Addis Ababa Electric Service Administration Authority

Addis Ababa Electric Service Administration Authority This is Official Page of Addis Ababa Electric Service Administration Authority/
ይህ የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ይፋዊ ገፅ ነው

25/08/2026

በአዲስ አበባ የመብራት መሰረተ ልማትን በጋራ መጠበቅ ያስፈልጋል !!

**********************
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው  የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!በዓሉን  ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመ...
24/08/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ፤ እንኳን ለ1 ሺህ 501ኛው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤ ለሌላቸው በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የታመሙትን በመጠየቅ እንዲሆን እመኛለሁ።

በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ - ኢድ ሙባረክ!
ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ነዋሪዎች ለባለስልጣኑ ምስጋና አቀረቡ።በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 14 ገርጂ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ለአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ምስጋና አቀረቡ።ነዋሪ...
24/08/2026

ነዋሪዎች ለባለስልጣኑ ምስጋና አቀረቡ።

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለከተማ ወረዳ 14 ገርጂ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ለአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ምስጋና አቀረቡ።

ነዋሪዎች በአካባቢው የመንገድ መብራት ባለመኖሩ ለችግር ሲጋለጡ የቆዩ ሲሆን፤ ባለስልጣን መስሪያቤቱ ችግሩን በአፋጣኝ መፍትሄ በመስጠቱ የምስጋና ምስክር ወረቀት አቅርበዋል ።

ባለስልጣን መስሪያቤቱ በዋና ዋና መንገዶች እየሰራቸው ካሉ የመብራት መሰረተ ልማቶች በተጨማሪ በውስጥ ለውስጥ የመኖሪያ መንደሮች የመብራት ጥገና በማከናወን ለህብረተሰቡ እያስረከበ ይገኛል።

*************************************
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ 522 የመብራት ምሰሶዎች በትራፊክ አደጋዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ባለስልጣኑ ገለፀ።በአዲስ አበባ ከተማ የተደራጀ ስርቆት እና የተሽከርካሪ አደጋ በመ...
23/08/2026

በአዲስ አበባ ባለፉት ሁለት አመታት ብቻ 522 የመብራት ምሰሶዎች በትራፊክ አደጋዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ባለስልጣኑ ገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተደራጀ ስርቆት እና የተሽከርካሪ አደጋ በመብራት መሰረተ ልማት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት እየጨመረ ይገኛል።

ይህን ለመከላከል አላማ ያደረገ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ በአድዋ ድል መታሰቢያ ተካሂዷል።

መድረኩ በአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን እና የከተማ አስተዳደሩ ዋና ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት ትብብር የተዘጋጀ ነው።

በመድረኩ ዳሰሳዊ ፅሁፍ በአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የፍቃድና የደንበኞች አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጁናይድ ከማል አቅርበዋል።

የቀረበው ፅሁፍ እንዳመለከተው በ2017 እና 2018 በጀት አመት 248 ነባር የመብራት ምሰሶዎች በትራፊክ አደጋዎች ከጥቅም ውጭ ሆነዋል ወይም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እንዲሁም በነዚህ ሁለት አመታት በኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች በከፍተኛ ወጪ የተገነቡ 274 አዳዲስ የመብራት ፖሎች በትራፊክ አደጋዎች ተገጭተው ጉዳት እንደደረሰባቸው አመልክቷል።

ይህም በድምሩ በሁለት አመት ብቻ 522 የመብራት ምሰሶዎች በትራፊክ አደጋዎች የጉዳት ሰለባ ሆነዋል።

ሌላኛውና በጣም አሳሳቢው ደግሞ በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆት ሲሆን በሁሉም ክፍለከተሞች ተባብሶ መቀጠሉን የቀረበው ፅሁፍ አመልክቷል።

ይህ ተግዳሮት የአገልግሎት መቆራረጥን በማስከተል የጸጥታ ስጋት መፍጠሩ እንዳለ ሆኖ፣ በሕዝብና በመንግሥት ከፍተኛ ሃብት የተገነቡ ንብረቶች ላይ እያደረሰ ያለው የኢኮኖሚ ኪሳራ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል።

በመሆኑም ይህ አንገብጋቢ ጉዳይ የሁሉንም ህብረተሰብ ክፍልና የአስፈጻሚ ተቋማት ቅንጅት የሚፈልግ ስለሆነ፣ በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈፀም ስርቆትና አደጋን በጋራ ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ምክክር ወሳኝ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።

