የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Halaba Zone Prosperity Party Branch Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Halaba Zone Prosperity Party Branch Office

የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት  Halaba Zone Prosperity Party Branch Office This is Central Ethiopia Region Halaba'S Zone Prosperity Party Branch Office Official page

to organize political participation, to lead government,to use people etc...

የሀላባ ዞን ሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ወቅታዊ ስራዎች እና በሀላባ ሴራ በዓል ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ድጋፍና ክትትል አደረገ ‎‎የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደ...
05/12/2025

የሀላባ ዞን ሱፐርቪዥን ቡድን በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ወቅታዊ ስራዎች እና በሀላባ ሴራ በዓል ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ድጋፍና ክትትል አደረገ

‎የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ደረጃ በደረጃ ለመመለስ በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን የተሰሩ የስራዎች አፈጻጸም በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

‎''ሴራ በዓላችን በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን'' በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የሀላባ ሴራ በዓልን በዚህ ዓመት በድምቀት ለመክበር አመራሩ በአንድነት ውጤታማ ስራ እየሰራ እንደሚገኝም ተጠቁመዋል።

‎በከተማ አስተዳደሩ በንቅናቄ የሚሰሩ ተግባራትን በቅንጅት በመስራት እየታዩ ያሉ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አመራሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ተገልጿል።

‎በድጋፍና ክትትሉ ላይ የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮችን ጨምሩ የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት ተገኝተዋል።
የከተማው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት

ለ20ኛው የኢትዮጵያ  ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ወደ ሆሳዕና ለገቡ የባህል አምባሳደሮችና እንግዶች አቀባበል ተደረገ። (ህዳር 26/2018)፣  በመጪው ሰኞ ለ20ኛ ጊዜ  በማዕከ...
05/12/2025

ለ20ኛው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ወደ ሆሳዕና ለገቡ የባህል አምባሳደሮችና እንግዶች አቀባበል ተደረገ።

(ህዳር 26/2018)፣ በመጪው ሰኞ ለ20ኛ ጊዜ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የኢትዮጵያ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ወደ ሆሳዕና ለገቡ የባህል አምባሳደሮችና እንግዶች በኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስ አደባባይ ደማቅ አቀባበል ተደርጓል።

በእንግዶች አቀባበል ስነ ስርኣቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ስርሞሎ፣የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ፣ ሌሎች የክልሉ፣ የሀድያ ዞንና የሆሳዕና ከተማ አመራሮችና ነዋሪዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች የባህል አምባሳደሮች በአደባባዩ በመዞር የባህል ትርኢት አሳይተዋል ።

በነገው እለትም ሌሎች የኢትዮጵያዊያንን አብሮነትና ወንድማማችነት የሚያመልክቱ በርካታ ፕሮግራሞች የሚቀርቡ ይሆናል።

በሀላባ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ"በሚል መሪ ቃል የፀረ ፆታዊ ጥቃትና ነጭ ቀን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የጽ...
05/12/2025

በሀላባ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ"በሚል መሪ ቃል የፀረ ፆታዊ ጥቃትና ነጭ ቀን ምክንያት በማድረግ
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የጽዳት ተግባር ተከናወነ

በዞኑ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ"ጥቃትን የማይታገስ ማህበረሰብ ለትውልድ ግንባታ"በሚል መሪ ቃል የፀረ ፆታዊ ጥቃትና ነጭ ቀን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የጽዳት ተግባር ተከናውኗል።

በጽዳት ዘመቻው ላይ የሀላባ ዞን ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ መምሪያ ሀላፊ ወይዘሮ እመቤት ጀማል ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የተለያዩ ሴት አደረጃጀቶች ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም በመርሀግብሩ ላይ ልጆቻቸው የተጠቁ እናቶች ከቀይ መስቀል ድጋፍ ተደርጓል።
ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።
ህዳር 26/2018 ዓ.ም፣ሀላባ ቁሊቶ፤

የሴቶች ህጻናት ነው ጧት የጽዳት መርሃግብር ፤ቀይ መስቀል ድጋፍ ወስደው እዛው ልጆቻቸው ለተጠቁ እናነቶች መልሰው ድጋፍ አድርጓል

