Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን

Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን Official page of the Ethiopian Capital Markets Authority
(1)

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚያዘጋጀው የኢንቬስተሮች ኤክስፓ ሊካሄድ ሶስት ቀናት ብቻ ቀሩት !!ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ...
16/06/2026

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚያዘጋጀው የኢንቬስተሮች ኤክስፓ ሊካሄድ ሶስት ቀናት ብቻ ቀሩት !!

ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ ፋላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ

መግቢያ፦ በነጻ!

መሳተፈዎን ቀደም ብለው ለማሳወቅ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡፡


https://lnkd.in/eQgfRjvD

Meet and Greet with the Ethiopian Capital Market Authority Director General*********************************************...
15/06/2026

Meet and Greet with the Ethiopian Capital Market Authority Director General
****************************************************************
The Ethiopian capital market is evolving fast, and this is your rare opportunity to sit down face-to-face with the Director General of the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA).

This exclusive individual session is designed for active, high impact engagement. Come ready to:

✅ Ask questions and gain insights into the emerging Ethiopian Capital Market.

✅ Present your new ideas, products, alternatives, and innovative market solutions.

✅ Share a document or do a quick presentation to showcase your strategic vision.

✅ Flag operational bottlenecks or administrative challenges affecting your business operations.

✅ Appointments are strictly limited and granted on a first-come, first-served basis. Secure your preferred executive session for June 19 or 20, 2026, by registering today:

🔗 Register Here https://lnkd.in/efM7j_J4

ልዩ የውይይት እና የምክክር መድረክ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር
*******************************************************
የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ በከፍተኛ ፍጥነት በማደግ ላይ ይገኛል፤ ይህ መድረክ በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሙያዎች፣ ኢንቨስተሮች እና ተዋናዮች ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጋር በቀጥታ ለመገናኘት እና ለመወያየት የተዘጋጀ ልዩ መድረክ ነው።

ይህ የተለየ የአንድ ለአንድ የውይይት መድረክ በገበያው ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ጠቃሚ ውይይቶችን ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ለውይይት ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው እንዲቀርቡ ተጋብዘዋል፦

✅ አዲስ እየተገነባ ስላለው የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ማብራሪያዎችን እንዲጠይቁ ብሎም ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲቀስሙ፤

✅ አዳዲስ የገበያ ሀሳቦችን፣ የፋይናንስ አማራጮችን እና የገበያ መፍትሄዎችን እንዲያቀርቡ፤
የእርስዎን ስትራቴጂካዊ ራዕይ የሚያሳዩ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ወይም አጭር ማብራሪያ እንዲሰጡ፤

✅ በስራዎ ላይ ተጽዕኖ እያሳደሩ ያሉ የአሰራር ማነቆዎችን ወይም አስተዳደራዊ ተግዳሮቶችን እንዲያነሱ።

✅ የቀጠሮ አሰጣጥ መረጃ፦ የምክክር ጊዜዎቹ በጣም ውስን በመሆናቸው ቀጠሮ የሚሰጠው ቀድመው ለተመዘገቡ ቅድሚያ በመስጠት ይሆናል።

በመሆኑም ለሰኔ 12 ወይም 13 ቀን 2018 ዓ.ም በተመደቡት ልዩ የውይይት ክፍለ-ጊዜ ዛሬውኑ እንዲመዘገቡ ተጋብዘዋል።

🔗 ለመመዝገብ ይህንን ሊንክ ይጫኑ፦ https://lnkd.in/efM7j_J4

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚያዘጋጀው የኢንቬስተሮች ኤክስፓ ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ ቀሩት !!ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ...
15/06/2026

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚያዘጋጀው የኢንቬስተሮች ኤክስፓ ሊካሄድ አራት ቀናት ብቻ ቀሩት !!

ቦታ፦ በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ ፋላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ

መግቢያ፦ በነጻ!

መሳተፈዎን ቀደም ብለው ለማሳወቅ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡፡

https://lnkd.in/eQgfRjvD

ECMA and Luxembourg Delegation Discuss Collaboration***************************************************The Ethiopian Cap...
12/06/2026

ECMA and Luxembourg Delegation Discuss Collaboration
***************************************************
The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) was pleased to welcome H.E. Jeanne Crauser, Ambassador of Luxembourg to Ethiopia, Ms. Ariane Moayed, Chargé d’Affaires, and Mr. Maxime Ladriere, First Secretary, for a productive discussion on strengthening cooperation between Luxembourg and Ethiopia’s emerging capital market.

