Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /

Ministry of  Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር / The Ministry of Revenues is the body responsible for collecting revenue from domestic taxes.

«ገቢ ለልማት» ጋዜጣሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው «ገቢ ለልማት» ጋዜጣ ቁጥር 196 ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዞ ቀርቧል፡፡ ያንብቡት ብዙ ...
25/06/2026

«ገቢ ለልማት» ጋዜጣ

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም

ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው «ገቢ ለልማት» ጋዜጣ ቁጥር 196 ብዙ ጠቃሚ መልዕክቶችን ይዞ ቀርቧል፡፡ ያንብቡት ብዙ ቁም ነገር ይገበዩበታል፡፡

የተከበራችሁ የጋዜጣችን አንባቢዎች በገቢ ለልማት ቁጥር 197 ይዘን እንድንቀርብ የምትፈልጉት ርዕሰ ጉዳይ ካለ በ011-617-84 90 (2133) ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ጋዜጣውን ይህንን ሊንክ በመጫን አውርደው ያንብቡ፡- https://t.me/MoREthiopiaOfficial/9822

የሞጁላር ስልጠና የታክስ ህግ ተገዥነትን በማጎልበት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸሰኔ 17/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)በገቢዎች ሚኒስቴር መካከለኛ ቁጥር 1 ግብር ከፋዮች ቅርን...
24/06/2026

የሞጁላር ስልጠና የታክስ ህግ ተገዥነትን በማጎልበት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑ ተገለጸ

ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር መካከለኛ ቁጥር 1 ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት፣ 4ኛው ዙር የሞጁላር ስልጠና ያጠናቀቁ 192 ግብር ከፋዮችን በዛሬው ዕለት አስመረቀ።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተገኙት የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ታምሩ እንደተናገሩት፤ የሞጁላር ስልጠናው ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ እየተሰጠ ያለ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዚህም እስካሁን ድረስ ከ2 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮችን ማሰልጠንና ማስመረቅ ተችሏል። ስልጠናው ግብር ከፋዮች የታክስ ህጎችን ጠንቅቀው እንዲረዱ በማድረግ፣ የታክስ ህግ ተገዢነት እንዲጎለብት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም ሥራ አስኪያጁ አስገንዝበዋል።

በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የታክስ ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ተግባሩ ታምሩ በበኩላቸው፤ የስልጠና ፍላጎቶችን መነሻ በማድረግና ምቹ የስልጠና ፎርማቶችን በመቅረጽ ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ በ13 ሞጁሎች ተከታታይ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን ተናግረው በገቢ አሰባሰብ ረገድ አዎንታዊ ለውጦች ስለመመዝገባቸው ገልጸዋል።

በመድረኩ ማጠቃለያ ላይ በአገልግሎት አሰጣጥ እና ተቀራርቦ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ 13ቱንም ሞጁሎች በተገቢው መንገድ ተከታትለው ላጠናቀቁ ግብር ከፋዮች የሥልጠና ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።

በተክሉ ኤልያስ
ፎቶ፦ የትናየት እንዳያፍሩ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

“ገቢ ለልማት” ጋዜጣ ቁጥር 196 በቅርብ ቀንሰኔ 17/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው “ገቢ ለልማት” ጋዜጣ ቁጥር 196 ብዙ ጠቃሚ መ...
24/06/2026

“ገቢ ለልማት” ጋዜጣ ቁጥር 196 በቅርብ ቀን

ሰኔ 17/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ውድ የገቢ ለልማት ጋዜጣ አንባቢዎች፤ እንደተለመደው “ገቢ ለልማት” ጋዜጣ ቁጥር 196 ብዙ ጠቃሚ መልእክቶችን ይዞ ይቀርባል፡፡ ይጠብቁን!

በተጨማሪም ክቡራን የጋዜጣችን አንባቢዎች በገቢ ለልማት ቁጥር 197 ይዘን እንድንቀርብ የምትፈልጓቸው ርዕሰ ጉዳዮች ካሉ በ011-617-84 90 (2133) ማሳወቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት (ቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት ) ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዓ.ም እና በመመሪያ ቁጥር 2/201...
22/06/2026

ከተከፋይ ሂሳቦች ላይ ግብርን ቀንሶ ስለማስቀረት (ቅድመ ግብር ክፍያ ስርዓት )

ሰኔ 15/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በአዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዓ.ም እና በመመሪያ ቁጥር 2/2011 መሰረት ከጥቃቅን ኢንተርፕራይዝ በስተቀር ማንኛውም ድርጅት፤ የመንግስት መስሪያ ቤት ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ወይንም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጀት ባለስልጣኑ በሚያወጣው መመሪያ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ግብር ከፋዮች ለሚከተሉት ግብይቶች ከሚፈጽሙት ጠቅላላ ክፍያ ላይ 3% (ሶስት በመቶ) ግብር ቀንሰው የማስቀርት ግዴታ አለባቸው፡፡

👉በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ ግዢ ወይም በአንድ የዕቃ አቅርቦት ውል ከብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በላይ ለሆነ የዕቃ አቅርቦት የሚፈጸም ክፍያ፤
👉በኢትዮጵያ ውስጥ በአንድ የአገልግሎት ውስጥ አቅርቦት ውል ከብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በላይ የሚፈጸም ክፍያ፤

በበላይነሽ እጅጉ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

https://youtu.be/vtaLdMY5qVk
20/06/2026

https://youtu.be/vtaLdMY5qVk

Enjoy the videos and music you love, upload original content, and share it all with friends, family, and the world on YouTube.

19/06/2026

ኩራት ነው ክብር...!