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ በቀጣዩ ወር ለሚሰጠው ለአራተኛ ዙር የተቀናጀ  የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የአሰልጣኞች  ስልጠና  እየሰጠ ነውህዳር 25/2018ዓ.ም  ቁሊቶ፣የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ከታ...
05/12/2025

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ በቀጣዩ ወር ለሚሰጠው ለአራተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው

ህዳር 25/2018ዓ.ም ቁሊቶ፣
የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ከታህሳስ 3 እስከ 6/2018 ዓ.ም ለሚሰጠው ለአራተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ያአሰልጣኞች ስልጠና እየሰጠ ነው።

ስልጠናው ህዳር 26 እና 27 ለሁለት ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በዞኑ ከ75 ሺ በላይ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት አራተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በቤት ለቤት ጉብኝት እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

የሀላባ ዞን ጤና መምሪያ ሀላፊ ዶ/ር ሸምሱ ረሺድ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች ለሆኑ ህፃናት ከታህሳስ 3 እስከ 6/2018ዓም ቤት ለቤት በሚደረግ ጉብኝት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።

በዞኑ እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ከ75 ሺ በላይ ህፃናት 4ኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት በዘመቻ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት በተጨማሪ በመደበኛ ክትባት መርሀ-ግብር ተደራሽ ያልሆኑ፣ ክትባት ጀምረው ያቋረጡ እድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ ህፃናትን የመለየትና የመከተብ አገልግሎት ከዘመቻው ጋር ተቀናጅቶ ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ቆልማማ እግርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸው ህፃናት ተለይተው ህክምና እንዲያገኙ እንደሚደረግ አብራርተዋል።

ሰልጣኞች ስልጠናውን በተገቢው በመከታተል በቀጣይ በወረዳና ከተማ ማእከል ስልጠናውን ለመስጠት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁና ክትባቱ ለሁሉም ህፃናት በተገቢው ተደራሽ እንዲሆን የበኩላቸው እንዲወጡ አሳስበዋልል።

በስልጠናው ከወረዳና ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት የተወጣጡ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል

"Seeri Kabajjanne Xataali Wolk'anne Lalliinsaammiha!!!" yeenno xawoonsitto laagaani kabajjeenno Halaabi haaxroo zamaani ...
05/12/2025

"Seeri Kabajjanne Xataali Wolk'anne Lalliinsaammiha!!!" yeenno xawoonsitto laagaani kabajjeenno Halaabi haaxroo zamaani dooranshi kabajjaata habayi wogareetiini xiillishshohixne!!
''ሴራ በዓላችን የመቻል አቅም መሳያችን''በሚል መሪ ቃል ለሚከበረዉ ለሀላባ ዘመን መለወጫ በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!
አቶ መሀመድከማል ኑሪዬ የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የዞኑ መንግስት ዋና ተጠሪ!
ህዳር 26/2018 ዓ.ም፣ሀላባ ቁሊቶ፤

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰመስተዳደርና ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ  ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ...
05/12/2025

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰመስተዳደርና ስራ እና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን የተመራ ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አናጋገሩ

ህዳር 26/2018 ዓ.ም
‎ምክትል ርዕሰ መስተዳደሩ በውይይቱ ወቅት ትኩረት ያደረጉት በህጻናት ቀዳማዊ ልጅነት (Early Childhood) ላይ በወጣዉ ፖሊሲ ትግበራ ላይ መሆኑን አንስተዉ መንግሥት በትውልድ ግንባታ ላይ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ ለማስቀጠል አስቀድመን በህጻናት ላይ መሥራት ትልቅ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

ለቀዳማዊ-ልጅነት ዕድገት ባለድርሻ ከሆኑ ተቋማት ውስጥ የጤና ሴክተር ቀዳሚ መሆኑ ይታውቃል በመሆኑም ዘርፉ ህጻናት ከእርግዝና ግዜ ጀምሮ እስከ 6 ዓመት ድረስ በሚደረገው የጤና እንክብካቤ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዝ እንደመሆኑ መጠን ለህጻናት ጤናማ የአመጋገብ ስርዓት እና የዕድገት ክትትል ከማድረግ አኳያ በክልላችን በሁሉም ዞኖች እየተሰራ መሆኑን አንስተው ቀጣይ የማጠናከር ስራ በስፋት ይሰራልም ብለዋል።

