Ethiopian Football Federation

Ethiopian Football Federation ይህ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው። ይህን ገፅ ላይክ በማድረግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን መረጃዎችን ይከታተሉ። It organizes the national football leagues and the national team.

The Ethiopian Football Federation ( EFF ) is the governing body of football in Ethiopia. It was founded in 1943 and became affiliated with FIFA in 1952 and with CAF in 1957.

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር የሚሰጠው የካፍ ኤ ላይሰንስ  ስልጠና ሦስተኛ ሞጁል ስልጠና በትላንትናው ዕለት በአዲስ አባባ የካፍ የልህቀት ማዕከል ተጀምሯል። ስልጠናው...
05/06/2026

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከካፍ ጋር በመተባበር የሚሰጠው የካፍ ኤ ላይሰንስ ስልጠና ሦስተኛ ሞጁል ስልጠና በትላንትናው ዕለት በአዲስ አባባ የካፍ የልህቀት ማዕከል ተጀምሯል።

ስልጠናው ለቀጣይ 10 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናውን በበላይነት በካፍ ኤሊት ኡንስትራክተር አብርሃም መብራቱ እና ሌሎች ተጋባዥ ኢንስትራክተሮች አማካኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡

የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እና ማላዊ አሰልጣኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ
05/06/2026

የነገውን ጨዋታ አስመልክቶ የኢትዮጵያ እና ማላዊ አሰልጣኞች የሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል። ቡድናችን ከማላዊ የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ነገ ግንቦት 29 በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ...
05/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ነገ ከሚያደርገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል።

ቡድናችን ከማላዊ የሚያደርገው የመጀመርያ ጨዋታ ነገ ግንቦት 29 በድሬዳዋ ስታዲየም ምሽት 12፡00 ላይ የሚካሄድ ሲሆን ጨዋታውን የጅቡቲ ዳኞች ይመሩታል።

ተጋጣሚያችን የማላዊ ብሔራዊ ቡድን በዛሬው ዕለት ድሬዳዋ የገባ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በድሬዳዋ ስታዲየም ልምምዳቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በድሬዳዋ የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል።የቡድናችን አባላት በዛሬው ዕለት ወደ ድሬዳዋ ማምራታቸው የሚታወቅ ሲሆን ጥቂት እረፍት ካደረጉ በኋላ ከ11፡40 ጀምሮ ልምም...
04/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በድሬዳዋ የመጀመርያ ልምምዱን አከናውኗል።

የቡድናችን አባላት በዛሬው ዕለት ወደ ድሬዳዋ ማምራታቸው የሚታወቅ ሲሆን ጥቂት እረፍት ካደረጉ በኋላ ከ11፡40 ጀምሮ ልምምዳቸውን አከናውናዋል። በስብስቡ የሚገኙት 21 ተጫዋቾችም በተሟላ ሁኔታ ልምምዳቸውን አከናውነዋል።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ የተከበሩ አቶ ከድር ጁሃር በስፍራው በመገኘት የብሔራዊ ቡድናችንን ልምምድ ተከታትለዋል።

04/06/2026

The Ethiopian National Team has arrived in Diredawa ahead of its upcoming international friendly matches against Malawi.

Our team will face Malawi at Diredawa Stadium on Saturday, June 6, and Tuesday, June 9.

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድሬዳዋ ደርሷል። የልዑክ ቡድናችን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ሲደርስ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ጀማል ኢብራሂም (ኢ/ር)፣ የድሬዳዋ አስተዳደ...
04/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድሬዳዋ ደርሷል።

የልዑክ ቡድናችን ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ሲደርስ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ሥራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ኃላፊ ጀማል ኢብራሂም (ኢ/ር)፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሸን ኮሚሸነር አቶ ካሊድ መሐመድ፣ የድሬዳዋ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮቤል ጌታቸው እንዲሁም የከንቲባ ጽሕፈት ኃላፊ አቶ ከድር አሊዬ በተገኙበት በፖሊስ ማርሽ ባንድ የታጀበ ደማቅ አቀባበል አድርገዋል።

ቡድናችን ማረፍያውን ታቴኖ ሮያል ሆቴል ያደረገ ሲሆን አመሻሽ ላይ በድሬዳዋ የመጀመርያ ልምምዱን ያከናውናል።

የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች እና ሴቶች ውድድር ከሐምሌ 5 - ነሐሴ 3 በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።
03/06/2026

የ2018 የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና የወንዶች እና ሴቶች ውድድር ከሐምሌ 5 - ነሐሴ 3 በድሬዳዋ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአዲስ አበባ የመጨረሻ ልምምዱን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል።ቡድናችን በነገው ዕለት 6፡35 ላይ ወደ ድሬዳዋ የሚያመራ ሲሆን ከማላዊ ጋር ...
03/06/2026

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአዲስ አበባ የመጨረሻ ልምምዱን በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ አከናውኗል።

ቡድናችን በነገው ዕለት 6፡35 ላይ ወደ ድሬዳዋ የሚያመራ ሲሆን ከማላዊ ጋር የሚያደርገው የመጀመርያ የወዳጅነት ጨዋታ ቅዳሜ፣ ሁለተኛው ደግሞ ማክሰኞ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በ10 ክለቦች መካከል ከሰኔ 7-21 በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ...
02/06/2026

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የማጠቃለያ ውድድር በ10 ክለቦች መካከል ከሰኔ 7-21 በሀዋሳ ከተማ እንደሚካሄድ የውድድር ዳይሬክቶሬት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ መረጃዎችን ለማግኘት ማህበራዊ ገፆች ይከታተሉ
————————————————
Telegram -
Facebook - facebook.com/ethiopiaYF
X - twitter.com/EthiopiaLYFL

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ቡሩንዲን በድምር ውጤት 4-2 አሸንፎ ወደ መጨረሻው ዙር ማለፉ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶም አሰልጣኝ ...
02/06/2026

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ቡሩንዲን በድምር ውጤት 4-2 አሸንፎ ወደ መጨረሻው ዙር ማለፉ ይታወቃል። ይህንን አስመልክቶም አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ዙር ማጣርያ ቡሩንዲን በድምር ውጤ...

Address

Https://maps. App. Goo. Gl/xEZrZeUbcRzWernFA
Addis Ababa
1080

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Football Federation posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Football Federation:

Share