አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac

አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - AACAPRAC

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን 🇪🇹

Addis Ababa City Administration Public Recreational Areas Corporation 🇪🇹

Bulchiinsa Magaalaa Addis Ababa Korporeeshinii Bulchiinsa Iddoowwan Bashannanaa Uummataa 🇪🇹

🌐 Website
AACAPRAC.gov.et
👉FaceBook
fb.com/AACAPRAC
👉Instagram
instagram.com/AACAPRAC
👉Telegram
t.me/AACAPRAC
👉Titkok
Tiktok.com/AACAPRAC
👉YouTube
youtube.com/
👉Twitter( X )
twitter.com/AACAPRAC

20/08/2026
ቦሌ መድሀኒአለም
20/08/2026

ቦሌ መድሀኒአለም

ጽዳትና ውበት፥  ዓለምዓቀፍ ተወዳዳሪነት- አዲስ አበባ !ከተማችን አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት፥ መልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተሞሽራለች፥ ፍጹም ተቀይራለች፡፡ የከተማ ውበት ልክ መሆን...
20/08/2026

ጽዳትና ውበት፥ ዓለምዓቀፍ ተወዳዳሪነት- አዲስ አበባ !

ከተማችን አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት፥ መልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ተሞሽራለች፥ ፍጹም ተቀይራለች፡፡ የከተማ ውበት ልክ መሆን ጀምራለች፡፡

መንገዶች ሰፍተወል፡ ጨለማ የነበሩ ጐዳናዎቿ በርተዋል፡፡ የእግረኛ መንገድ ተለይቶ ተገንብቷል፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበሩ የብስክሌት መንገዶች ዛሬ የአዲስ አበባ መገለጫ መሆን ችለዋል።

ትላንት መንገዶች በመኪና ፓርኪንግ ይጨናነቁ ነበር ዛር ግን የለም፡፡ በየቦታው የመኪና ፓርኪንግ ቦታዎች ለምተዋል፡፡ የትራፊክ ፍሰቱንም እንዲሣለጥ የከተማዋ ውበት መጠበቅ ተችሏል፡፡

አዲስ አበባ 2.8% ላይ የነበረውን አረንጓዴ ሽፋኗ ወደ 24% አድጓል፡፡ ከአፍሪካ አስሩ ፅዱ ከተሞች አንዷ በመሆንም በዓለም አቀፍ ደረጃም እውቅናን አግኝታለች፡፡

አዲስ አበባ ጽዱ፡ ውብ እና መሰረተ ልማቶች የተሟሉላት ከተማ መሆን በመቻልዋ በርካታ ኮንፈረንሶች፡ ስብሰባዎችና ጎብኚዎች የማስተናገድ ብቃቷ እያደገ ፡ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ይበልጥ ጎልብቶ፣ ለኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን መላው አፍሪካውያን ዋና ከተማችን ብለው የሚጠሯት የጋራ ኩራታችን ሆናለች።

ከተማችን የነበራት 74% የጎስቋላነት ገጽታ ወደ 30% ዝቅ ማድረግ ተችሏል፡፡ በከተማችን ምንም እንኳን መሰረታዊ ለውጦችን ቢመዘገብም ዛሬም ብዙ መስራት ይጠበቃል፡፡ለዚህም በቀጣይ በጀት ዓመት የሚተገበሩ የትኩረት ማዕከል ተብለው የተለዩ ዋናዋና ተግባራት በዋናነትም ከተማችን አዲስ አበባ ለነዋሪዎች ምቹ፡ እና ዓለማቀፍ ተወደዳሪ ከተማነትዋን የሚያረጋግጡ ናቸው።

ውበት!
18/08/2026

ውበት!

አራዳ ፓርክ ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናፀፈ ነውበአዲስ አበባ ከተማ በቂ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማቅረብ ከለሙ ቦታዎች አንዱ የሆነው አራዳ ፓርክ ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቾት ብሎም ለ...
18/08/2026

አራዳ ፓርክ ለአዲስ አበባ ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናፀፈ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ በቂ የመዝናኛ ቦታዎችን ለማቅረብ ከለሙ ቦታዎች አንዱ የሆነው አራዳ ፓርክ ለከተማዋ ነዋሪዎች ምቾት ብሎም ለቱሪስት ፍሰት ትልቅ ፋይዳ ያለው ነው፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፤ አራዳ ፓርክ ለወጣቶች፣ ለአዛውንቶች፣ ለህፃናት፣ ለስፖርተኞች፣ ለነጋዴው እንዲሁም ለተማሪዎች በጠቅላላ ለሁሉም የማህበረሰብ ክፍሎች በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በከተማችን የገነባነው ውቡ የአራዳ ፓርክ ለሁሉም ማህበረሰቦች በእኩልነትና አካታች በሆነ መንገድ በነፃ የቀረበ የጋራ መገልገያ ስፍራ ነው፡፡ ፓርኩ ለበርካታ ዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠርም በላይ ቱሪዝምን በማሳደግ ለአጠቃላይ ኢኮኖሚው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታልም ነው ያሉት፡፡

የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው- ነዋሪዎችAMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ምበአዲስ አበባ የተገነ...
18/08/2026

የኮሪደር እና የወንዝ ዳር ልማቶች በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው- ነዋሪዎች

AMN- ነሐሴ 12/2018 ዓ.ም

በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች ገጽታን ከመቀየር ባለፈ በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመገንባት ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ነዋሪዎች ገለጹ።

በአዲስ አበባ ከተማ የተከናወኑ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች የከተማዋን መሠረተ ልማት ከዘመኑ ጋር በማስተሳሰር፣ የነዋሪዎችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደህንነት ማሻሻልና አረንጓዴ ቦታዎችን በማስፋፋት ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት ችለዋል።

ከተማዋን ለቱሪስቶች ማራኪ ከማድረጉም በላይ በወንዞች ዳርቻዎች ላይ የነበሩ የጎርፍ አደጋ ስጋቶችን በመቀነስ ህብረተሰቡ ንጽህናው የተጠበቀ የመኖሪያ እና መዝናኛ ስፍራዎችን እንዲያገኝ አድርጓል።

በዚህም ዘላቂ የከተማ ልማት እውን እንዲሆን በማስቻል የዜጎችን የኑሮ ጥራት ከፍ አድርጓል።

አስተያየታቸውን የሰጡ የመዲናዋ ነዋሪዎች፣ የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት ሥራ ከፍተኛ የገጽታ ግንባታ ከመፍጠሩም በላይ ሁሉንም ተጠቃሚ ማድረግ የቻለ አካታች ልማት መሆኑን ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሳይ ተስፋዬ እንደገለጹት፣ የተከናወኑት ግዙፍ የልማት ሥራዎች ለንባብ፣ ለምርምር እና ለህፃናትና ወጣቶች መዝናኛ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ነው።

በተለይም የቱሪዝም ፍሰትን በማሳደግና የውጭ ምንዛሬ ገቢን በመጨመር ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት እምነታቸውን ገልጸዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ የተገነቡት መሠረተ ልማቶች ያላቸውን ዘርፈ ብዙ ፋይዳ በመገንዘብ በባለቤትነት ስሜት ሊንከባከባቸውና ሊጠብቃቸው እንደሚገባ አንስተዋል።

አልማዝ ባሻ በበኩላቸው፣ መንግሥት በከተማዋ ያከናወናቸው የልማት ሥራዎች አዲስ አበባን ዘመናዊ፣ ጽዱ እና ለኑሮ ተስማሚ እንዳደረጓት ገልጸዋል።

ሀገር ተረካቢው ትውልድም የእረፍት ጊዜውን በመናፈሻዎችና በስፖርት ማዘውተሪያዎች የሚያሳልፍበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ጠቁመዋል።

ይህም መንግስት ለአሁን እና ለቀጣዩ ትውልድ የምትሆን ሀገር እየገነባ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

ደስታ መአረንዳ እና አዱኛ ጌትነት እንዳሉት በአዲስ አበባ አሁን ላይ የሚገባትን ውበት እና ክብር መጎናጸፍ ችላለች።

ይህ ሊሆን የቻለው በአእምሮ፣ በጤና እና በአካል የበለጸገ ትውልድን ለመፍጠር ታሳቢ ያደረጉ ሁለንተናዊ የከተማ ልማት ሥራዎች በስፋት በመሰራታቸው መሆኑን አንስተዋል።

የወንዝ ዳርቻ፣ መጽዳት ቤቶችና ቆሻሻ አወጋገድ በመስተካከሉ መጥፎ ሽታዎችን በማስቀረት ለነዋሪዎች፣ ለህፃናት፣ ለሁሉም ህብረተሰብ ክፍሎች እንዲሁም ለቱሪስቶችም ጭምር ዘመኑን የሚመጥን ከተማ ተፈጥሯል ያሉት ደግሞ ክብሩ ወልደሰንበት እና ወልዱ ግርማ ናቸው።

መንግስት ቀደም ሲል የተዘነጉ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ በጀት በመመደብ ለዜጎች የኑሮ ዘይቤ መሻሻል የሚያደርገው ቁርጠኛ አካሄድ የሚደነቅ እንደሆነ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የአረንጓዴ አሻራና የኮሪደር ልማት ለአእምሮ እፎይታና ለከተሞች አዲስ ህይወት*****************ሕይወት በውጥረትና በተደጋጋሚ እንቅስቃሴ በምትሞላበት በዚህ ዘመን፣ አእምሮ ከዕለት ተዕ...
18/08/2026

የአረንጓዴ አሻራና የኮሪደር ልማት ለአእምሮ እፎይታና ለከተሞች አዲስ ህይወት
*****************

ሕይወት በውጥረትና በተደጋጋሚ እንቅስቃሴ በምትሞላበት በዚህ ዘመን፣ አእምሮ ከዕለት ተዕለት ጫና ራሱን ለማሳረፍና ሰላምን ለማግኘት ተፈጥሯዊ መጠለያዎችን ይፈልጋል።

