የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ, Government Organization, Mexico, Addis Ababa.

19/08/2026
‎መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ‎*******************************‎ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ተ...
06/08/2026

‎መንግሥት ሌብነትን እና ሕገወጥነትን ለመከላከል ጠንካራ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን አስታወቀ
‎*******************************
‎ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ተግባራዊ እየተደረገ ያለውን ሰፊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማደናቀፍ በሚንቀሳቀሱ እና የሀገር ሀብት በሚመዘብሩ አካላት ላይ መንግሥት የማያዳግም እርምጃ እየወሰደ መሆኑን የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት አስታውቋል።

‎​የኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ እናትዓለም መለሰ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የልማት ጉዞው አልጋ በአልጋ እንዳልነበር ገልጸው ሕገ-ወጥነትና የሙስና ተግባራት ከውስጥም ከውጪም ተደራጅተው የልማቱ ዋና ፈተና ሆነው መቆየታቸውን አብራርተዋል።

‎​እንደ ክብርት ሚኒስትሯ ገለጻ እነዚህ አካላት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ከቁጥጥር ውጭ ለማድረግ በፋይናንስ እና በንግድ ሥርዓቱ ውስጥ ሰርገው በመግባት የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የዋጋ ንረት፣ ኮንትሮባንድ እና ሰው ሠራሽ የፍጆታ እቃዎች እጥረት እንዲባባስ አድርገዋል።

‎​የሚመለከታቸው የሕግ አካላት ባከናወኑት ሰፊ ኦፕሬሽን ይህንን የተደራጀ አሻጥር ማክሸፍ መቻሉ የተገለፀ ሲሆን በመንግሥት አገልግሎት ሰጪ እና አስተዳደር አካላት እንዲሁም የሕዝብ ተቋማት ውስጥ የተሰገሰጉ ሌቦችን በማጽዳት በቁልፍ ዘርፎች ላይ ሰፊ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት መስፈኑ ተመላክቷል።

‎​በዚህም መሠረታዊ የፍጆታ ምርቶችን በማከማቸት እጥረት እንዲፈጠር በማድረጋቸው በ13 አቅራቢ ድርጅቶች ላይ ማስጠንቀቂያ የተሰጠ ሲሆን፣ ከ7 ሺህ በላይ ሕገ-ወጥ የንግድ ድርጅቶችና መጋዘኖች፣ 169 በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር የተሳተፉ ግለሰቦች፣ 38 የቤቲንግ ድርጅቶች እንዲሁም 183 በኮንትሮባንድ ወንጀል የተሳተፉ አካላት ላይ ሕጋዊ እርምጃ መወሰዱ ተገልጿል።

‎​ክብርት ሚኒስትሯ መንግሥት የልማት እንቅፋት የሆኑትን ሙስና እና ሌብነት ዘመናዊ አሠራሮችን በመዘርጋት በከፍተኛ ትኩረት እየተከላከለ መሆኑን አረጋግጠው ከእነዚህ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ ሕዝቡ የሚያነሣቸውን ጥያቄዎች ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ማኅበረሰቡ ሙስናን በማጋለጥ ከመንግሥት ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።


የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዑክ በዓለም አቀፍ የፀረ-ሽብር ሴሚናር ላይ ተሳተፈ************************************************************ ሐምሌ 29 ቀን ...
05/08/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ልዑክ በዓለም አቀፍ የፀረ-ሽብር ሴሚናር ላይ ተሳተፈ
************************************************************
ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም
በክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል ርስቱ ይርዳው የተመራ ልዑክ በቻይና ዋይኒንግ ከተማ ከሐምሌ 27 እስከ 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ዓለም አቀፍ የፀረ-ሽብር ሴሚናር (International Counterterrorism Seminar) ላይ ተሳትፏል።
ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ በሰሚናሩ ላይ ባስተላለፉት መልእክት፣ ሽብርተኝነት ድንበር ዘለልና ዓለም አቀፍ አድማሱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን እንዲሁም አሁን ያለው ፈጣን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት በተለይም የሰው ሰራሽ አስተውሎት (artificial intllgence) በሽብርተኞች ዘንድ ለጥፋት ማቀጃ፣ ለገንዘብ ማሰባሰቢያ፣ ለአባላት መመልመያና ጥቃቶችን በከፍተኛ ፍጥነትና ስፋት ለማስፈጸሚያነት መሣሪያ እየሆነ መምጣቱን ገልፀዋል።
ሽብርተኝነት ከጊዜ ወደ ጊዜ ውስብስብና እየተቀያየረ የመጣ የደህንነት ስጋት በመሆኑ በሕግ አስከባሪ አካላት እና በአጠቃላይ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ደኅንነት ላይ ከፍተኛ ፈተና ደቅኗል ሲሉ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ገልፀዋል።
አንድ ሀገር በብቸኝነት ሽብርተኝነትን መግታት ስለማይችል የዓለም አቀፍ ትብብርን የሚጠይቅ በመሆኑ በቴክኖሎጅ የታገዘ የፀረ-ሽብር እርምጃን መውሰድ፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥን እና የተቀናጀ የድንበር ደኅንነት አሠራርን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ በመግለፅ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በፀረ-ሽብር ትግል ግንባር ቀደም ሀገር መሆኗንና በዚህ ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ማካበቷን ተናግረው ይህንን ልምድ ለአጋር ሀገራት ለማካፈል ቁርጠኛ መሆኗን አብራርተዋል፡፡
አያይዘውም የዚህ አይነት ሴሚናሮች በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ተማራማሪዎችን፣ መሪዎችንና ፈፃሚዎችን በማገናኘት የምርምር ውጤቶችን፣ ልምድን እና መልካም ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ያላቸው ፋይዳ የጎላ መሆኑን አንስተው፤ በባለሙያዎችና አመራሮች ዘንድ ሙያዊ ግንኙነት (Professional Network) በመፍጠር ለፈጣን የመረጃ ልውውጥና ውጤታማ የሽብር መከላከልና መቆጣጠር ሥራ መደላድል እንደሚፈጥሩም ጠቁመዋል።
በመጨረሻም ቻይና ለኢትዮጵያ መንግስት እና በተለይም ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በፀረ-ሽብርተኝነት፣ በደህንነት እና በሕግ ማስከበር ዙርያ ለምታደርገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፣ ትብብሩ በቀጣይ ወደ ስትራቴጂክ ደረጃ እንደሚሸጋገር ያላቸውን እምነትም ገልጸዋል፡፡

"የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል" የኢትዮጵያ ፌደራል...
03/08/2026

"የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል" የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ ኣዛዥ
********************************
ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጠቅላይ ኣዛዥ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመላው ሀገራችን በተሳተፈባቸው ቦታዎች ሁሉ እየተከለ ይገኛል ያሉት በዛሬው ዕለት በጋራ ተስፋን እንትከል በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ነው ።
ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሀገራችንን ሰላምና ደህንነት ከማስከበር ጎን ለጎን የሀገራችንን ልማት ለማፋጠን የራሱን አሻራ እያስቀመጠ ይገኛል ብለዋል ።
በዚህም በጋራ ተስፋን እንትከል በሚል መርሃ ግብር ዛሬ በመላው ሀገራችን የሚገኙ የፖሊስ አመራርና አባላት ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ሆነው መትከላቸውን ገልጸዋል።
ሰንዳፋ በሚገኘው የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በወንጀል ምርመራ አካዳሚ ውስጥ ተገኝተን ዛሬ በጋራ ችግኝ ተክለናል ያሉት ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተከታትሎ እንዲጸድቅ አስፈላጊውን እንክብካቤና ክትትል ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በተለይ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታችሁ ጊዜ የተከልነውን ችግኝ በቅርበት እየተከታተላችሁ እንድታጸድቁ በዚህ አጋጣሚ አደራ ለማለት እወዳለሁ ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከዋና መምሪያ፤ ከምክትል ዋና መምሪያና ከመምሪያዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ተፈራረመ***************ሐምሌ 14 ቀን ...
21/07/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከዋና መምሪያ፤ ከምክትል ዋና መምሪያና ከመምሪያዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ተፈራረመ
***************
ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከዋና መምሪያ፤ ከምክትል ዋና መምሪያና ከመምሪያዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ተፈራርሞ ወደ ሥራ ገብቷል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርስቱ ይርዳው በፊርማ ሥነ- ሥርዓቱ ላይ በሰጡት የስራ መመሪያ ጠቅላይ መምሪያው በ2018 በጀት ዓመት በርካታ ስኬታማ እና ሀገርን የሚያኮራ የምርመራ ስራ የተሰራበት አመት እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ በ2018 በጀት ዓመት ሀገራችን 7ተኛውን ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ለማደናቀፍ የሞት ሽረት አድርገው የተነሱ የሀገራችን ስትራቴጂክ ጠላቶች ተልእኮ ተቀብለው የሽብር ተግባር ለመፈፀም ሲሰሩ ተላላኪ ባንዳዎች ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሽብር መረባቸውን በመበጣጠስ የሽብር ቡድኖቹ አባላትን በመቆጣጠር ምርመራዎችን በማደራጀት ለህግ በማቅረብ እኩሪ ተግባር መፈፀሙ ጠቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በ2018 በጀት አመት አቅሙን በቴክኖሎጂ እያሳደገ በመምጣቱ በምርመራ ስራዎቹ በተለያዩ ሀገራዊ፣ አህጉራዊና አለማቀፋዊ የምርመራ ስራዎችን በተለይም ከኢትዮጵያ እስከ አውሮፓ ያለውን እንዲሁም ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሚካሄደው ህገወጥ የሰዎች ዝውውር መስመር ላይ በዜጎቻችን ላይ እጅግ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ተጠርጣሪዎችን በመቆጣጠርና የምርመራ መዝገቦች በማደራጀት ለህግ እንዲቀርቡ መደረጉ ገልፀዋል፡፡
በኢኮኖሚ ረገድ ሀገር ላይ ሊደርሱ የነበሩ በርካታ የምርመራ ስራዎች የተሰሩ መሆኑንና የሀገርን እድገት የሚገቱ ትልልቅ የኢኮኖሚ ወንጀሎችን በመመርመር ሀገራዊ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን በታቀደው ደረጃ ውጤታማ ሆኖ እንዲሄድ የወንጀል ምርመራ ዘርፉ ውጤታማ ስራ መስራቱ ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ገልፀዋል፡፡
በ2019 በጀት ዓመትም የወንጀል ፍትህ ስርዓቱን የተቀላጠፈና ውጤታማ ለማድረግ በዋናነት የመመርመር አቅማችንን፣ የቴክኖሎጂና የሎጂስቲክስ አቅማችንን ለማጠናከር ስትራቴጂክና ከፍተኛ አመራሩ ያለውን የካበተ ልምድና ዕውቀት ተጠቅሞ ሠራዊቱ የበለጠ ተልዕኮውን እንዲፈፅም ለማድረግ ዕቅዱን እስከታችኛው ፈጻሚ ድረስ በማውረድና በቅንጅት በመምራት የህዝባችንን ሰላምና ደህንነት የበለጠ በማረጋገጥ የሃገራችንን ልማትና ዕድገት ለማፋጠን በተሻለ ድሲፕሊንና ሀላፊነት ከተጠያቂነት ጋር መስራት ይኖርበታል ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ክቡር ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል በጠቅላይ መምሪያው ከሚገኙ ከኦፕሬሽን ዋና መምሪያ፣ ከአስተዳደርና ድጋፍ አገልግሎት ም/ዋና መምሪያ እና ከጠቅላይ መምሪያው ፅ/ቤት ኃላፊዎች ጋር የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድን ተፈራርመዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመሐመድ ጣሂር አደን (ወርዲ) የሚመሩ 17 አደገኛ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ መዝገብ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለፍትሕ ሚኒስቴር ...
21/07/2026

