የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ይህ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሥራዎች ዙሪያ መረጃ የምናንሸራሸርበት ህጋዊ ፌስቡክ ገጽ ነው።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቤተሰብ አባላት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ እጩዎችን ማስታወቂያ ዉይይት ተካሄደ።መጋቢት 03/2018 ዓ.ም የሀላባ ቁሊቶ ከተማ...
12/03/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቤተሰብ አባላት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ እጩዎችን ማስታወቂያ ዉይይት ተካሄደ።

መጋቢት 03/2018 ዓ.ም

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቤተሰብ አባላት 7ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ እጩዎችን ማስታወቂያ በዛሬው ዕለት ውይይት አድርገዋል።

ወቅታዊ የመንግስትና የፓርቲ ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል በየዘርፉ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስና የተሻለ ለውጥ ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ተገልጿል።

በከተማው እየተከናወኑ ያሉ የልማት ትሩፋቶችና የተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ አባላቱ በግንባር ቀደምትነት መስራት እንዳለበት ተገለዋል።

ህብረተሰቡን ከተረጂነት አስተሳሰብ ለማውጣት ለአካባቢው ምሳሌ የሚሆኑ ተግባራትን በማስፋፋት አባላቱ የድርሻቸውን ልወጡ ይገባል ተብሏል።

ዉይይቱን የመሩት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ ሀቢብ ገለቶ ሲሆኑ የቤተሰቧ አባላትም ተገኝተዋሉ።

የዘገበው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት

የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በመገኘት ድጋፍ ክትትል አደረገ።30/06/2018 ዓ/ም እስከአሁን በተሰሩት...
09/03/2026

የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት በመገኘት ድጋፍ ክትትል አደረገ።

30/06/2018 ዓ/ም

እስከአሁን በተሰሩት ስራዎችን በስፋት በማየት ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ወይይት በማድረግ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የታዩትን ክፍተቶች ላይ ትኩረት በመደረግ መስራት እንደለበት ተገልጿል።

ድጋፍና ክትትሉ ላይ የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ሀላፊና የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዴታሞ ከድር እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ እና የማኔጅመንት አካለት ተገኝተዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ዉይይት አደረገ።የካቲት 10/06/2018 ዓ/ምቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ በከተማችን በሚገኙ ...
17/02/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ዉይይት አደረገ።

የካቲት 10/06/2018 ዓ/ም
ቀጣይ በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ በከተማችን በሚገኙ የታክሲ ማህበራት ተወካዮች ጋር ዉይይት ተደረገ።

በቁሊቶ ከተማ ዉስጥ በሚገኙ ታክሲዎች ሁሉም በተመደበላቸው ፌርማታ እንድሰሩ እና በወጣው ታሪፍ መስራት እንዳለባቸው ተገልጿል።

የዉይይት መድረኩን የመሩ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ ሲሆኑ በዉይይቱ የትራፊክ ፖሊስ አስተባባሪዎች እንድሁም የታክሲ ማህበር ተወካዮችና የማኔጅመንት አካለት ተገኝተዋል።

በከተማዉ በኢኮኖሚ ዘርፍ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸዉን፦ ክቡር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ ገለጹ፤===============የካቲቲ-09/2018ዓ.ም በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስ...
16/02/2026

በከተማዉ በኢኮኖሚ ዘርፍ በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸዉን፦ ክቡር ከንቲባ አቶ ገመዳ መሀመድ ገለጹ፤
===============
የካቲቲ-09/2018ዓ.ም

በሀላባ ዞን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት 2ኛ ዙር 6ኛ አመት 19ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

የኢኮኖሚ ስራዎችን በተመለከተ የከተማ አስተዳደሩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የግማሽ አመቱን የፊዝካል ስራዎች አፈፃፀም በመገምገም በሴክተሮች የታዩ ጠንካራ ጎኖችን እንዲቀጥሉና ታቅደዉ ያልተሰሩ ስራዎች በመለየት በቀጣይ ግማሽ አመት ተጠናክረዉ እንዲሰሩ ግብረ መልስ በመስጠት ተቋማትን አፈፃፀም መሠረት መመዘን መቻሉን ክብር ከንቲባዉ ገልጸዋል።