*******************************
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

የመብራት መሠረተ ልማትን ከስርቆትና ከጥፋት ለመጠበቅ የጋራ ትብብር ያስፈልጋል።በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ ስርቆቶችንና የአደጋ ምንጮችን በጋራ ለመከላከል የባለድርሻ ...
22/08/2026

የመብራት መሠረተ ልማትን ከስርቆትና ከጥፋት ለመጠበቅ የጋራ ትብብር ያስፈልጋል።

በአዲስ አበባ የመብራት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸሙ ስርቆቶችንና የአደጋ ምንጮችን በጋራ ለመከላከል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ተካሄዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢ/ር ወንድሙ ሴታ የመብራት መሠረተ ልማት የከተማዋ የጋራ ሀብት በመሆኑ ከስርቆትና ከጥፋት መጠበቅ የሁሉም የጋራ ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

አክለውም ችግሩን በዘላቂነት ለመቆጣጠርም ተቋማት መረጃ በመለዋወጥ፣ የህብረተሰቡን ንቃተ ህሊና በማሳደግ በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል ብለዋል።

በመብራት መሠረተ ልማት ላይ የሚፈጸም ስርቆት የከተማዋን የመብራት አገልግሎት ከማስተጓጎል ባለፈ የነዋሪዎችን ደህንነትና የከተማዋን ልማት የሚጎዳ በመሆኑ ማንኛውም አካል የሚያገኘውን ጥቆማ ለህግ አካላት በአፋጣኝ ማሳወቅ እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰብስብ ሁሴን በበኩላቸው የመብራት መሠረተ ልማት የከተማዋን ውበትና ደህንነት ከማሻሻል ባለፈ ለከተማዋ እድገት ወሳኝ መሠረተ ልማት መሆኑን ጠቁመዋል።

ይሁን እንጂ የመብራት መሠረተ ልማቱ በስርቆትና በተሽከርካሪ አደጋ ጥፋት ሲጎዳ የሀገር ሀብት ከማባከን ባለፈ የከተማዋን የመብራት አገልግሎትና የነዋሪዎችን ደህንነት እንደሚጎዳ አስረድተዋል ።

በመሆኑም ችግሩ በአንድ ወይም ሁለት ተቋም ብቻ መፍታት እንደማይቻል ጠቅሰው የፀጥታ አካላት፣ የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት፣ የፍትህ አካላት፣ እና ህብረተሰቡ በቅንጅት መሥራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

በመድረኩ የመብራት መሠረተ ልማት ስርቆት የሚፈጸምባቸውን አካባቢዎች በመለየት ቅድመ መከላከልን ማጠናከር፣ የጥበቃ ሥርዓትን ማሻሻል፣ ሕገወጥ የመሠረተ ልማት ንግድን መቆጣጠር፣ የሕግ አፈጻጸምን ማጠናከርና የህብረተሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

በቀጣይም የተቀናጀ የጥበቃ፣ የክትትልና የፈጣን ምላሽ ሥርዓትን በማጠናከር የከተማዋን የመብራት መሠረተ ልማት ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገልጿል።

**************
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የመግባቢያ ስምምነት ከተለያዩ ተቋማትና ማህበራት ጋር ተፈራረመ።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣ...
21/08/2026

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የመግባቢያ ስምምነት ከተለያዩ ተቋማትና ማህበራት ጋር ተፈራረመ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የተፈራረመው የመግባቢያ ስምምነት በ2019 በጀት አመት ከተቋማት ጋር በትብብርና በቅንጅት በመስራት በከተማዋ የተሻለ የመብራት መሰረተ ልማት ለመዘርጋትና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።

ይህ የመግባቢያ ስምምነት የተፈረመው የባለስልጣኑ የ2019 በጀት አመት ዕቅድ ማጠቃለያ ውይይት ለባለድርሻ አካላት ቀርቦ ውይይት ከተካሄደ በኃላ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራ አስኪያጅ ጽህፈት ቤት እና በአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን መካከል የተካሄደው የመግባቢያ ስምምነትን በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተፈራ ሞላ እና የአዲስ አበባ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰብስብ ሁሴን ተፈራርመዋል።