በትምህርቱ ዘርፍ በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተደራሽነትን ማስፋት ፤የትምህርት ቤቶች ምገባ እና ልጆች ወደ ቀጣዩ የትምህርት ደረጃ እስኪያድጉ ድረስ የሚደረገውን የድጋፍና የክትትል ሥራ መጠናከር እንዳለበትም አንስተዋል።

በተጨማሪም ዶ/ር አበባየሁ ከተሞች ስገነቡ አስቀድሞ የከተማ ፕላን የህጻናትን ዕድገት ታሳቢ ያደረገ መሆን አለበት ያሉት ስሆን በከተሞቻችን የኮሪደር ስራ መነሻ በማድረግ ለህጻናት የመጫወቻ እና የመዝናኛ ቦታዎችን በማካተት አረንጓዴ እና ለህጻናት ምቹ ስፍራ ከመፍጠር አንጻር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶችና ህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታዋ ክብርት ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ተቋማት በአጠቃላይ በህጻናት ቅዳማዊ ልጅነት ዕድገት ላይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በህጻናት ዕድገት ዋና ዋና ጉዳዮች በተለይም አካላዊ እና አዕምሯዊ ዕድገታቸው ላይ በስፋት እየተሰራ እንደሆነ አስገንዝበዋል።

ቀዳማዊ-ልጅነት ላይ አስቀድሞ መስራት በነገ ህጻናት እጣ ፈንታቸው ላይ ትልቁን አስተዋጽኦ ያደርጋል ያሉት ሚንስትር ደኤታዋ የህጻናት ማቆያ (ዴይ ኬር) ማዕከል መገንባት እና ማዘጋጀት ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ማግኘት የሚችሉትን እንክብካቤ እያገኙ እንድሁም በስራ ላይ የተሰማሩ ቤተሰቦቻቸው ያለ ስጋት ኃላፊነታቸውን እንድወጡ የሚያደርግ በመሆኑ ክልሉ በትኩረት መስራት ይኖርበታል ብለዋል ።

አክለውም ሚንሰተር ደኤታዋ በቀጣይ በህጻናት በቅድመ ልጅነት ዙርያ በተዘጋጀው ፖሊስ ላይ አስፈላጊውን የአድቮኬሲ ስራ እንድሁም በሀገራችን ውስጥ አድስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ አከባቢዎች የተሰሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማጋራት ክትትላቸውን እንደሚያጠናክሩ ተጠቋሟል።

ለህጻናት የሚደረጉ የተኛውም እንክብካቤ የቅንጅት ስራ ድምር ውጤት ነው ያሉት የክልሉ ሰቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ካሴች ኤልያስ ሴክተሩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የማህበረሰብ አቀፍ ህጻናት ማቆያ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ ፤ የህጻናት ማገገሚያ ህንጻ (rehabilitation center) እንድሁም ሌሎች የግንዛቤ ስራ በተገቢው እየተሰራ እንደሆነ አንስተዋል።

South Ethiopia Regional government Communication Affairs Bureau

የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር የጀመራቸው የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ናቸው :-አቶ ዘሪሁን እሸቱ ህዳር 26/2018)የማዕከላዊ ...
05/12/2025

የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር የጀመራቸው የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ናቸው :-አቶ ዘሪሁን እሸቱ

ህዳር 26/2018)የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘሪሁን እሸቱ ነገ ህዳር 27/ 2018 የሚከበረውን 'የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ቀን" በማስመልከት በጽ/ቤታቸው መግለጫ ሰጥተዋል

ኃላፊው በመልዕክታቸው እንዳስታወቁት የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር የጀመራቸው የልማት፣የመልካም አስተዳደር እና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።

