Grand Ethiopian Renaissance Dam

Call Directions Website Contact the organization

Grand Ethiopian Renaissance Dam የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል በዓል አደረሳችሁ!ሀገራችንን ከድህነት ለማላቀቅ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተበሰረበት ቅጽበት ጀምሮ፣ መላው ኢትዮጵያው...
26/09/2026

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2019 ዓ.ም የመስቀል በዓል አደረሳችሁ!

ሀገራችንን ከድህነት ለማላቀቅ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከተበሰረበት ቅጽበት ጀምሮ፣ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በህዝባዊ ንቅናቄ፣ በሞራል፣ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲና በአካባቢ ጥበቃ ላደረጋችሁት ያልተቋረጠ ድጋፍና ላሳያችሁት ጽናት እናመሰግናለን።

በታላቁ ህዳሴ ግድብ ያሳየነውን የማይበገር ቁርጠኝነት፣ አንድነትና ህዝባዊ ርብርብ ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነትና የጋራ እድገት በመድገም፣ አዳዲስ ታሪኮችንና ስኬቶችን በጋራ እንድንጽፍ መልካም ምኞታችንን እንገልፃለን።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት
መስከረም 16፣ 2019 ዓ.ም

የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዘላቂነት በአድዋ ድል መታሰቢያ ተቀመጠበመላው ኢትዮጵያውያን ትብብር ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት፣ የአንድነትና ጽናት ተምሳሌ...
25/09/2026

የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በዘላቂነት በአድዋ ድል መታሰቢያ ተቀመጠ

በመላው ኢትዮጵያውያን ትብብር ግንባታው ተጠናቆ ለምረቃ የበቃው፤ የሁሉም ኢትዮጵያውያን አሻራ ያረፈበት፣ የአንድነትና ጽናት ተምሳሌት የሆነው ታላቁ የህዳሴ ግድብ በርካታ ውጣ ውረዶችን አልፎ በመጠናቀቁ ዳግማዊ የአድዋ ድል ነው፡፡ ግድቡ መላው ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዕርስ በዕርስ ያስተሳሰረና ያቆራኘ እንዲሁም በአንድነት እንዲቆሙ ያደረገ የዘመናችን በታሪክ ተጠቃሽ ክስተት ነው።

የህዳሴ ዋንጫ መላው ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች የታላቁ ህዳሴ ግድብ እንደተበሰረ ለግድቡ ግንባታ ስራ እውን ለማድረግ ላሳዩት የላቀ አስተዋፅኦ የተበረከተ ያሸናፊነት ማረጋገጫ ምልክት ነው፡፡ “የታላቁ ህዳሴ ግድብ ዋንጫ” ስለግድቡ ታላቅ የንቅናቄ ስራ ከተሰራባቸው ስልቶች መካከል አንዱ ሲሆን የህብረተሰቡ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማሰባሰብ ላለፉት 14 ዓመታት አንድነትና ሠላም ተሰብኮበታል።

የህዳሴ ግድብ ዋንጫ በመላው ሀገሪቱ በመዘዋወር በቦንድ ግዥ እና በስጦታ ከ6.8 ቢሊዮን ብር በላይ ሃብት ለማሰባሰሰብ ምክንያት ሆኗል። ላለፉት 14 ዓመታት ከህብረተሰቡ በአጠቃላይ የተሰበሰበው ገንዘብ ከ25.2 ቢሊዮን ብር በላይ ሲሆን ለግድቡ ግንባታ ከዋለው ጠቅላላ ወጪ 10.3 በመቶ ከህዝቡ የተሰበሰበ ነው፡፡ በተጨማሪ ሀገራዊ አንድነትና ሠላም እንዲጠናከር፤ የቁጠባ ባህል እንዲያድግ፣ “የይቻላል!” መንፈስ እንዲጎለብት ታላላቅ ህዝባዊ የንቅናቄ ስራዎች ተሰርተውበታል።

