የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ

የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ https://youtube.com/?si=0AgS5fdDK0fxiZF5
ለህዝብ ትክክለኛውን መረጃ በወቅቱ ማስተላለፍ ልዩ ምልክታችን ነወ።

ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ =====ግንቦት 21/2018 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬ...
29/05/2026

ለምርጫው ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ - ኢጋድ
=====

ግንቦት 21/2018 የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) በኢትዮጵያ ለሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ስኬታማነት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አደርጋለሁ አለ፡፡

ምርጫው ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች እንዲሆን የድርሻውን እንደሚወጣ አረጋግጧል።

ኢጋድ በማህበራዊ ትስስር ገጹ እንዳስታወቀው÷ የኢጋድ የምርጫ ታዛቢ ልዑክ ከኢትዮጵያ ሲቪል ማህበራት የምርጫ ትብብር ጋር በመሆን የምርጫውን ሂደትን መደገፍ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክሯል።

በውይይቱ የሲቪል ማህበረሰቦች የዴሞክራሲ ሂደቶችን፣ የምርጫ ዝግጅት እና የአካባቢ ምርጫን በመታዘብ ረገድ የሚኖራቸውን ሚና በተመለከተ ምክክር መደረጉን አንስቷል፡፡

ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ ለማካሄድ የመራጮች የሲቪክ ትምህርት አስፈላጊ መሆኑ በውይይቱ መነሳቱን ተጠቅሷል፡፡

ውይይቱ ኢጋድ በኢትዮጵያ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ፣ ተዓማኒ እና አካታች ምርጫ እንዲኖር የሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አካል መሆኑንም አስታውቋል፡፡(ኤፍ ኤም ሲ)

ኡሁሩ ኬንያታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገቡ=====ግንቦት 21/2018 7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ለመታዘብ የተሰየመውን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድ...
29/05/2026

ኡሁሩ ኬንያታ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመታዘብ አዲስ አበባ ገቡ
=====

ግንቦት 21/2018 7ኛውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ለመታዘብ የተሰየመውን የአፍሪካ ኅብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድንን በሊቀመንበርነት የሚመሩት የቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አዲስ አበባ ገብተዋል።

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል አምባሳደር መለስ ዓለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ይወዳደራሉ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ=====ግንቦት 21/2018 በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ...
29/05/2026

42 የፖለቲካ ፓርቲዎች በዚህ ምርጫ ይወዳደራሉ - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
=====

ግንቦት 21/2018 በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በአጠቃላይ 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚወዳደሩ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ 10 ሺህ 438 የፖለቲካ ፓርቲ እጩዎች እና 80 የግል እጩዎች በምርጫው ይወዳደራሉ።

ፓርቲዎች በተደለደለላቸው የአየር ሰዓት 19 የክርክር መድረኮች በአምስት ቋንቋዎች ማካሄዳቸውንም ሰብሳቢዋ አንስተዋል።

ተፎካካሪዎቹ ከ250 ሺህ በላይ ተወካዮቻቸውን የምርጫውን ሂደት እንዲከታተሉ እንደሚልኩም ገልጸዋል።

ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ቦርዱ=====ግንቦት 21/2018 ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።ቦርዱ በ7ኛው...
29/05/2026

ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል - ቦርዱ
=====

ግንቦት 21/2018 ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ54 ሚሊየን በላይ መራጮች ተመዝግበዋል አለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ።

ቦርዱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሂደት ዙሪያ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንዳሉት፤ ለምርጫው 54 ሚሊየን 571 ሺህ 871 መራጮች ተመዝግበዋል።

የምርጫውን ሂደት የአፍሪካ ህብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) ልዑካን እንደሚታዘቡ ገልጸዋል።

ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።(ኤፍ ኤም ሲ)

ቁሳቁስ በማጓጓዝ በኩል ያጋጠመ እክል የለም - ምርጫ ቦርድ=====ግንቦት 21/2018 በምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሂደት እስካሁን እክል እንደገጠመው ሪፖርት ያደረገ የቦርዱ ቡድን አለመኖሩን ብሔ...
29/05/2026

