05/03/2026
ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር!!
የልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ በዛሬው እለት የ7ኛው ሀገራዊ እና ከተማ አቅፍ ምርጫ ማኒፌስቶ እና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ ፕሮግራም አካሄደ።
በመድረኩም ብልፅግና ፓርቲ ወጣቱ የሀገሪቱ የብልፅግና መሠረት መሆኑን በማመን በኢኮኖሚው ዘርፍ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ወጣቶች በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፍ ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲያገኙ መደረጉን የተጠቁማል።
በውይይቱ ላይም የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ም/ል እና ፓለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ሀብታሙ ጋረደው ባስተላለፉት መልዕክት ብልፅግና ፓርቲ የወጣቶች የሥራ ዕድል ዋስትና በመሆን ተጨባጭ ውጤቶችን እያስመዘገበ ያለ ፓርቲ ነው። ብልፅግናን መምረጥ የኢትዮጵያን አንድነት ማስቀጠል፣ ሰላምን ማረጋገጥና የጀመርነውን የልማት ጉዞ ዳር ማድረስ ማለት ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
በተጨማሪም የወረዳው ብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ወጣቶች ክንፍ ሰብሳቢ ወጣት አቤል ሙሉጌታ ባለፉት አመታት በተለያዩ ደረጃዎች ለሚገኙ ወጣቶች የተለያዩ ስልጠናዎች በመስጠት፣ ለሀገር ግንባታ የሚሆኑ ብቁ መሪዎችን የማፍራት ስራ የተከናወነ እና የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት እንዲሁም በማህበራዊ ተሳትፎ ወጣቱ በሀገራዊ አንድነትና በበጎ አድራጎት ስራዎች ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲወጣ መደረጉን በመናገር ብልፅግናን መምረጥ የኢትዮጵያን አንድነት ማስቀጠል፣ ሰላምን ማረጋገጥና የጀመርነውን የልማት ጉዞ ዳር ማድረስ ማለት ነው በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።