29/03/2025
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1446 ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኮሚሽን የወራቤ ማረሚያ ተቋም ኃላፊ ኮማንደር አወል ሁሴን ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች፤ በማረሚያ ተቋማት ለሚገኙ የፓሊስ አባላት፤ሲቪል ሠራተኞች እና የህግ ታራሚዎች በሙሉ እንኳን ለ1446 ኛው ኢድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የእስልምና እምነት ተከታዮች በዓሉን ሲያከብሩ እርስ በእርሱ በመደጋገፍ እና በመተባበር አብሮነትን በማጠናከር ሊሆን እንደሚገባ ኮማንደሩ ተናግረዋል።
የኢድ አል ፈጥር በዓል ሲከብር የተቸገሩ ወገኖችን በማብላት፤በማጠጣት የተለመደ የመተዛዘንና የመረዳዳት ባህሉን ፍቅሩን በማዳበር እንዲሁም የህግ ታራሚዎች በመጠየቅ በመተሳሰብ ማክበር እንዳለበት ጥሪ አቅርበዋል።