ቁሳቁስ በማጓጓዝ በኩል ያጋጠመ እክል የለም - ምርጫ ቦርድ
=====

ግንቦት 21/2018 በምርጫ ቁሳቁስ ስርጭት ሂደት እስካሁን እክል እንደገጠመው ሪፖርት ያደረገ የቦርዱ ቡድን አለመኖሩን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ፣ የመኪና ብልሽት እና የመንገድ አለመመቸትን ጨምሮ በተለያዩ ጥቃቅን ምክንያቶች የዘገየ ካልሆነ በስተቀር፣ በየትኛውም የምርጫ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት የተስተጓጎለ የቁሳቁስ ማጓጓዝ እክል እንዳላጋጠመ ገልጸዋል።

ቦርዱ ከመራጮች ምዝገባ ጀምሮ የመጓጓዣ መዘግየቶችን ለመፍታት በቂ ዝግጅት አድርጎ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን እና አሁን ላይ ሁሉም ነገር በትክክል እየሄደ እንደሆነ ሰብሳቢዋ አረጋግጠዋል።

የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ሥራቸውን ጀምረዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ=====ግንቦት 21/2018 ከቦርዱ ፈቃድ ያገኙ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ምርጫውን ለመታዘብ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ሥራ መጀመራቸ...
29/05/2026

የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ሥራቸውን ጀምረዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
=====

ግንቦት 21/2018 ከቦርዱ ፈቃድ ያገኙ የምርጫ ታዛቢ ቡድኖች ምርጫውን ለመታዘብ ዝግጅታቸውን አጠናቅቀው ሥራ መጀመራቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ዛሬ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የአፍሪካ ሕብረት እና የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) ተወካዮቻቸውን ልከው ሥራ ጀምረዋል።

ሁለቱ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተጨማሪ በሀገር ውስጥ የተደራጁ 55 ሲቪክ ማኅበራትም ፈቃድ ወስደው ወደ ሥራ መግባታቸውን ገልጸዋል።

55ቱ የሀገር ውስጥ ታዛቢዎች፣ 1 ሺህ 562 የምርጫ ታዛቢዎችን ማሰማራታቸውንም ነው ሰብሳቢዋ የጠቀሱት።

59 አባላት ያሉት የአፍሪካ ሕብረት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን በቀድሞው የኬንያ ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታ እየተመራ ሥራውን እንደሚሠራ አስታውቀዋል።

ኢጋድ በበኩሉ 26 አባላት ያሉት የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን እንደሚያሰማራ ጠቅሰዋል።

በአዲስ አበባ የሚገኙ ዲፕሎማቶችም የምርጫውን ሂደት ተዘዋውረው እንዲመለከቱ የእንግድነት ማለፊያ ተሰጥቷቸዋል ብለዋል ሰብሳቢዋ።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ረቂቅ አጀንዳዎችን ለተባባሪ ምሁራን እና ተቋማት አቀረበ =====ግንቦት 21/2018 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ...
29/05/2026

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ረቂቅ አጀንዳዎችን ለተባባሪ ምሁራን እና ተቋማት አቀረበ
=====

ግንቦት 21/2018 የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ረቂቅ አጀንዳዎችን ለኮሚሽኑ ተባባሪ አካላት ለሆኑት ለግል፣ ለመንግሥት፣ ለሃይማኖት ተቋማት፣ ለዩኒቨርሲቲዎች፣ ለዩኒቨርሲቲ ኮሌጆች እና በቲንክ ታንክ ውስጥ ለሚሠሩ ምሁራን አቅርቦ ሰፊ ምክክር አካሂዷል።

ለባለድርሻ አካላት ረቂቅ አጀንዳዎችን አሳውቆ ምክረ-ሐሳብ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ባደረጉት ንግግር፥ በመንግሥት፣ በግል፣ በሃይማኖት ተቋማት፣ በዩኒቨርሲቲዎች እና በቲንክ ታንክ (እንደ ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ፣ ፖሊሲ ምርምር እና ልህቀት ማዕከላት) የሚሠሩ ምሁራን በምክክሩ ሂደት ውስጥ እጅግ ወሳኝ ሚና ሲወጡ መቆየታቸውን ገልጸዋል።

