የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ

የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ This is the official page.

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በቅድመ በልግ የተመረተ ድንች ለገበያ እየቀረበ ይገኛል።ሲል የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።
05/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ በቅድመ በልግ የተመረተ ድንች ለገበያ እየቀረበ ይገኛል።
ሲል የዞኑ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዘግቧል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በሲንቢጣ ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኝ ሙዝ አሁናዊ ገጽታ!!የሀላባ ቲቪ ዘገባ ያመለክታል።
05/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወረዳ በሲንቢጣ ቀበሌ በክላስተር እየለማ የሚገኝ ሙዝ አሁናዊ ገጽታ!!
የሀላባ ቲቪ ዘገባ ያመለክታል።

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረደ በተለየዩ ቀበሌያት የ30 40 30 ኤንሼትቪ አከል የሆናው የቡና ታከለ መረሃ ግብር በተለየዩ ቀበሌያት ተጠናክሮ የቀጠለ ስሆን በዘሬ ቀንም የተገኛው የዝናብሁኔተ...
05/06/2026

በሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረደ በተለየዩ ቀበሌያት የ30 40 30 ኤንሼትቪ አከል የሆናው የቡና ታከለ መረሃ ግብር በተለየዩ ቀበሌያት ተጠናክሮ የቀጠለ ስሆን በዘሬ ቀንም የተገኛው የዝናብሁኔተን በመጠቀም በሸዋኮ ቀበሌ በበንበና ብልፅግና ህብረት መንደርን መሰረት በመድረግ ተከለ የተከሄደ ስሆን ተግበሩ በሁሉም ቀበሌየት ተጠናክሮ መቀጠል እንደለበት የግብርና ጽ/ቤት አሰስቧል።

የቅድመ በልግ ምርትን ለማሳደግ የተደረገው የተቀናጀ ጥረት ውጤት እያሳየ ነው:- አቶ ገመዳ ሄለሞ******በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ የቅድመ በልግ እርሻ ስራ በጥ...
05/06/2026

የቅድመ በልግ ምርትን ለማሳደግ የተደረገው የተቀናጀ ጥረት ውጤት እያሳየ ነው:- አቶ ገመዳ ሄለሞ
******
በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክልል ሀላባ ዞን አቶቲ ኡሎ ወረዳ የቅድመ በልግ እርሻ ስራ በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝና የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብ ስራ መጀመሩ ተገለጿል

በወረዳው የተለያዩ ቀበሌያት በጥረት እየለሙ ያሉ የደረሱ ሰብሎችን የመሰብሰብና በአዝመራ ላይ ያሉትን የመንከባከብ ስራ በአመራሮች ምልከታ ተደርጓል።

የዝናብ እርጥበትን በመጠቀም በቅድመ በልግ የተዘራው በቆሎ ሰብል ተስፋ ሰጭ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ሰፊ ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ የወረዳው ምክትል አስተዳደርና የግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ ተናግረዋል።

​በ2018 ምርት ዘማን የቅድመ በልግ እርሻን በቦቆሎ፤ በሎቄና በድንች 1610 ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ተቅዶ 1605 ሄክታር መሬት በዘር የተሸፈነ ስሆን ከዚህም 193,200 ኩንታል ምርት ይጠበቃል።

በትኩረት እየለሙ ከሚገኙ ሰብሎች መካከል በቆሎ ሰብል በጥሩ የዕድገት ደረጃ ላይ እንደሚገኝና አርሶ አደሩ አስፈላጊውን የእንክብካቤ ስራ በማከናወን የልማት ጣብያ ሰራተኞችም አስፈላጊውን ድጋፍና ክትትል እያደረጉ እንደሚገኝ አቶ ገመዳ ተናግረዋል።

በቅድመ በልግ የለሙ ​ድንችና ቦሎቄ፦ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ምርታማነት የታየባቸው ሲሆኑ የደረሱ ሰብሎችን አርሶ አደሩ ምርቱ ሳይባክን በጥራት እንዲያሰባስብ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በዚህም አሁን ላይ ትኩረታችን የደረሰውን ምርት በአግባቡ መሰብሰብና ቀሪዎቹን መንከባከብ ላይ ይሆናል" ሲሉ ተናግረዋል።

​የወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊና የመንግስት ተጠሪ አቶ በክሪ አብደላ በበኩላቸው ከምርጫ ማግስት በወረዳው ሁሉንም ልማታዊ የለውጥ ተግባራት አቀናጅቶ በመምራት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አቶ በክሪ በቦታው ተገኝተው የሰብሎቹን ምርታማነትና የአሰባሰብ ሂደቱን የተመለከቱ ሲሆን የቅድመ በልግ እርሻ የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና መኖሩን ተናገረዋል ።

አያይዘውም አርሶ አደሩ በአመት ሶስት ጊዜ በላይ የመምራት ባህልን ለማሳደግ ቅድመ በልግ እርሻ ወሳኝ መሆኑን አክለዋል።
ሀላባ ቲቪ ዘገባ ያመለክቴል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርናው ሴክተር  የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና 15ቱ ኢኒሼቲቮች
05/06/2026