መንግስት የኑሮ ሁኔታን ደረጃ በደረጃ ለማሻሻል ፈጣንና ዘላቂ ልማትን እዉን ለማድረግ የልማት ፖሊስዎችን ፕሮግራሞችን ቀርፆ እየሰራ መሆኑን የጠቀሱት ከንቲባዉ በዝህም በትምህርት ቤቶች የስነህዝብ ክበባትን በማቋቋም የግንዛቤ ስራ መሰራቱንም አብራርተዋል።

በበጀት አመቱ 668,516,152 ብር በመደበኛና በማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ ለገቢ አሰባሰቡ ዉጤታማነት ከዕቅድ ቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ አንስቶ እስከ ተግባር ምዕራፍ ድረስ የባለድርሻዎች ቅንጅት በማጠናከር ከታቀደዉ 403,207,913 መሰብሰብ መቻሉን ከንቲባዉ በሪፖርታቸዉ አክለዋል።

የታክስ ህጎችን ከማክበር አኳያ በግማሽ አመቱ ጠንካራ የቁጥጥርና የኢንተለጀንስ ስራ በመስራት ከ56 በላይ ግብር ከፋዮች ወደ ጀረጃ "ሀ"ማሸጋገር መቻሉን የገለጹት አቶ ገመዳ በአከፋፈል ሂደቱ ደረሰኝ በአግባቡ ባልሰጡ 24 በግብር ከፋዮች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

የግብርና ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዕድገት እና ለድህነት ቅነሳ የሚያበረክተዉ አስተዋፆ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዉ በግማሽ አመቱ በበልግ ወቅት 1,994 ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች መሸፈን መቻሉን አብራርተዋል።

በመኸር ወቅትም 1,405 ሄክታር መሬት በተለያዩ የሰብል አይነቶች የተሸፈነ ሲሆን በአጠቃላይ በምርት ዘመኑ ከ120,394 በላይ ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን አክለዋል።

በሌማት ትሩፋት ዘርፍ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በማርና በዶሮ ልማት 8 መንደሮችን መመስረት መቻሉን ጠቁመዋል ።

መሠረተ ልማት ስራዎችን በተመለከተ የመንገድ ልማት ተደራሽነትን ለማስፋት በተደረገዉ ጥረት 24 ኪ/ሜ አድስ የጥርጊያ መንገድና የከፈታ ለማድረግ መቻሉን ክብር ከንቲባዉ በሪፖርታቸዉ አሳይተዋል።

በህብረተሰብ ተሳትፎ 57,500,000 በጉልበት ማሳተፍ የተቻለ ስሆን ህብረተሰቡ በመሰረተ ልማት ግንባታዎች በገንዘብ በሃላባ ኢንተርናሽናል ስታድየም ግንባታ ፣ለኮሊደር ልማት እና ለደሃ ደሃ ቤት ግምባታ በብር 151,000 000 ሚሊዮን ብር እንዲሳተፉ መደረጉን ገልጸዋል።

04/02/2026
የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ከቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖትና መንገድ ልማት ጋራ በመሆን በተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ቁጥጥር ተደረገ።ጥር 21/05/2018...
29/01/2026

የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ከቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖትና መንገድ ልማት ጋራ በመሆን በተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ቁጥጥር ተደረገ።

ጥር 21/05/2018 ዓ/ም

የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ከቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖትና መንገድ ልማት ጋራ በመሆን ከአሽርከርካር ተሽከርካሪ ስራ ሂደት እና የህዝብ ትራንስፖርት ሥራ ሂደት በጋራ በመሆን የተወጣጠ ቡድን በተሽከርካሪዎች ላይ ድንገተኛ የቴክኒክ ቁጥጥር በቁሊቶ ከተማ መናኸሪያ የቴክኒክ ቁጥጥር ስራ አከናውኗል ።

