Namyohia for Individual Development
ናምዮህያ ለግለሰብ እድገት
ናምዮህያ ማለት ሁለንተናዊ ሕግ ማለት ነው ወይም Universal Law ማለት ነው።
ናምዮህያ በሚል ስያሜ በሁለንተናዊ ህግ ላይ የተመሰረተ ዩኒቨረሳል ድርጅት ነው።
አለም አዲስ ነገርን ትፈልጋለችና ናምዮህያ እነሆ ዮዳእትበር ይላል።
ዮዳእትበር አድራሽ ሌላ መንገድ ነው።
እስካሁን የመጣንበት መንገድ አላደረሰንምና ደግመን አንሄድበትም!
ናምዮህያ ለግለሰብ እድገት ይተጋል። የግለሰብ እድገት ማለት የአንድ ግለሰብ ማህበራዊ ህይወት፥ ግለሰባዊ ህይወት፥ ቤተሰባዊ ህይወት፥ ፍትህ፥ ጤንነት፥ ደህንነት፥ ገንዘብና ማንኛውም ግለሰባዊ ግዳዩ ይገ
ነባል።
አስተውል! ይገነባል እንጂ ይጠገናል አላልኩም። መጠገን አሮጌውን ማደስ ሲሆን መገንባት ግን አዲስ መመስረት ነው ምክንያቱም የአለም አሁናዊ ፖሊሲ አዲስ ነገርን ለሚፈልግ አድራሽ ሌላ መንገድን ማዘጋጀት ነው።
ለብዙ ሺህ ዘመናት በድህነትና በጉስቁልና ስንኖር በዚህም መካከል ብዙ ትውልዶች ድህነትና ጉስቁልናን ተቀባበሉትና እነሆ ዛሬ ላይም ከቀድሞው ይልቅ የከፋ መከራ ላይ እንገኛለን። ይህም የሆነበት ምክንያት ድህነትና ጉስቁልና የበረታብን ምክንያቱ ከጥንት ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣንበት አድራሽ ያልሆነ የተመሳሳይ መንገድ የጉዞ ውጤት ነው። የሚያሳዝነው ነገር በተመሳሳይ ድርጊት የተለየ ለውጥ መጠበቃችን ነው።
አሁን በቃ!
የእስካሁኑን ድንቁርናችንን መግፈፍ፥ ሞኝነታችንንም መተው አለብን።
እነሆ ዮዳእትበር “አድራሽ ሌላ መንገድ” አለ።
የመጣንበት መንገድ አላደረሰንምና ደግመን አንሄድበትም!
ናምዮህያ ዩኒቨርሳል ነው።
በዚህ ዩኒቨርሳል ድርጅት ውስጥ የችግሮች ምንጭ ይለያሉ፥ መፍትሄዎች ይቀመጠሉ፥ ተጨባጭና ተቆጣሪ ለውጦች ይታያሉ።
እኛ የቆምንበት መሬት ይጠበናል የደረስንበትም ምድር ያንሰናል ምክንያቱም እኛ ዩኒቨረሳል ነንና መስፋት፥ ማቀፍና ማሳተፍ መገለጫችን ነው። ወሰን በሌለው ዩኒቨርስ ውስጥ በላቀው አእምሮአችን በናምዮህያ መሪነት ምድራችንን አዳርሰን ዩኒቨርሱን እናስሳለን። የመጣንበትን መንገድ በዮዳእትበር ተክተን ከትቢያ ላይ ተነስተን የአለም ቁንጮ እንሆናለን ምክንያቱም ናምዮህያ የአለም ሁሉ ገዢ ነውና።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን!
በናምዮህያ መሰረት በዚህ ዩኒቨርስ ውስጥ ሕግ እንጂ ገደብ፥ ስርአት እንጂ እስራት የለም።
የትኞቹም ኃያላንና ኃይላቸው ከናምዮህያ በታች ነው።
እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን ደግሞም ዮህያዊያን እንሆናለን።
እያንዳንዱ ዮህያዊ ግለሰብ ደራሽና አድራሽ ነው።
አንዱ ዮህያዊ ግለሰብ በየትኛውም ቁጥር ከሚገለፅ ጋልሞር ህዝብ ይልቅ እሱ ክቡር ነው።
ጋልሞር ማለት ህገወጥ ወይም ፈር የለቀቀ ወይም መረን የወጣ ማለት ነው። በተጨማሪም ጋልሞር ማለት ግፍና በደልን የሚፈፅም ፍትህንም የሚያጎድል ማለት ነው። በርግጥ በማህበረሰብ ስርአት ውስጥ ሕዝብ ህገወጥ አይባልም ምክንያቱም ህዝብ እንደማእበል ስለሆነ የነበረውን ወዳልነበረ ሊቀይረው፥ ሊያወርድና ሊያፈርስ ስለሚችል ተፈርቶ ነው እንጂ በናምዮህያ መሰረት ፈሩን ለቅቆ መረን የወጣውን ህገወጥ ህዝብ ጋልሞር ማለት ትክክል ነው።
በተቃራኒው ዮህያዊነት ሕጋዊነት ሆኖ የላቀው ስብእናና ከፍተኛው ልእልና ነው። ዮህያዊ በዋናነት ለህግና ለስርአት ተገዢ ሆኖ አስተዋይና ጠያቂ ነው። አንድ ዮህያዊ ግለሰብ ህግ እንጂ ጉልበት ስርአት እንጂ አመፅ ከንቱ እንደሆነ የሚያውቅ ነው። ብዙ ዮህያዊያን ግለሰቦች ሕዝብ የሆኑ እለት እንኳን የጋልሞሮችን ጉልበት ከውቅያኖስ የሚነሳውን ማእበል ማምከን ይችላሉ።
“ናምዮህያ” በሚል መጠሪያ የተመሰረተው ኢትዮጵያዊው ዩኒቨረሳል ድርጅት የህጋዊያንን መሪነትና አሸናፊነት ያረጋግጣል። ዮህያዊነት ከፍታና ልህቀት መሆኑን ይመሰክራል።
ጉልበተኞችና የአሁኑ ኃያላኖች በገዢነትና በበላይነት የሚኖሩባት የ “Survival of the Fittest” ስርአት ጀምበሯ እየጠለቀች ነው። በምትኩ ዮህያዊያን በበላይነትና በመሪነት የሚኖሩባት “Survival of Legality” የአዲሷ አለም ስርአተ ንጋት ጮራው በናምዮህያ ፍንትው እያለ ነው።
አለም አዲስ ነገርን ትፈልጋለች እነሆ ዮዳእትበር “አድራሽ ሌላ መንገድ” በናምዮህያ