የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice ዜግነትን መሠረት ያደረገ ፖለቲካን እና ማኅበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን እንሰራለን።
(1)

01/06/2026
01/06/2026
01/06/2026

የኢዜማ ፓርቲ መሪ ኢዮብ መሳፍንት ድምፅ ሰጥተዋል

የምርጫ ክልል 18 ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ነው ድምፅ የሰጡት።

በምርጫ ጣቢያው 7 ፓርቲዎች እየተወዳደሩ ሲሆን 53 እጩዎች ቀርበዋል።

ለአዲስ አበባ ምክር ቤት ደግሞ 12 ተወዳዳሪ እጩዎች አሉ።

እንቁጣጣሽ ኃ/ማርያም



የአራዳን ገጾች በመወዳጀት ቤተሰብ ይሁኑ

Youtube:https://www.youtube.com/.1

Tiktok:https://www.tiktok.com/.1offical

Telegram:-https://t.me/Arada_Fm

Telegram:-https://t.me/aradaFmdigital

Facebook:-https://web.facebook.com/aradafm

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሠጠ መግለጫየኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ግንቦት 07/2018 ዓ.ም. "ዴሞክራሲያዊ መብቶች በብሔር ማንነት እና በመንግሥት አሉታ...
29/05/2026

ከኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የተሠጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ግንቦት 07/2018 ዓ.ም. "ዴሞክራሲያዊ መብቶች በብሔር ማንነት እና በመንግሥት አሉታዊ ተፅዕኖ ውስጥ መውደቃቸው ምርጫውን ችግር ውስጥ ይከታል" ሲል ባወጣው መግለጫ፤

የሐረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ለሐረሪ ክልል ም/ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ መሆን ለመመረጥ እንደ አስገዳጅ መስፈርት መቀመጥ በኢፌዴሪ ሕገመንግስት የተደነገገውን ዜጎች ያለምንም ዘር፣ ሐይማኖት እና ሌሎች ማንነት ልዩነቶች ሊጎናፀፉት የሚገባን የመምረጥ እና መመረጥ መብትን የሚጥስ መሆኑን ገልፆ መቃወሙ ይታወሳል።

በተጨማሪም በዚሁ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የሚወዳደሩ እጩዎች ለሐረሪ ም/ቤት እንደሚወዳደሩ ዕጩዎች የሐረሪ ብሔረሰብ ተወላጅነትን እንደ አስገዳጅ መስፈርት ባያስቀምጥም በክልሉ ኢዜማን ወክሎ ለሕ/ተ/ም/ቤት እንዲወዳደር ያቀረብነው እጯችን በሐረሪ ጠ/ፍ/ቤት የወንጀል እና ፍትህ ብሔር ችሎት መዝገብ ቁ 08916 ከሕግ አግባብ ውጪ የሐደሬ ብሔር ተወላጅ አይደሉም በሚል ፓርቲያችን ባልተሣተፈበት እና ባላወቀው ክርክር እጩው እንዳይወዳደሩ ወስኗል።

የውሳኔው ይዘት ምንም እንኳን ስለ ሐረሪ ክልል ም/ቤት ተወዳዳሪዎች የተሰጠ ቢሆንም ለሕ/ተ/ም/ቤት ያቀረብነው አባላችን ስም ተካቶ የተሠጠው ውሳኔ ሕጋዊ ባለመሆኑ ምርጫ ቦርድ ለፍ/ቤቱ ማብራሪያ ቢጠይቅም እንዲሁም ፓርቲያችን በሌለበት የተሠጠው ውሳኔ ተገቢ አለመሆኑንና የክርክሩ አካል እንድንሆን ያቀረብነውን ጥያቄ ከፍትሕ ይልቅ ፖለቲካዊ ውሳኔ ተጭኖት ሳይቀበል ቀርቷል።

በመሆኑም ምርጫ ቦርድ የፓርቲያችንን እጩ ተወዳዳሪ ሕጋዊ ባልሆነ/ባልተሠጠ ውሳኔ ላይ በመመሥረት ከእጩነት ማገዱ ተገቢ አለመሆኑን በመጥቀስ እንዲታረም ለፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታችንን ያቀረብን ሲሆን ክርክሩ ውሳኔ እስከሚያገኝ ድረስ የምርጫ ቦርድ እጯችንን ለመሠረዝ የሠጠው ውሳኔ እንዲታገድ የፍ/ቤቱን ውሳኔ የጠየቅን ቢሆንም ፍ/ቤቱ ግን ተከሳሽ የሆነውን ምርጫ ቦርድን ሳያስቀርብ በእራሡ የተከሳሽን የመከራከርያ ነጥቦች በማንሳት ውሳኔ አሳልፏል።

የተላለፈው ውሳኔ አግባብነት ያለው እና ፍትሐዊ ነው ብለን የማናምን መሆኑን እየገለጽን ኢዜማ የዚህ ዓይነት ኢፍትሐዊ አሠራሮች ከሀገራችን እስከሚጠፉ ድረስ እስከመጨረሻው ድረስ እንደሚሞግት ለመግለጽ ይወዳል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

ከኢዜማ የቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብር የተወሰዱ ምስሎችኢትዮጵያዊነት የእኩልነታችን መሠረት!! ⚖️ #ኢዜማ  #ኢትዮጵያ
27/05/2026

ከኢዜማ የቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብር የተወሰዱ ምስሎች

ኢትዮጵያዊነት የእኩልነታችን መሠረት!! ⚖️

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

ከቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብር ላይ የተወሰዱ ምስሎች ኢትዮጵያዊነት የእኩልነታችን መሠረት ⚖️
27/05/2026

ከቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብር ላይ የተወሰዱ ምስሎች

ኢትዮጵያዊነት የእኩልነታችን መሠረት ⚖️

በሴቶች መብትና በሥረዓተ ፆታ እኩልነት ፖሊሲ ላይ የተደረገ ክርክር እንዲከታተሉ ጋበዝን ፓርቲያችን ኢዜማ በፓርቲው የሴቶች መምሪያ ኃላፊ እመቤት ቢራራ እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሐሮሌ...
27/05/2026

በሴቶች መብትና በሥረዓተ ፆታ እኩልነት ፖሊሲ ላይ የተደረገ ክርክር እንዲከታተሉ ጋበዝን ፓርቲያችን ኢዜማ በፓርቲው የሴቶች መምሪያ ኃላፊ እመቤት ቢራራ እና የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሐሮሌ ዮሴፍ ተወክሏል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

የሴቶች መብት መከበር እና የስርዓተ ፆታ እኩልነት መረጋገጥ ለአንድ ሀገር ሁለንተናዊ እድገት፣ ሰላምና የዲሞክራሲ ግንባታ ወሳኙ መሰረት ነው። በዛሬው እለት የፖለቲካ ፓርቲዎች በሴቶ.....

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)
27/05/2026

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ)

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የቅስቀሳ መዝጊያ መርሐግብርን በሚመለከት የተሰጠ ማብራሪያበቅድሚያ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል አድሐ (አረፋ)...
26/05/2026

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) የቅስቀሳ መዝጊያ መርሐግብርን በሚመለከት የተሰጠ ማብራሪያ

በቅድሚያ ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ። በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የመተሣሠብ እንዲሆንላችሁ እየተመኘን የቅስቀሳ መዝጊያ መርኃግብራችን ላይ የሚከተለውን ማብራሪያ ለመሥጠት እንወዳለን።

ፓርቲያችን ኢዜማ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ2018 ምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩን ካወጀበት ቀን ጀምሮ በተለያዩ መንገዶች ለማኅበረሰቡ ያዘጋጃቸውን አማራጭ የፖሊሲ ሀሳቦች አቅርቦ ለመመረጥ ሲቀሰቅስ መቆየቱ ይታወቃል።

ምርጫ ቦርድ ባስቀመጠው የቅስቀሳ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ፓርቲያችን ያዘጋጀውን የመዝጊያ መርኃግብር አስመልክቶ ሚዲያዎች እንዲዘግቡ ጥሪ ያቀረበበትን ደብዳቤ በማያያዝ መርኃግብሩ በበዓሉ ቀን መደረጉ ግርታ የፈጠረባቸው ወገኖች በቀናነት ማብራሪያ እንድንሰጥበት ጠይቀውናል።

የምርጫ ቅስቀሳ ማጠቃለያችንን በዚህ ዕለት ማድረግ የተመረጠበት ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው

1. ከበዓሉ ማግስት አንስቶ ማንኛውም ከቅስቀሳ ጋር የተያያዙ ተግባራት የማይፈጸምበት የጽሞና ጊዜ በመሆኑ፤

2. በሥራ ቀናት አባላቱን (ሁሉንም የእምነት ተከታዮች) የማሣተፍ እድሉ ዝቅተኛ በመሆኑ፤

3. መርሐግብሩን አመሻሽ ላይ ማድረግ ያስፈለገው የእስልምና እምነት ተከታይ አባላት እና ደጋፊዎቻችን በበዓሉ የሚደረጉት የሶላት ስግደት እና ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚያሳልፉትን የበዓል ጊዜ ታሣቢ በማድረግ ምሽት ላይ መርሐግብራችንን እንዲካፈሉ በማሰብ፤

4. የመርኃግብሩ ይዘት ሰላማዊ ሰልፍ ሳይሆን የፓርቲው ቅስቀሳውን ማገባደዱን የሚገልጽበት መሆኑን ለማሣወቅ እንወዳለን።

አስተያየታችሁን በቀናነት የገለፃችሁልን ወገኖቻችንን ሁሉ ከልብ እያመሰገንን በድጋሚ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

በኢኮኖሚ፣ ሰላምና ደኽንነት እንዲሁም የዜጎች ተሳትፎ ላይ የተደረገ ክርክር ይመልከቱ። ኢዜማ በመሪው እዮብ መሣፍንት እና ም/መሪው ንጋቱ ወልዴ ተወክሎ ሙግቱን አቅርቧል። #ኢዜማ  #ኢትዮጵያ...
25/05/2026

በኢኮኖሚ፣ ሰላምና ደኽንነት እንዲሁም የዜጎች ተሳትፎ ላይ የተደረገ ክርክር ይመልከቱ። ኢዜማ በመሪው እዮብ መሣፍንት እና ም/መሪው ንጋቱ ወልዴ ተወክሎ ሙግቱን አቅርቧል።

#ኢዜማ
#ኢትዮጵያ

EBS TV-Watch on Roku(PC/Mac & iPhone/iPad & Android Devices) : https://live.ebstv.tv/ያለዎትን ጥያቄና አስተያየት በአጭር መልዕክት 7696 ላይ ይላኩልንFollow us on: https://linktr.e...

Address

Ras Desta Damtew Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:00 - 17:00
Tuesday 08:00 - 17:00
Wednesday 08:00 - 17:00
Thursday 08:00 - 17:00
Friday 08:00 - 17:00
Saturday 08:00 - 12:00

Telephone

+251944107661

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ - ኢዜማ Ethiopian Citizens for Social Justice:

Share