ሌሎች ከተቋማትና ማህበራት ጋር የተካሄደውን የመግባቢያ ስምምነት ደግሞ የባለስልጣኑ የየዘርፎች ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች እና የፅህፈት ቤት ኃላፊ ከተቋማቱ ኃላፊዎችና ተወካዮች ጋር ተፈራርመዋል።

**********
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

ባለስልጣኑ አብረውት ለሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት እውቅና ሰጠ ።በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅ...
20/08/2026

ባለስልጣኑ አብረውት ለሚሰሩ የተለያዩ ተቋማት እውቅና ሰጠ ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የ2018 በጀት አመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ውይይት የማጠቃለያ መድረክ አካሂዷል።

በዝግጅቱ ለባለስልጣኑ የ2018 ዕቅድ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱ የተለያዩ ተቋማት የምስጋና የምስክር ወረቀት እውቅና አበርክቷል።

እውቅና የተበረከተላቸው ተቋማቱም ከዝግጅቱ የክብር እንግዳ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶ/ር ተፈራ ሞላ እና ከባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሰብስብ ሁሴን የምስክር ወረቀቱን ተቀብለዋል ።

************
የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

19/08/2026

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማት መሟላት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ አድርጓል ።በ2018 በጀት ዓመት የከተማዋን ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማት ሽፋን ማሳደግ እንደተቻለ የአዲስ አበ...
18/08/2026

በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማት መሟላት የምሽት ንግድ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃ አድርጓል ።

በ2018 በጀት ዓመት የከተማዋን ዘመናዊ የመብራት መሰረተ ልማት ሽፋን ማሳደግ እንደተቻለ የአዲስ አበባ ከተማ የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን አስታውቋል።

ባለስልጣኑ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ከባለድርሻ አካላት ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በመድረኩ እንደተገለጸው፤ ከ41 ሺህ በላይ የከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማቶች በመረጃ ዲጂታላይዜሽን እና በጂኦግራፊያዊ መረጃ መሰረተ ልማት (GIS) ስርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በበጀት ዓመቱ ከ14 ሺህ በላይ የመብራት ፖሎች የጥገና ሥራ ተከናውኗል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሰብስብ ሁሴን (ዶ/ር) እንዳሉት፤ በ9101 ነጻ የስልክ ጥሪ እና በሌሎች አማራጮች ከማህበረሰቡ የሚነሱ የመብራት መሰረተ ልማት ጥገና ጥያቄዎች ላይ ፈጣን ምላሽ እየተሰጠ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በከተማዋ የመብራት መሰረተ ልማቶች መሟላት ለመዲናዋ የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል።

መሰረተ ልማቱ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን በመከላከል እና የምሽት የንግድ እንቅስቃሴ ስኬታማ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና አበርክተዋል፡፡

በመድረኩ ባለስልጣኑ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መሥራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ሰነድ ስምምነትም ተፈራርሟል።

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

የጥንቃቄ መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት መሰረተ ልማት ላይ የተሽከርካሪ አደጋ (ግጭት) በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን የአዲስ አበባ መብረት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ይገልጻል ።...
17/08/2026

የጥንቃቄ መልዕክት

በአዲስ አበባ ከተማ የመብራት መሰረተ ልማት ላይ የተሽከርካሪ አደጋ (ግጭት) በየጊዜው እየጨመረ መሆኑን የአዲስ አበባ መብረት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ይገልጻል ።

ይህም በንብረት እና በሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ይታወቃል ።

በመሆኑም አደጋውን መቀነስና ሙሉ በሙሉ ማስቆም እንዲቻል ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ርብርብ እንዲያደርጉ እና አሽከርካሪዎችም በጥንቃቄ እንዲያሽከረክሩ ባለስልጣኑ ጥሪ ያቀርባል።

ለማንኛውም የመብራት ጥቆማ በነፃ የስልክ ጥሪ 9101 ይደውሉ !!

"ዘመናዊ መብራት ለብሩህ አዲስ አበባ !"

የአዲስ አበባ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ትክክለኛ የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በመወዳጀት ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ያግኙ !

በፌስቡክ
https://www.facebook.com/share/1HJwuSw1Ni/

በቴሌግራም
https://t.me/AACA_ESAA

Address

Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Electric Service Administration Authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share