የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito city Addmin.Fainance Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Alaba K'ulito
  • የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito city Addmin.Fainance Office

የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito city Addmin.Fainance Office Government Organization

🔑የሀላባ ቁሊቶ ከተማ መልሶ ማልማት ስራ ያለበትን ደረጃ እናስቃኛችሁ🔑✅ከተሞች ከሚገጥማቸው ፈተናዎች መካከል የከተሞች ድቀት ወይም እርጅና አንዱና ዋናው ችግር ነው፡፡✅የሀላባ ቁሊቶ ከተማ በ...
08/04/2022

🔑የሀላባ ቁሊቶ ከተማ መልሶ ማልማት ስራ ያለበትን ደረጃ እናስቃኛችሁ🔑

✅ከተሞች ከሚገጥማቸው ፈተናዎች መካከል የከተሞች ድቀት ወይም እርጅና አንዱና ዋናው ችግር ነው፡፡

✅የሀላባ ቁሊቶ ከተማ በከተማው መሀል አከባቢ በ1956-60ዎቹ ጀምሮ በግለሰቦች የተያዘ ቦታ በመልሶ ማልማት ድንቅ ስራ እተሰራ መሆኑን ማየት ችለናል፡፡

✅ለክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መረጃ የሰጡት የሀላባ ዞን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ሀላፊ አቶ አንዋር ሲርጋፋ ከተማዋ የተቆረቆረችው ከዛሬ 100 ዓመት በላይ በመሆኑ በርካታ የደቀቁ ቦታዎች አሉ ብለዋል፡፡

✅ይሄንን የደቀቁ ቦታዎች መልሰን ማልማት እንዳለብን ከህብረተሰቡ ጋር መተማመን በመፍጠር እየተሰራ እንደሆነ አቶ አንዋር ገልጸዋሉ ፡፡

✅ከክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ጋር በመቀናጀት ግለሰቦቹ ሳይፈናቀሉ ባሉበት በማህበር ተደራጅተው በአካውንታቸው ቆጥበው መሬቱ ተሸንሽኖ ለኮመርሻል፣ ለአረጓዴ ልማት እንዲሁም ለኢንቨስትመንት እንዲህ በሚያምር መልኩ እንዲውል ተደርጓል ይላሉ አቶ አንዋር፡፡

✅ነዋሪዎቹም ከታች በፎቶ ላይ እንደሚናየው የሚያምር ገጽታ ያለው የመኖሪያ ቤት እየተገነባላቸው እንደሆነ አስተያየታቸውን ገልጿሉ፡፡

✅የተረፈው መሬትም ለተለያዩ አገልግሎቶች በማዋል የደቀቀውን ገጽታ ከመቀየር ባለፈ ህዝቡና መንግስት ማግኘት የሚገባውን ገቢ እያገኘ ይገኛል፡፡

✅አሁንም በመልሶ ማልማቱ በርካታ የሚሰሩ የከተማው ቦታዎች እንዳሉ የስራ ኃላፊው አቶ አንዋር ሲርጋፋ ተናግረዋል፡፡

✅የደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ የመሬት ልማት ማነጅመንት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ዝናቡ ተካቤ እንደ ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት ግንዛቤ ተሰጦ በትኩረት እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አንዱ የከተማ መልሶ ማልማት ነው ብለዋል።

✅ከሀላባ ቁሊቶ ከተማ መልሶ ማልማት ስራ ለሎች ከተማ ተሞክሮ መውሰድ አለባቸው ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልጸዋል።

✅ይህ ተግባር የከተማ ገጽታን የሚቀይር፣ ገቢን የሚያሳድግና ለዜጎች የስራ ዕድልን የሚፈጥር ነው።

✅እንደ ኢንጅነር ዝናቡ ገለጻ ከደቀቁ የከተማ ቦታዎች የሚነሱ ሰዎች ካሳ ወይም ምትክ ቦታ መስጠት ተገቢ መሆኑን አስታውቀዋል።

✅በመልሶ ማልማት ስራ ሌሎች ከተሞችም እንደ ሀላባ ቁሊቶ ከተማ መረባረብ እንዳለባቸው ኢ/ር ዝናቡ አስገንዝበዋል።

✅ዋና ዳይሬክተሩ ቀጥሎ ለህብረተሰቡንና ለአመራሩ ግንዛቤ በማስፋት ወደ ሌሎች ከተሞች ማስፋፋት ተገቢ ነው ይላሉ።

✅በዲላ ከተማ፣ ወላይታ ዞንና ጉራጌ ዞን ከተሞችም ተመሳሳይ ስራዎች እንዳሉ ጠቁመው በሌሎች ከተሞች የማስፋቱን ስራ ክልሉ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

👉መረጃው የደቡብ ክልል ከተማ ልማትና ቤቶች ቢሮ ነው።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ  ዘርፋ ቁ.1 መሠረታዊ ድርጅት የፋይናንስ ሴክተር ህዋስ በዛሬዉ ዕለት  "ልሳነ-ብልፅግና "በብልጽግና ፓርቲ ንድፈ -ሀሳብ መጽሄት  ላይ ሰፋ ያለ ዉ...
08/04/2022