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በመሐመድ ጣሂር አደን (ወርዲ) የሚመሩ 17 አደገኛ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ መዝገብ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን አስታወቀ
*******************************
ሐምሌ 14 ቀን 2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በምሥራቅ ሀገራችን በኩል በጂቡቲ እና በየመን አድርገው ወደ ሳውዲ አረቢያ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ሲልኩ የቆዩና ከተጎጂዎች ከአንድ ቢሊዮን ብር በላይ የተቀበሉ፣ በአደገኛ ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪ መሐመድ ጣሂር አደን (ወርዲ) የሚመሩ የተደራጁ 17 የወንጀል ቡድን አባላትን በቁጥጥር ሥር አውሎ የምርመራ መዝገብ በሰውና በሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ባሰባሰበው የሰው እና የሰነድ ማስረጃ ተጠርጣሪዎቹ በሰው ልጅ ለመነገድ በማሰብ የወንጀል ቡድን በማደራጀት በወንጀል ድርጊቱ ውስጥ በከፍተኛ ደረጃ መሳተፋቸውን በምርመራ መዝገቡ ማጣራቱን ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ የሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መረብ በመዘርጋት፣ ተጎጂዎቹ በየመን በኩል ወደ ሳውዲ አረቢያ ገብተው የተሻለ ኑሮ እንደሚኖሩ ሐሰተኛ ተስፋ በመስጠትና በማሳመን ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች በደላሎች አማካኝነት ተጎጂዎችን በመመልመል ሲልኩ መቆየታቸውንም ፖሊስ አረጋግጧል።
በምርመራ መዝገቡ እንደተመለከተው በሕገ-ወጥ መንገድ የተወሰዱ ተጎጂዎች የኢትዮጵያን ድንበር እንደተሻገሩ ወደ የመን ተወስደው በየመን ሀገር ውስጥ በሚገኙ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጁ መጋዘኖች ታጉረው ከፍተኛ ኢሰብአዊ ድርጊቶች ይፈጸሙባቸው ነበር።
በተለይም ተጠርጣሪዎቹ ተጎጂዎችን በመያዣነት በመያዝ ወደ ቤተሰቦቻቸው ስልክ በማስደወል ከፍተኛ ገንዘብ ሲጠይቁ እንደነበር እና ገንዘብ መክፈል ላልቻሉ ቤተሰቦች ተጎጂዎችን እየደበደቡ እንዲሁም እያሰቃዩ ቪዲዮ በመቅረጽ የሥነልቦና ጫና ሲፈጥሩ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል።
በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከፍትህ ሚኒስቴር፣ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ባደረገው ጠንካራ ክትትልና ምርመራ በርካታ ከባባድ ግኝቶችን ይፋ አድርጓል።
ከእነዚህም መካከል ሕገ-ወጥ አዘዋዋሪዎቹ ከተጎጂዎች ከ1 ቢሊየን ብር በላይ በሕገ-ወጥ መንገድ መቀበላቸውን፣ ከ40,000 በላይ ሰዎችን በሕገ-ወጥ መንገድ ማዘዋወራቸውን፣ ከ60 ሰዎች በላይ ለሕልፈተ ህይወት መዳረጋቸው እንዲሁም በርካታ ሴቶች መደፈራቸው በምርመራ ተደርሶባቸዋል።
በዚህ ወንጀል ጉዳይ በርካታ ሰዎች የምስክርነት ቃላቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ከሳውዲ አረቢያ እና ከኢትዮጵያ በቀጥታ መስመር በቪዲዮ የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።
ተጠርጣሪዎቹ በሕገ-ወጥ መንገድ ያገኙትን ከፍተኛ ገንዘብ በመጠቀም በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረት ማፍራታቸውን ፖሊስ ያረጋገጠ ሲሆን በስማቸው የነበረ ቤት፣ ተሽከርካሪ እና ገንዘብ እንዲታገድ አድርጓል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን በሰው የመነገድ፣ በሕገወጥ ሀዋላ እና በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር (Money Laundering) ወንጀሎች ምርመራውን አጠናቆ ለፍትሕ ሚኒስቴር መላኩን አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችና ተባባሪዎቻቸው በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋናውን እያቀረበ፤ ኅብረተሰቡ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp)፣ 991 ነፃ የስልክ መስመር እና ሰው አልባ ፖሊስ ጣቢያ (SPS)ን በመጠቀም መረጃ በመስጠት ትብብሩን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪውን አስተላልፏል።

ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊዎች እና መርማሪዎች የወንጀል መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CRIMS) አተገባበር ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡************...
16/07/2026

ለኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊዎች እና መርማሪዎች የወንጀል መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CRIMS) አተገባበር ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጠ፡፡
**********************************************************
ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ከፍትህ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የወንጀል ምርመራ ስራዎችን ከወረቀት ወደ ዲጂታል ስርዓት ለማስገባት የወንጀል መረጃ አስተዳድር ስርዓት ለመዘርጋት ለወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊዎች እና መርማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰቷል።

በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ የኦፕሬሽን ዋና መምሪያ ኃላፊ ክቡር አቶ ሙሊሳ አብዲሳ የወንጀል መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CRIMS) በፍትሕ ሚኒስቴር፣ በፌደራል ፖሊስ እና በአዲስ አበባ ፖሊስ በጋራ የሚመራና በኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት አማካኝነት እየለማ የሚገኝ ዘመናዊ ሶፍትዌር መሆኑን የገለፁ ሲሆን፤ ኃላፊዎችና እና መርማሪ ፖሊሶች ስለ ሲስተሙ አላማ፣ አስፈላጊነት፣ የአሰራር ስነ ስርዓት፣ ይዘት፣ እንዲሁም ስለሚጠበቅባቸው ዝግጅት እና ተያያዥ ጉዳዮች ግልፅ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ክቡር አቶ ሙሊሳ አብዲሳ አያይዘውም ከሀገራችን የዲጂታል 2030 እቅድ አንጻር የመንግስት አሰራሮችን እና የህዝብ አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ስትራቴጂ መሠረት የወንጀል ፍትህ አስተዳድርም ዲጂታላይዝ እየተደረገ መሆኑም ገልፀዋል።

በመድረኩም የተቀናጀ የወንጀል መረጃ አስተዳደር ስርዓት (CRIMS) ከወንጀል ጥቆማ ጀምሮ የምርመራ፣ የዐቃቤ ሕግ ውሳኔ አሰጣጥ፣ የክስ ምስረታ፣ የፍርድ ቤት ክርክር እና የፍርድ ውሳኔን ጨምሮ የወንጀል ፍትሕ ሂደቱን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በማስደገፍ የፍትሕ ሥርዓቱን የተሳለጠ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሲስተሙ ቀደም ባለው ጊዜ ከፍተኛ ጊዜና ጉልበት ያባክን የነበረውን የማኑዋል አሰራር ሙሉ በሙሉ ወደ ወረቀት አልባ (ዲጂታል) በመቀየር ረገድ ጉልህ ሚና ይጫወታል፡፡ በተለይም መርማሪዎች ቃል በመቀበል ወቅት ከንግግር ወደ ጽሁፍ በሚቀይር ቴክኖሎጂ ታግዘው መስራት የሚሰችል፣ በዐቃቢያነ ሕግ ዘንድ የሚመነጩ መረጃዎችን በተገቢው መንገድ በመያዝ ስራቸውን ከማቀላጠፉም በላይ በወንጀል ፍትሕ አስተዳደሩ ውስጥ የሚከናወኑ ስራዎች በቅልጥፍና፣ በግልፅነት እና በተጠያቂነት ለማከናወን ትልቅ ድርሻ እንደሚኖረው ተብራርቷል፡፡

የምርመራ ኃላፊዎችና መርማሪዎች ስርአቱን ተግባራዊ ለማድረግ በአእምሮ እና በክህሎት ተገቢውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ተነስቷል፡፡ በአጀንዳው ላይ ተሳታፊዎች ሰፊ ውይይት ያካሄዱ ሲሆን፣ ስርአቱ ተጠናቆ ወደ ስራ ሲገባ ከባለሙያዎች ምን ይጠበቃል በሚለውና በቀጣይ ሂደቶች ዙሪያ ገንቢ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ተገቢው ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ የተሳተፉ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ ኃላፊዎች እና መርማሪዎች በበኩላቸው ስልጠናው ወቅቱን ያገናዘበ ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት የሚያስችል ስልጠና መሆኑን ገልጸው ሲስተሙ ስራን የሚያቀል መሆኑን ተናግረዋል።

Address

Mexico
Addis Ababa

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share