Addis Ababa City Manager's Office

Addis Ababa City Manager's Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Addis Ababa City Manager's Office, Government Organization, Addis Ababa.

For a Vibrant Addis Ababa: Efficient and Effective Service

This page presents information on the Addis Ababa City Manager’s Office, particularly its mandate, responsibilities, and work in the municipal service sector.

08/09/2026

EBS TV-Watch on Roku(PC/Mac & iPhone/iPad & Android Devices) : http...

በ2019 በጀት ዓመት የሚጠኑ የጥናትና የምርምር ስራዎች ላይ ዉይይት ተካሄደ።የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በውጤታማነ...
08/09/2026

በ2019 በጀት ዓመት የሚጠኑ የጥናትና የምርምር ስራዎች ላይ ዉይይት ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን በውጤታማነት ለመምራትና ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የሚረዱ በ2019 በጀት ዓመት በዉስጥ አቅምና በዉጭ አካላት የሚጠኑ አምስት ጥናቶች በተመለከተ ከተጠሪ ተቋማት የስራ ሀላፊዎች ጋር ዉይይት ተካሂዷል።

በዚሁ መድረክ በ2019 በጀት ዓመት በዉስጥ አቅም እንዲሁም በዉጭ አካላት የሚጠኑ ጥናቶች አላማ፣የጥናቶቹ አስፈላጊነት እንዲሁም የሚፈቱትን ችግሮችና ሌሎች ርዕሰ ጉዳዮችን ያለመ ሰነድ ቀርቦ የጋራ ዉይይት ተደርጎበታል።

በመድረኩ በቢሮ ሃላፊ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ እና የጥናትና ልማት ትግበራ ዘርፍ ሃላፊ ወ/ሮ ይመኙሻል ታደሰ እንደገለፁት በጽ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት በ2019 በጀት ዓመት በዉስጥ አቅምና በዉጭ አካላት የሚጠኑ አምስት ጥናቶች አስመልክቶ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ጥናቶቹ በተለይም የተቋሞቻችን የአገልግሎት አሰጣጥን ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከተማችን የደረሰችበት እድገት የሚመጥን ከማድረግ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል።

በ2019 በጀት አመት 5 ጥናቶች እንደሚጠኑ እና 4 ጥናት በዉስጥ አቅም 1 ጥናት በዉጭ አካላት ለማስጠናት እንዲሁም የሚጠኑት ጥናቶች ከጥናትነት አልፈዉ መፍትሄ እንዲሰጡና ወደ ተግባር ለመግባት እተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

ወ/ሮ ይመኙሻል አክለዉም የሚሰጡ ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶችን የተገልጋዩን የእርካታ መጠን ከፍ ያለ እንዲሆንና ውጤታማ ለማድረግ ጥናቶችን በምርምር ላይ እና የነበሩ ችግሮች እንዲሁም የአሰራር ክፍቶች ላይ ተመስርቶ ዉጤታማ አሰራሮችን ለመዘርጋትና መፍትሄም አመላካች ጥናቶች ለማካሄድ በጋራ ተቀራርቦ መስራት ለቀጣይ ስራዎቻችን ከፍተኛ አቅም እንደሚሆንም አስገንዝበዋል።

08/09/2026
የአዲስ አመትና በቀጣይ የሚከበሩ በአላትን አስመልክቶ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶችን በተሻለ የቅድመ ዝግጅት ስራን በማጠናከርና ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናወኑን ተገለፀ።የአዲስ አበ...
08/09/2026