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር የኢኮኖሚ ዘርፋ ቁ.1 መሠረታዊ ድርጅት የፋይናንስ ሴክተር ህዋስ በዛሬዉ ዕለት "ልሳነ-ብልፅግና "በብልጽግና ፓርቲ ንድፈ -ሀሳብ መጽሄት ላይ ሰፋ ያለ ዉይይት አድርጓል።

መጽሄቷ በጽሁፏ የዳሰስችያቸዉ ዋና ዋና ጉዳዮች ማለትም
1 የቀጠናዉ አገራት ፋላጎት ፣የዉጭ ኃይሎች አሰላለፋና የኢትዮጵያ ሚና፣
2 አገራዊ ክብርን ያማከለ የዉጭ ግንኙነት ፖሊሲያችን ስኬቶች ፣ፈተናዎችና ቀጣይ አቅጣጫዎች፣
3 ሀገራዊ ምክክር ፤ለሀገራዊ ትንሳዔ
4 የብልጽግና እሳቤዎች እና ፖሎትካዊ ሁኔታዎችን የተመለከቱ ነጥቦች በጽ/ቤቱ ኃላፊ ለአባላቱ ቀርበዉ ጥሩ ዉይይት ተደርጓል።

በመድረኩ ከከፓርቲ ሥራዎች የህዋስ ዉይይት በተጨማሪ በሴክተሩ አጠቃላይ የመንግስት ሥራዎች አፈጻጸምን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይም ጠንከር ያለ ዉይይት በማድረግ ቀጣይ አቅጣጫዎችን በማስቀመጥ ዉይይቱ ተጠናቋል።

21/03/2022
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በካፒታል በጀት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው እየተከናወኑ ነው ተባለ።መጋቢት 4/2014ሀላባ ቲቪ=========በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አ...
13/03/2022

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በካፒታል በጀት እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ጥራታቸውን ጠብቀው እየተከናወኑ ነው ተባለ።
መጋቢት 4/2014
ሀላባ ቲቪ
=========
በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በካፒታል በጀት እየተሰሩ የሚገኙ የፕሮጀክት ልማት ስራዎች ጥራታቸውን በጠበቀ መልኩ በፍጥነት በመሰራት ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል።

የፕሮጀክት ስራዎችን የከተማውን መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታገል ጌታቸውን ጨምሮ፣የከተማው ከፍተኛና መካከለኛ የስራ ሀላፊዎች ፕሮጀክት ስራዎቹ እየሄዱ ያሉበትን ሂደት ተመልክተዋል።

በከተማዋ በአራቱም አቅጣጫና በተለያዩ አከባቢዎች ላይ የህዝብን ጥያቄ መሰረት በማድረግና የከተማዋን እድገትና ደረጃ በሚመጥን መልኩ የጌጠኛ ድንጋይ ኮብልስቶን መንገድ ስራዎች በተደራጀ መልኩ እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል።

ፕሮጀክት ስራዎቹ በ UIIDP ካፒታል በጀት እንደሚገነቡ የተገለፀ ሲሆን ፕሮጀክት ስራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ዘርፈ ብዙ ተግባራትም እየተከናወነ እንደሚገኙ ተብራርቷል።

የከተማው መንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታገል ጌታቸው በምልከታው ወቅት እንደተናገሩት የከተማዋን የእድገት ጉዞ የሚያፋጥኑት የልማት ስራዎች በፍጥነት በመሰራት ላይ ነው ብለዋል።

በከተማዋ በተለያዩ አከባቢዎች የውስጥ ለውስጥ የጌጠኛ ድንጋይ የኮብልስቶን መንገድ ስራዎች በሚገርም መልኩ እየተሰሩ መሆናቸውን በመግለፅ የየአከባቢው ማህበረሰብ ለመንገድ ስራዎቹ ስኬት እያደረጉ ያሉትን ተሳትፎ አድንቀው በከተማ አስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ረሻድ ኪያር በበኩላቸው በከተማዋ በካፒታል UIIDP በጀት እየተሰሩ የሚገኙ ስራዎች በታቀደላቸው እቅድ መሰረት እየተሰሩ ነው ብለዋል።

በከተማዋ የጌጠኛ ድንጋይ ኮብልስቶን መንገድ ስራ ጥራቱን ጠብቆ ከመሰራቱም ባሻገር በፍጥነት እየተሰሩ ያሉት አቶ ረሻድ እንደ ከተማ አስተዳደር ፕሮጀክት ስራዎቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በትኩረት እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።

ከጌጠኛ ድንጋይ ኮብልስቶን መንገድ ባሻገር በከተማ አስተዳደር የጎርፍ አደጋ የሚዘውትርባቸውን አከባቢዎች በመለየት የውሀ መውረጃ ድሬኔጅ ግንባታ ስራዎችም እየተሰሩ መሆናቸውን ሀላፊው አብራርተዋል።

