የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau በክህሎት የበለፀገ እና ሥራን ባህሉ ያደረገ ትውልድ ለኢትዮጵያችን ብልፅግና መሠረት ነው!!
(1)

17/09/2026
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን! ‎‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆ...
16/09/2026

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት

በመላው ሀገራችን ለሚገኙ ተማሪዎቻችን አዲሱ የትምህርት ዘመን ስኬታማ እንዲሆን እንመኛለን!

‎ወጣቱ ትውልድ ለኢትዮጵያ ትልቁ ሀብቷ በመሆኑ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጅማሮን ተከትሎ፤ እያንዳንዱ ተማሪ ለላቀ እውቀት በትጋትና ጉጉት ትምህርቱን እንዲከታተል፣ ለጥሩ ውጤት በጽናት እንዲተጋ፣ እንዲሁም የሀገራችንን የወደፊት ዕድል መቅረጽ በሚያስችሉ ክህሎቶች እንዲገነባ አበረታታለሁ።

‎ ዛሬ እየተገበርነው ያለው በርካታ የልማት ሥራዎች የነገን ትውልድ ታሳቢ ያደረጉ በመሆናቸው፣ የዚህ ቀጣይ ዕድል ተጠቃሚ እና ባለአደራ እንደመሆናችሁ መጠን፣ የኢትዮጵያን ታላቅ የስልጣኔ ታሪክ ወደፊት ለማስቀጠል የእናንተ ቁርጠኝነት መሠረት እንደሆነ ሙሉ እምነቴ ነው።

‎ብቁ እና በራሱ የሚተማመን ትውልድ ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የመምህራኖቻችን ትጋትና መሰጠት መሰረታዊ ምሰሶ ነው። ተማሪዎቻችንን ማነቃቃት፣ አቅማቸውን ማውጣት፣ እንዲሁም ነገ ተፎካካሪ ሆነው እንዲወጡ የሚያስችሏቸውን ዕውቀት፣ ክህሎትና እሴቶችን የማስታጠቅ አደራን ቀጥሉበት ስል በትህትና አሳስባለው።

‎በትምህርት ዘርፉ ውስጥ ለምትገኙ ባለድርሻ አካላት በሙሉ፤ ስኬታማ እና ፍሬያማ የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ።

16/09/2026

🎓 ክህሎትን በልዩነት፣ ብቃትን በተግባር!

የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በተግባር የታገዘ ስልጠናን በመስጠት ብቁ፣ ተወዳዳሪና ለሥራ ዓለም ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል ለማፍራት በትጋት እየሰራ ይገኛል።

በልዩነት ይሰልጥኑ!
በአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ
የደጃዝማች ገረሱ ዱኪ ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ

#ክህሎት

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የጋራ አብሮነታችን መገለጫዎች ናቸው።🌼 መስከረም 5፤ ቀን 2019 ዓ.ም 🌼የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና መንፈሳዊ እሴታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲ...
15/09/2026

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት የጋራ አብሮነታችን መገለጫዎች ናቸው።

🌼 መስከረም 5፤ ቀን 2019 ዓ.ም 🌼

የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓላት ባህላዊና መንፈሳዊ እሴታቸው ተጠብቆ በሰላም እንዲከበሩ የሁሉም ወገን ጥረት እንደሚያስፈልግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ ገለጹ።

ኃላፊው ይህንን ያሉት ክብረ በዓላቱን አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ነው።አቶ አበበ በመስከረም ወር የሚከበሩት እኚህ ታላላቅ በዓላት በዩኔስኮ የተመዘገቡ የዓለም ቅርሶች መሆናቸውን አስታውሰዋል። እነዚህ በዓላት የሕዝብ የጋራ ሀብቶች እንጂ የነጠላ ትርክት ማራገፊያ ሊሆኑ እንደማይገባም ተናግረዋል።

"ህዝባዊና ሃይማኖታዊ በዓላት የሁሉም ናቸው" ያሉት አቶ አበበ፤ መንግሥት የጸጥታና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎችን የመስራት ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል።

ዜጎችም በዓላቱ በሰላም ተከብረው እንዲያልፉ ከስጋትና ከከፋፋይ አስተሳሰቦች የጸዳ አቀባበል ሊያደርጉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የዘንድሮውን የመስቀልና የኢሬቻ በዓላት ልዩ የሚያደርጋቸው ሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ስኬታማ በሆነ መንገድ መጠናቀቁ ተከትለዉ የሚከበሩ በዓላት እንደሆነ በሰነዱ ላይ ተመላክቷል።

የእርቅ፣ የይቅርታና የአብሮነት እሴቶች ለሀገራዊ መግባባት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸውም ተገልጻል።

በመጨረሻም በዓላቱ ኃይማኖታዊና ባህላዊ ቱፊታቸውን ጠብቀው እንዲጠናቀቁ እያንዳንዱ ዜጋና ባለድርሻ አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://aabols.gov.et/qr.html

አዲስ ልሳን ጋዜጣ በመስከረም 1፤2019 ዕትሟ።የሥራ ዕድል ፈጠራ መረጃ አያያዝ ስርአቱን ከማንዋል ወደ ዲጂታል የቀየረው የተቀናጀ የሥራ ዕድል ፈጠራ አስተዳደር ሲስተም።ሰፊ ትንታኔ ይዛ ወጥ...
14/09/2026

አዲስ ልሳን ጋዜጣ በመስከረም 1፤2019 ዕትሟ።

የሥራ ዕድል ፈጠራ መረጃ አያያዝ ስርአቱን ከማንዋል ወደ ዲጂታል የቀየረው የተቀናጀ የሥራ ዕድል ፈጠራ አስተዳደር ሲስተም።ሰፊ ትንታኔ ይዛ ወጥታለች ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ።

ከተጠሪ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ ክብረ በዓላት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።🌼 መስከረም 4፤ ቀን 2019 ዓ.ም 🌼የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ...
14/09/2026

ከተጠሪ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ ክብረ በዓላት ዙሪያ የውይይት መድረክ ተካሄደ።

🌼 መስከረም 4፤ ቀን 2019 ዓ.ም 🌼

የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ከተጠሪ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ጋር በመስቀል ደመራ እና በኢሬቻ ክብረ በዓላት ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሂዷል።

በውይይቱ በመስከረም ወር የሚከበሩ የመስቀል ደመራ እና የኢሬቼ ክብረ በዓላት ኃይማኖታዊና ባህላዊ እሴቶቻቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ መደረግ ስለሚገባቸው የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሰፊ ውይይት ተካሂዷል።

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቼ ክብረ በዓላት በባህሪያቸው የአደባባይ ላይ በዓላት በመሆናቸውና ሰፊ ህዝብ የሚታደምባቸው በመሆኑ ፍፁም ሰላማዊ ሆነው እንዲጠናቀቁ ሁሉም የድርሻውን መወጣት እንደሚገባው ተጠቁሟል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ
https://aabols.gov.et/qr.html

Address

5 Kilo
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ- Addis Ababa Labor and Skill Bureau:

Shortcuts

Share