Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ

Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ ይህ የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ-ከተማ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ይፋዊ ገፅ ነዉ!
*****
This is the Official page of Akaki Kality Sub-City Communication Office
(1)

02/06/2026
02/06/2026

ኢትዮጵያ መርጣለች ፤ አሸንፋለች!

7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ በድምጹ የሚመራውን ሕጋዊ መንግሥት ለማቋቋም ያለው ጉጉት እጅግ በጣም የላቀ መሆኑን ትልቅ አስረጅ ሆኖ በፖለቲካ ታሪካችን ውስጥ ተመዝግቧል።

የፖለቲካ ሀሳብን በሰላማዊ መንገድና በሕዝበ ውሳኔ መዳኘት የሰለጠነ ፖለቲካ ነው።

የሌሊት ብርድና ጨለማ፣ የቀን ፀሃይና ሀሩር ሳይበግረዉ ነዋሪዉ በነቂስ ወጥቶ የመረጠዉን በየምርጫ ጣቢያዉ የተለጠፈዉን ዉጤት አሁንም በነቂስ ወጥቶ በጉጉት እየተመለከተ ይገኛል:-መላዉ የክ/ከ...
02/06/2026

የሌሊት ብርድና ጨለማ፣ የቀን ፀሃይና ሀሩር ሳይበግረዉ ነዋሪዉ በነቂስ ወጥቶ የመረጠዉን በየምርጫ ጣቢያዉ የተለጠፈዉን ዉጤት አሁንም በነቂስ ወጥቶ በጉጉት እየተመለከተ ይገኛል:-

መላዉ የክ/ከተማችን ነዋሪዎች ይበጀኛል፣ ይወክለኛል ብለዉ ድምፅ በመስጠት የመረጡበት ጣቢያ በመገኘት የተለጠፈዉን ዉጤት መመልከት እንደሚችሉ በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ እንወዳለን።

ግንቦት 25/2018 ዓ.ም

ለዚህ አስደናቂ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ስለሰራንለት ደስ ይለናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤበጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ በተመረቀው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ የወንዝ ...
02/06/2026

ለዚህ አስደናቂ የዕደ-ጥበብ ባለሙያዎች ማህበረሰብ ስለሰራንለት ደስ ይለናል፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በይፋ በተመረቀው የእንጦጦ እስከ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት ማጠናቀቂያ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ፣ ለአካባቢው ታታሪ ማህበረሰብ መስራት በመቻላቸው የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የቀጨኔና እንጦጦ ነዋሪዎች በሸማና ሸክላ ስራ የሚደነቁ ቢሆንም የሚገባቸውን ክብር አላገኙም ያሉት ከንቲባዋ፣ ፕሮጀክቱ ይህንን የተሳሳተ አመለካከት እንደሚቀይር ጠቁመዋል።

ቀደም ሲል የሚመረተውን አክምባሎ በማስታወስ፣ የእጅ ጥበብ ስራዎች ለጎብኚዎች የሚቀርቡባቸው ሱቆች መዘጋጀታቸውንና የባህል ማስታወሻ ቅርጻ ቅርጾች መካተታቸው ለአካባቢው ሙያተኞች “ስራችሁ ክቡር እንጂ የሚታፈርበት አይደለም” የሚል መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢው በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በዚህ ልማት አብዛኞቹ የአካባቢው ነዋሪዎች የሆኑ እስከ 10 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ እድል አግኝተዋል።

ወጣቶችም ከአደገኛ ሁኔታዎች ርቀው በካፌዎች፣ ልብስ ስራና ስፖርት ማዕከላት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል።

እያንዳንዱ ተቋም የራሱ ታሪክ እንዲኖረው ተደርጎ የተገነባ ሲሆን፣ የሀገር ባህልን ከሚያንጸባርቁ ቅርጻ ቅርጾች ባሻገር የኢትዮጵያን ክብር ያሳዩ አትሌቶችን የሚዘክሩ ሃውልቶችም ተቀምጠዋል። ከንቲባዋ ነዋሪዎች የጋራ ሀብታቸው የሆነውን ስፍራ እንዲጎበኙ ጥሪ አቅርበዋል።

በመጨረሻም ለማህበረሰቡ፣ ለወጣት ኮንትራክተሮችና ፕሮጀክቱን በግንባር ቀደምትነት ላስተባበሩት የከንቲባ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጥላሁን ምስጋና አቅርበው፣ ወንዙን በማጽዳት ሂደት የተከፈለውን መስዋዕትነት አድንቀዋል።

የተሰራው ስራ ታሪካዊ ስኬት መሆኑን በመግለጽም “እኛ እናልፋለን፤ ታሪክ ግን አያልፍም” ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

02/06/2026

ከጎርፍ አደጋ ወደ አረጏዴ ገነት
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ  ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው! የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ...
02/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው!

