብ አባላት ለ7ኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ ከመላው አበላቱ ጋር የውይይትና የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ-ግብር ሰፍዉ ዉይይት ተዳርጎል!

‌‎ “ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” የማድረስ ታላቅ ራዕይን ለማሳካት እያንዳንዱ አባል የበኩሉን ሚና መወጣት እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል።

‌‎ #ምርጫችን ብልፅግና!
#ምልክታችን የስንዴ ነዶ!
#መልዕክታችን ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!
#ብልፅግናን ይምረጡ!
#የምርጫው ቀን ግንቦት24


#አቶቲ አሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት

22/05/2026

በሀገራችን ብልፅግና ተረጋግጦ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር ሰው ተኮር የሆነው መንግስታችን ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ይገኛል።

የማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር መሀመድ ኑሪዬ

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው:- መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)****************(ግንቦት 14/2018 ዓ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ...
22/05/2026

ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው:- መሀመድ ኑሪዬ (ዶ/ር)
****************
(ግንቦት 14/2018 ዓ/ም) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድንና ልማት ቢሮ በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት አስመርቋል።

በምርቃት መርሃ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሰረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ሀላፊ መሀመድ ኑሪዬ(ዶ/ር) አካባቢው ከፍተኛ የውሃ ችግ ያለበት በመሆኑ ለማህበረሰቡ ትልቅ እፎይታ በመስጠት የህዝብ መልካም አስተዳደር ጥያቄ ምላሽ የሰጠ መሆኑንም ተናግረዋል።

በሀገራችን ብልፅግና ተረጋግጦ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር ለማሸጋገር እየተሰራ ያለው ስራ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው ብለዋል።

የለውጡ መንግስት የሰው ተኮር ነው ያሉት ዶክተር መሀመድ ዛሬ የተመረቁት ሁለቱም ፕሮጀክቶች የዚሁ ማሳያ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ውሃ ህይወት ነው ያሉት ዶክተር መሀመድ የውሃ ፕሮጀክት ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ በመሆኑም ከመነሻው ጀምሮ የአካባቢ ጥበቃ ስራ በተገቢው በመስራት የገፀምድርና የከርሰምድር የውሃ ሀብት በዘላቂነት መንከባከብ ይገባል ብለዋል።

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ፣ መስኖና ማዕድን ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዳዊት ሀይሉ እንደተናገሩት ጥራት ያላቸው የመጠጥ ውሃ ተቋማትን በመገንባት የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግርን ለማቃለል በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የውሃን ችግር መቅረፍ የጤናን፣ የትምህርትን የግብርናንና ሌሎችንም ልማቶች ማስቀጠል በመሆኑ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ከ126 ሚሊዩን ብር በላይ ወጪ የተገነባ መሆኑን የተናገሩት ሀላፊው 9 ኪ.ሜ የሚሸፍን ዝርጋታ የተደረገለት 9 የውሃ ቦኖዎች እና 7 የእንስሳት ማጠጫ ገንዳዎች ያሉት ከ10 ሺ በላይ ለሚሆኑ የአካባቢው ማህበረሰብ አገልግሎት የሚሰጥ ነው ብለዋል።

በኢፌድሪ የውሃና ኢነርጂ ሚንስቴር የመጠጥ ውሃና ሳንቴሽን መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ታምሩ ገደፉ እንደተናገሩት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሀገሪቱ የውሃና ሳኒቴሽን ፕሮጀክቶች በመቅረፅ የዜጎችን የውሃ ችግር ለመቅረፍ እየሰራ ነው ብለዋል።

በሀገራችን በድርቅ በሚጠቁና በበረሃማ አካባቢዎች በአለም ባንክ ድጋፍ የሚተገበር ፕሮጀክት እንደሀገር በ55 ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን በዚህ ክልልም በሦስት ወረዳዎች እየተተገበረ መሆኑን አመልክተዋል።

ፕሮጀክቱ የፍሎራይድ ማጣራት የተገጠመለት በመሆኑ ከዚህ ቀደም በእናቶችና ህፃናት ጤና ላይ የሚያስትለውን ጉዳት የሚያስቀር መሆኑንም ተናግረዋል።

የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሙህዲን ሁሴን በበኩላቸው እንደተናገሩት በዞኑ ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በርካታ የመጠጥ ውሃና ሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጡ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ውሃ በሌለበት ልማት አይታሰብም ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ይህን ውድ ሀብት በተገቢው ማስተዳደርና መጠበቅ ከሁሉም ይጠበቃል ብለዋል።

የለውጡ መንግስት ፍሬ የሆኑት በዛሬው እለት የተመረቁት የበሸኖ የሶላር ፕሮጀክት እና የአንደኛ ጤፎ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት በአጠቃላይ ከ167 ሚሊዮን በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ኢንጅነር አ/ቃድር አማን በበኩላቸው ባለፉት የለወጡ ዓመታት መንግስታችን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

ወረዳው ከመንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የወረዳውን የንፁህ መጠጥ ውሃን ተደራሽነት ለማስፋፋት በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

የውሃ መስፋፊያ ግንባታ በማከናወኑ በህዝቡ ስም ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን በርካታ ስራዎች ቢኖሩም ካሉብን ውዝፍ የውሃ ጥያቄዎች አንፃር በቀጣይም ተግተን እንሰራለን ብለዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ   የሴቶች ገንዛብ ቁጣባና ብድር ህብራት ስራ ማህባር ለኣባላቱ ብድር ስርጭት አዳራገ(ግንቦት 13/2018 ዓ/ም ጉባ)በአቶቲ ኡሎ ወራዳ ሻዋኮ ቀባሌ
21/05/2026

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ የሴቶች ገንዛብ ቁጣባና ብድር ህብራት ስራ ማህባር ለኣባላቱ ብድር ስርጭት አዳራገ

(ግንቦት 13/2018 ዓ/ም ጉባ)
በአቶቲ ኡሎ ወራዳ ሻዋኮ ቀባሌ

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በየዬ ቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተካሄዷል።ግንቦት፣11/2018 ዓ.ም ጉባ የአቶቲ ኡሎ ኮሚዩኒኬሽን:በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወ...
19/05/2026

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በየዬ ቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳና የቡና ጠጡ ፕሮግራም ተካሄዷል።

ግንቦት፣11/2018 ዓ.ም ጉባ የአቶቲ ኡሎ ኮሚዩኒኬሽን:በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በየዬ ቀበሌ የብልፅግና ፓርቲ አበለት የምርጫ ቅስቀሳና ቡና ጠጡ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን በፕሮግራሙ ላይ የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ሃላፊ አቶ አብዲ መሀመድ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የቀበሌው ደጋፊ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላቶች ተገኝተዋል።

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251922468603

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when በሀላባ ዞን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ህብረት ስራ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share