25/10/2025
ትምህርት ለትውልድ
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተጨባጭ ዉጤት ለማምጣት የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል።
ጥቅምት 15/2018 ዓ.ም
ኮልፌ ወረዳ 06 ኮሚኒኬሽን
በኮልፌ ወረዳ 06 የማነብርሀን 1ኛና2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2018ዓ.ም የተማሪዎችን የመማር ማስተማር ሂደትና በተማሪ ስነ ምግባር መሻሻል ዙሪያ ከተማሪ ወላጅና የትምህርት ቤት አመራር ጋር ሰፊ ውይይት ተካሄዷል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ትምህርት ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አንበሴ ነጋሽ እንደገለጹት ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ልዩ ትኩረት በመስጠት እያደረገ ያለዉ ድጋፍ አመስግነው በ2018 የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትን በትኩረት በመያዝ ብቁና የተሻለ ውጤት የሚያመጡ ተወዳዳሪ ተማሪዎችን ለማፍራት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ገልፀው፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ተጨባጭ ዉጤት ለማምጣት ተማሪዎችና የትምህርት ባለድርሻ አካላት በቅንጅት እና በቁርጠኝነት መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
የተማሪ ውጤት ለማምጣት የሁላችንም ሀላፊነት ነው በማለት በ2017 በጀት አመት ከሌላ ጊዜ የተሻለ ውጤት ማምጣት ቢቻልም በተፈለገውን ልክ ውጤት ለማምጣት ባለመቻሉ የተነሳ ለቀጣይ ይህን ችግር ለቅሞ በማውጣት ሁሉም መምህራንና የተማሪ ወላጅ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የተፈለገውን የተማሪ ውጤት ለማምጣት ከጀምሩ መስራት ይጠበቃል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ስራዎችን በማጠናከር የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ከማሻሻል አኳያ በተማሪዎች ምቹና የተሟላ የመማር ማስተማር አካባቢ ለመፍጠር ከሚሰሩ ስራዎች ብዙ የቤት ስራ መኖሩን ያሳያል ብለዋል።
ወላጆች የልጆችን የትምህርት ክትትል እና ውጤት በየጊዜው መመልከትና ፈተናቸውን ማየት እና ከወዲሁ ጅምር ላይ መስመር ማስያዝ ላይ ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው ገልፀዋ ል::