በፌደሬሸን ምክር ቤት አሰተባባሪነት እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አሰተናጋጅነት "ዴሞክራሲያዊ መግባባት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሀሳብ የሚከበረዉ የ20ኛዉ ብሔር ብሔረሰቦች ቀን በዓል በህዝቦች መካከል ጠንካራ የወንድማማችነት እሴት እንዲጎለብት ያግዛል ብለዋል።

ህብረ ብሔራዊነት በአንድ ሀገር ውስጥ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች ወይም ህዝቦች አብረው የሚኖሩበትንና ያላቸውን ማንነት፣ ቋንቋ፣ ባህልና መብት እውቅና አግኝቶ የሚተዳደሩበትን ሥርዓት ወይም አስተሳሰብ ያመለክታል ያሉት ኃላፊው በክልሉ የሚገኙ ብሔር ብሔረሰቦች በጋራ ማንነት ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ክልል መመስረት መቻላቸውንም አብራርተዋል።

የብዝሀ ማዕከላትን መነሻ በማድረግ የተመሰረተው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ እንደ ስያሜው ሁሉ የግብርና፣የኢንቬስትመንት የቱሪዝም እና የሌሎችም አያሌ ጸጋዎች ማዕከል መሆኑንም አቶ ዘሪሁን በመግለጫቸው አመላክተዋል።

በክልሉ በሁሉም አካባቢዎች ሰለምን በማጽናት ህብረተሰቡ በልማት ስራው ላይ እንዲያተኩር እየተሰራ መሆኑንም አብራርተዋል።

የክልሉ መንግስት ለሰላም ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑንም ኃላፊው አስረድተዋል።

ክልሉን የሰላም ተምሳሌት ለማድረግ እየተደረገ ባለው ጥረት ማህበረሰቡ ፣የሀገር ሸማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶችና የፀጥታ አካላት የነበራቸው ሚና እጅግ የላቀ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ክልሉ የበርካታ ታሪካዊ ተፈጥሯዊ እና ሰው ሰራሽ የቱሪዝም መዳረሻዎች ባለቤት መሆኑን ተከትሎ ለዘርፉ እድገት አዎንታዊ ሚና ያላቸው ተግባራት ልዩ ትኩረት እንደተሰጣቸውም አቶ ዘሪሁን አስረድተዋል።

ለም መሬት፣ውሃ ሰፊ የሰው ጉልበት እና ተስማሚ የአየር ንብረት እያለ ተመጽዋች መሆን የለብንም በሚል እሳቤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የተጀመረው ጥረት ስኬታማ ስለመሆኑም ኃላፊው በአብነት ጠቅሰዋል።

የህዝብን የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሁሉም መስኮች ውጤታማ ስራዎች ማከናወን መቻሉን አቶ ዙሪሁን አብራርተዋል።

በነገው እለት የሚከበረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቀን የክልሉን ጸጋዎች በማስተዋወቅ ረገድ የላቀ ትርጉም እንደሚኖረውም ኃላፊው በመግለጫቸው አብራርተዋል።

በግብርና ሴክተር የተለዩ ስድስት የግብርና ምሰሶዎችን ለማሳካት ግብ ተጥሎ እየተሰራ ይገኛል ያሉት አቶ ዘሪሁን፣ የአርሶ አደሩን የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ መሰራቱን ተናግረዋል።

ለምግብነት የሚያገለግሉ የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይ ያተኮረ ምርት በስፋት ማምረት፣ የገቢ ግብርና ምርቶች መተካት፣ ከሀገር ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በመጠን፤ በጥራት እና በዓይነት በመጨመር የወጪ ምርትን ማሳደግ ላይ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውንም አብራርተዋል።

በክልሉ በትምህርት፣በጤና በንግድና ገበያ ልማት፣በገቢ አሰባሰብ ፣በስራ እድል ፈጠራ እና በሌሎችም ሴክተሮች የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑንም ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

በመሰረተ ልማት ዘርፍ በመንገድ፣በንጹህ መጠጥ ውሃ ፣በኤሌክትሪክ፣በቴሌኮሙኒኬሽን እና በሌሎችም መስኮች የህዝብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ስራዎችን ማከናወን ስለመቻሉም አቶ ዘሪሁን አብራርተዋል።