ቁጥጥሩ ላይ የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ም/ሀላፊ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዴታሞ ከድር እና የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ እና የዘርፉ ባለሙያዎች ተገኝቷል።

በተደረገው ቁጥጥር በሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ላይ አለስፈላጊ ባውዛዎችን የማስወገድ ፣ ትርፍ /ተለጣፊ/ ወንበር ማስወገድ ፣ የተሽከርካሪ ጤንነት ማረጋገጫ የአደጋ ጊዜ ህክምና ኪት መኖሩን ፣ የደረጃ ወረቀት መኖሩን ፣ በሎ መለጠፉንና ሌሎች መሟላት ያለባቸውን ሁሉን በትኩረት ለማየት ተችሏል።

ተከታታይ የድንገተኛ የቁጥጥር ስራ በመሰረቱ ብዙዎቹ ችግር የሌለባቸው መሆኑ ቲሙ ተገልጿል ።

የድንገተኛ የቁጥጥር ስራ ስሰራ በተሽከርካሪዎች በቴክኒክ ችግር ምክንያት የምከሰተዉን የትራፊክ አደጋንና በንብረት ላይ የምደርሰዉን ዉድመት መቀነስ እንደሚቻል ነው የመምሪያ ም/ኃላፊና ትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊው አቶ ዴታሞ ገልጸዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ ለሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ 2ኛ ዙሪ ግንባታ ምዕራፍ ማስጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ቻሌ...
28/01/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ ለሀላባ ኢንተርናሽናል ስታዲየም ግንባታ 2ኛ ዙሪ ግንባታ ምዕራፍ ማስጀመሪያ የሞባይል ባንኪንግ ቻሌንጅ ተቀላቅሏል።

በዞኑ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ ***********ጥር 15/2018 የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የ201...
23/01/2026

በዞኑ ለተገልጋዩ ህብረተሰብ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተገለጸ
***********
ጥር 15/2018 የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ የ2018 በጀት ዓመት የስድስት ወራትን ዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ ተካሄደዋል።

በአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የታችኛው መዋቅሮች ሪፖርታቸውን በዝርዝር ያቀረቡ ስሆን በሂዳቱ የተለዩ ጥንካሬዎችና ጉድለቶች እንዲሁም ግቦችን ከማሰከት አኳያ አዳጋች የነበሩ ጉዳዮችን በሰፊው ቀርቦ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሱልጣን አ/ቃድር እንደገለጹት ለማህበረሰቡ ምቹና ቀልጣፋ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

አንዳንድ ግዜ የሚታየው የተሽከርካሪዎች ከመናሀሪያ ውጪ የሚሰጠውን አገልግሎት የመንገድ ደህንነቶች በሚገባ መቆጣጠር እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በዘርፉ አልፎ አልፎ የሚስተዋሉ አላስፈላጊ የታሪፍ ጭማሪዎችን ታችኛው መዋቅር በየግዜው ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልገው አመላክተዋል።

በገጠር መንገድ አካባቢ በተለይም የአርሶአደሩን እንግልት የሚያበዙ መንገዶችን ትኩረት በማድረግና በመለየት በግዜው ህብረተሰቡን በማስተባበር መስራትና የተመላሹ መንገድ ማስጠገን እንደሚገባ ገልጸዋል።

የገጠሩ ማህበረሰብ ምርቶቹን ለገበያ የሚያቀርበው በዚህ መንገድ መሆኑን ያነሱት አቶ ሱልጣን ይህን በመገንዘብ የህብረተሰቡን ችግር በተቻለ መጠን መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል።

በተለይም ክረምት ውቅት የገጠሩ መንገድ ጭቃማ በመሆን በተደጋጋሚ ብልሽት እንደሚያጋጥመው ያነሱት ሀላፊው መዋቅሮች ይህን ታሳቢ ያደረገ እንቅስቃሴ ማድረግ እንደሚገባቸው ገልጸዋል።

