Abel Selomon Research And Others Consultancy Center

Abel Selomon Research And Others Consultancy Center ጌታዬ ካንተ አትለየኝ አትጣለኝ

06/04/2026
02/10/2021

በስልክም በአካልም እየሠጣችሁኝ ላለው ገንቢ አስተያየት ሣላመሠግን አላልፍም። ፈጣሪ ያክብርልኝ።

ጥናታዊ ጽሁፍ/research ማዘጋጀት ትፈልጋለህ? እነዚህን 15 ነጥቦች ልብ በል።የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን...
25/09/2021

ጥናታዊ ጽሁፍ/research ማዘጋጀት ትፈልጋለህ? እነዚህን 15 ነጥቦች ልብ በል።
የጥናት/ሪሰርች ይዘት፣ ስፋትና ጥልቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ ተጨባጭ ችግርን ለመፍታት ይሁን የተደበቀ ምስጢርን ፈልፍለን ለማግኘት ወይንም ከዚሁ ለተለየ ዓላማ ጥናት ሊታቀድና ሊከናወን ይችላል፡፡
በዚሁ መሰረት አንድ ጥናት/ሪሰርች ሲዘጋጅ ከዚህ በታች የተመለከቱትን ብዙዎች ዘንድ የተለመዱ ዋና ዋና ይዘቶችን ሊያካትት ይችላል፡፡ ዝርዝሩን ተመልከቱት፤
የጥናቱ ርዕስ/ Topic
የጥናት ርዕስ ቃላት ጥንቃቄ ይፈልጋል፡፡ ትክክለኛ ስዋሰው፣ ገላጭ ቃላት፣ የጥናቱን ችግር፣ ሥፍራ/ቦታ በተቻለ መጠን በሚስብ ሁኔታ ቢጻፍ ይመረጣል፡፡ ርዕሱን የሚያነብ ሰው የጥናቱን ይዘት በቀላሉ እንዲረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚሁ በፊት ገጽ ላይ ከርዕስ በተጨማሪ፣ የአጥኚው/ዎቹ ሙሉ ሥም፣ ጥናቱ የሚቀርብለት ሠው/ተቋም፣ጥናቱ የተዘጋጀበት ወቅትና ሥፍራ ይጠቀሳሉ፡፡
ምስጋና/ Acknowledgement
የምሥጋና መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ ጥናቱ ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በተለያዩ መልኩ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሠዎች የሚመሰገኑበት ክፍል ነው፡፡ ሠው ብቻ ላይመሰገንበትም ይችላል፡፤ ሥፍራዎች፣ ሁኔታዎች፣ ወቅቶችና ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ክፍል ሊመሰገኑ ይችላሉ፡፡
ማውጫ/Table of content
በማውጫ የጥናቱ የተለያዩ አቢይና ንዑስ ክፍሎች የሚገለጽበት ገጽ ይጠቀሳል፡፡
መግቢያ/ Introduction
በዚህ ክፍል የጥናቱን መነሻ ለአንባቢዎች መረጃ የሚሰጥበት ነው፡፡ መግቢያ መንዛዛት የለበትም፡፡ አንድ ገጽ ይበቃል፡፡ ዞሮ ዞሮ የአንድ ጥናት መግቢያ የአንባቢውን ስሜት የሚቀሰቅስ፣ የጥናቱን ወሰንና አቅጣጫ የሚያመላክት፣ጥናቱን እንዴት እንደሚሰራና የጥናቱን ጭብጥ የሚያሳይ ይዘት እንዲኖረው ተደርጎ ይዘጋጃል፡፡
የጥናቱ ዓላማ /Objective
የጥናት ዓላማ ከተለያዩ ርዕሶች ጋር ጥልቅ ቁርኝት አለው፡፡ የጥናት ዓላማ፣ ከጥናቱ ችግሮች፣መላ ምቶች መረጃና ውጤት አቀራረብና አተናተን፣ ማጠቃለያና መደምደሚያ ጋር ይተሳሰራል፡፡ የጥናት ርዕሰ ከተመረጠ በኋላ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ያሉ ችግሮችን በሚገባ ከተረዳን በኋላ የጥናት ዓላማዎች ይዘጋጃሉ፡፡
የጥናት ዓላማዎች አቢይና ዝርዝር ተብለው ሊቀመጡ ይችላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ዓላማዎች በጥናቱ የተጠቀሱ ቁልፍ ችግሮችን ወይንም መላምትን መሰረት ተደርገው ይቀረጻሉ፡፡
Statement_of_the_problem ፦ ይኸኛው ዋና መሠረት ነው። ትክክለኛ ገለጻም ይጠይቃል። “የጥናቱ ርዕስ ለመስራት ያነሳሳህ/ሽ ምን ችግር ኖሮ ነው[what is the problem that initiate you to apply your research over this title?.....]” ለሚል ጥያቄ ተገቢ መልስ የምትሰጡበት የጥናት ሰነድ ክፍል ነው። ለጥናት የተሰማራችሁበትን ችግር ወይም የአንድ ነገር እጥረት ለማስቀመጥ ሞክሩ። ገለጻችሁም "There is lack of/a problem of/ ____" የሚል አይነት ቢሆን መልካም ነው።