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የግብርናው ሴክተር የተቀናጀ ግብርና ለቤተሰብ ብልጽግና 15ቱ ኢኒሼቲቮች

‎በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወራዳ በ2018 ዓ/ም ምርት ዘማን  በመደባኛ በልግ የታዛራ ቦቆሎ ቁሉብ እነ ኡዳና ጮሎቅሳ ቀበሌዎች የዞኑ የግብርና ከዘርፍ ባለሙያዎች የሜጋ ክላስተር የተዘራ የቦቆሎ...
05/06/2026

‎በሀላባ ዞን ዌራ ዲጆ ወራዳ በ2018 ዓ/ም ምርት ዘማን በመደባኛ በልግ የታዛራ ቦቆሎ ቁሉብ እነ ኡዳና ጮሎቅሳ ቀበሌዎች የዞኑ የግብርና ከዘርፍ ባለሙያዎች የሜጋ ክላስተር የተዘራ የቦቆሎ ክላስተር ድጋፍና ክትትል አደረጉ ።

‎የዌራ ዲጆ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት መረጃ ያመለክታል።

የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠንና አዳዲስ ኢንሼቲቮችን በሁሉም  አካባቢ በማስፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የግብርና ልማት ሰራተኞች የማይተካ ሚና አላቸው -አቶ ኡስማን ሱሩርግንቦት...
05/06/2026

የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማፋጠንና አዳዲስ ኢንሼቲቮችን በሁሉም አካባቢ በማስፋት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የግብርና ልማት ሰራተኞች የማይተካ ሚና አላቸው -አቶ ኡስማን ሱሩር

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ዱራሜ ካምፓስ እየተካሄደ በሚገኘው የተቀናጀ ግብርና ስልጠና ላይ፣ ከተሳታፊ የልማት ጣቢያ ሰራተኞችና ባለሙያዎች ለተነሱ ዘርፈ-ብዙ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር ሰፊ ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።

አርሶ አደሩ በቴክኖሎጂ የታገዘ ዘመናዊ የግብርና አሰራርን ተከትሎ ተጠቃሚነቱን ለማሳደግ የግብርና ልማት ጣቢያ ሰራተኛዉ በባለቤትነት ሊሰራ እንደሚገባም አሳስበዋል።

ቢሮዉ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እየተደረገ ያለዉን ጥረት ለማጠናከር ከግብዓአት አቅርቦትና ከሌሎች ተያያዥ ነገሮች ተያይዞ የሚነሱ ማነቆዎችን ለመፍታት በትኩረት እንደሚሰራም ገልጸዋል።

በዚህም የልማት ጣቢያ ሰራተኛ ሲባል የግብርና ባለሙያዎችን ብቻ ሳይሆን የእንስሳት ጤና፣ የመስኖ፣ የህብረት ስራ እና በየቀበሌው ያሉ ሁሉንም የዘርፉ ተዋናዮች የሚያካትት በመሆኑ፤ በባለሙያዎች መካከል የሚደረግ የተቀናጀ ጥረት ለስኬቱ ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል።

አርሶ አደሩን ከግብዓት አቅርቦት እስከ ገበታ በተሟላ የእሴት ሰንሰለት ውስጥ ዋና ተዋናይ በማድረግ የገበያ ችግሮችን በዘላቂነት መፍታትና የገቢ አቅሙን ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል።

በስልጠናው የተነሱ መመሪያዎችና አቅጣጫዎች እዚህ ተነግረው የሚቀሩ ሳይሆኑ፣ ወደ መሬት ወርደው በተግባር ሊተረጎሙና ተጨባጭ ውጤት ሊያመጡ እንደሚገባ በጥብቅ አሳስበዋል።
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

በሀለባ ዞን ዌራ ድጆ ወረዳ ለይ ጡቃ ቀበሌ የገበሬዎች ማሠልጠኛ FTC የተለያዩ ፍራፍሬ እና ቡና ምርት ያለበት ደረጃ
04/06/2026

በሀለባ ዞን ዌራ ድጆ ወረዳ ለይ ጡቃ ቀበሌ የገበሬዎች ማሠልጠኛ FTC የተለያዩ ፍራፍሬ እና ቡና ምርት ያለበት ደረጃ

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በቅድመ በልግ የተዘራው የበቆሎ ሰብልን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ ተዟዙሮ ምልከታ አደረ...
04/06/2026

በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በተለያዩ ቀበሌዎች በቅድመ በልግ የተዘራው የበቆሎ ሰብልን የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ ተዟዙሮ ምልከታ አደረጉ
**************
(ግንቦት፣27/2018 ዓ.ም)ጉባ አቶቲ ኡሎ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን በሀላባ ዞን በአቶቲ ኡሎ ወረዳ በጉባ ሸራሮና በመቃላ ለ ቀበሌ የዝናብ እርጥበት በመጠቀም በቅድመ በልግ የተዘራው ሰብል ተስፋ ሰጭ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ገመዳ ሄለሞ እንደገለጹት የተገኘውን የዝናብን እርጥበት መጠቀም የምግብ ዋስትናችንን ለማረጋገጥ አይነተኛ ሚና መኖሩን ተናገረዋል

አያይዘውም አርሶ አደሩ በአመት ሶስት ጊዜ በላይ የመምራት ባህልን ለማሳደግ ቅድመ በልግ ስራ አስፈለጊ በመሆኑ የቅድመ በልግ ስራ ምርትና ምርታማነትን እና ተጨማሪ ምርት ለማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አስፈላጊውን ድጋፍ እና ክትትል እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል።

የአቶቲ ኡሎ ወረዳ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዘግቧል !!