The meeting served as a follow-up to previous engagements and focused on potential areas of technical assistance and collaboration that the Embassy of Luxembourg may facilitate in support of ECMA’s market development initiatives.

Discussions explored opportunities for cooperation with the Luxembourg Stock Exchange and LHoFT (Luxembourg House of Financial Technology), a Luxembourg government-supported financial technology and innovation hub. Key areas of collaboration were identified, including knowledge sharing, capacity building, market development, and the promotion of innovation within Ethiopia’s capital market ecosystem.

The meeting concluded with a shared understanding to pursue these collaboration opportunities and further strengthen ties between the two institutions for the benefit of Ethiopia’s capital market development.

ECMA extends its appreciation to Ambassador Jeanne Crauser and Ms. Ariane Moayed for their continued engagement and support in advancing international partnerships that contribute to the growth and development of Ethiopia’s capital market.

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከሉክሰምበርግ ልዑካን ቡድን አባላት ጋር ውይይት አደረገ
***************************************************************

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ አምባሳደር ከሆኑት ክቡርት ዣን ክራውዘር፣ ሻርዠ ደፌር አሪያን ሞያ እንዲሁም የመጀመሪያ ጸሀፊ ከሆኑት ማክስም ላድሪየርን ጋር በሉክሰምበርግ እና በኢትዮጵያ መካከል በካፒታል ገበያ ያለውን ትብብር ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ውጤታማ ውይይት አድርጓል።

ውይይቱ ቀደም ሲል የነበሩ ግንኙነቶችን መሰረት አድርጎ የቀጠለ ሲሆን በኢትዮጵያ የሉክሰምበርግ ኢምባሲ የኢትዮጵያን የካፒታል ገበያ ልማት ሥራዎች ለመደገፍ በሚችላቸው የቴክኒክ ድጋፍ እና የትብብር መስኮች ላይም ትኩረት ሰጥቷል፡፡

በውይይቱ ከሉክሰምበርግ ስቶክ ኤክስቸንጅ (Luxembourg Stock Exchange) እና በሉክሰምበርግ መንግሥት ከሚደገፈው የፋይናንስ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ማዕከል (Luxembourg House of Financial Technology) ጋር በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይም ምክክር ተደርጓል፡፡

በዚህም የእውቀት ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የገበያ ልማት እና በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ሥነ-ምህዳር ውስጥ ውስጥ በጋራ የሚስሩ የትብብር መስኮችን በመለየት እነዚህን የትብብር ዕድሎች በተግባር ለማዋል እና ያለውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ለኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዕድገት መጠናከር አጋርነትን በማሳደግ ረገድ በኢትዮጵያ የሉክስምበርግ ኢምባሲ እያደረገ ላለው እገዛ እንዲሁም ለአምባሳደር ዣን ክራውዘር እና ለባለደረቦቿ ያለውን ምስጋና ይገልጻል።

የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅትዎን ያጠናቅቁ !*******************************************************✅ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ...
12/06/2026

የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ኤክስፖ ላይ ለመሳተፍ ዝግጅትዎን ያጠናቅቁ !
*******************************************************

✅ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያን (ESX) ጨምሮ ከዋና ዋና የካፒታል ገበያ ተዋናዮች ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ።

✅ በቦታው ላይ ወዲያውኑ የኢንቨስትመንት አካውንት መክፈት ይችላሉ!

ቀን፦ ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም

ቦታ፦ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ግቢ (ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ)

መሳተፈዎን ቀደም ብለው ለማሳወቅ ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡፡

https://lnkd.in/eQgfRjvD

Regional Regulators Roundtable Series – East Africa*****************************************************The East Africa ...
10/06/2026

Regional Regulators Roundtable Series – East Africa

*****************************************************

The East Africa Regional Regulators Roundtable is underway at the United Nations Economic Commission for Africa (ECA) in Addis Ababa, convening capital market and pension regulators from across the region to strengthen regulatory cooperation and advance capital markets development.

Hosted by the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), FSD Africa, United Nations Economic Commission for Africa (ECA), FSD Ethiopia the series provides a high-level platform for peer learning, policy dialogue, and knowledge exchange among regulators.

Discussions focus on enhancing regulatory and supervisory frameworks that support domestic capital mobilization, local currency market development, institutional investment, and sustainable cross-border capital flows.