የጥናቱ አስፈላጊነት/ Significance of the study
ጥናት ለተለያየ አገልግሎት ይውላል፡፡ በዚህ ክፍል የዚህን ጥናት ውጤት አስፈላጊነት ግልጽ በሆነ መልኩ በዝርዝር ይቀመጣል፡፡
የጥናቱን ወሰን/ Scope of the study
በዚህ ንዑስ ክፍል የጥናቱ አጠቃላይ ስፋት፣ ርዝመትና ጥልቀት ይገለጻል፡፡ ለምሌ ያህል፣ ጥናቱ የት እንደሚሰራ፣ በእነማን ላይ እንደሚሰራ፣ ጊዜና የመሳሰሉ ወሰኖች በግልጽ ይቀመጣሉ፡፡ ወሰን ያልተበጀለት ጥናት መጀመሪያውንና መጨረሻውን ማወቅ ይቸግራል፡፡
የጥናቱ ታሳቢ ክፍተቶች/ Limitation
አንድ ጥናት ሲካሄድ ሁሉም ነገር አልጋ ባልጋ ሊሆን አይችልም፡፡ የተለያዩ ክፍተቶች ሊፈጠሩ ይችላሉና በዚህ ክፍል በጥናቱ ወቅት ሊገጥሙን የሚችሉ ችግሮች ይጠቀሳሉ፡፡ ይሁን እንጂ እነዚህ ችግሮች ከአጥኚው አቅም በላይ ሊሆኑ ይገባል እንጂ ሁሉንም ችግር መጥቀስ አይገባም፡፡ ታዲያ በዚህ ክፍል ክፍተቶቹን ለማጥበብ በአጥኚው ሊደረጉ የሚገቡ ጥረቶችም ሊካተቱ ይገባል እንጂ ክፍተቶችን ብቻ ጠቅሶ እጅን አጣጥፎ መቀመጥ አይገባም፡፡
የጥናቱ ዘዴና አካሄድ/ Methodology of the study
የአንድ ጥናት ዘዴና አካሄድ/ Methodology እንደየ ጥናቱ ጠባይ፣ችግር፣አይነትና ዓላማ የተለያየ ሊሆን ይችላል፡፡ ዘዴና አካሄድ መጥቀስ ማለት በአጭሩ ጥናቱ እንዴት እንደሚሰራ፣ የት እንደሚሰራ፣ የመረጃ መሰብሰቢያ ዘዴ ፣ የመረጃውም መሰብሰቢያ ዘዴ እንዴት አንደተዘጋጀ፤ ምን አይነት ጥናት እንደሆነ፣ የናሙና ይዘት፣ አመራረጥና መጠን (ናሙና ያለው እንደሆነ) ፣ ውጤቱ እንዴት እንደሚተነተን፣ውጤቱ እንዴት እንደሚሰራጭና የመሳሰሉ የጥናቱን አጠቃላይ አሰራርና አካሄድ መግለጽ ማለት ነው፡፡
የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ/ Literature Review
በዚህ ክፍል ከዚህ በፊት የተደረጉ ጥናቶችንና ስምምነቶችን የተቀመጡ ንድፈ-ሃሳቦችን በጥልቀት ይመረመራሉ፡፡ ተዛማጅ ጽሁፍ በጥናት ውስጥ በተለያየ መልኩ ማካተት የሚስችል የጥና ጽሁፍ ምልከታ አጻጻፍ አለ፤ ከዚህ ውስጥ የሚስማማንን መርጠን መጠቀም የእኛ ምርጫ ነው፡፡ የተዛማጅ ፅሁፍ ምልከታ ሥራ ሰፊና ጥልቅ ነውና በዚህች አጭር ንዑስ ርዕስ ሁሉን መግለጽ ይከብዳል፡፡
የጥናት ግኝት አቀራረብ ትንተና/ Data analysis & Interpretation
የአንድ ጥናት ውጤት እንደ ጥናቱ አይነትና የመረጃ ማጠናቀሪያ ሥልት ሁኔታ፣ በተለያየ መልክ ሊቀርብና ሊተነተን ይችላል፡፡ አንድን ጥናት ጥናት የሚያሰኘው አጥኚው የሳይንስና የሎጂክን ስልት በመከተል በግኝቶቹ ላይ የሚደረገው ትንታኔና ትርጉም እንጂ ጥሩ የሆኑ መረጃ ማቅረብ ብቻ ሊሆን አይችልም፡፡
በመሆኑም በግኝት አቀራረብና አተናተን ወቅት አስተያየትን ከተጨባጭ ሁኔታ መለየት፤የጥናቱን ወሰን ማስታወስ እንዲሁም የተሳሳተ ትንታኔና ትርጉም ላለመስጠት ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
ማጠቃለያ/ Conclusion
ጥናቶች የተለያየ ስፋትና ጥልቀት አላቸው፡፡ ታዲያ ይህ ክፍል ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ያሉ የወቅቱን ሁኔታና ግኝቶች በማጠቃለል አጠር ተደርጎ የሚቀርበት ነው፡፡
የመፍትሔ ሐሳብ/ Recommendation
በጥናቱ የተለዩ ችግሮችና መንስዔዎቻቸው ከታወቁ በኋላ የመፍተሄ ሃሳቦች በዝርዝር ይቀመጣሉ፡፡ ስለዚህ የመፍተሄ ሃሳቦችን ከማቅረባችን በፊት ችግሮቹን በሚገባ መረዳት ይገባል፡፡
በዚህ ክፍል ሁሉም የመፍሔ ሀሳብ ሊገለጽ አይገባም፡፡ ተጨባጭ ሁኔታን በመረዳት ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉትን በመለየት በቅደም ተከተል ማቀመጥ ያስፈልጋል፡፡
አባሪ/ Appendices
በዚህ ክፍል ለጥናቱ የተገለገልንባቸውን ዝርዝር የመረጃ ማጠናቀሪያ ቅጾችና ሌሎች ዝርዝር ግብዓቶች ይቀመጣሉ፡፡
ጥናቱ ለማካሄድ የተጠቀምናቸውን መረጃዎች ማለትም መጠይይቆች፤ የተለያዮ ፕሮግራሞች እና ሌሎች ፎርማቶች ከጥናቱ ጋር ተያይዘው የሚቀርቡበት ነው፡፡
ማጣቀሻ /Reference