የክልሉን ከተሞች ለመኖሪያ፣ለንግድ እና ኢንቬስትመንት ምቹ ለማድረግ እየተካሔደ ያለው ጥረት ውጤታማ መሆኑንም ኃላፊው ጠቅሰዋል።

ይህን ተከትሎም እንደ ክልል 165 ኪ.ሜት የኮሪደር ልማት ስራ ለማከናወን ታቅዶ በክልሉ በ7ቱ የክላስተር ከተሞች ተግባራዊ እየተደረገ ስለመሆኑም አብራርተዋል።

በከተሞች እየተካሔደ ባለው ስራ ማህበረሰቡ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉንም ተናግረዋል

በአጠቃላይ የክልሉ ህዝብ ለቀረበለት የልማት ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠቱ ከ12 ቢሊየን በላይ ብር ድጋፍ ማድረጉን አቶ ዘሪሁን በአብነት ጠቅሰዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) በአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ኢኒሼቲቭ መሰረት በክልሉ 90 ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች ለማከናወን ታቅዶ 83 ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል ብለዋል።

በክልሉ በሰባቱም ማዕከላት የቢሮ ግንባታ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ያነሱት አቶ ዘሪሁን በተለይ በሆሳዕና ከተማ እየተገነቡ ያሉ ተቋማት ፕሮጀክቶችን በአጭር ጊዜ መፈጸም እንደሚቻል ማሳያ መሆናቸውንም አብራርተዋል።

የክልሉ መንግስት 20ኛዉ የኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ደማቅ በሆነ መልኩ ለማክበር ልዩ ትኩረት በመስጠት እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል ።ይህን ተከትሎም በወልቂጤ ከተማ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝቦች የጋራ ባህላዊ እሴት መገለጫ የሆነውን የእንሰት ተክል ሀውልት ምረቃን ጨምሮ ባዛር እና ኤግዚቢሽን እየተካሔደ መሆኑንም አስረድተዋል።

በዓሉን በማስመልከት ወደ ክልሉ እየገቡ ላሉ ልኡካን ቡድኖች ህዝቡ የቆየ የእንግዳ አቀባበል እሴቶቹን በመጠቀም ደማቅ አቀባበል እየተደረገ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል።
Central Ethiopia Regional Government Communication Affairs bureau

የሚዲያ ባለሙያዎች (ሴራ) በዓላችን በተደረጃና በተቀናጃ መልኩ የሚዲያ ስራ በአግበቡ መጠቀም ወጥ የሆነ መልዕክቶች በአንድ ማዕከል በመቅረጽ ሁሉም የሚዲያ አውታር እንዲደርስ መስራት ይገባል ...
05/12/2025

የሚዲያ ባለሙያዎች (ሴራ) በዓላችን በተደረጃና በተቀናጃ መልኩ የሚዲያ ስራ በአግበቡ መጠቀም ወጥ የሆነ መልዕክቶች በአንድ ማዕከል በመቅረጽ ሁሉም የሚዲያ አውታር እንዲደርስ መስራት ይገባል - አቶ ሀሩና አህመድ
====

ህዳር 26/2018 የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በዞኑ 2018 ዓ/ም የሀላባ (ሴራ) መንገሳ በዓል ከወትሮው በተለያ መልኩ ሚዲያ ለመስጠት ለሚዲያና ኮሙኒኬሽን አካላት ኦረንቴሽን ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅት የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ሀላፊ አቶ ሀሩና አህመድ እንደገለጹት የሚዲያ ባለሙያዎች (ሴራ) በዓላችን በተደረጃና በተቀናጃ መልኩ የሚዲያ ስራ በአግበቡ መጠቀም ወጥ የሆነ መልዕክቶች በአንድ ማዕከል በመቅረጽ ሁሉም የሚዲያ አውታር እንዲደርስ መስራት እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

በዘንድሮው አመት የሚከበረውን የሀላባ ሴራ በዓል በቂ የሚዲያ ሽፍን እንዲያገኝ ለማድረግ ኮሚቴ ተቋቋመው እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በዞኑ መልካም ገጽታ ግንባታ በማጎልበት በሚዲያ ዘርፍ የተጀመሩ ሁሉ አቀፍ ልማት እንቅስቃሴ አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ አብራርተዋል።

