የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication

የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication ይህ የየካ ክ/ከተማ ወረዳ 02 ኮሙዩኒኬሽን ፅ/ቤት የፌስቡክ ገፅ ነው።

ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ።

31/05/2026
የፀጥታ አካላት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁግንቦት 21/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽንየየካ ክፍለ ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት እና የሸገር መ...
29/05/2026

የፀጥታ አካላት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ዝግጁ መሆናቸውን ገለፁ

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም | የካ ኮሙኒኬሽን

የየካ ክፍለ ከተማ ጥምር የፀጥታ አካላት እና የሸገር መና አቢቹ ክፍለ ከተማ የፀጥታ አካላት ጋር 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የአንድ ማዕከል የፀጥታ ስምሪት ተሰጥቷል።

በዕለቱ ተገኝተው ለፀጥታ አካላት ስምሪት የሰጡት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሊዲያ ግርማ፣ “ከዚህ ቀደም የከተማችንን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ እንዳደረግነው ሁሉ፣ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫም ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ በልዩ ትኩረት እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው “መላው የፀጥታ መዋቅራችን 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እንደሁልጊዜውም ዝግጁ ነው” ሲሉ ገልፀዋል።

የየካ ክፍለ ከተማ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሀብታሙ ደረጀ በበኩላቸው የሰላም ሰራዊት ከፀጥታ መዋቅሩና ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት የከተማዋን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ፀረ-ሰላም ኃይሎችን ሴራ በማክሸፍ ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልፀዋል።

በስምሪት መርሃ ግብሩ ላይ የሸገር ሲቲ መና አቢቹ ክፍለ ከተማ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን ለፀጥታ አካላቱ አስፈላጊውን የቁሳቁስና የግብዓት ድጋፍ ተደርጓል።

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች👉የቤት ለ...
28/05/2026

ከዛሬ ግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. (በጥሞና ወቅት) ጀምሮ ምን ምን ማድረግ አይቻልም?

1. በአካልና በዐደባባይ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች
👉ፖለቲካ ተኮር የሕዝብ ስብሰባዎችና ሠልፎች
👉የቤት ለቤትና የዐደባባይ ላይ ቅስቀሳዎች
👉የቅስቀሳ ኅትመቶችን እና ቁሳቁሶችን መለጠፍና ማሠርጭት
👉የቅስቀሳ አልባሳትን መልበስ

2. የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት
👉የቀጥታም ሆነ የተቀረጹ የዕጩ ወይም የፓርቲ ፕሮግራሞች ሥርጭት
👉የማኅበራዊ ትሥሥር ገጾችን በመጠቀም ቅስቀሳ ማድረግ
👉ፕሮጀክት ማስጀመር እና ማስመረቅ
"የጥሞና ጊዜን ማክበር የምርጫውን ተዓማኒነት ያረጋግጣል! መራጩም ያለ ምንም ውጫዊ ተፅዕኖ፣ ግርግርና ቅስቀሳ በሰላም አስቦ እንዲወሥን ይረዳል።"

የተረጋገጡ መረጃዎችን ይፋዊ የቦርዱን የፌስቡክ ገጽ እንዲሁም በሌሎች የቦርዱ የማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ አማራጮች አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ ሲል ምርጫ ቦርድ አስታውቋል::

27/05/2026

Address

Ferensay Legasion
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የካ ወረዳ 2 ኮሙዩኒኬሽን - Yeka Woreda 2 Communication:

Share