ፋግታ ለኮማ ወረዳ ሴቶች ሊግ

ፋግታ ለኮማ ወረዳ ሴቶች ሊግ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ፋግታ ለኮማ ወረዳ ሴቶች ሊግ, Political organisation, Adis K'idame.

11/09/2020

እንኳን ለአዲስአመት አደረሳችሁ መጭውአመት የሰላም የፍቅር የጤና የብልፅግና ይሁንላችሁ

10/09/2020
12/08/2020

ማንነታችን ፍቅራችን እንጂ ጠባችን ሊሆን አይገባም

ማንነት(Identity) ምንድን ነው ?

ሳይንስ (Sociology) ማንነትን በሁለት ይከፍለዋል:-
1-የግል ማንነት(Self Identity)
2-የጋራ ማንነት(Collective Identity)

-የግል ማንነት --:-አመለካከት፣አነጋገር፣ቁመት፣ቅርጽ፣
እውቀት ፣ጠባይ፣እድሜ ፣ቅላት፣ድምጽ፣ባህሪ የመሳሰሉት..ናቸው

የጋራ ማንነት --- :-ሐይማኖት ፣ዜግነት ፣ቋንቋ ፣ብሔር ፣ጎሳ ፣ ባህል፣አካባቢ፣ጾታ፣ቀለም፣ሙያ የመሳሰሉት...ናቸው

የግል እና የጋራ ማነነቶች የተፈጥሮ ናቸው(ስንወለድ ያገኘናቸው ናቸው )።ሰው ሰራሽ ሊሆኑም ይችላሉ ፦ምሳሌ ሙያ፣እውቀት፣ማዕረግ... የመሳሰሉት። ማንነቶች የነበሩ አሁንም ያሉ ወደፊትም የሚኖሩ ናቸው።በመጠን እና በአይነት እንደ ጊዜው ሁኔታ የሚፈጠሩ፣የሚያድጉ፣ሊቀየሩ ወይም ሊጠፉ የሚችሉም ነቸው።

የማንነት መለያየት (Diversity) ችግር ይፈጥራል ?

መልሱ :-ችግር አይፈጥርም ነው።
የምንኖርባት አለም ሙሉ የሆነችው በልዩነቶች ነው። ክርስቲያን-ሙስሊም፣ ኮኪዥያን(Caucasian)-ሞንጎልያን(Mongolian)-ኔግሮይድ(Negroid) ፣ያደጉ-ያላደጉ ፣እንግዚዘኛ ተናጋሪዎች-ፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች..ሌሎችንም ልዩነቶች ይዛ አንዱ በሌላው የሚኖርባት ነች።
ሁሉንም አሟልቶ የያዘ ክፍለዓለም ፣ አገር፣ ከተማ ወይም ሰው የለም። አለማችን የመስጠት እና የመቀበል ውጤት ነች።

የማንነት ልዩነት (Diversity) ጥቅም አለው ?

አዎ ይጠቅማል ።በልዩነት አንዱ ከሌላው
ስለሚቀበል የጎደለን ይሞላል ፤አቅምን ይጨምራል ፤መፈላለግን ያመጣል። ልዩነት መስጠት፣መቀበል ይስማማዋል ። በዚህ ልዩነት ብዙዎች በፍቅር ኖረዋል፣ሰተው ተቀብለዋል ፤ አትርፈውበታል ፤ በጎ ነገር ሰርተውበታል።
ለዚህ ጥሩ ምሳሌ የጾታ ማንነት ልዩነት ነው :-
ወንድ እና ሴት በጾታ ማንነት ቢለያዩም አንዱ ከሌላው በመቀበል ፣ በመፈላለግ በጥምረት ትዳር መስርተው ልጆች አፍርተው የቤተሰብ አንድነትን ያመጣሉ።

ዘረኝነት (Racism) ምንድን ነው ?

እራስን መውደድ ዘረኝነት ነው ? መልሱ :- አይደለም ነው
የራስን መውደድ ዘረኝነት ነው ? መልሱ ፡- አይደለም ነው
በራስ መኩራት ዘረኝነት ነው ? መልሱ :- አይደለም ነው

