Ethiopian Enterprise Development

Call Directions Website Contact the organization

Ethiopian Enterprise Development ራዕያችን ለኢንዱስትሪው ልማት አስተማማኝና ሰፊ መሰረት ያለ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን የተቋማት አመራሮች ሾመዋል፦

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦   #የመደመርመንግሥት
10/10/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው ዕለት የሚከተሉትን አመራሮች በሚኒስትር ዴዔታነት ሾመዋል፦


#የመደመርመንግሥት

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአመራር ስራ ርክክብ ተካሄደ ፡፡==========================EED መስከረም 29/2019 ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቀድሞ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ...
09/10/2026

በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአመራር ስራ ርክክብ ተካሄደ ፡፡
==========================
EED መስከረም 29/2019 ዓ.ም

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቀድሞ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና አዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ የስራ ርክክብ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የቀድሞው ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ ተቋሙን በበላይነት በመሩባቸው ያለፉት ዓመታት ከፈታኝ ወቅቶች ጋር ተጋፍጠው በቡድን ጥንካሬ የተሻሉ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።

አዲሱ ሚኒስትር ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ኮርፖሬሽንን ሲመሩና በኢንዱስትሪ ካውንስል ውስጥ ሲሰሩ የቆዩ፣ ዘርፉን በቅርበት የሚያውቁ እና ለቦታው ብቁ አመራር መሆናቸውን በመግለጽ መልካም የስራ ዘመን ተመኝተውላቸዋል።

አክለውም በቀጣይም የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ስትራቴጂዎችን፣ የ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄን እና ሌሎች የተመረጡ ፕሮጀክቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል።

አዲሱ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በበኩላቸው ዶ/ር ፍሰሐ ይታገሱ፣ ከአቶ መላኩ ጋር ላለፉት ዓመታት በታላቅ ወንድምነትና በአማካሪነት አብረው ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ ላበረከቱት አስተዋጽኦ እና ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

የተጀመሩ አገራዊ እና ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን በዱላ ቅብብል መርህ ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን ተደጋግፈውና ተባብረው ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመጨረሻም ሁለቱም አመራሮች የስራ ርክክብ ሰነድ አካሂደዋል፡፡

‹‹ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት!››

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦ የውጭ ጉዳይ...
08/10/2026

ኢትዮጵያን የሚመስል ስብጥር ያለውና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላትን ያቀፈ የመደመር መንግሥት ካቢኔ
1. አቶ ተመስገን ጥሩነህ፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር
2. ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
3. አቶ አዲሱ አረጋ፦ የግብርና ሚኒስትር
4. ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፦ የገንዘብ ሚኒስትር
5. መሐመድ እድሪስ ፦ የመከላከያ ሚኒስትር
6. ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ፦ የትምህርት ሚኒስትር
7. ሀና አርያስላሴ ፦ የፍትህ ሚኒስትር
8. ያስሚን ወሃብረቢ፦ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር
9. ፍስሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፦ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር
10. ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር)፦ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትር
11. ዶክተር መቅደስ ዳባ፦ የጤና ሚኒስትር
12. አቶ አወሉ አብዲ፦ የስራ እና ክህሎት ሚኒስትር
13. ወይዘሮ አይናለም ንጉሴ፦ የገቢዎች ሚኒስትር
14. አቶ በረከት ፍሰሃጽዮን፦ የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር
15. ሰላማዊት ካሳ፦ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር
16. ወይዘሮ ዓለምፀሐይ ጳውሎስ፦ የማዕድን ሚኒስትር
17. አቶ ሳዳት ነሻ፦ የሎጅስቲክስ ሚኒስትር
18. ወይዘሮ ሸዊት ሻንካ፦ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር
19. አቶ ሙሳ አደም፦ የሰላም ሚኒስትር
20. ወይዘሮ ፍሬህይወት ታምሩ፦ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር
21. ኢንጂነር መሐመድ አብዱራህማን፦ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር
22. ኢንጂነር ሱልጣን ወሊ(ዶ/ር)፦ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር
23. አክሊሉ ታደሰ (ዶ/ር)፦ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስትር

እንኳን ለ7ኛው ሀገራዊ አዲስ የመንግሥት ምሥረታ በሰላም አደረሳችሁ!የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሕዝብን ድምፅ በማግኘት በስኬት ከተካሄደው አዲስ የመንግሥት ምሥረታ...
07/10/2026

እንኳን ለ7ኛው ሀገራዊ አዲስ የመንግሥት ምሥረታ በሰላም አደረሳችሁ!

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሕዝብን ድምፅ በማግኘት በስኬት ከተካሄደው አዲስ የመንግሥት ምሥረታ ጋር ተያይዞ ለመላው የሀገራችን ሕዝቦች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላልፋል!

ተቋማችን አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች በበቂ የፋይናንስ፣ የማምረቻ ማዕከላት፣ የግብዓት፣ የቴክኖሎጂ፣ የክህሎትና የገበያ ትስስር አቅማቸው ጎልብቶ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲሸጋገሩ፣ ምርታማነታቸውን እንዲያሳድጉና የተኪና የወጪ ምርት አቅማቸውን እንዲገነቡ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፤ በዚህም ተስፋ ሰጪ ውጤቶች ተመዝግበዋል።

በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት ሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርምን መነሻ በማድረግ ዘርፉን ይበልጥ ውጤታማ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል። በተለይም የዘርፉን ተወዳዳሪነት የሚያረጋግጠውን የአምራች ኢንዱስትሪ አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም የዝግጅት ምዕራፍ ስራዎችን በስኬት አጠናቀን ወደ ትግበራ ምዕራፍ ተሸጋግረናል። በተጨማሪም የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽን ኢንሼቲቭን ወደ ትግበራ በማስገባት የአካባቢን ፀጋ ወደ ምርት የመቀየርና ሰፊ የሥራ ዕድል የመፍጠር ሥራ የተሠራ ሲሆን፣ በ“ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄም አምራቾቻችን ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና ሰፊ የገበያ ዕድል የሚያገኙበት መድረክ ተፈጥሯል።

በአዲሱ የመንግሥት ምሥረታና በያዝነው አዲስ የበጀት ዓመትም የተጀመረውን የሪፎርም ትግበራ አጠናክረን በመቀጠል፣ የኢንተርፕራይዞቻችንን የምርት ጥራትና ተወዳዳሪነት የሚያሳድጉ ሁለንተናዊ የአቅም ግንባታ ሥራዎችን እንሰራለን። የሀገራችንን የኢኮኖሚ ጥገኝነት ለመቀነስና የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ የሚደረገውን የሀገር ውስጥ ምርት የመተካትና የወጪ ምርት ድጋፍም አጠናክረን እንቀጥላለን።

ለእቅዶቻችን ስኬትና ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ እድገት ለምትተጉ የተቋማችን ሠራተኞችና አመራሮች፣ አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንተርፕራይዞች እንዲሁም ከጎናችን ለሆናችሁ ባለድርሻ አካላትና የልማት አጋሮቻችን በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ በአዲሱ የመንግሥት ምሥረታ የተጣለብንን ሀገራዊ ኃላፊነት በሙሉ አቅማችን በመወጣት የሀገራችንን የአነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለማጠናከር ያለንን ዝግጁነት እናረጋግጣለን።

‹‹ኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት!››

የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት

ለተጨማሪ መረጃ የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን ይጎብኙ፡

https://linktr.ee/ethiopianenterprisedevelopment

Address

Ras Abebe Aragay Street
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 09:00 - 17:30

Telephone

+251115150333

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Enterprise Development posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Enterprise Development:

Shortcuts

Share