13/05/2026
ዓለም አቀፍ የሚድዋይፎች ቀንን በማስመልከት ለወላድ እናቶች ስጦታ ተበረከተላቸው
አዲስ አበባ - ግንቦት 5 - 2018 (ቅ.ጴ.ስ.ሆ)
ዘንድሮው በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ36'ኛ ጊዜ እየተከበረ የሚገኘውን የሚድዋይፎች ቀን በማስመልከት በቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ውስጥ በዕለቱ ለወለዱ እናቶች የተለያዩ ስጦታዎች ተበርክቶላቸዋል።
የሆስፒታሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም እሸቱ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የእናቶች ጤና ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል ናደው ፣ የኢትዮጵያ ሚድዋይፍ ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሜሮን ተሰማ እና ባለሙያዎች ስጦታውን ለወላድ እናቶች አበርክተዋል።
▬▬▬▬▬▬▬▬▬
"መኖራችን ለእርስዎ ነው!"
"OUR EXISTENCE IS FOR YOU!"