የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ This Page Gives The Correct and real Inforemation of Halaba Zone Finance Departement

16/09/2026
የሀላባ ዞን የ 2019 ዓ/ም የዞን ማዕከል የበጀት ዕቅድ ለዞኑ ካቢኔ አባላት ቀረበ______ መስከረም 5/2019 ዓ/ም የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የዞን ማዕከል የ...
15/09/2026

የሀላባ ዞን የ 2019 ዓ/ም የዞን ማዕከል የበጀት ዕቅድ ለዞኑ ካቢኔ አባላት ቀረበ
______

መስከረም 5/2019 ዓ/ም

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2019 በጀት ዓመት የዞን ማዕከል የበጀት ዕቅድን ለሀላባ ዞን ካቢኔ አባላት አቅርቧል።

የቀረበው የበጀት ዕቅድ የዞን ማዕከል ባለ በጀት መ/ቤቶችና ከፑል ውጭ ዞናዊ ተቋማት (ማለትም የሀላባ ቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ፣የበሸኖ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት )የ2019 በጀት ዓመት የሚያከናውኗቸውን የሥራ ዕቅዶች ለማስፈጸም የሚያስፈልጋቸውን የሀብት አመዳደብ በዝርዝር ቀርቧል።

በዚህም የመምሪያዎችና ከፑል ውጭ ተቋማት የደመወዝ፣ የሥራ ማስኬጃ እና የካፒታል በጀት በዕቅዱ ውስጥ ተካተዋል።

የ2019 በጀት ዓመት የበጀት ዕቅድ በልማት ሥራዎች ላይ የተለየ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ታቅደው ለተያዙ የልማት ሥራዎች የሚያስፈልጋቸውን በጀት በዕቅዱ ውስጥ ተካቷል

የበጀት አመዳደቡ የዞኑን የልማት አቅጣጫና የህዝብን ፍላጎት በማገናዘብ የተመደበው ሀብት ከፍተኛ ውጤት በሚያስገኙ ሥራዎች ላይ እንዲውል ትኩረት ያደረገ መሆኑም ተመላክቷል።

የተመደበው በጀት ለታቀደለት ዓላማ ብቻ በማዋል በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባም ተጠቁሟል።

በጀት ተጠቃሚ መምሪያዎችና ተቋማት የተመደበላቸውን ሀብት በሕግና በመመሪያ መሠረት በመጠቀም የሀብት ብክነትን በመከላከልና ለተመደበው በጀት ተገቢውን ተጠያቂነት በመውሰድ የበጀት አፈጻጸሙን ማሻሻል እንደሚጠበቅ ተገልጿል።

የ2019 በጀት ዓመት የበጀት ዕቅዱ በተገቢው ሁኔታ ተፈጻሚ ሆኖ የታቀዱ የልማትና የአገልግሎት ሥራዎች እንዲሳኩ እና የመንግስት ሀብት ለህዝብ ተጨባጭ ጥቅም እንዲውል ትኩረት ይደረጋል።

✍️ የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

በሀላባ ዞን በመሰረተ ልማት ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚድርግ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው=====መስከረም 5/2019 በሀላባ ዞን በመሰረተ ልማት ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚድ...
15/09/2026

በሀላባ ዞን በመሰረተ ልማት ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚድርግ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው
=====

መስከረም 5/2019 በሀላባ ዞን በመሰረተ ልማት ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚድርግ ውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።

በዋናነት የመብራት ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ ኢትዮ ቴሌኮም በመሰረተ ልማት ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በሰፊው ነው ውይይት እየተካሄደ የሚገኘው።

በውይይቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ልዬ አማካሪ ዶክተር ንጉሱ አስረስ፣ የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን፣ ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት፣ ከምባታ ዞን፣ ጠምባሮ ልዩ ወረዳ፣ የሀዲያ ዞንን በከፍል ጨምረው ተወካይ ህብረተሰብ ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የወላይታ ሪጅን እና ኢትዮ ቴሌኮም ለውይይት መነሻ ሪፖርት እየቀረቡ ይገኛል።

ሲል የሀላባ ዞን መ/ኮሚኒኬሽን ዘግቧል.

🌼🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት — 2019 ዓ.ም.! 🇪🇹🌼እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ!አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ዕቅድ፣ አዲስ ጉልበትና አዲስ የሥራ ዘመን የሚጀምርበት ...
10/09/2026

🌼🇪🇹 መልካም አዲስ ዓመት — 2019 ዓ.ም.! 🇪🇹🌼

እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት አደረሳችሁ!

አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ፣ አዲስ ዕቅድ፣ አዲስ ጉልበትና አዲስ የሥራ ዘመን የሚጀምርበት ወቅት ነው። ያለፈውን ዓመት በልምድና በትምህርት ተሞልተን ስንሸኝ አዲሱን ዓመት ደግሞ በተሻለ አስተሳሰብ፣ በተጠናከረ ትብብርና በተሻለ የሥራ አፈጻጸም ለመቀበል ዝግጁ ነን።

በ2019 ዓ.ም. የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በሕዝብ ሀብት በኃላፊነት አጠቃቀም፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት፣ በተሻለ የፋይናንስ አስተዳደር እና በተቀላጠፈ አገልግሎት ላይ ያለውን ተግባር በበለጠ ትጋት ይቀጥላል።

አዲሱ ዓመት ለመላው የሀላባ ዞን ሕዝብ፣ ለመምሪያችን ሠራተኞች፣ ለአጋር ተቋማትና ለሁላችንም የሰላም፣ የጤና፣ የስኬትና የበረከት ዓመት እንዲሆን እንመኛለን።

አዲሱ ዓመት የተሻለ ሥራ የተሻለ አገልግሎትና የተሻለ ውጤት የምንፈጥርበት ዓመት ይሁን!