የሚዲያው ዘርፍ በተለየዩ ዝግጅት የሚከበረው ሴራ በዓል ለህብረተሰቡ ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃን ተደራሽ በማድረግ በቅንጅት መስራት እንዳለበት ተናግረዋል።

የሀላባ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ የሆነው የሀላባ ሴራ በዓል መላው የዓለም ህዝብ ለማስተዋወቅና የብሔረሰቡን ቱባ ባህል ማጉላት እንደሚገባ አቶ ሀሩና አህመድ አሳስበዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሚዲያ ዘርፍ ሀላፊ አቶ በድሩ ከድር በበኩላቸው በዞኑ ማዕከል የሚተላለፈው የበዓሉን አከባበር ህዳት ተዓማኒነት ያለውን መረጃ የብሄረሰቡን እሴቶች ለህብረተሰቡ ማስተዋወቅ ይገባል ብለዋል።

የሀላባን ባህላዊ ስርዓት በማይዳሰስ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ሰፊ ጥረት እየተደረገ መሆኑን የገለጹት አቶ በድሩ ለዚህም የሚዲያ ባለሙያዎች የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመድረኩ ላይ ከተሳታፊ የሚዲያ ባለሙያዎችና ሀላፊዎች ዘንድም የተለያዩ ሀሳብና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸው ቀጠይ አቅጣጫ ተቀምጠዋል።

በመድረኩ ላይ የዞኑ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ጠይባ ዩሱፍ፣ የሀላባ ቲቪ ባለሙያዎች፣ ከሀላባ ዞን ማዕከል እና ከወረዳዎች ከተማ የተወጣጡ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎችን እና የአራቱም ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ሚዲያ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

በሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአርሶአደሩ ግንባር አባላት የ2018 ዓ.ም የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር እና የተለየዩ የመንግስት እና የፓርቲ መዋጮ  መሰብሰቢያ ...
05/12/2025

በሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአርሶአደሩ ግንባር አባላት የ2018 ዓ.ም የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር እና የተለየዩ የመንግስት እና የፓርቲ መዋጮ መሰብሰቢያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ!

በዞኑ በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በጉባ ሸራሮ ቀበሌ 3ቱም ብልፅግና ህብራት አ/አደር አባለት የ2018 ዓ.ም የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር እና የተለየዩ የመንግስት እና የፓርቲ መዋጮ ለመሰብሰብ መስጀመርያ የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ!

(ሕዳር፣26/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በጉባ ሸራሮ ቀበሌ 3ቱም ብልፅግና ህብራት አ/አደር አባለት የ2018 ዓ.ም የገጠር መሬት መጠቀሚያና የእርሻ ስራ ገቢ ግብር እና የተለየዩ የመንግስት እና የፓርቲ መዋጮ ለመሰብሰብ መስጀመርያ የንቅናቄ መድረክ ተካሂዷል
ሲል የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ መንገሳ"ሴራ" በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!አደረሰን!ህዳር 26/2018 የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ መንገሳ "ሴራ" በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!...
05/12/2025

የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ መንገሳ"ሴራ" በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!!አደረሰን!

ህዳር 26/2018 የሀላባ ብሄረሰብ ዘመን መለወጫ መንገሳ "ሴራ" በዓል እንኳን በሰላም አደረሳችሁ!፤አደረሰን!!።

የዘንድሮው ዓመት የሀላባ ሴራ በዓል"ሴራ በዓላችን በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን"በሚል መሪ ቃል በወረዳ/ከተማ ደረጃ ተከብሮ ማጠቃለያ ታህሳስ 26 በዞን ደረጃ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች ከወትሮው በተለያ መልኩ በድምቀት ይከበራል።

