Addis Ketema W11 CRRSA

Addis Ketema W11 CRRSA Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ketema W11 CRRSA, Government Organization, Addis Ababa.

‎በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ  ስልጠና እና የንቅናቄ  መድረክ ተካሄደ ‎‎ADDIS KETEMA W11 CRRSA:  መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ‎‎የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወ...
08/04/2026

‎በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እና የንቅናቄ መድረክ ተካሄደ

‎ADDIS KETEMA W11 CRRSA: መጋቢት 30/2018 ዓ.ም

‎የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ ላይ በተዘጋጀ የንቅናቄ ሰነድ ዙሪያ ከጽ/ቤቱ ሰራተኞች ጋር ውይይት አድርጓል፡፡

‎የጽ/ቤቱ የኩነት ዘርፍ ቡድን መሪ አቶ እዮብ ወ/አማኑኤል የንቅናቄ መድርኩን ዓላማ፣የአገልግሎትና አሰጣጥ ጽንሰ-ሀሳብ፣ ለአገልግሎት አሰጣጡ ምቹ ሁኔታ ከመፍጠር አንጻር፣የአገልግሎት ሰጪውና ተቀባዩ መብትና ግዴታዎች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

‎አገልግሎት እውቀትን እና ሙያን መሰረት አድርጎ የተገልጋይን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረግ ጥረት ነው ያሉት አቶ እዮብ የተገልጋይን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ዓላማ ተኮር ተግባር የሚሰጡ አገልግሎቶች ስኬታማና ኢኮኖሚያዊ ቅልጥፍናን በተላበሰ መልኩ የሚከናወን በጊዜ፣ በመጠን፣ በጥራትና በወጪ የሚለካ፣የተገልጋይ እርካታ ሊለኩ የሚችሉ፣ በአገልግሎት ተቀባዩ ዘንድ እሴት የሚጨምሩ መሆን እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

‎መዲናችን አዲስ አበባ የያዘችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ በማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት አቶ እዮብ መንግስት ያወጣቸውን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እና ፕሮግራሞች በመፈፀምና በማስፈፀም ረገድ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሚና የማይተካ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‎በየደረጃው የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመለየት መፍታት፣ለተገልጋዩ ማህበረሰብ እና ለአገልግሎት አቅራቢው ተቋም መብትና ግዴታ ዙሪያ ግንዛቤ ለመፍጠር፣የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጣቸው እንዲሻሻል በማድረግ የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ የሰነዱ ዋና ዓላማ መሆኑን አቶ እዮብ አስረድተዋል፡፡

‎የጽ/ቤቱ ሰራተኞች ደንበኞችን በቅንነት በታማኝነትና በትጋት በማገልገል የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባ በመድረኩ መልዕክት ተላልፏል፡፡

‎***
‎👉አዲስ ከተማ ወረዳ 11 የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት

‎ለበለጠ መረጃ:

‎✅ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=61563255924975

‎✅ቴሌግራም(Telegram):https://t.me/addisketemaw11crrsa

‎✅ቲክቶክ(Tiktok):https://www.tiktok.com/.ketema.were?_t=ZM-8zVfRON9tuo&_r=1

‎✅ኢንስታግራም(Instagram):https://www.instagram.com/addis_k_wereda11_crrsa_office/

‎✅ትዊተር(Twitter):https://x.com/AdA_K_W11_CRRSA?t=6s06OHhfEvSQefw8JA0y_w&s=35




አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ  የወረዳው ነዋሪዎች በተገኙበት የእንጠያየቅ መድረክ አካሄደ።በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ከወረዳው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግ...
09/11/2025

አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የወረዳው ነዋሪዎች በተገኙበት የእንጠያየቅ መድረክ አካሄደ።

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ከወረዳው የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ጋር የወረዳው ነዋሪ በተገኙበት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የእንጠያየቅ መድረክ በዛሬው ዕለት አካሄደ።

በመድረኩም በርካታ ሀሳቦች የተነሱ ሲሆን በጽ/ቤቱ ዙሪያ ለተነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥያቄዎች የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ተፈሪ ምላሽና ማብራራያ ሰጥተዋል።

የወረዳው ኮሙንኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ህይወት ወንድሙ እንደገለፁት የዛሬ መድረክ አጠቃላይ በወረዳው ላሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል እንዲሁም የግልፀኝነት ክፍተቶችን የሚሞላ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በመግለፅ የእንጠያየቅ መድረኮች በቀጣይ የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል ።