አርሶ አደሮችንና አርብቶ አደሮችን በማስተባበር በአባይ ተፋሰስ አካባቢዎች የአካባቢ ጥበቃና የተፋሰሱ የልማት ሥራዎች በጉልበት የተሰራው ወደ ገንዘብ ሲቀየር በጠቅላላ ከ84.49 ቢሊዮን ብር በላይ እንደሚገመት መረጃዎች ይገልፃሉ፡፡

ቀደምት ኢትዮጵያውያን ወደነበሩበት የዓለም ስልጣኔ ጠርዝ ላይ ለመድረስ በረጅሙ ህዳሴ ጉዞ ለመራመድ የመነሳታቸው ማሳያና መላው ኢትዮጵያውያን በዳግማዊ አድዋ ግድቡን እውን ለማድረግ የከፈሉትን ዋጋ የሚያሳይና ታሪኩን በአግባቡ የሚተርኩ ቅርሶች በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ተደራጅተው ለህዝብ እይታ እንዲውሉ መደረጋቸው አዳዲስ ሀገራዊ የጋራ ትርክቶችን ለመፍጠር ተምሳሌት ሆኖ ከማገልገሉም በተጨማሪ ዘርፈ-ብዙ ፋይዳዎች አሉት፡፡

የኢትዮጵያውያን የትብብር ማሳያ የሆነው የህዳሴን ግድብ ዋንጫ የኢትዮጵያን የጋራ ጥረት ስኬት የሚዘክር ቅርስ በመሆኑና የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልዶች ታላላቅ የጋራ ታሪክ ለመስራት መነሳሳትን ለመፍጠር ለህዝብ እይታ እንዲውል ታሳቢ በማድረግና ሁለተኛው አድዋ መሆኑን ለማዘከር በአድዋ ድል መታሰቢያ በዘላቂነት እንዲቀመጥ ተደርጓል።

የግብጽ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቦታ የሌለው ኋላቀር አካሄድ ነው፡፡የግብጽ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እና የውሃ የበላይነት ህልም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈጽሞ ቦታ የሌለውና...
22/09/2026