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነትና ፍላጎት በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

ምክር ቤቱ የ7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ማሩ ጃኔ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ምርጫው ግልጽነት እና ፍትሐዊነት ከመላበሱም ባሻገር በመራጩ የከተማዋ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቅቡልነት ያሳየ ነው።

ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ስኬታማነት መሥራቱን አስታውሰው፤ ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አብራርተዋል።

የምርጫ ሂደቱም እጅግ የተረጋጋ፣ የሰለጠነ እና የዴምክራሲ ሥርዓት ትግበራ ሂደትን ያጠናከረ ሆኖ ማለፉንም ጠቅሰዋል።

መገናኛ ብዙሃንም ለፓርቲዎች የሰጡት የአየር ሰዓት ፍትሐዊ፣ ግልጽና ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ የሰጠ ነው ያሉት አቶ ማሩ፤ ይህም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ያሉትን የፖሊሲ አማራጭ ሀሳቦች ያለምንም ገደብና ጫና ለሕዝቡ የሚያቀርብበት ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።

የጸጥታ አካላትም ያለምንም ወገኝተኝነት ፍጹም ገለልተኛ በሆነና ሙያዊ አካሄዶችን በተከተለ መንገድ የአዲስ አበባ ምርጫ ጣቢያዎችንና የመራጩን ሕዝብ ደህንነት ሲጠብቁ መዋላቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢው፤ የጸጥታ አካላት ያከናወኑት ተግባር ሊመሰገን የሚገባው ነው ብለዋል።

የድምጽ ቆጠራውና ውጤቱን የማደራጀት ሥራ የሚያከናወነው በሕጉ መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመሆኑም ውጤቱ በከተማ ደረጃ በኦፊሴላዊ መልኩ እስኪገለጽ ድረስ በትዕግስት እንዲጠበቅ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል ነው ያሉት።

ማንኛውም ወገን የምርጫ ውጤቱን በጸጋ የመቀበል ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለበት አመልክተው፤ ቅሬታዎች ቢኖሩ እንኳን በሕጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው፤ በምርጫው አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳዩት ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት ተምሳሌታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ለምርጫው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረገው መራጩ ሕዝብ፣ ለምርጫ ቦርድ፣ የከተማዋ የጸጥታ አካላት ጨምሮ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የምርጫ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን የሕዝብ ድምጽ ልናከብር ይገባል ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ የሰለጠነና ብስለት የተሞላበት የፖለቲካ አካሄድም ይሄው መንገድ ነው ብለዋል።

!

የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች ፕሮጀክት በውስጡ ምን ይዟል፦👉 597 ሄክታር ቦታ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት፤👉 15 ሄክታር መሬትን በማልማት በአረንጓዴ ተ...
02/06/2026

የእንጦጦ ቀጨኔ የወንዝ ዳርቻ ልማት እና የአገልግሎት መስጫዎች ፕሮጀክት በውስጡ ምን ይዟል፦

👉 597 ሄክታር ቦታ የሚሸፍን የወንዝ ዳርቻ ልማት፤

👉 15 ሄክታር መሬትን በማልማት በአረንጓዴ ተሸፍኗል፤

👉 የ210 ቀፎ ዘመናዊ የንብ እርባታ፤

👉 የአበባ እና የእጽዋት ጋርደኖች ልማት፤

👉 የአካባቢውን ማህበረሰብ የስራ ባህል የሚዘክሩ ሃውልቶችና ቅርሶች ግንባታ፤

👉 22 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፤

👉 8 ኪሎ ሜትር የብስክሌት መንገድ፤

👉 6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር የተሽከርካሪ መንገድ፤

👉 4 ኪሎ ሜትር የሃይኪንግ መንገድ፤

👉 2 አዲስ የተሽከርካሪ ድልድዮች ግንባታ፤

👉 3 ነባር የተሽከርካሪ ድልድዮች ዕድሳት ፤

👉 39 የውሃ መከላከያ ግድቦች ግንባታ (ቼክ ዳም) ወዘተ... በስጡ አጠቃልሎ ይዟል።

ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ ...
02/06/2026

ኢትዮዽያ አሸነፈች!!!

የሀገረ መንግስቱን ግንባታ ከዴሞክራሲያዊ ሥርዓት አቅጣጫ ውጭ ባንዳና ባዳ ጥምረት ፈጥረው በአመፅና በኃይል ሀገራችንን ወደ ጥፋት መንገድ ለመክተት ያሴሩትን ደባ ሕዝቡ በዴሞክራሲያዊው ምርጫ እምቢተኝነቱንና ለሀገር ያለውን ፅኑ ፍቅር በተግባር በማሳየት አክሽፎታል።

በተለይ በአዲስ አባባ ረጃጅም ሰልፍ ቢፈጠርም ህዝቡ በእንቅልፍ እና በብርድ ሳይበገር ተራ እስኪደርሰው እስከ ለሊቱ 10:30 ሰአት ድረስ ተሰልፎ በሚገርም ጨዋነት፣ መሰጠት፣ ቁርጠኝነትና ፅናት መርጧል።

የሀገራችን ፖለትከኞችና ልሂቃን ይህንን ታላቅ ጽኑ ጨዋና ቆራጥ ሕዝብ የምንረዳውና የሚንመጥነው መሆን ይጠበቅብናል።

ፈጠሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Address

Ak'ak'i Besek'a

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Akaki Kality Communication-አቃቂ ቃሊቲ:

Share