የአረንጓዴ አሻራ የጋራ ጥረት ውጤት የሆኑ ለምለም ስፍራዎች አካባቢን ከማስዋብ ባለፈ ሰዎች ቆም ብለው እንዲያርፉ፣ እንዲወያዩና ከዕለታዊ ጫና ለጥቂት ጊዜ እንዲርቁ አዲስ የመንፈስ እፎይታና የአእምሮ እረፍት ይሰጣሉ።

በአረንጓዴ እፅዋት ከተከበቡ መናፈሻዎች የሚገኘው ተፈጥሯዊ ጸጥታ፣ የአእዋፍ ድምፅና የአበቦች መዓዛ አእምሮን ከተወጠረበት ሁኔታ ቀስ ብሎ ወደ መረጋጋት እንዲመለስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል።

ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከተፈጥሮ ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ችግኞችን መትከል፣ ማጠጣት፣ አረም ማረምና መንከባከብ በጭንቀትና በውጥረት ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ አላቸው።

እነዚህ ትኩረትን የሚጠይቁ ተግባራት ሰውን ከዕለታዊ ሀሳቦች አርቀው በሚያደርገው የበጎ ስራ ላይ እንዲያተኩር ከማድረጋቸውም በላይ፣ ከቀላል እስከ መካከለኛ የአካል ብቃት እንቅስቃሴን ከማስገኘታቸው ጋር ተያይዞ የአንድን ተክል እድገት ከትንሽ ችግኝነት እስከ ለምለምነት ማየት የስኬትና የዓላማ ስሜትን ያጠናክራል።

ይህም ከተፈጥሮ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት በመፍጠር ለሰውነት እንቅስቃሴና ለስሜት መረጋጋት ትልቅ ድርሻ አለው።

ይህንን የተፈጥሮ እፎይታ በከተሞች ውስጥ ለማስፋፋት እየተከናወነ ያለው የኮሪደር ልማትም በከተማዋ መሃል የሚገኙ አረንጓዴ ስፍራዎችን፣ የእግረኛ መንገዶችን፣ መናፈሻዎችንና የመዝናኛ ቦታዎችን ከዘመናዊ የከተማ ልማት ጋር በማዋሃድ የነዋሪዎች ማረፊያና መገናኛ እያደረጋቸው ይገኛል።

የአረንጓዴ አሻራና የኮሪደር ልማት ተፈጥሮን የመጠበቅና ከሰው ልጅ ዕለታዊ ኑሮ ጋር የማገናኘት ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ በመሆናቸው፣ ዛሬ የተተከለው ዛፍ የነገ ጥላ፣ ዛሬ ያለማነው አረንጓዴ ስፍራ ደግሞ ነገ ሰዎች የሚገናኙበት፣ የሚያስቡበትና እፎይታ የሚያገኙበት ዘላቂ ሀብት ሆኖ የሚያገለግል ነው።

ለተጨማሪ መረጃ :-ማስፈጠሪያዉን ይጫኑ

Telgram:-

👇👇👇👇
https://t.me/addisabebagreenarea
Twitter:-

👇👇👇👇
https://twitter.com/urbanbeauty1
YouTube:-

👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UC3jdcm6b4ib7WIAfVAsmgcA
Tiktok

👇👇👇👇
https://www.tiktok.com/

Website
👇👇👇👇
https://www.aaubgdb.gov.et

የእረፍት ቀንዎትን በእንጦጦ ፓርክ ያሳልፉ!ከከተማዋ ለጥቂት ሰዓታት ወጣ ብለው፣ በተፈጥሮ ውበት፣ በልዩ የእንጦጦ እይታ፣ በንጹህ አየር የተሞላ የእረፍት ጊዜ ያሳልፉ።ከተፈጥሮ ጋር በቅርበት ...
18/08/2026

የእረፍት ቀንዎትን በእንጦጦ ፓርክ ያሳልፉ!

ከከተማዋ ለጥቂት ሰዓታት ወጣ ብለው፣ በተፈጥሮ ውበት፣ በልዩ የእንጦጦ እይታ፣ በንጹህ አየር የተሞላ የእረፍት ጊዜ ያሳልፉ።

ከተፈጥሮ ጋር በቅርበት ይተዋወቁ!
የማይረሱ የፎቶ ትዝታዎችን ይፍጠሩ!
ከቤተሰብና ከጓደኞችዎ ጋር የማይረሳ ጊዜ ያሳልፉ!
እንጦጦ ፓርክ: ተፈጥሮ፣ መዝናኛ እና የማይረሳ የእረፍት ጊዜ!

#እንጦጦፓርክ

Address

Bole
Addis Ababa
1000

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when አ.አ የህዝብ መዝናኛ ቦታዎች አስተዳደር ኮርፖሬሽን - aacaprac posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share