የዞናችን ህዝብ በምርጫው ወቅት ያሳየውን ቆራጥነት በዞኑ በተጀመሩ ሌሎች የልማት ዘርፎች ሊደግሙት ይገባል - ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን******ግንቦት 28/2018 የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ...
04/06/2026

የዞናችን ህዝብ በምርጫው ወቅት ያሳየውን ቆራጥነት በዞኑ በተጀመሩ ሌሎች የልማት ዘርፎች ሊደግሙት ይገባል - ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን
******
ግንቦት 28/2018 የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሀላባ ዞን ባሉ የተለያዩ ምርጫ ክልሎች የተደረገው የምርጫ ሂደት ከድምጽ አሰጣጥ ጀምሮ እስከ ድህረ ምርጫ ድረስ በሰላም፣ በቅንጅት እና በትብብር በመጠናቀቁ ለመላው ለዞኑ ህዝብ እንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በዚህም የሀላባ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ ሙህዲን ሁሴን እንደገለጹት የዞናችን ህዝብ በምርጫው ያሳዩትን ቆራጥነት በተጀመሩ በሌሎች የልማት ዘርፎች ሊደግሙት እንደሚገባ ገለጹ።

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪው ገለጻ የዞኑ ህዝብ በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ላሳየው ትዕግስትና ቆራጥነት ምስጋና አቅርበዋል።

በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በምርጫው ዕለት ህዝቡ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው ድምጻቸውን ሰጥተዋል ብለዋል።

የዞናችን ህዝብ ሁልጊዜም ለሀገራዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ያላቸውን ቀዳሚና የነቃ ተሳትፎ በከፍተኛ አክብሮት ማድነቃቸውን ተናግረዋል።

ለሀላባ ዞን ህዝብና ለመላው የሀገራችን ህዝቦች ግንቦት 24 በዞናችንም ሆነ በሀገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የተጻፈበት ታላቅ ቀን መሆኑን ገልጸዋል።

ዜጎች ሉዓላዊ ስልጣናቸውን በምርጫ ካርዳቸው አማካኝነት በነፃነት የሚገልጹበት 7ኛው ሀገራዊ እና ክልላዊ ምርጫ በሀላባ ዞን በሁሉም የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች ፍጹም ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ነፃ እና ስኬታማ በሆነ መልኩ ተጠናቀዋል ብለዋል።

ይህም የምርጫ ሂደት ማህበረሰባችን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማስቀጠል ያለውን የበሰለ የፖለቲካ ባህል እና ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያሳየበት መሆኑን ተናግረዋል።

በሂደቱም የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች ላሳዩት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች ታዛቢዎችና ወኪሎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካለት ላሳያችሁት የሀገርና የህዝብ ውግንና በዞኑ አስተዳደርና በሀላባ ህዝብ ምስጋና መቅረባቸውን ገልጸዋል።

በዞኑ የተካሄደው የምርጫ ሂደት ያለምንም የጸጥታ ስጋት ሙሉ በሙሉ ሰላማዊና ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ታላቅ ሀላፊነት ለተወጡ የጸጥታ አካላት፣ ለመላው የዞኑ ማህበረሰብ፣ እና ሌሎች ለሚመለከታቸው ባለድርሻ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በተለይም ሚዲያዎች በተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት የምርጫ ሂደቱ ተጀምሮ እስኪጠናቀቅ ወቅታዊና ፈጣን መረጃዎችን ለህብረተሰቡ በማድረሳቸው ምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከምርጫው ማግስትም መላው የዞናችን ነዋሪዎች የተለመደውን አንድነት፣ አብሮነት እና ወንድማማችነት ይበልጥ በማጠናከር፣ ፊታችንን ሙሉ በሙሉ ወደ ልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በማዞር የጋራ ብልጽግናችንን ለማረጋገጥ በጋራ መቆም እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም፣ በአሁኑ ወቅት በየምርጫ ጣቢያው የተለጠፉ ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶችን በትዕግስት በመመልከት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋዊ ውጤት እስኪሰጥ ድረስ መላው የዞኑ ህዝብ በተለመደው ትብብር እንዲጠባበቅ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የሀላባ ቲቪ መረጃ ያመለክታል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ዞን ግብርና መምሪያ:

Share