05/06/2026
መጪውን ጊዜ ከዓለም ጋር እኩል ለመራመድ የአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ክህሎትን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ተገለጸ።
***ግንቦት 27/2018 ዓ.ም**
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የሚያዘጋጀው የቴክኖሎጂና ፈጠራ ባህል ግንባታ ውይይት አራተኛ ፕሮግራም The future is made locally በሚል መልዕክት በኢንስቲትዩቱ ስታርትአፖች፣ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ የክህሎት ኢትዮጵያ ፕሮግራም ተሳታፊዎች፣ እና የስራ ፈጠራ ባለቤቶች በተገኙበት ተካሂዷል።
በውይይቱ ላይ የቴክኖሎጂ ማምረትና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ሃላፊ ኢንጂነር ገዛኢ መብራቱ፣ የነጻ ትሬዲንግ መስራች ኢንጂነር ብሩክ አዲስ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የታገዘ የSSB ካምፓኒ መስራቾችና የክህሎት ኢትዮጵያ አባላት ኢንጂነር ካሳ ደጀኔ እና ባለቤቱ ኢንጂነር ወ/ሮ ሰብለወንጌል ተስፉ ተሞክሯቸውን ለታዳሚው አቅርበዋል።
ኢንጂነር ገዛኢ በገለጻቸው እንደተናገሩት በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት ውስጥ የክህሎት ክፍተት አለ። ይህንን ችግር ለመቅረፍ አጫጭር እና በረጅም ጊዜ በሚሰጡ የስልጠና መርሃ ግብሮች ተጠናክረው ቀጥለዋል።
የአገር ውስጥ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ለማስፋት ኢንዱስትሪ 4.0 ላይ በደንብ ቢሰራ ከተለዋዋጩ የዓለም የቴክኖሎጂ ፈጠራ ጋር ለመስማማት ያስችላል ብለዋል።
ኢትዮጰያዊያን ርስበርሳቸው ተባብረው መስራት ቢችሉ ከውጭ የሚመጡ ቴክኖሎጂዎችን ማስቀረት እንደሚቻል የገለጹት ደግሞ የስራ ፈጣሪዎች ናቸው።
ፓናሊስቶቹ፣ አገር ውስጥ የተፈጠሩ የቴክኖሎጂ ምርቶችን አምኖ ለመግዛት ዜጎች የሚያሳዩት እምነት ማጣት መሻሻል ቢያሳይም አለመቀረፉን አንስተዋል።
የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች ጥራት ያላቸውን ፈጠራዎችን እንዲያፈልቁ ቀድሞ የተፈጠሩ ምርቶችን አድንቆ በመግዛት ማበረታታት ቢቻል እና የመንግስት አስገዳጅ ደንብ ቢታከልበት ውጤቱ የኢትዮጵያን ፈጠራ ያልቃል ብለዋል።
ኢንጂነሮቹ ባላፉባቸው የስራ ተሞክሯቸው ላይ ያጋጠማቸውን ተግዳሮቶች እንዴት እንደተሻገሩና ከታዳሚያን ለተነሱ ሌሎች ጥቄዎች ማብራሪያ ያሰጥተዋል።
Telegram; https://t.me/fdretvtinstitute
Website: https://www.ftveti.edu.et/
Youtube ;
https://www.youtube.com/fdretvtinstitute
Tiktok; www.tiktok.com/
Twitter (X); https://x.com/FDRETVTI
WhatsApp: https://whatsapp.com/channel/0029Vb73e9cGOj9ooFTo2u1R