የግብጽ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቦታ የሌለው ኋላቀር አካሄድ ነው፡፡

የግብጽ የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ እና የውሃ የበላይነት ህልም በ21ኛው ክፍለ ዘመን ፈጽሞ ቦታ የሌለውና ኋላቀር አካሄድ መሆኑን የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ኢትዮጵያ ዓባይን ጨምሮ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶቿን የማልማት እና የቀጣዩን ትውልድ ፍላጎት የማሟላት ሉዓላዊ መብቷን በአግባቡ እንደምትጠቀምም ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።
ኢትዮጵያ ዓባይን ጨምሮ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶቿን የማልማት ሉዓላዊ መብቷ የተጠበቀ መሆኑንም አመልክቷል።
በቅርቡ የግብፅ የውሃ ሀብትና መስኖ ሚኒስትር ኢትዮጵያውያንን በመዝለፍ የሰጡት አስተያየት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለውና ግብጽ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ባላት ግንኙነት የምትከተለውን የቅኝ ግዛት አስተሳሰብ በግልጽ ያሳየ መሆኑን አመልክቷል።
ግብጽ ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት የውሃ ሀብታቸውን የሚጠቀሙት እሷን ጠይቀውና ፈቃድ አግኝተው ብቻ ነው ብላ ማመኗ ሁልጊዜም የበላይ ልሁን ከሚለው ኋላ ቀር እሳቤዋ የሚመነጭ መሆኑን ገልጿል።
ይህ የግብጽ አቋም ከእውነት የራቀ እና ፍጹም አስመሳይነት የተሞላበት መሆኑን ሚኒስቴሩ ጠቁሟል።
ግብፅ ከዚህ ቀደም የትኛውንም የተፋሰሱ ሀገራት ፈቃድ ሳትጠይቅ የአስዋን ታላቁን ግድብ መገንባቷን መግለጫው አውስቷል።
የግብፅ ባለሥልጣናት የሚያሰሙት ጥላቻ የሞላበት ንግግር እና የሚከተሉት አሻሚ አካሄድ፤ በተፋሰስ ሀገራት መካከል ሊኖር ከሚገባው የትብብር መንፈስ ጋር ፈጽሞ የሚቃረን መሆኑ ተመላክቷል።
ኢትዮጵያ ዓባይን ጨምሮ ያሏትን የተፈጥሮ ሀብቶቿን የማልማት እና የቀጣዩን ትውልድ ፍላጎት የማሟላት ሉዓላዊ መብቷ የተጠበቀ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።
ኢትዮጵያ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች የአለመግባባትና የንትርክ ምንጭ ሳይሆን ትብብርን፣ የጋራ እድገትንና የቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ መሆን እንዳለባቸው በጽኑ ታምናለች ብሏል ሚኒስቴሩ በመግለጫው።
አንዱ አካል ብቻ ተጠቃሚ የሚሆንበት እና የተፋሰሱ ሀገራትን መብት ነፍጎ የበላይነትን በጉልበት ለመጫን የሚደረግ ጊዜ ያለፈበት አካሄድ ፈጽሞ ተቀባይነት የለውም ሲል ሚኒስቴሩ አስገንዝቧል።
አንዳንድ አካላት የዓባይን ወንዝ እንደ ጸጥታና ግጭት አጀንዳ ብቻ ማየትን ሲመርጡ፣ ኢትዮጵያ ግን የተፋሰሱን የረጅም ጊዜ ደህንነትና ዘላቂነት ለማረጋገጥ ሰፊ ተግባራትን ማከናወኗን ገልጿል።
ኢትዮጵያ በውሃ ተፋሰስ አካባቢዎች የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ማድረጓን፣ ሰፊ የችግኝ ተከላና የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ማከናወኗን እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን በዘላቂነት እየሰራች እንደሚገኝ ሚኒስቴሩ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ አዎንታዊ እርምጃ ከግብጽ ጠላትነት ከሞላበት የተሳሳተ ትርክት አንጻር ሲታይ ፍጹም የተለየ እና የሰለጠነ አካሄድ መሆኑን አመልክቷል።
በመሆኑም ግብጽ ጊዜው ካለፈበት ፖሊሲ ወጥታ፣ ጉዳዩን በጋራ መከባበርና የሁሉንም ወገኖች የረጅም ጊዜ ጥቅም በሚያከብር የ21ኛው ክፍለ ዘመን አስተሳሰብ ልትመለከተው ይገባል ብሏል።
ግብጽ አሮጌና ጊዜ ያለፈባቸውን የበላይነት ህልሞች በመተው፣ አዲሱን የትብብር እውነታ መቀበል የሚገባበት ጊዜ አሁን መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ምንጭ፡- የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴርን ጠቅሶ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደዘገበው

Statement on Recent Remarks by the Egyptian Minister of Water Resources and IrrigationThe recent remarks by the Egyptian...
22/09/2026

Statement on Recent Remarks by the Egyptian Minister of Water Resources and Irrigation

The recent remarks by the Egyptian Minister of Water Resources and Irrigation, suggesting that Ethiopians lack education, are deeply regrettable. The statement is once again a manifestation of a crude colonial mentality that defines Cairo’s policy in its relations with African states. For Cairo, its approval is a prerequisite for riparian countries of the Abay/Nile to develop their water resources. This is despite the fact that Egypt proceeded with the construction of the Aswan High Dam with no consultation with any upstream riparian state. Inflammatory remarks by Egyptian officials and the double standards they espouse have no place in the context of basin wide cooperation.
Ethiopia reaffirms its sovereign right to utilize its natural resources including Abbay River to meet the needs of its present and future generations. Ethiopia has consistently maintained that Transboundary Rivers should drive cooperation, shared prosperity, and regional integration rather than monopolistic contention, and exclusion. It rejects any notion of hydro-imperialism that seeks to deny source countries their inherent rights as sovereign nations.
While some continue to frame the Abay river primarily through the lens of security and zero-sum competition, Ethiopia has invested heavily in watershed rehabilitation, afforestation, and environmental conservation to strengthen the long-term sustainability of the basin. Ethiopia's approach stands in sharp contrast to the hostile narrative that has too often dominated official discourse in Cairo. It is time for Cairo to move from its obsolete policy and approach the matter with a 21st century outlook grounded in mutual respect and the enlightened long-term interests of all. It is time to retire outdated hegemonic dreams and embrace the dawn of a new reality.