ኮሚሽኑ ከእነዚህ ተቋማት እና ምሁራን ጋር በቅንጅት መሥራቱ የሂደቱን የገለልተኝነት እሴት ይበልጥ ለማስጠበቅ እንዳስቻለውም ተናግረዋል።

የተቀረጹ ረቂቅ የአጀንዳ ሐሳቦችን አስመልከቶ ማብራሪያ የሰጡት ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገብረሥላሴ በበኩላቸው፣ አጀንዳዎቹ በአሁኑ ወቅት በመጀመሪያ ደረጃ የረቂቅ ሂደት ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው፣ የሚመለከታቸው አካላት ግብዓት በስፋት ተካትቶበት ይበልጥ እንደሚዳብር እና ይዘቱም እንደሚያድግ አረጋግጠዋል።

ኮሚሽኑ እስካሁን ባደረገው እንቅስቃሴ የኢትዮጵያን 93 በመቶ ወረዳዎች እና የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ ማድረግ የቻለ ሲሆን፣ በሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚታዩት ሀገርን ሊያስቀጥሉ የሚችሉ ሀገራዊ አጀንዳዎች በመሆናቸው በቀጣይ በሚካሄደው ታላቅ ጉባኤ ላይ 4 ሺህ ተሳታፊዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

በመንግሥት፣ በግል፣ በሃይማኖት እና በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚሠሩ ምሁራን ለዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ ጉባኤ ስኬት የተጣለባቸውን ከፍተኛ ኃላፊነት እንዲወጡ ጥሪ አቅርብዋል።

ኮሚሽኑ ይህንን የግብዓት ማሰባሰብ ሂደት ካጠናቀቀ በኋላ የተገኙትን አዳዲስ ሐሳቦች በማካተት የመጨረሻውን እና ዋናውን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳ እንደሚያቀርብ አመላክተዋል።

ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆን በኃላፊነት ሾመ =====ግንቦት 21/2018 ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ዋና አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ...
29/05/2026

ሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆን በኃላፊነት ሾመ
=====

ግንቦት 21/2018 ፖርቹጋላዊው አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ የስፔኑ ክለብ ሪያል ማድሪድ ዋና አሰልጣኝ ሆነዋል፡፡

አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ በሪያል ማድሪድ ቤት እስከ ፈረንጆቹ 2029 ድረስ የሚያቆያቸውን ውል ተፈራርመዋል፡፡

አሰልጣኙ ከዚህ ቀደም ከፈረንጆቹ 2010 እስከ 2013 ሪያል ማድሪድን ማሰልጠናቸው ይታወሳል፡፡(ኤፍ ኤም ሲ)

ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበትን መድረክ በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ሥራ ተከናውኗል - ምርጫ ቦርድግንቦት 21 ፣ 2018 በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አ...
29/05/2026

ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለሕዝብ የሚያስተዋውቁበትን መድረክ በመፍጠር ረገድ ተጨባጭ ሥራ ተከናውኗል - ምርጫ ቦርድ

ግንቦት 21 ፣ 2018 በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለሕዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ በመፍጠር በኩል ተጨባጭ ተግባራት ተከናውነዋል አሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ሀይሉ።

በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በአጠቃላይ 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦቻቸውን ለሕዝብ በስፋት የማስተዋወቅ ሥራ ተሰርቷል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች ምርጫ ቦርድ ባዘጋጀው መድረክ ለምርጫ ክርክሩ በ19 ዙር ያካሄዱ ሲሆን ÷ክርክሩም በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እንዲሁም ዲጂታል አማራጮች ለመራጩ ሕዝብ ተደራሽ ተደርጓል።

ወ/ሮ ሜላትወርቅ ሀይሉ÷በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለሕዝብ ማስተዋወቅ የቻሉበትን መድረክ መፍጠር እንደተቻለ ገልጸዋል።

መራጩ ሕዝብም በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ድምፅ በመስጠት ወኪሎቹን እንዲመርጥ ለማስቻል የምርጫ ቅስቀሳና ክርክር ክህሎት ማዳበሪያ የተግባር ልምምድ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰዋል።

በፖሊሲ ጥናት ምሁራንና ሙያተኞች በመታገዝ የፖለቲካ ፓርቲዎችን አማራጭ ሃሳብ ልዩነትና ተመሳሳይነት የሚለካበትን መረጃ የመሰብሰብ ሥራ በጥንቃቄ መሰራቱን ተናግረዋል።