በግምገማው መድረኩ ላይ የዞኑ ትራንስፖርት መንገድ ልማት መምሪያ ምክትል ሀላፊዎችና የማኔጅመንት አካላት፣ የታችኛው መዋቅር የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ማኔጅመንት አባላት ተገኝተዋል።

በሚፍታህ አብደላ

ለተጨማሪ መረጃዎች በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተላሉን 👇

ቴሌግራም፦ https://t.me/+eIbzwXJYyQNlYjVk

ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/profile.php?id=100083958027668

በቲክቶክበ፦ tiktok.com/

በቲውተር፦ https://x.com/Halabazonecomun?t=jrF0ELvPbOBJOuLT6X3G1A&s=09

ዋትስአፕ፦ https://whatsapp.com/channel/0029Vb3YNPxJZg4GKKQ3Om3v

ዩቲዩብ፦ https://youtube.com/?si=SJOXf764DKjW1CUe

ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/halabazonecomunication?igsh=a3NwdTUwand6NWhn

ምርጫችሁ ስላደረጋችሁን እናመሰግናለን!!

ከትጋት ማማ ላይ የተቃኘ የብልጽግና ድል!!‎‎​በጥር ወር ማለዳ ላይ እንደሚፈነጥቅ የንጋት ፀሐይ የሀላባ የድል ብርሃን በክልሉ ሰማይ ላይ ደምቆ ይታያል ።‎‎ በእነዚህ ምስሎች ላይ የምታዩአ...
22/01/2026

ከትጋት ማማ ላይ የተቃኘ የብልጽግና ድል!!

‎​በጥር ወር ማለዳ ላይ እንደሚፈነጥቅ የንጋት ፀሐይ የሀላባ የድል ብርሃን በክልሉ ሰማይ ላይ ደምቆ ይታያል ።

‎ በእነዚህ ምስሎች ላይ የምታዩአቸው የዋንጫ የሜዳሊያና የሰርተፊኬት መዓቶች ዝም ብለው ከመሬት የተቆለሉ ግዑዝ ቁሶች አይደሉም ።

‎እነዚህ የሺዎች ሌተ ቀን ድካም የሺዎች ላብና የእልፍ አእላፍ ዜጎች ተስፋ ያፈራቸው የብልጽግና ህያው ፍሬዎች ናቸው ። ይህ ድል የሀላባ ህዝብና አመራር በጋራ የደረሱበት የልህቀት ማማ ማሳያ ነው ።

‎​ያልተበገረ የአንድነት ኃይልና የፖለቲካ ቁርጠኝነት

‎​ይህ ታላቅ ውጤት አንድ ትልቅ እውነትን መስክሯል የሀላባ አመራርና የሕዝቡ አንድነት በማንኛውም ማዕበል የማይናወጥና የማይበገር መሆኑን!

‎ እንደ ቋጥኝ የጠነከረው ይህ ትስስር በመንገዳችን ላይ የገጠሙንን ፈተናዎች ሁሉ ወደ ዕድል በመቀየር ለዛሬው ደማቅ ድል አብቅቶናል ። አመራር ማለት በቢሮ ወንበር ላይ ተመቻችቶ ትዕዛዝ ማስተላለፍ ብቻ አለመሆኑን የሀላባ አመራር በተግባር መስክሯል ።

‎የብልጽግና ፓርቲ መሠረታዊ ፍልስፍና የሆነውን ሰው ተኮር አገልግሎት እንደ ቋሚ መመሪያ አንግበው የአመራርና የሕዝብን አደረጃጀት እንደ ድርና ማግ አስተሳስረው የሰሩት ስራ ዛሬ የክልሉን አንደኛነት በኩራት አጎናጽፎናል ።

‎​የሀላባ አመራር ከፍተኛ የሆኑ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እየመራ በዚህ ሁሉ ዉጥረት ዉስጥ ሆኖ በመደበኛዉ ስራም ከፊት ሆኖ መገኘት በእዉነቱ የሚያኮራ ተግባር ነዉ! በእውነትም እንችላለን! ይህ ስኬት በመንግስት ፖሊሲና በህዝብ ፍላጎት መካከል ምንም ዓይነት ክፍተት አለመኖሩን ያረጋገጠ የታሪክ ማህተም ነው ።