በመጨረሻም በእንጠያየቅ መድረክ መዘጋጀቱ ለችግሮቻችን የጋራ መፍትሄን እንድናበጅ ያስችላል ሲሉ ነዋሪዎች የገለፁ ሲሆን የሲቪል ምዝገባ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚሰሩ ተግባራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥሉ በመድረኩ ላይ መግባባት ተፈጥሯል።

ጥቅምት 29/02/2018

'ከተቋም ሪፎርም እምርታ ወደ ላቀ አገልግሎት ከፍታ''በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ነዋሪ የተሳፈበት ከተቋም ሪፎርም እምርታ ወደ ላቀ አ...
09/11/2025

'ከተቋም ሪፎርም እምርታ ወደ ላቀ አገልግሎት ከፍታ''

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ጽ/ቤት ነዋሪ የተሳፈበት ከተቋም ሪፎርም እምርታ ወደ ላቀ አገልግሎት ከፍታ ላይ የህዝብ መድረክ አካሄደ።

መድረኩን የመሩት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ምክትልና ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ጀማል ሂያር መድረኩ ማዘጋጀት ያሰፈለገበት ዋነኛ አላማው በወረዳ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል እና ችግሮችን በጋራ ለመፈታት ያስችል ዘንድ ነው ሲሉ ገልፀዋል።

የወረዳው ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ተፈሪ እስካሁን በሪፎርም ሂደት ያሳካናቸዉ ለዉጦችና ቀሪ የአገልግሎት አሰጣጥ እና የብልሹ አሰራር ጉለቶች ላይ የተደረገ ባለሙያዉ እና ሀላፊዎች ባሉበት በቀጥታ የፊት ለፊት ጥያቄ የቀረበበት የእንጠያየቅ መድረክ ነው። ህብረተሰቡም በቀጣይ ለተቋሙ ቀጣይነት ያለዉ ሪፎርም ባለቤት ሆኖ በጋራ መግባባትን ለመፍጠር ያለመ መድረክ ነዉ በመድረኩ የተገልጋይ የማህበረሰብ ቀጥተኛ ተሳትፎ የሚረጋገጥበት የመማክርት አባላት መረጣ እና በብልሹ አሰራር እና በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ቀጥታ ጥቆማ የሚያደርሱበት የአስተያየት መስጫ ስርአት የተዘረጋበት መድረክ መሆኑን የሚያመላክት መድረክ ነው ብለዋል።

በመጨረሻ በህዝብ መድረኩ የተነሱ ጥያቄዎችን ወደ ተግባር በመቀየር በቀጣይ የሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ፅ/ቤት የተሻሉ ሰራዎችን በጋራ ለመሰራት በመግባባትና 35 አባላትን የያዘ የመማክርት ጉባኤ በማቋቋም መድረኩ ተጠናቋል።

ጥቅምት 29/2018

የሰኞ ማለዳ ወርቃማው ሰኞ “የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ፡፡‎‎መስከረም 05/2018 ዓ.ም፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ  ወረዳ 11 ሲቪል...
15/09/2025

የሰኞ ማለዳ ወርቃማው ሰኞ “የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው” በሚል ርዕስ ውይይት ተካሄደ፡፡

‎መስከረም 05/2018 ዓ.ም፡- አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት ሰራተኞች “የህዳሴ ግድባችን የኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት ነው” በሚል ርዕስ የሰኞ ማለዳ የእውቀት ሽግግር መድረክ ተካሂዷል፡፡

‎በውይይት ሰነዱ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅን አስመልክቶ የግድቡ እንደምታዎችን ለሀገሪቱ ህዳሴ፣ ለተፋሰሱ እና ቀጠናዊ ትስስር እንዲሁም ለአፍሪካ ትንሳኤ የሚኖረው ሚና በዝርዝር ቀርቧል፡፡

‎ባለሙያዎቹ ግድቡ ለሀገሪቱ ብሎም ለዜጎች ያለዉን ሰፊ ጠቀሜታ አንስተዋል።

‎ መስከረም 5/1/2018 ዓ.ም

‎ለበለጠ መረጃ:

‎✅ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=61563255924975

‎✅ቴሌግራም(Telegram):https://t.me/addisketemaw11crrsa

‎✅ዩትዩብ(YouTube):https://youtube.com/?si=qiU91pnKULzUOP0k

‎✅ቲክቶክ(Tiktok):https://www.tiktok.com/.ketema.were?_t=ZM-8zVfRON9tuo&_r=1

‎✅ኢንስታግራም(Instagram):https://www.instagram.com/addis_k_wereda11_crrsa_office/

‎✅ትዊተር(Twitter):https://x.com/AdA_K_W11_CRRSA?t=6s06OHhfEvSQefw8JA0y_w&s=35

‎‎ነገ ማለትም ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም የእምርታ ቀንን ምክኒያት በማድረግ   " እምርታ ለዘላቂ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የተቋማችንን የድጅታል ሪፎርም እምርታ ለተገልጋዩ እና ለተጋባዥ እንግ...
07/09/2025


‎ነገ ማለትም ጳጉሜ 3/2017 ዓ.ም የእምርታ ቀንን ምክኒያት በማድረግ " እምርታ ለዘላቂ ከፍታ " በሚል መሪ ቃል የተቋማችንን የድጅታል ሪፎርም እምርታ ለተገልጋዩ እና ለተጋባዥ እንግዶች በማሳየት እንደምከበር ተገልጿል።

‎በተቋማችን የምንሰጣቸው አግልግሎቶች በቴክኖሎጂ የተደገፈ በመሆኑ በዲጂታሉ ዘርፍ የተገኙ እምርታ በአካል ምልከታ እና ቀደም ብሎ በክ/ከተማ በartificial intelligence የተዘጋጀ የድጅታል ሪፎርሙን የሚቃኝ ቪድዎ ፤ ለተገልጋዩ ህብረተሰብና ተጋባዥ እንግዶችን በቀጥታ በቲቪ እንድታይ ይደረጋል።

‎በተጫማሪም ቀድሞ የተለዩ ማንዋል የሚፈልጉ የአልጋ ቁራኛ የሆኑ ተገልጋይዎችን በእለቱ የቤት ለቤት አገልግሎት በመስጠት እንደሚከበር የወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባና ነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የሆኑት አቶ ቶሎሳ ተፈሪ ገልጸዋል ።

‎✅ፌስቡክ(Facebook):https://www.facebook.com/profile.php?id=61563255924975

‎✅ቴሌግራም(Telegram):https://t.me/addisketemaw11crrsa

‎✅ዩትዩብ(YouTube):https://youtube.com/?si=qiU91pnKULzUOP0k

‎✅ቲክቶክ(Tiktok):https://www.tiktok.com/.ketema.were?_t=ZM-8zVfRON9tuo&_r=1

‎✅ኢንስታግራም(Instagram):https://www.instagram.com/addis_k_wereda11_crrsa_office/

‎✅ትዊተር(Twitter):https://x.com/AdA_K_W11_CRRSA?t=6s06OHhfEvSQefw8JA0y_w&s=35

ከ2800 በላይ ተማሪዎች ለልደት ሰርቲፊኬት ተመዝግበዋል‎‎Woreda 11 CRRSA: ነሐሴ25 /2017ዓ.ም‎አዲስ አበባ‎‎ከሐምሌ ወር ጀምሮ 2890 ተማሪዎች የልደት ሰርቲፊኬት ለማወጣት መ...
31/08/2025

ከ2800 በላይ ተማሪዎች ለልደት ሰርቲፊኬት ተመዝግበዋል

‎Woreda 11 CRRSA: ነሐሴ25 /2017ዓ.ም
‎አዲስ አበባ

‎ከሐምሌ ወር ጀምሮ 2890 ተማሪዎች የልደት ሰርቲፊኬት ለማወጣት መመዝገባቸውን የወረዳ 11 የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡

‎የጽ/ቤቱ ሃላፊ አቶ ቶሎሳ ተፈሪ እንደገለፁት ከአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 11 ትምህርት ጽ/ቤት ጋር በቅንጅት በመሰራት ከሀምሌ ወር ጀምሮ እስከ ነሃሴ 24/2017 ድረስ ብቻ 2890 ተማሪዎች የልደት ሰርተፊኬት ለማውጣት መመዝገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