የክርክር ሒደቱን ቅርፅ ውጤታማነት ለማስጠበቅ የሚዲያና ኮሙኒኬሽ ሙያተኞች የተሳተፉበት ተከታታይ ውይይት በማድረግ ፖለቲካ ፓርቲዎች ከተለምዷዊ ክርክር ወጣ ያለ ክርክር አካሂደዋል ነው ያሉት፡፡

የክርክር ሒደቱ ተጋባዥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎችና ገለልተኛ ተቋማት ወኪሎችም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ጥያቄ የሚያቀርቡበት ዕድል እንደተፈጠረ አንስተዋል።

በዚህም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከታዳሚ በሚቀርብላቸው ጥያቄ የሕዝብን ፍላጎት በመረዳት መለካት የሚችሉበትን የክርክር ቅርፅ መስጠት እንደተቻለ አብራርተዋል።

የክርክር መሪዎችም ረጅም ጊዜ በሚዲያና ኮሙኒኬሽን የሰሩና ገለልተኝነታቸውን ለማረጋገጥ ለፓርቲዎች በመላክ አስተያየት እንዲሰጡበት መደረጉን ጠቅሰዋል።

የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ተፎካካሪ ፓርቲዎችም ፖሊሲና የፕሮግራም ዓላማ ለሕዝብ በግልፅ በማስተዋወቅ መራጮች በቂ ግንዛቤ የሚያገኙበትን ዕድል መፈጠሩን አስረድተዋል።

በምርጫ ሒደቱ የጥሞና ጊዜም ዜጎች በየቤታቸው ለማን ድምፅ መስጠት እንዳለባቸው ሃሳብ የሚያሰላስሉበትና ፓርቲዎችም ዕጩዎች ያለውን ድባብ የሚከታተሉበት እንደሆነ መጠቆማቸውንም ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡

በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሂደቱን ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ተዓማኒ፣ ገለልተኛ ሆኖ እንዲጠናቀቅ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።

በግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሚካሄደው ምርጫም የአፍሪካ ሕብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) እና የሀገር ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች በታዛቢነት እንደሚታደሙ አስታውቀዋል።

የምርጫ ሒደቱን ለመጎብኘት ጥያቄ ያቀረቡ 16 የዲፕሎማቲክ ማሕበረሰብ አባላትንም ምላሽ ለመስጠት በሒደት ላይ መሆናቸውንም ሰብሳቢዋ አስረድተዋል።ሲል የዘገበው FBC ነው።

29/05/2026

በድምፅ መስጫ ቀን በምርጫ ጣቢያዎች ለመግባት ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው እነማን ናቸው?
ምርጫ 2018! በምርጫ ብቻ! ለድምፅዎ የሚያምኑን!

የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ የማሰራጨት ስራ በጅማ ከተማ ****** ግንቦት 21፣ 2018 በጅማ ከተማ የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ነው።የከተማዋ ምርጫ ክ...
29/05/2026

የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ የማሰራጨት ስራ በጅማ ከተማ
******
ግንቦት 21፣ 2018 በጅማ ከተማ የድምጽ መስጫ ቁሳቁስ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማሰራጨት ስራ እየተከናወነ ነው።

የከተማዋ ምርጫ ክልል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ነብያት አብርሃም በጽሕፈት ቤቱ ስር ለሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች የቁሳቁስ ስርጭት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።

በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ለድምፅ አሰጣጡ ሂደት መሳካት የተሟላ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።

በዚሁም ለድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ አስፈላጊ የሆኑት የድምፅ መስጫ ሳጥኖች፣ የምርጫ ወረቀቶች፣ የመመዝገቢያ ወረቀት ማህተሞች እና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች በከተማው ስር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች በወቅቱና በሰዓቱ እንዲደርሱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በምርጫ ክልሉ 117 የምርጫ ጣቢያዎች እንዳሉ ጠቁመው÷ ለአብዛኛው ጣቢያዎች ቁሳቁስ ተደራሽ መደረጉን መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Address

Alaba K'ulito

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ:

Share