Through evidence-based dialogue and practical problem-solving, participants are working to identify actionable reforms that can deepen, strengthen, and better integrate capital markets across East Africa.

The series reflects a shared commitment to building resilient, inclusive, and well-functioning financial systems that can drive long-term economic growth and expand investment opportunities in the region

የምስራቅ አፍሪካ የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪዎች መድረክ

********************************************

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካ (FSD Africa)፣ ከተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ለአፍሪካ (ECA) እና ከኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ (FSD Ethiopia) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የምስራቅ አፍሪካ የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪዎች የጋራ ልምድ ልውውጥና የፖሊሲ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

በተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ለአፍሪካ እየተካሄደ የሚገኘው የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪዎች ውይይት በቀጣናው የቁጥጥር ጥራትን ለማስፈን እና ቀጣናዊ ትብብርን ለማጠናከር ከተለያዩ የአካባቢው አገራት የተወከሉ የካፒታል ገበያ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎችን አገናኝቷል፡፡

በውይይቱ የአገር ውስጥ የካፒታል አቅምን ማሳደግ ስለሚቻልበት ሁኔታ ፣የቁጠባና የኢንቨስትመንት ተቋማት ተሳትፎን ስለማሳደግ እንዲሁም ዘላቂ የካፒታል ፍሰትን ሊደግፉ የሚችሉ የቁጥጥርና የክትትል ማዕቀፎችን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ምክክር እየተደረገ ነው፡፡

ይህ መድረክ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የኢኮኖሚ ዕድገትን ሊያፋጥኑ እና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ሊያሰፉ የሚችሉ ይበልጥ ጥልቅ፣ ጠንካራ፣ አካታች እና እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ ቀጣናዊ የካፒታል ገበያን ለመገንባት ጉልህ ድርሻ አለው ፡፡

The countdown is on for Ethiopia’s first-ever Capital Market Investor Day Expo !****************************************...
09/06/2026

The countdown is on for Ethiopia’s first-ever Capital Market Investor Day Expo !

*****************************************************************

Whether you are looking to engage directly with key market leaders including the Ethiopian Capital Market Authority (ECMA), the Ethiopian Securities Exchange (ESX), and Capital Market Service Providers or wanting to open an investment account on the spot, this landmark event is for you.

✅ Date: June 19 & 20, 2026

Venue: Addis Ababa Culture and Fine Arts Bureau Compound (located near Flamingo Restaurant)

Secure your spot and let us know you are coming by registering here: https://forms.office.com/r/RTvzCL0uiv

We look forward to welcoming you!

Disclaimer: Registration is not mandatory to attend, as this event is free and fully open to the public. However, we highly encourage prior registration to help our team better estimate crowd size and ensure adequate preparation for the event.

የመጀመሪያው የካፒታል ገበያ ኢንቬስተሮች ኤክስፖ (Capital Market Investor Day Expo) ሊካሄድ ቀናት ብቻ ቀሩት !

***********************************************************************

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ECMA)፣ የኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX) እና የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጨምሮ ከዋና ዋና የገበያው ተዋናዮች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት በቦታው በመገኘት የኢንቨስትመንት አካውንት ለመክፈት የሚችሉበት እድል እርስዎን እየጠበቀ ነው።

✅ ቀን፦ ሰኔ 12 እና 13 ቀን 2018 ዓ.ም

ቦታ፦ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነጥበብ ቢሮ ግቢ (ፍላሚንጎ ሬስቶራንት ገባ ብሎ )

በኤክስፖው መሳተፈዎን ቀደም ብለው ለማሳወቅ ይህን https://forms.office.com/r/RTvzCL0uiv ማስፈንጠሪያ በመጫን መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ማሳሰቢያ፦ ይህ ኤክስፓ ሙሉ በሙሉ ለህዝብ ክፍት የሚሆን በመሆኑ ለመታደም የግድ መመዝገብ አያስፈልገዎትም !!

