የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office new official page of K'Ulito city Finance Office

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ህብረት አመራሮች ለተለያዩ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ!!‎‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ...
26/05/2026

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር ህብረት አመራሮች ለተለያዩ አቅመ ደካሞች ማዕድ አጋሩ!!

‎በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የብልጽግና ፓርቲ የፐብሊክ ሰርቫንት ግንባር የብልጽግና ህብረት አመራሮች፣ በከተማዋ ለሚገኙ አቅመ ደካማ እና አነስተኛ ገቢ ያላቸው ወገኖች ለበዓል የሚሆን የአስቤዛ ድጋፍ በማድረግ ደስታቸውን ተጋርተዋል።

‎ይህ የማዕድ ማጋራት መርሃ ግብር "አብሮነትና መረዳዳት የባህላችን መገለጫ ነው" በሚል መሪ ቃል የተከናወነ ሲሆን፣ ዋና ዓላማውም በዓላትን አስመልክቶ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ያለምንም ችግር በዓሉን በደስታና በሰላም እንዲያሳልፉ ለማስቻል ነው።

‎የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የኢኮኖሚ ቁ 1 ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሱልጣን እማም ሁሴን በማዕድ ማጋራት ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ማዕድ ማጋራት ልመናን ከመቅረፍ ባለፈ፣ በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ፍቅር፣ አንድነት እና የመረዳዳት እሴት ይበልጥ ያጠናክራል ብሏል።

‎ ድጋፉ ለበዓል ብቻ የሚቆም ሳይሆን፣ ወደፊትም አቅመ ደካሞችን በዘላቂነት ለመደገፍ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑን ገልጸዋል።

‎የማዕድ ማጋራቱ ተጠቃሚ የሆኑት አቅመ ደካሞች በበኩላቸው፤ በአስቸጋሪ ወቅት የተደረገላቸውን ይህንን የበዓል አስቤዛ ድጋፍ ስለተደረገላቸው፣ስላስታወሷቸውና ከጎናቸው ስለቆሙ ያላቸውን ታላቅ ምስጋና እና ምርቃት ለግሰዋል።

25/05/2026
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከዛሬው የአረፋ በዓል የቁም ከብቶች ግብይት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገለጸ!ግንቦት 15/2018 ዓ/ምሀላባ ቁሊቶበሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከ...
23/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከዛሬው የአረፋ በዓል የቁም ከብቶች ግብይት ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ መቻሉ ተገለጸ!

ግንቦት 15/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከዛሬው የአረፋ በዓል የቁም ከብቶች ግብይት 535,300 (አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ) ብር ገቢ መሰብሰብ የተቻለ መሆኑ ተገልጿል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ም/ካንቲባ እና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አ/ቃድር ኢማም ሎላሶ እንደገለፁት የዕለቱን የበዓል ገበያውን ታሳቢ በማድረግ ከከተማው የቅዳሜ ገበያ የከብት ተራ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ሥራ ይህንን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

አቶ አብዲልቃድር አያይዘውም ከተማችን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው በቀጣይም ለገቢ አሰባሰብ ስኬታማነት በጋራ እርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ም/ካንቲባው ለዚህ ስኬት መገኘት በቅንጅት ለሠሩት አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የፀጥታ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከአረፋ በዓል የከብት ገበያ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከከብት በረት (ገበያ) 535,300 (አምስት...
23/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከአረፋ በዓል የከብት ገበያ ከግማሽ ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ።

የአረፋ በዓልን ምክንያት በማድረግ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ ከከብት በረት (ገበያ) 535,300 (አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ሶስት መቶ) ብር ገቢ መሰብሰቡ ተገለፀ።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ም/ካንቲባ እና የገቢዎች ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አ/ቃድር ኢማም ሎላሶ እንደገለፁት የዕለቱን የበዓል ገበያውን ታሳቢ በማድረግ ከከተማው የቅዳሜ ገበያ የከብት ተራ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በተሰራው ሥራ ይህንን ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል።

አቶ አብዲልቃድር አያይዘውም ከተማችን የምታመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ በርካታ የልማት ሥራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመው በቀጣይም ለገቢ አሰባሰብ ስኬታማነት በጋራ እርብርብ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል።

ም/ካንቲባው ለዚህ ስኬት መገኘት በቅንጅት ለሠሩት አመራሮች፣ ባለሙያዎች እና የፀጥታ አካላት በሙሉ ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የኢድ አል አደሃ በዓል ግብይት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው!!!በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር በዓል መቃረብን ተከትሎ የከተማው የገበያ እንቅ...
23/05/2026

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የኢድ አል አደሃ በዓል ግብይት በደማቅ ሁኔታ እየተካሄደ ነው!!!