ይህ ክፍል ለጥናቱ የተጠቀምናቸው መረጃዎች የሚገለጽበት ነው፡፡ መረጃዎቹ በማን፣ መቼ፣የት እንደተጻፉ በግልጽ መቀመጥ አለባቸው፡፡ ስምምነት የተደረሰባቸው የተለያዩ ማጣቀሻ አጻጻፍ ስልቶች አስተምህሮዎች አሉና በተፈላጊው ስልት ማጣቀሻን በግልጽ በማስቀመጥ የጥናቱ እውነተኛነት በዚህ ክፍል ይረጋገጣል፡፡
ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!
Automatic References
Automatic List of tables
Automatic List of figures
Citation
በምርጥ አቀራረብ በYouTube ተዘጋጅቶ ለእይታ ዝግጁ ነው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን መመልከትና መማር ትችላላችሁ!
https://youtu.be/VujbubSHkZs
ከዚህ በታች የዘረዘርኳቸው
Automatic Tables of Content.
Page Break እንዴት እንሰራለን? ለሚለው ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን ይመልከቱ
https://youtu.be/aB-z5uKq75U
ስልክ ለመጥለፍ፣ መጠለፉን ለማወቅ፣ ከጠለፋ ስልካችንን ማውጣት፣ ስልካችን እንዳይጠለፍ ማድረግ እንዴት እንችላለን?
ሊንኩን በመጫን ማየት ይቻላል
https://youtu.be/-z9ciu-7rAo
ፌስቡካችሁ መጠለፉን ለማወቅ፣ ፌስቡካችንን ከጠለፋ ማውጣት፣ የተጠለፈበትን ቦታ ለማወቅ፣ በስልካችን ገብተን የጠለፈብንን ሰው እንዳይጠቀምበት Logout መዝጋት
ሊንኩን በመጫን በማየት ይቻላል
https://youtu.be/azdo0eTD4XY
Delete Format የተደረገ ሜሞሪ፣ ፍላሽ፣ ኮምፒውተር ሀርድዲሰክ ፋይል እንዴት መመለስ እንችላልን HOW TO RECOVER DELRTED DATA Amharic
https://youtu.be/G8HQeWaIUKY
50 GB በነጻ! ሜሞሪ ሞላብኝ መረጃየ ይጠፋብኛል ብሎ መጨነቅ ቀረ 50GB Free storage በነጻ መረጃችሁን ያስቀምጡ! Amharic(በአማርኛ)
https://youtu.be/V0Hq7k92XGY
ኢሜይል በሞባይል እንዴት መላክ እንችላለን? በአማርኛ How to send email using Mobile Phone Amharic
https://youtu.be/s1JcnGOcWeg
ከኮምፒወተር ላይ ያለ ፋይሎችን እንዳይክፍትብንና Delete እንዳይድርግብን በኮምፒውተር፣ በፍላሽ፣ በHard Disk ያሉ ፋይሎችን መደበቅና
https://youtu.be/4IdgIEE675s
እንዴት የኮምፒተር Usersና (Password) በCMD መስበር አንችላለን How to Crack Computer Password?
https://youtu.be/9BHgunGi2vc
ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel እንዴት መስራት አንችላለን ክፍል 2 Payroll Part 2
https://youtu.be/AsQhn_ua3Cg
ፔሮል በማይክሮሶፍት ኤክሴል MS-Excel መስራት አንችላለን? ክፍል -1 How to make payroll using Microsoft Excel in amharic
https://youtu.be/rNcfrxbTyxo
ኮምፕዩተር ፎርማት በፍላሸ ዲሰከ ለማድረግ ፍላሹን እንዴት ቡቴብል ማድረግ እንችላለን! How to Create a Bootable USB Flash Drive
https://youtu.be/bLCoN7LFhvA
በቫይረስ የተጠቃን ፍላሽ እንዴት ቫይረሱን ማጥፋት እንችላለን?
https://youtu.be/FGNbefApawM
እንዴት አድርገን በስልካችን ኢሜይል መክፈት እንችላለን? How can we create Email Using Mobile Phone
https://youtu.be/N-aoXuQRCXc
15GB ነፃ Storage እንዲሁም ወደ Google Drive ፋይል መጫንና ከ ወደ ሌላሰው በኢሜይል(Email) እንዴት መላክ እንችላለን ፋይል ማስቀመጥ ይቻላል?
https://youtu.be/HEvXJo8E3k0
# Subscribe በማድረግ ምርጥና ወቅታዊ የቴክኖሎጂ ትምህርቶችን ይከታተሉ!
በነዚህ አድራሻዎቼ ያልገባዎት ነገር ካለ ወይንም ግር ያሎትን ነገር ካለምንም ስጋት ፈታ ብለው መጠየቅ ይችላሉ። Follow me with telegram