ዘገባው የሀላባ ቲቪ ነው

ተርን ኦቨር ታክስተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ ...
10/03/2022

ተርን ኦቨር ታክስ

ተርን ኦቨር ታክስ በአገር ውስጥ በሚከናወን የዕቃ ወይም የአገልግሎት ሽያጭ ወቅት በየደረጃው የሚጣል የታክስ ዓይነት ነው፡፡
ተርን ኦቨር ታክስን ሰብስቦ ገቢ የማድረግ ግዴታ


ለተጨማሪ እሴት ታክስ ያልተመዘገበ ወይም ዓመታዊ የንግድ አንቅስቃሴው ከብር 1 ሚሊየን በታች የሆነ ማንኛውም በንግድ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ወይም ድርጅት በአገር ውስጥ ከሚሸጣቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች ላይ ሰብስቦ ለሚመለከተው የታክስ መስሪያ ቤት/ሚኒስቴር ገቢ ያደርጋል፡፡

ዕቃዎች ወይም አገልግሎቶችን የሚሸጥ ማናቸውም ሰው ወይም ድርጅት በሽያጭ ላይ ሊከፈል የሚገባውን ታክስ ከገዥው ሰብስቦ ለሚስቴሩ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ስለሆነም ሻጩ ለታክሱ የመጀመሪያ ተጠያቂ ይሆናል፡፡

የተርን ኦቨር ታክስ የስሌት መሠረት

ተርን ኦቨር ታክስ የሚሰላበት የዋጋ መሠረት የዕቃው ወይም የአገልግሎት ጠቅላላ የሽያጭ ገቢ ይሆናል፡፡

የሚከተሉት ከተርን ኦቨር ታክስ ክፍያ ነፃ ናቸው፡-

1. ቢያንስ ሁለት ዓመት ያገለገለ መኖሪያ ቤት ሽያጭና የመኖሪያ ቤት ኪራይ፤

2. የፋይናንሰ አገልግሎቶች፤

3. ለሳንቲሞችና ሜዲሊያዎች ጥናት አገልግሎት ከሚውሉት በስተቀር የአገር ውስጥና የውጪ አገር ገንዘቦችና የዋስትና ሰነዶች ማሰራጨት፤

4. በኃይማኖት ድርጅቶች የሚሰጡ የእምነት ወይም ከአምልኮ ጋር የሚገናኙ አገልግሎቶች፤

5. የሕክምና አገልግሎትና አግባብ ባለው የመንግስት መ/ቤት በሚወጣ መመሪያ መሠረት በሐኪም የሚታዘዙ መድኃኒቶች፤

6. በትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የማስተማር አገልግሎቶች እንዲሁም ለሕፃናት ጥበቃ በመዋዕለ ሕፃናት የሚሰጡ አገልግሎቶች፤

7. የኤሌክትሪክ፣ የኪሮሲን የውሃ አቅርቦት፤

8. የትራንስፖርት አገልግሎት፤

9. ማናቸውንም የሥራ እንቅስቃሴ ለማከናወን ለሚሰጥ ፈቃድ ለመንግስት የሚፈፀም ክፍያ፤
10. 60% እና ከዚያ በላይ ሠራተኞቹ አካል ጉዳተኞችን ቀጥሮ የሚያሰራ ድርጅት የሚያቀርባቸው ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤

11. መጽሐፍት፤

12. ሌሎች ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ የሆኑ ሁሉ ናቸው፡፡

መረጃዉ ከገቢዎች ሚኒስቴር fb ገጽ የተወሰደ ነው።

28/02/2022
25/02/2022
በከተማዋ ውስጥ በተለያዩ ቀጠናዎች የተጀመረው የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ።በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም  በUIDP በጀት ለመሰራት ...
22/02/2022

በከተማዋ ውስጥ በተለያዩ ቀጠናዎች የተጀመረው የኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በጥራትና በፍጥነት እየተሰራ እንደሆነ ተገለፀ።

በሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር በ2014 ዓ.ም በUIDP በጀት ለመሰራት ዕቅድ ተይዞ ወደ ተግባር የተገበው የጌጠኛ ድንጋይ/ኮብልስቶን ንጣፍ ስራ በጥራትና በፍጥነት እየተካሄደ መሆኑ ተገልጿል።

በዛሬው ዕለት የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ሃሩና አህመድ እና በቁሊቶ ከተማ አሰተዳደር የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ታጋል ጌታቸው እንዲሁም የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች የኮብልስቶን ንጣፍ ስራውን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም የኮብልስቶን ንጣፍ እና የድርኔጅ ስራ በጥራት እና በፍጥነት እየተሰራ እንደሆነና ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልጸዋል ስል የዘገበው የሀላባ ቁሊቶ ከተማ መንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ነው።

የካቲት 15/2014 ዓ.ም ቁሊቶ

Address

Alaba K'ulito

Telephone

+251465560853

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ቁሊቶ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት-Halaba K'Ulito city Addmin.Fainance Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share