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የዘንድሮው የኢድ አልፈጥር በዓል መቃረብን ተከትሎ የከተማው የገበያ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ድምቀትና ፍሰት እየተካሄደ ይገኛል።

የበዓል ግብይቱ ሰላማዊ፣ ሸማቹንና ነጋዴውን ያማከለ እንዲሁም ፍትሐዊ እንዲሆን ለማድረግ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች በቅንጅት እየሰሩ ይገኛሉ።

በግብይት ሂደቱ ላይ ሊከሰቱ የሚችሉ ሕገ-ወጥ አሰራሮችን ለመከላከልና ውጤታማ፣ ግልጽና ሕጋዊ የሆነ የገበያ ሥርዓት ለመዘርጋት እየተሠራ ነው።

ከሕጋዊው የገበያ ሥርዓት ውጪ የሚደረጉ ማናቸውንም ሕገ-ወጥ የግብይት እንቅስቃሴዎችና ያለአግባብ ዋጋ ለመጫን የሚሞክሩ አካላትን የመከላከልና የማስተካከል ሥራ በጥብቅ እየተከናወነ ይገኛል።

መልካም የኢድ አልፈጥር በዓል ለሁሉም!

22/05/2026
የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የበጀት ሰሚ ኘሮግራም ማካሄድ ጀመረ።ግንቦት 13/2018 ዓ/ምበዛሬው ዕለት የዞኑ ኢኮኖሚ ዘርፍ መምሪያዎች በ2019 ዓ/ም የበጀት ...
21/05/2026

የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2019 ዓ/ም በጀት ዓመት የበጀት ሰሚ ኘሮግራም ማካሄድ ጀመረ።

ግንቦት 13/2018 ዓ/ም

በዛሬው ዕለት የዞኑ ኢኮኖሚ ዘርፍ መምሪያዎች በ2019 ዓ/ም የበጀት አመት ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት ለሚያከናውኑ የልማት ስራ ዕቅዳቸውንና ለሚያቀርቡት አገልግሎት የሚያስፈልጋቸውን የበጀት ፍላጎት አቅርበው በጋራ እያስገመገሙ ይገኛሉ።

የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ምክትልና የመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዲ በዚህ ግዜ እንደገለጹት ዞኑ የውስጥ ገቢ አቅሞች ላይ ትኩረት በማድረግ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አቶ አብዲ አያይዘውም ከህብረተሰቡ የተሰበሰቡ ሀብቶችን በአግባቡ የህብረተሰቡን ማህበራዊ ፣ኢኮኖሚያዊ ፣መሠረተ ልማትና አስተዳደራዊ ተቋማት ላይ በማፍሰስ የመንግስት አገልግሎት አሰጣጡን በከፍተኛ ደረጃ ማሻሻል መቻሉን ነው ያብራሩት።

ተቋማት የቀጣይ አመት ዕቅዳቸውን በሚያቀርቡበት ወቅት በተለይም የዞኑን የውስጥ ገቢ አቅም ያማከለ ዕቅድ ማቅረብ እንደሚገባቸውም ም/ኃላፊው አሳስበዋል።

በመጨረሻም የበጀት ሰሚ ፕሮግራሙ በነገው ዕለትም የሚቀጥል መሆኑን የገለጹት አቶ አብዲ በነገው ፕሮግራም የማህበራዊ ዘርፎች እንዲሁም አስተዳደራዊና ዴሞክራሲ ተቋማት ዘርፎች የ2019 የሚያከናውኑትን የሰራ ዕቅድና የበጀት ፍላጎታቸውን አቅርበው በጋራ የሚገመግም መሆኑን አመላክተዋል፡ ሲል የሀላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ዘግቧል።

በክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ አማካኝነት በቁሊቶ ከተማ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና በአረንጓዴ ልማት የተሰማሩ ማህበራትን በደረጃ-1 ለመመዘን የተዘጋጀ መድረክ ተጀመረ።ግንቦት 13/2018 ዓ/ምሀላባ...
21/05/2026

በክልሉ ከተማ ልማት ቢሮ አማካኝነት በቁሊቶ ከተማ በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና በአረንጓዴ ልማት የተሰማሩ ማህበራትን በደረጃ-1 ለመመዘን የተዘጋጀ መድረክ ተጀመረ።

ግንቦት 13/2018 ዓ/ም
ሀላባ ቁሊቶ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ አማካኝነት በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ፣ አሰባሰብ እና እንዲሁም በአረንጓዴ ልማት መስኮች የተሰማሩ ማህበራትን በደረጃ አንድ ለመመዘን የተዘጋጀ የምዘና መድረክ በዛሬው ዕለት በሀላባ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳራሽ በይፋ ተጀምሯል።

መድረኩን የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ማዘጋጃ ቤት ም/ስራ አስኪያጅ እና የማስፈፀም አቅም ግንባታና መሰረተ-ልማት ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ኢ/ር ሸምሰዲን መሀመድ በመክፈቻ ንግግር አስጀምረዋል።

ኃላፊው በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ እንደተናገሩት፡ በከተማችን የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድና አሰባሰብ እና እንዲሁም የአረንጓዴ ልማት መስኮችን የስራ አፈፃፀምን በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል፡ የዘርፉ ባለሙያዎችም ክፍተቶቻቸውን በመለየትና በሚሰጣቸው ስልጠና ለማሻሻል እንዲያስችላቸው፡ ሁሉም አባላት ስልጠናውን በልዩ ትኩረት መከታተል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የከተሞች ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሰብስቤ አበራ በበኩላቸው፡ ይህ የስልጠና ሂደት በዘርፉ በተሰማሩ ማህበራት ዘንድ የሚጠበቀውን የስራ ደረጃና እውቀት ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ የሚያግዛቸው እጅግ ወሳኝ ሂደት መሆኑን ተናግረዋል።

ይህም በሙያቸው ብቁ የሆኑ አባላትን በመፍጠር የአገልግሎት ጥራትን የሚያሳድግ ከመሆኑም በተጨማሪ በሁለቱም ዘርፎች ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎችም የሙያ ዕውቅናን ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነም አቶ ሰብስቤ በመድረኩ ላይ አብራርተዋል።

የቁሊቶ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የከተማ ጽዳት አስተዳደርና አረንጓዴ ልማት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪ አቶ ኢብሬ ይማም፡ “የምዘና ስርዓቱ ሁሉም የማህበራቱ አባላት በእውቀታቸውና በችሎታቸው እንዲተማመኑ ከማድረግም ባሻገር ተገቢውን የስራ ዕውቅና እንዲያገኙ የሚያስችላቸው መሆኑን በመገንዘብ ስልጠናውን በሙሉ አትኩሮት መከታተል ይገባል” ሲሉ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ ከማዘጋጃ ቤቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዳይዜሽን ዳይሬክቶሬት እና ከሁለቱ ሂደቶች የተወጣጡ ባለሙያዎችም የተገኙበት ሲሆን፡ ስልጠናው ለተከታታይ ቀናት የሚቀጥል እንደሚሆን ይጠበቃል።

⚠️📢  የገንዘብ ሚኒስቴርን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ ተብለው የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን ተቋሙ አስታወቀ፡፡ስለ ሚኒስቴር መስሪያ...
21/05/2026

⚠️📢 የገንዘብ ሚኒስቴርን ስምና መለያ በመጠቀም ለክልሎችና ለከተማ አስተዳደሮች ስለ ስራ ግብር ቅናሽ ተብለው የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ መሆናቸውን ተቋሙ አስታወቀ፡፡

ስለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራዎች ተዓማኒነት ያላቸውን መረጃዎችን ለማግኘትም የገንዘብ ሚኒስቴርን ትክክለኞቹን ኦፊሻል የማህበራዊ ሚዲያ ገፆችን በመከተል ማግኘት እንደሚገባም ተቋሙ አስገንዝቧል።

Ministry of Finance - Ethiopia

19/05/2026

Address

Alaba K'ulito

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251465560853

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito City Admin.Finance Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share