Source: Ministry of Water and Energy - Ethiopia

18/09/2026
የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የኢትዮጵያን ህዝብ አመሰገነአዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 03፣ 2018 ዓ.ም፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት መላው የኢትዮጵያን...
09/09/2026

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የኢትዮጵያን ህዝብ አመሰገነ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 03፣ 2018 ዓ.ም፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት መላው የኢትዮጵያን ህዝብ አመሰገነ፡፡
የታላቁ ህዳሴ ግደብ ህዝባዊ ተሳትፎ ግቡን እንዲመታ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጎን ተሰልፈው ሁለንተናዊ ድጋፍ ሲያደርጉ ለነበሩ መላው ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የምስጋና ፕሮግራም ጳጉሜን 03 ቀን 2018 ዓ.ም. ተካሄደ፡፡
ሀገራችንን ከድህነት ለማላቀቅ በዐባይ ወንዝ ላይ ታላቁ የህዳሴ ግደብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጅምሮ እስኪጠናቀቅ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የግድቡ ባለቤት በመሆን በህዝባዊ ንቅናቄና በሞራል፣ በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በጉልበት፣ በሀሳብ፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲና በአካባቢ ጥበቃ ያልተቋረጠ ድጋፍ አድርገዋል፡፡
መላው የኢትዮጵያ ህዝብና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ያለ ምንም ልዩነት በዐባይ ወንዝ ላይ በአንድነት ለጋራ ዕድገታቸው በይቻላል መንፈስ በትብብር በማዋል በዓለም ፊት ታላቅ ገድል ፈጽመዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ስራ አስፈጻሚ ክቡር አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ላላፉት ዓመታት ሀብታችሁን፣ ዕውቀታችሁንና ጉልበታችሁን ሳትሰስቱ ለሰጣችሁ መላው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በፕሮጀክት ጽ/ቤቱና በሀገራችን ኢትዮጵያ ስም ከጉልበቴ ዝቅ ብየ በሀገራችን ባህል “እናመሰግናለን!” በማለት ገልጸዋል፡፡
የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር) በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በንግግራቸው ሁላችንም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ታላቁ የህዳሴ ግድባችንን ተረባርበን በመገንባት ያለምንም ልዩነት በራስ አቅም ድህነትን ማሸነፍ እንደምንችል በተግባር አረጋግጠናል ብለዋል፡፡
መላው የሃገራችን ህዝቦች ከጫፍ ጫፍ ተነሳስተው የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በአጠቃላይ ከ25.2 ቢሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ተሰብስቧል፤ እንዲሁም ከ84.49 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት በአካባቢ ጥበቃና የጉልበት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በመርሃ-ግብሩ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በአንድ አዳራሽ መሰብሰብ ስለማይቻል የፌዴሬሽን ም/ቤት፣ የተወካዮች ም/ቤትን ጨምሮ ከፌዴራል እና የክልልና ከተማ አስተዳደር የስራ ሀላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተወካዮች፣ የመገናኛ ብዙሃን፣ የኪነ-ጥበብ ሥራ የሚሰሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚወክሉ፣ የማስታወቂያ ባለሙያዎች እና ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች በተገኙበት የምስጋና እና እውቅና ተሰጥቷል፡፡
ታላቁ ህዳሴ ግድብ፤ ጽኑ መሰረት ለማንሰራራት!

08/09/2026

Address

Yared Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+2515570588

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Grand Ethiopian Renaissance Dam posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Grand Ethiopian Renaissance Dam:

Shortcuts

Share