18/09/2019
የፓስፖርት እድሳትን እና አዲስ ፓስፖርት ማውጣትን በሚመለከት በውስጥ መልእክት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እየደረሱን በመሆኑ ጠቅለል አድርገን ምላሽ ለመስጠት ወደናል፡፡
አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት
የሚያስፈልጉት የልደት ምስክር ወረቀት እና የአገልግሎት ጊዜው ያላለቀ የቀበሌ መታወቂያ ብቻ ሲሆኑ ምንም አይነት ተጨማሪ ማስረጃ አያስፈልግም፡፡የሚወስደው ጊዜ ከአመለከቱ በኋላ 2 ወር፡፡
ሆኖም በተለያዩ አስገዳጅ ምክንያቶች ፓስፖርት በአስቸኳይ ማግኘት ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ጉዳዩን አስቸኳይነት የሚያሳዩ ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ፡፡
ጉዳዩ የስራ ከሆነ ከመስሪያቤት የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤ እና የመስሪያ ቤቱ መታወቂያ
ዲቪ
የህክምና ወረቀት(ሪፈር)
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር መኖሪያ ፍቃድ
ጊዜ ያለው የውጪ ሃገር የስራ ፍቃድ
የኢምባሲ ቀጠሮ
ተመላላሽ መንገደኞች ሆነው ፓስፖርት ገፁ ያለቀባቸው ፓስፖርቱን ይዞ መቅረብ
የአለም አቀፍ ድርጅቶች
ጊዜ ያለው የባህረኞች መታወቂያ (ሲማንቡክ)
ሆነው የሁሉም አገልግሎቶች አከፋፈል ሁኔታ እንደአገልግሎቶ የተለያየ ነው፡፡
ለፓስፖርት እድሳት
የቀበሌ መታወቂያ እና ፓስፖርት ኮፒ
የጠፋ ፓስፖርት የቀበሌ መታወቂያ እና የፖሊስ ማስረጃ
ስለሆነም ማንኛውም ዜጋ እነዚህን ቅድመ ሁኔታዎች አሟልቶ ከቀረበ አገልግሎቱን የማግኘት ሙሉ መብት እንዳለው እየገለፅን በአገልግሎታችን ላይ ለሚኖራችሁ አስተያየትም ሆነ ቅሬት በውስጥ መልእክታችን (inbox) እንድታደርሱን እንጠይቃለን