‎​ከሁሉም በላይ ግን ልብን የሚነካውና በታሪክ ድርሳናት የሚዘከረው ስኬት በጤናው ዘርፍ የተመዘገበው ድል ነው ይህም የፓርቲያችን መደመር እሳቤ አንዱ አካል የሆነው ለወገን ደራሽነትና ርህራሄ በተግባር የታየበት ነው ።

‎ ወገናችን ታሞ የሚታከምበት አጥቶ ለነፍስ ማቆያ የሚሆን መድኃኒት ፍለጋ ብቸኛ መተዳደሪያ አንጡራ ሀብቱን የሚሸጥበት ያ መሪር የታሪክ ምዕራፍ እንዲያበቃ ተደርጓል ፤ሰው ለሰው መድኃኒቱ ነው እንዲሉ አቅም ያለው አቅም ለሌለው ወገኑ ደራሽ ሆኖ ለህክምና ስቃይ የዳረገው ድህነት በአንድነት ኃይል ተሸንፏል ። ይህ ድል የሀላባ አመራር የላቀ የርህራሄ ልብና የህዝቡ ጥልቅ እምነት የተዋሃዱበት የሀላባ ማንነት ምስክር ነው ። ድህነትን በትብብር መዋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየንበት የሞራል ድላችን ነው ።

‎​የአመራር ብስለትና የህዝብ ተሳታፊነት

‎​ዛሬ ያገኘናቸው ዋንጫዎች የሀላባ አመራር ብቁ አስተባባሪነትና የህዝቡ ቀጥተኛ ተሳታፊነት ውጤቶች ናቸው ። የፓርቲያችንን የብልጽግና ጉዞ ስኬታማ የሚያደርገው ይሄው ከአመራር እስከ ታችኛው የህብረተሰብ ክፍል ድረስ ያለው የተቀናጀ እንቅስቃሴ ነው ። እያንዳንዱ የልማት ስራ የህዝብ ባለቤትነት የተረጋገጠበት በመሆኑ ዛሬ የተገኘው ድል የሁሉም ሀላባዊ የኩራት ምንጭ ሆኗል ። ይህ የአሸናፊነት መንፈስ ማንኛውንም መሰናክል አልፎ ግቡን መምታት እንደሚችል በተግባር የታየበት ነው ።እንኳን ደስ አላችሁ
‎!
‎​ወደ 2018፡ የድል ዳግም የከፍታ ጉዞ

‎​የ2017 ስኬታችን የጉዟችን ማሳረጊያ
‎ ሳይሆን የ2018 ታላቅ ጉዞ መነሻችን ነው ። ዛሬ በእጃችን የያዝናቸው ዋንጫዎች ለነገው ከበድ ያለ ኃላፊነት ትከሻችን ላይ አኑረዋል ። ይህ ወዝ ያለው ድል በ2018 ዓ ም ይበልጥ ተጠናክሮ የሀላባን የከፍታ ዘመን በወርቅ ቀለም ለመጻፍ ቃል የምንገባበት ወቅት ነው ። ትላንት በብልጽግና አስተሳሰብ በትጋት ዘራን ዛሬ በአንድነትና በክብር አጨድን ነገ ደግሞ ሀላባን የክልሉ ብቻ ሳይሆን የሀገር ኩራትና የብልጽግና ተምሳሌት አድርገን እናቆማታለን!

‎​ድል ለትጉሃን! ከፍታ ለሀላባ ህዝብ!

‎ለዚህ ሁሉ ስኬት ላበቀዉ አመራርና የሀላባ ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና ይገበዋል!!

እንኳን ደስ አላችሁ !!



ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በ2017 በጀት ዓመት በማህበረሰብ ጤና መድህን የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ተቋማት እውቅና ሰጡ

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በየቀጠናው የሚከናወኑ ተግባራትን የሚያጠናክር የድጋፍና ክትትል ተካሄደ።በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የመንግስትንና የፓርቲ ...
17/01/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በየቀጠናው የሚከናወኑ ተግባራትን የሚያጠናክር የድጋፍና ክትትል ተካሄደ።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የመንግስትንና የፓርቲ ስራዎችን በውጤታማነት ለመፈጸም በየቀጠናው ሰፊ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በየቀጠናው በመገኘት የስራዎችን ሂደት በቅርበት ተመልክተዋል።

በየዘርፉ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎች አሁን ላይ ያሉበትን ደረጃ በዝርዝር ተገምግሟል።

ከሁሉም የቀጠና አመራሮች ጋር በተደረገው ሰፊ ውይይት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በብቃት ለማድረስና የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በታቀደላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ በቁርጠኝነት መስራት እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።

በስራ ላይ የታዩ ክፍተቶችንና ማነቆዎችን በመለየት በቀጣይ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሰፊ ውይይት ከቀጠና አመራሮች ጋር ተካሄዷል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ ሁሉም የቀጠና አመራሮች የተሰጡ ጥንካሬዎችን በማስፋትና ድክመቶችን በማረም ለተሻለ ስራ ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንግስት የፓርቲ ስራዎችን ገመገመ።ጥር 08/05/2018 ዓ/ምየመንግስት የፓርቲ ስራዎች እስካሁን ያሉበትን ደረጃ በመገም...
16/01/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንግስት የፓርቲ ስራዎችን ገመገመ።

ጥር 08/05/2018 ዓ/ም

የመንግስት የፓርቲ ስራዎች እስካሁን ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ቀጣይ በሚሠሩት ስራዎች ዙሪያ በስፋት ዉይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ በታዩት ጉደለቶችን በማረም መቀጠል እንደለበት ተገልጿል።
የዉይይት መድረኩን የጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሀቢብ ገለቶ የመሩት ሲሆን የጽ/ቤቱ የማኔጅመንት አካለት የተገኙ ሲሆን ዉይይቱ የጋራ አቅጣጫ በማስቀመጥ ተጠናቀዋል።

የሀላባ ሴራ በዓል ቅድመ ዝግጅትን ምክንያት በማድረግ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች በከተማው በተለያዩ አከባቢዎች እየተተኩ ይገኛሉ።የሀላባ ሴራ በዓልን በድምቀት ለማክበር እየተደረገ ያለው...
09/01/2026

የሀላባ ሴራ በዓል ቅድመ ዝግጅትን ምክንያት በማድረግ የመንገድ ዳር የትራፊክ ምልክቶች በከተማው በተለያዩ አከባቢዎች እየተተኩ ይገኛሉ።

የሀላባ ሴራ በዓልን በድምቀት ለማክበር እየተደረገ ያለው ቅድመ ዝግጅት በትራፊክ ደህንነት ዙሪያም ተጠናክሮ ቀጥሏል።

የትራፊክ ምልክቶች መተካታቸው ለከተማዋ ውበት ብቻ ሳይሆን ለህዝቡ ደህንነትም ትልቅ ፋይዳ እንዳለባቸው የሀላባ ዞን መንገድና ትራንስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሱልጣን አ/ቃድር ገልጸዋል።

በበዓሉ ወቅት የተሽከርካሪና የእግር ተጓዥ ቁጥር ስለሚጨምር አዳዲስና ግልጽ የሆኑ ምልክቶች መኖራቸው ሊከሰቱ የሚችሉ የትራፊክ አደጋዎችን ለመቀነስ ይረዳልም ተብሏል።

የሀላባ ሴራ በዓል የሀላባ ብሔረሰብ የባህል፣ የማንነት እና የእርቅ እሴቶች የሚንጸባረቁበት ታላቅ በዓል እንደሆነ የከተማ አስተዳደሩ የመንገድና ትራንስፖርት ሃላፊ አቶ ሐቢብ ገለቶ ገልጸው እንዲህ ያሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በዓሉ በሰላም እና በስርአት እንዲጠናቀቅ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ ብለዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251926294758

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share