የአዲስ አመትና በቀጣይ የሚከበሩ በአላትን አስመልክቶ ማዘጋጃቤታዊ አገልግሎቶችን በተሻለ የቅድመ ዝግጅት ስራን በማጠናከርና ተደራሽ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናወኑን ተገለፀ።
የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ፅ/ቤት ከአዲሱ አመትና በቀጣይ ከሚከበሩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በአላት አከባበር ጋር ተያይዞ ለነዋሪው ህብረተሰብ የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎትን ከሚከውኑ ተጠሪ ተቋማት ማለትም የእሳትና አደጋ፣ከፅዳት ፣ከኤሌክትሪክ አገልግሎት እና የመብራት አገልግሎት ባለስልጣን ጋር እና እንዲሁም ከዉሀና ፍሳሽ ባለስልጣን ጋር በዛሬው እለት የጋራ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
በመግለጫው በቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአዲስ አበባ ከተማ ም/ዋ/ስራ አስኪያጅ ተፈራ ሞላ(ዶ/ር) እንደገለፁት ለአዲስ አመት በአል እና በቀጣይ ለሚከበሩ ህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ፅ/ቤቱ በልዩ ትኩረት ሲሰራ መቆየቱን አስገንዝበዋል።
ተፈራ ሞላ (ዶ/ር) አክለዉም የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት የሚሰጡት ተቋማት ማለትም ከእሳት አደጋ፣ከኤሌክትሪክ አገልግሎት፣ከፅዳት እና ከውሃና ፍሳሽ ከማእከል እስከ ዲስትሪክትና ቅርንጫፎች የማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት መቆራረጦችን በተቻለ መጠን ለመቀነስና ከተከሰተም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም የእርድ ተረፈ ምርት ቆሻሻ የከተማዋ ፅዳት እንዳያበላሽ በፍጥነት ከማንሳት አንፃር በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራ መከናወኑን አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሳዲቅ ሽኩር እንዳሳወቁት ከበአል ጋር ተያይዞ በከፍተኛ ሁኔታ የሚመነጨዉ ቆሻሻ የከተማችንን ጽዳት እንዳያጓድል ስለቆሻሻ አወጋገድ ለህብረተሰቡ ሰፋፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች መሠራቱን ተናግረዋል።
ከበአሉ አከባበር ጋር ተያይዞ የሚኖረው የእርድ ተረፈ ምርቶችን አካባቢን እንዳያቆሽሽ ህብረተሰቡ በተዘጋጁ የቆሻሻ ማስወገጃዎች ቦታዎች በአግባቡ ማስወገድ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሞገስ አርጋዉ በበኩላቸው ባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ በቀጣይ የሚከበሩ በአላት ያለምንም የዉሃ አቅርቦት ችግር አገልግሎቱን ሳይቆራረጥ ለማቅረብ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መከናወኑን ገልፀዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል በበኩላቸው በቀጣይ የሚከበረዉ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በዓል ህብረተሰቡ ከአደጋ ተጠብቆ እንዲያከብር አስፈላጊዉ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን አስታውቀው ህብረተሰቡ በዓሉን ሲያከብር ራሱንና አካባቢዉን ከእሳትና መሰል አደጋዎች እንዲጠብቅ አሳስበዋል።
የኢትዮጲያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የአዲስ አበባ ሪጅን ማስተባበሪያ ም/ስራ አስፈፃሚ አቶ ጂሳ ካሳ በቀጣይ የሚከበሩ በአላትን አስመልክቶ የአገልግሎት ሽያጭና ቅሬታ እንዲሁም የኤሌክትሪክ አገልግሎት መቆራረጥ ችግርን ለመቀነስ በሃይል መጨናነቅ ሳቢያ የሚቆራረጡ መስመሮች ልየታና ጥገና እንዲሁም ያረጁ መሠረተ ልማቶችን በአዲስ የመቀየር ስራ ሲከናወን መቆየቱን ገልፀው ይህ ተግባር የሀይል መቆራረጡንም የሚቀንስ መሆኑን አመልክተዋል።
ለካርድ ተጠቃሚ ደንበኞች በአራቱም የአዲስ አበባ ሪጅን የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አገልግሎት ለመሰጠት ዝግጁ መደረጋቸውን አስታውቀዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ዮሀንስ ለገሰ እንደገለፁት በቀጣይ የሚከበሩትን በአላትን አስመልክቶ በቂ የቅድመ ዝግጅቶች መከናወናቸዉን ገልፀዉ።የመብራት መሠረተ ልማት ስራዎችን ህብረተሰቡ እንክብካቤና ጥበቃ እንዲያደርግላቸው ጥሪ አቅርበዋ

የጽናት ቀንኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡...
08/09/2026

የጽናት ቀን
ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡
ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡ ይህ በራስ የመቆም አቅም፣ የሕዝባችን ሰላምና የሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሀገራዊ ጽናታችንን በተጨባጭ ልማትና በጠንካራ የመጠበቅና የመከላከል አቅም እያረጋገጥን የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልጽግና እናጸናለን!



Guyyaa Ciminaa

Itoophiyaa wayita yaaadnu, humnootii nageenyaa keenya jaboo biyya diinarraa eeguudhaaf halkaniifi guyyaa cimanì dhaabachuudhaan bakkee bulaniif dursa utuu hin kenniin waa'ee olka'insa gama hundaa yaaduun gonkumaa hin danda'amu. Guyyaa ciminaa kanatti waaromuufi birmadummaa biyya keenyaaf jecha gootota keenya aarsaa seena-qabeessa lubbuusaanii qaalii kanfalan kabaja biyyummaa olaanaadhaa kan yaadannu kanaafi.

Har'a biyyi keenya beekumsa mataasheefi humna ijoolleesheetiin xiyyaarota mama maleessa ta'aniifi gahumsa teknooloojii olaanaa qaban, konkolaattota loltummaa ammayyaa hidhatan, meshaalee gurguddoofi madfiiwwan akkasumas rasaasota dhuka'an indaastirii loltummaa mataasheetiin homishuu dandeesseetti. Humni ofiin dhaabbachuu kun nageenyaafi guddina dinagdee gama hundaa uummata keenyaaf bu'ura cimaa waan ta'eef, cimina biyya keenyaa misooma qabatamaafi humna cimaa eeguufi ittisuutiin mirkaneessaa badhaadhina waaraa Itoophiyaa ni itichina!

07/09/2026

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa City Manager's Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Shortcuts

Share