ሪሰርች ስትሰሩ ከዚህ በታች የጠቀስኳቸው ከከበዷችሁ ነገ በምርጥ አቀራረብ ቪዲዮ ይዥላችሁ ቀርቤያለሁ!✅ Automatic References✅ Automatic List of tables ✅ Automatic List of figures ✅ Citation በምርጥ ...

21/09/2021

ለመጀመሪያ ዲግሪ እና ማስተርስ ተማሪዎች በሙሉ፡
ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በተመጣጣኝ ዋጋ እና ተጨማሪ አገልግሎቶችን በማካተት ሥራ ጀምረናል።
በመሆኑም ለሚፈልጉ ሁሉ ዝግጅታችንን አጠናቀን ጨርሠናል።
# ለመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች
- Assignment መስራት ማማከር
- Research Proposal መስራት ማማከር
- Research መስራት ማማከር
- SPSS ሥልጠና መስጠት
- STATA ስልጠና መስጠት
- ለ Research Presentation Power Point ማዘጋጀት
# ለሁለተኛ ዲግሪ(ማስተርስ) ተማሪዎች
- Article Review መስራት
ማማከር
- Term Paper ማዘጋጀት
ማማከር
- Literatur Review መስራት
ማማከር
- Research Proposal መስራት ማማከር
- Research መስራት ማማከር
- SPSS ስልጠና መስጠት
- STATA ስልጠና መስጠት
- ለ Research Defence and presentation power point ማዘጋጀት
በአዲስ ዓመት አዳዲስ አገልግሎቶችን ጨምረን ብቅ ያልን ሲሆን እስካሁን አብራችሁን ለነበራችሁ ሁሉ እያመሠገንኩኝ ማንኛውም ግለሠብ ወይም ድርጅት ቢያነጋግረን እንደፍላጎታችሁ የምናስተናግድ ሲሆን አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ በዚህ 0948690446 በመደወል ማማከር የሚቻል መሆኑን እናሣውቃለን።

Address

Ethiopia, Gondar
Addis Zemen

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Abel Selomon Research And Others Consultancy Center posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Abel Selomon Research And Others Consultancy Center:

Share