‎የልደት ሰርቲፊኬት ለትምህርት እንደ ቅድመ ሁኔታ መቀመጡን የገለፁት አቶ ቶሎሳ ይህም ለምዝገባው ቁጥር መጨመር አወንታዊ ሚና መጨወቱን እና በወረዳ ደረጃ ለሚደረገው የኩነት ምዝገባ መደላድል እየፈጠረ መሆኑን በመግለፅ የቅንጅት ስራውም ውጤታማ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

‎የልደት ሰርቲፊኬት ማውጣት ለልጆች መብት ሲሆን ለወላጆች ደግሞ ግደታ ነው ያሉት የጽ/ቤቱ ኃላፊ የልደት ምስክር ወረቀት ማንነትንና ዜግነትን ለማረጋገጥ፣ ዕድሜን መሰረት ያደረገ የጤና እና ማህበራዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት፣ በትክክለኛ ዕድሜ ትምህርት ለመጀመር፣የንብረት ወራሽነት መብትን ለማስከበር፣የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን ለመከላከል፣መደበኛ ስራን በህግ በተፈቀደው የመስሪያ ዕድሜ ለመጀመር፣ የማሽከርከር ፍቃድ ለማግኘት፣ፓስፖርት ለማውጣት፣የባንክ አካውንት ለመክፈት እና ሌሎች በርካታ ጠቀሜታዎች ያሉት በመሆኑ ወላጆች ለልጆቻቸው በወቅቱ የልደት ሰርቲፊኬት ማውጣት እንዳለባቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‎ለበለጠ መረጃ

‎ዌብ ሳይት (website): https://www.aacrrsa.gov.et

‎ቴሌግራም (Telegram): https://t.me/addisketemaw11crrsa

የውጤት ዜና‎በአዲስ ከ/ክ/ከተማ የወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት ምዘና  ከክፍለ ከተማ ስር ካሉት 12ቱ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አ...
05/08/2025

የውጤት ዜና
‎በአዲስ ከ/ክ/ከተማ የወረዳ 11 ሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት ምዘና ከክፍለ ከተማ ስር ካሉት 12ቱ የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ጽ/ቤት በጤና ተቋማት ወቅታዊ ምዝገባ ተወዳድሮ 3ኛ በመውጣት የሠርተፊኬት ተሸላሚ ሢሆን በ2017 በተቋም አጠቃላይ ምዘና ደግሞ ከ12ቱ ወረዳዎች ጋር ተወዳድሮ 3ኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆኗል።ወረዳ 11 በሁለቱም የውድድር ዘርፎች ተሸላሚ መሆኑ ልዩ ያደርጓል። እንኳን ደስ አላችሁ

በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ የአረንጓዴ አሻራ  መርሀ ግብር ላይ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ መርሀ ግብር ተካሄደ።የክፍለ ከተማው ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅህፈት ቤት ...
22/05/2025

በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ላይ የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ መርሀ ግብር ተካሄደ።

የክፍለ ከተማው ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅህፈት ቤት ከወረዳው የከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ፅ/ቤት አስተባባሪነት በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ፣ ሰራተኞች ፣ የወረዳው ነዋሪዎች ፣ የልማታዊ ሴፍትኔት ተጠቃሚዎች በተገኙበት ''የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትዉልድ'' በሚል መሪ ቃል በ2016/17 በአረንጓዴ አሻራ የተተከሉ ችግኞችን እንክብካቤና ለ7ኛ የአረንጓዴ አሻራ ጉድጓድ ቁፋሮ ቅድመ ዝግጅት መርሀ ግብር በወረዳ 11 ዘላቂ ማረፊያ አካባቢ በዛሬው እለት ተካሂዷል።

የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው የክፍለ ከተማው ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅ/ቤት ሀላፊ የሺድንበር አማረ በችግኝ ተከላው ከፍተኛ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው ፣ የተተከሉትን ችግኞች ለመንከባከብና ለማሳደግ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

የተካሔደው የተተከሉ ችግኞች እንክብካቤም ከተማዋን አረንጓዴ በማድረግ ለአካባቢ ጥበቃና ለዜጎች ጤናማ ኑሮ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እንደሚጠበቅም አንስተዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይም የክፍለ ከተማው ሲቪል ምዝገባና ነዋሪዎች አገልግሎት ፅ/ቤት በስድስተኛው ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብና የማሳደግ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑ ተገልዷል።

ግንቦት 14/2017 ዓ.ም

14/05/2025

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30
Saturday 08:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ketema W11 CRRSA posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share