--ክርስቲያኖች በሐይማኖታቸው ቢሰባሰቡ፣ ቢያስተምሩ ፣ ቢዋደዱ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:-አይደለም ነው
--ሙስሊሞች በሐይማኖታቸው ቢሰባሰቡ ፣ ቢያስተምሩ ፣ ቢዋደዱ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:- አይደለም ነው
--ሴቶች ስለመብታቸው ቢነጋገሩ ፣ቢያስተምሩ ፣ቢሰባሰቡ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:-አይደለም ነው
--ኢትዮጵያውያኖች ቢደጋገፉ፣ቢቀራረቡ ፣ ቢከባበሩ ፣ ቢዋደዱ ፣ ቢኮሩ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:- አይደለም ነው
--ጎንደሬዎች፣ወለዬዎች፣ኦሮሞዎች፣አማራዎች፤ትግራዬች፣ሱማሌዎች ፣አፋሮች፣ወላይታዎች፣...ሌሎችም እራሳቸውን ቢያደንቁ ፤ ስለራሳቸው ቢዘፍኑ ፤ በቋንቋቸው ቢናገሩ ፤ ቢሰባሰቡ ፣ ባህላቸውን ቢጠብቁ ፤ በማንነታቸው ቢኮሩ ...ዘረኝነት ነው?
መልሱ:- አይደለም ነው
--አፍሪካውያኖች ቢደራጁ፣ቢታገሉ፣ቢሰባሰቡ፣ቢሞጋገሱ ፣
ቢኮሩ ፣ ቢመኩ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:- አይደለም ነው
-ከጎረቤት አስበልጦ ቤተሰብን መውደድ ፤ ከሰፈር ሰው አስበልጦ ጎረቤትን ማቅረብ ፣ መውደድ ዘረኝነት ነው ? መልሱ:- አይደለም ነው
--ወንድሜ ፣እህቴ ፣ያገሬ ልጅ ፣የወንዜ ልጅ፣የሰፈሬ ልጅ ...እያሉ አብልጦ ማቅረብ ፣ መውደድ.......ዘረኝነት ነው ? መልሱ:- አይደለም ነው

ታዲያ ዘረኝነት ምንድን ነው ?

ዘረኝነት፡- ልዩነትን አለመረዳት ወይም አለመቀበል ነው ፤ልዩነትን መፍራት ነው ፤ የሌላውን መኖር(ህልውና) አለመቀበል ነው ፤ ሌላውን መጥላት፣መጉዳት፣መግፋት፣ማሳደድ፣መግደል...ነው።

በአለማችን የተፈጸሙ አበይት የዘረኝነት ጭፍጨፋዎች
(በፈረንጆች አቆጣጠር)

1-ሆሎካስት(Holocaust):-ስድስት ሚሊየን አይሁዶች በጀርመን ናዚ መንግስት 1942-1945 የተጨፈጨፉበት።
2-ሆሎዶሞር(Holodomor):- ሁለት ሚሊየን ዩክሬናውያን በቀድሞዋ ሶቭየት ሕብረት መንግስት 1932-1933 የተጨፈጨፉበት።
3-የአርሜኒያ ጅምላ ጭፍጨፋ (Armenian Genocide):-አንድ ሚሊየን አምስት ሞቶ ሺ አርሜኒያውያን በኦውቶማን ቱርክ መንግስት 1915-1923 የተገደሉበት።
4-የሩዋንዳ ጅምላ ጭፍጨፋ(Rwandan Genocide):-ከአንድ ሚሊየን በላይ የሩዋንዳ ቱትሲ ጎሳዎች በመንግስት በሚደገፉ ሁቱ ጎሳዎች 7 April- 15 July 1994 የተጨፈጨፉበት።

በጎነትን እና ፍቅርን በማንነት ልዩነቶች ውስጥ የምናይባቸው
ምሳሌዎች
ፈጣሪ እና ፍጡር ፤ ወንድም እና እህት ፤ ባል እና ሚስት ፤ ወላጅ እና ልጅ ፤ሰጪ እና ተቀባይ ፤ አስተማሪ እና ተማሪ ፤ ታማሚ እና አስታማሚ፤ ረጂ እና ተረጂ ፤ ሌሎችም ....

ለኛ የተሰጠንን ተጠቅመን ፤ እኛ የሌለንን ከሌሎች ተቀብለን ፤ሌሎች የሌላቸውን ከኛ ሰተን ፤ ይቺን አጭር ዘመናችንን እናጣፍጣት።


ዘመኑን በጎ የምናደርገው እኛ ነን።እኛ በጎዎች ስንሆን ዘመኑም በጎ ይሆናል።

አለማችን በሁሉም ነገር አንድ አይነት ብትሆን ሕይወት
ምን ትመስል ነበር ???

በጎ ሐሳቦች እንለዋወጥ♥♥በጎ ሕሊና♥

17/06/2020

በዚህ የእርሻ ወቅት ሁሉም የሚመለከተው አካል አርሶአደሩ እራሱን ከኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዲከላከል ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡

01/06/2020
27/09/2019

ዱርሳ

27/09/2019

ድሩሳ

Address

Adis K'idame
123456

Telephone

0584500151

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ፋግታ ለኮማ ወረዳ ሴቶች ሊግ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share