መልካም አዲስ ዓመት! 🎉🌼

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

ጳጉሜ 5 — የነገ ቀንነገ የሚጀምረው አዲስ ዓመት ዛሬ በምናቅደው እና በምንዘጋጀው ይጀምራል።ጳጉሜ 5 የትናንትን ልምድ በመያዝ ዛሬን በመገምገም እና ለነገ በተሻለ ተስፋና ዕቅድ ለመስከረም ...
10/09/2026

ጳጉሜ 5 — የነገ ቀን

ነገ የሚጀምረው አዲስ ዓመት ዛሬ በምናቅደው እና በምንዘጋጀው ይጀምራል።

ጳጉሜ 5 የትናንትን ልምድ በመያዝ ዛሬን በመገምገም እና ለነገ በተሻለ ተስፋና ዕቅድ ለመስከረም 1 የምንዘጋጅበት የመጨረሻዋ የዓመቱ ቀን ናት።

በፋይናንስ ሥራ ውስጥም የተሻለ ነገ የሚገነባው በዛሬ በሚደረግ ትክክለኛ ዝግጅት፣ በኃላፊነት አፈጻጸም፣ በግልጽነት እና በተጠያቂነት ነው።

እንደ መምሪያ ያለፈውን ዓመት በመገምገም የተማርነውን በማጠናከር እና ለተሻለ የፋይናንስ አስተዳደር በአዲስ ተስፋና ቁርጠኝነት ወደ አዲሱ ዓመት እንሻገራለን።

ጳጉሜ 5 — የነገ ቀን!

🌼 መልካም የአዲስ ዓመት!

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

የአብሮናት እሴቶች ለዘለቁ ሰለምና ለክልለችን ከፍታ!!በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የ 2018 ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በዓል አከባበር ''አብረን ነበር ፤ አብረን ነን ፤ አብረን አብ...
09/09/2026

የአብሮናት እሴቶች ለዘለቁ ሰለምና ለክልለችን ከፍታ!!

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን የ 2018 ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በዓል አከባበር ''አብረን ነበር ፤ አብረን ነን ፤ አብረን አብረን እንኖራለን'' በሚል መሪ ቃል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ጳጉሜን 4 — የኅብር ቀንኅብር ማለት በአንድ ዓላማ ዙሪያ ተሰባስቦ በመተባበር፣ በመረዳዳትና በጋራ ኃላፊነት ውጤት ማምጣት ነው። የአንድ ተቋም ውጤታማነትም ከእያንዳንዱ አካል በተናጠል ከሚያ...
09/09/2026

ጳጉሜን 4 — የኅብር ቀን

ኅብር ማለት በአንድ ዓላማ ዙሪያ ተሰባስቦ በመተባበር፣ በመረዳዳትና በጋራ ኃላፊነት ውጤት ማምጣት ነው። የአንድ ተቋም ውጤታማነትም ከእያንዳንዱ አካል በተናጠል ከሚያደርገው ጥረት በላይ በጋራ ከሚፈጥረው ቅንጅትና ትብብር ይመነጫል።

በሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሕዝብ ሀብት በተገቢው መንገድ እንዲመራ፣ የበጀት ሀብት በዕቅድና በቅድሚያ መሠረት እንዲመደብና እንዲጠቀም የፋይናንስ ሥርዓት እንዲጠናከር እና የሕዝብ ሀብት ለታለመለት ዓላማ ብቻ እንዲውል በትጋት እንሠራለን።

ይህንን ኃላፊነት በተሳካ ሁኔታ ለመወጣት በመምሪያችን ውስጥ ያለው የሠራተኞች ትብብር ብቻ ሳይሆን ከሌሎች የመንግሥት ተቋማት፣ ከዘርፎች እና ከሁሉም የሥራ አጋሮች ጋር የሚኖረን ቅንጅታዊ አሠራር ወሳኝ ነው።

የኅብር ቀን የሚያስታውሰንም ይህንኑ ነው። የተሻለ ውጤት የሚመጣው እያንዳንዳችን የየራሳችንን ድርሻ በኃላፊነት ስንወጣ እና ጥረታችንን በአንድ አቅጣጫ ስናስተባብር ነው። በኅብር ስንሠራ የሕዝብ ሀብትን በአደራ የመምራት ኃላፊነታችንን በተሻለ ሁኔታ መወጣት ግልጽነትንና ተጠያቂነትን ማጠናከር እና ለዞናችን የልማት ግቦች የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ማሳደግ እንችላለን።

ዛሬ በምናከብረው ጳጉሜን 4 — የኅብር ቀን የጋራ ዓላማችንን በማጠናከር፣ በትብብር በመሥራት፣ የሕዝብን ሀብት በኃላፊነት በመጠቀምና የፋይናንስ ሥርዓቱን በማሻሻል ለተሻለ ነገ በጋራ እንሥራ።

መልካም የኅብር ቀን!

✍️የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ

Address

Halaba Zone
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share