በዚህም መሰረት በበዓሉ መስተጋባት የሚገባቸው የመንገሳ (ሴራ) በዓል መልዕክቶች እነሆ፦
➡ የሴራ በዓላችን ለዞናችን ማንሠራራት፤
➡በሴራ በዓላችን በተደመረ አቅም የተሳካ ህልም፤
➡በሴራችን አብረን ሰላማችንን እናጸናለን፤
➡ ሴራችን ለሁለንተናዊ እምርታችን፣
➡ሴራችን የማንሰራራት መንገዳችን፤
➡ሴራችን የጽናትና የአርበኝነት መሰረታችን፤
➡ ሴራችን ለቱሪዝም እምርታችን፤
➡ሴራችን እያከበረን ስታዲየሙን ገንብተን እንጨርሳለን፤
➡የሴራ በዓላችን እያከበርን ለነገ ትዉልድ ብሩህ ተስፋ እንገንባ!!
➡የሴራ በዓል አቅማችን ለዘርፎች እምርታችን፤
➡የሴራ በዓላችን የአንድነታችንና የአብሮነታችን መሰረታችን ነው።
➡የዘርፎችን እምርታ በሴራ በዓል አቅማችን እናሳካለን!።

የሀላባ ሴራ በዓል ሽብርቅ እና የስፖርት ንዑስ ኮሚቴ "ሴራ በዓላችን!፣በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን!!"በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮው የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሴራ (መንገሳ...
05/12/2025

የሀላባ ሴራ በዓል ሽብርቅ እና የስፖርት ንዑስ ኮሚቴ "ሴራ በዓላችን!፣በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን!!"በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮው የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሴራ (መንገሳ)በዓል የቅድመ ዝግጅት ውይይት አደረገ

የሀላባ ሴራ በዓል ሽብርቅ እና የስፖርት ንዑስ ኮሚቴ "ሴራ በዓላችን!፣በህብር የመቻል አቅም ማሳያችን!!"በሚል መሪ ቃል ለሚከበረው ለዘንድሮው የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሴራ(መንገሳ)በዓል ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ውይይት አድርጓል።

የውይይት መድረኩ በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊና የዞኑ የመንግስት ረዳት ተጠሪ እንዲሁም የሀላባ ሴራ በዓል የሽብርቅ እና የስፖርት ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ በአቶ አደም ጀማል ተመርቷል።

በዚህ ወቅት አቶ አደም የሀላባን ቱባ ባህል ጠብቆና አልምቶ በመቆየት ለቀጣዩ ትውልድ ለመሸጋገር በሚደረገው የተቀናጀ ጥረት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ጀምሮ ኮሚቴ የሚጠበቅበትን በብቃት እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኮሚቴው አባላት ለዘንድሮው የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ሴራ(መንገሳ)በዓል ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ እስከ ማጠቃለያ በሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሲል የሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል፣
ህዳር 26/2018 ዓ.ም፤ሀላባ ቁሊቶ፤

20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ልዑክ እንግዶች ሳጃ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።ሆሳዕና፤ህዳር፤26/2018ዓ.ም20ኛ...
05/12/2025

20ኛውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ልዑክ እንግዶች ሳጃ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ነው።

ሆሳዕና፤ህዳር፤26/2018ዓ.ም
20ኛዉን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ለማክበር ወደ ክልሉ እየገቡ ላሉ ከተለያዩ ክልሎች የመጡ ልዑክ አባላት በየም ዞን ሳጃ ከተማ ሲደርሱ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ወንድማማችነትና እህትማማችነትን በሚያጠናክር መልኩ የየም ማህበረሰብ የእንግዳ ተቀባይነትን በሚያሳይ መልኩ በተለያዩ ኩነቶች አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሳጃ ከተማ የደረሱ የጋምቤላ ክልል የባህል ቡድን ፣አኙሃ ብሔረሰብ፣ኑዌር ብሔረሰብ ፣ማጃንግ ብሔረሰብ ፣የኮሞ ብሔረሰብ እና ኦፖ ብሔረሰብ የባህል ልኡካን እንግዶችን የክልል ክላስተርና የዞናችን መቀመጫ ሳጃ አቋርጠው በዓሉ ወደ ሚከበርበት ሆሳእና ከተማ ለሚያልፉ የክብር አቀባበል እየተደረገ ነው።

Address

Central ETHIOPIA Region
Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Halaba Zone Prosperity Party Branch Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት Halaba Zone Prosperity Party Branch Office:

Share