05/06/2026
በዲጂታል ፋይናንስ ወንጀሎች ዙሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ዎርክሾፕ በዛሬዉ እለት ተጀመረ።
**********
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በመተባበር “Combating Digital Banking Fraud: The Way Forward for Effective Prevention and Enforcement." በሚል ርዕስ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ዎርክሾፕ በዛሬዉ እለት ተጀመረ።
በ ዎርክሾፑ መክፈቻ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክብርት ወ/ሮ ሌሊሴ ደሳለኝ ፣ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ፋዓድ ኪያር ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት አጠቃላይ አገልግሎቶች ስራ አስፈፃሚ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በመገኘት የመክፈቻ ንግግሮች ያደረጉ ሲሆን የፌደራል የከፍተኛ እና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች ፣ ዐቃቢያን ህጐች እና የባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እየተሳተፋ ይገኛሉ ።
ለሁለት ቀናት በሚቆየዉ ዎርክሾፕ "Understanding Digital Banking Business, Combating Digital Banking Crimes - Legal and Regulatory Perspectives, Fraud Awareness and Cyber Security, Digital Banking Frauds in Financial Sector በሚሉ ርዕሶች ላይ ፁሁፎች ቀርበዉ ዉይይት የሚደረግባቸዉ ይሆናል።