                                                                                                                        ...
19/06/2026

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ሰኔ 12/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ዲጂታል የታክስ ክፍያ ሥርዓትን ለማጠናከር የሦስትዮሽ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሄደሰኔ 11/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)የገቢዎች ሚኒስቴር ዲጂታል የታክስ አስተዳደር ...
18/06/2026

የገቢዎች ሚኒስቴር ዲጂታል የታክስ ክፍያ ሥርዓትን ለማጠናከር የሦስትዮሽ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሄደ

ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

የገቢዎች ሚኒስቴር ዲጂታል የታክስ አስተዳደር ስርዓትን በማስፋት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት እያጠናከረ የመጣ ሲሆን፤ ሚኒስቴሩ በዛሬው እለት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር፣ ከስንቄ ባንክ እና ከጎህ ቤቶች ባንክ ጋር የሦስትዮሽ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት አካሂዷል።

በዚሁ ወቅት የገቢዎች ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዓይናለም ንጉሴ እንደገለጹት፣ የኤሌክትሮኒክስ የታክስ ክፍያ ሥርዓት ለታክስ ሰብሳቢው ተቋም የሥራ ቅልጥፍናን እና የአሰራር ግልጸኝነትን እደሚያስገኝ፣ ለባንኮች ደንበኛን ለመያዝ እና የአገልግሎት አሰጣጣቸውን እርካታን ከፍ እንደሚያርግላቸው እንዲሁም ፍትሀዊና ጤናማ ውድድር እንደሚፈጥር ገልጸው ስርዓቱ ለግብር ከፋዮች ታክስ ለመክፈል የሚስፈልገውን ጊዜና ወጪ አንደሚቆጥብ እና ፈጣን የክፍያ ማረጋገጫ ሰነድ የሚያስገኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ክብረት ሚንስትሯ የዛሬዎቹን ሁለት ባንኮች ጨምሮ በአሁኑ ሰዓት 25 ባንኮች የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ክፍያ አገልግሎት እንደሚሰጡ እና ሥርዓቱ ተግባራዊ በተደረገበት በ2010 በጀት ዓመት 6 ግብር ከፋዮች ብቻ 60 ግብይቶችን በማከናወን የ896 ሚሊዮን ብር የታክስ ክፍያ አንደፈጸሙና ታክስን በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓት ለመሰብሰብ በተሰራ ተከታታይ ተግባር በያዝነው በጀት ዓመት በ11 ወራት ክፍያ እንዳላቸው ካስታወቁት ውስጥ 38,420 ግብር ከፋዮች 372,113 የትራንዛክሽን መጠን በመፈጸም ብር 316 ቢሊዮን በላይ የታክስ ገቢ መሰብሰብ መቻሉን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም በቀጣይ ተግባር ዲጅታል ኢትዮጵያን 2030 እስትራቴጂ እውን እንዲሆን የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የኤሌክትሮኒክስ ታክስ ክፍያ ተጠቃሚዎችን ቁጥር አሁን ከደረሰበት 80% ሽፋን ወደ 100% የማድረስ እንዲሁም ቀሪ ባንኮችን ወደ ሥርዓቱ በማካተት እና በመተባበር ታክስ በኤሌክትሮኒክስ ስርዓት የሚሰበሰብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትእግስት ሃሚድ፣ የስንቄ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ ነዋይ መገርሳ እና የጎህ ቤቶች ባንክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ግሩም ጸጋዬ በየበኩላቸው ይህ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ለተቋሞቻቸው የዲጂታል ጉዞ ትልቅ ምዕራፍ መሆኑ፣ የአገሪቱን የገቢ አሰባሰብ አቅም ለማሳደግ ብሎም ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ለማሳካት መሠረታዊ ሚና እንደሚኖረው ገልፀዋል፡፡

በገዛኽኝ መካሻ
ፎቶ፡ የትናየት እንዳያፍሩ

፡-
#በድረ-ገጽ_እና_ማኅበራዊ_ሚዲያ፡-
🌐 ድረ ገጽ፦ www.mor.gov.et
🌐 ቴሌግራም፦ https://t.me/MoREthiopiaOfficial/169
🌐 ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/ERCA.info
🌐 ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
🌐 ቲክቶክ፡- tiktok.com/
፡-
📺 ፋና ቴሌቪዥን ሐሙስ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
📺 ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን /ኢ.ቢ.ሲ/ ቅዳሜ ማታ ከ2፡00 ዜና በኋላ፣
፡-
📻 ፋና ኤፍ ኤም ሬድዮ 98.1 ሐሙስ ማታ ከ2፡30 ጀምሮ፣
📻 የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሬድዮ 93.1 ማክሰኞ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ፣
፡-
📑 በገቢ ለልማት ወርሃዊ ጋዜጣ እንዲሁም
☎ በነጻ ጥሪ አገልግሎታችን፡- 8199 ላይ በነፃ በመደወል መረጃዎችን ማግኘት ይችላሉ፡፡

18/06/2026

የሞጁላር ስልጠና

ሰኔ 11/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

በገቢዎች ሚኒስቴር በስፋት እየተሰጠ የሚገኘው እና የግብር ከፋዮችን የታክስ ግንዛቤ እያሳደገ የሚገኘው የታክስ ሞጁላር ስልጠናን አስመልክቶ የሰልጣኝ መልእክት

በሽመልስ ሲሳይ
ካሜራ፡- የትናየት እንዳያፍሩ

ስለጉምሩክ ቀረጥ ለግንዛቤዎ! ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
17/06/2026

ስለጉምሩክ ቀረጥ ለግንዛቤዎ!

ሰኔ 10/2018 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)

ስለጉምሩክ ቀረጥ ምንነት እና አሰራር ለግንዛቤዎ!

Address

Megenagna, 24 Area
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 18:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር / posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ministry of Revenues of Ethiopia /የገቢዎች ሚኒስቴር /:

Share