ይሁን እንጂ የኤክስፓው አዘጋጆች የተሳታፊዎችን ብዛት አስቀድሞ ለመገመት እና በቂ ዝግጅት ለማድርግ ያስችላቸው ዘንድ ቅድመ-ምዝገባ እንዲያደርጉ እናበረታታለን።

የኢኮኖሚ ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ… የነገው የሀብት ማፍሪያ አማራጭዎ አሁን በእጅዎ ነው!******************************************************************...
09/06/2026

የኢኮኖሚ ጉዟችን አዲስ ምዕራፍ… የነገው የሀብት ማፍሪያ አማራጭዎ አሁን በእጅዎ ነው!
***********************************************************************

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ኢንቬስተሮችን ስለካፒታል ገበያው እና የካፒታል ገበያ ኢንቨስትመንት አማራጮች ግንዛቤን ለማስፋት እንዲሁም ከካፒታል ገበያ መሰረተ ልማት አቅራቢዎች እና አገልግሎት ሰጭዎች ጋር የሚገናኙበትን መድረክ በማመቻቸት የመጀመሪያውን '”የካፒታል ገበያ ኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ” በታላቅ ዝግጅት ወደ እርስዎ ይዞ እየቀረበ ነው፡፡

ወደዚህ ልዩ አውደ ርዕይ ሲመጡ ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ (ESX)፣ ከኢንቨስትመንት ባንኮች፣ ኢንቨስትመንት አማካሪዎች እና የሰነደሙዓለ ንዋይ አከናዋኞች ጋር ፊት ለፊት ይገናኛሉ።

ስለ ካፒታል ገበያ በቂ ግንዛቤ ያገኛሉ የኢንቨስትመንት ጉዞዎንም ያመቻቻሉ፡፡

የካፒታል ገበያ ኢንቨስተሮች ቀን አውደ ርዕይ ከሰኔ 12 እና 13 2018 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ፍላሚንጎ ሬስቶራንት አካባቢ ከባለስልጣኑ ቢሮ ፊት ለፊት በሚገኘው በአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ግቢ በመገኘት እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፡፡

መግቢያው ለሁሉም ፍላጎት ላላቸው ጎብኚዎች በነጻ ክፍት ነው!"
የወደፊት ዕድልዎን የሚወስኑበትን ይህንን ታላቅ አጋጣሚ እንዳያመልጥዎት፤ ዝግጅትዎን አሁኑኑ ይጀምሩ!

አካታች ፋይናንስ ለጋራ ብልጽግና!
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን።

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ኢንቬስተሮችን ስለካፒታል ገበያው እና የካፒታል ገበያ ኢንቨስትመንት ...

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) presents the English version of the Collective Investment Schemes (CIS) Dr...
08/06/2026

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) presents the English version of the Collective Investment Schemes (CIS) Draft Directive for public review and stakeholder consultation.

Stakeholders are invited to review the draft and submit their formal comments and recommendations through the FDRE public consultation portal.

English version: https://www.linkedin.com/.../urn:li:ugcPost.../...

Submit comments: https://lnkd.in/edXWjJBY

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን የጋራ ኢንቨስትመንት ፈንድ ረቂቅ መመሪያ የእንግሊዝኛ ቅጂ ለህዝብ እና ለባለድርሻ አካላት አስተያየት መስጫ ክፍት መሆኑን ይገልጻል።

ረቂቅ ሰነዱን በመገምገም አስተያየት እና ምክረ-ሀሳብዎን በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የህዝባዊ ምክረ-ሀሳብ መስጫ መድረክ ላይ በቀጥታ እንዲያጋሩ ተጋብዘዋል።

የእንግሊዘኛ ቅጅውን ከዚህ ያገኛሉ

https://www.linkedin.com/.../urn:li:ugcPost.../...

አስተያየት ለመስጠት፦ https://e-consultation.gov.et/draft/155

ECMA Social Media Links

Facebook https://lnkd.in/e5r8YzEh
X https://x.com/CMAEthiopia
You tube https://lnkd.in/euAsnu8b
Website ecma.gov.et
telegram https://t.me/ecma2026
WhatsApp https://lnkd.in/eKPbNMhR

This link will take you to a page that’s not on LinkedIn

ECMA Licenses United Capital Financial Services PLC as Investment Bank**************************************************...
08/06/2026

ECMA Licenses United Capital Financial Services PLC as Investment Bank
*************************************************************************

The Ethiopian Capital Market Authority (ECMA) has granted a Capital Market Service Provider (CMSP) license to United Capital Financial Services PLC, a subsidiary of United Capital Group Nigeria, making it the first foreign investment bank to establish a subsidiary in Ethiopia.

The license authorizes the company to operate under the Investment Banking category. The Authority has also approved the appointment of five Board Directors and licensed four Appointed Representatives within the company.

Issued on Friday, June 5, 2026, the license brings the total number of licensed CMSPs in Ethiopia to 18 and the number of investment banks to 7, reflecting the tangible and continuous development in the operationalization and expansion of the country’s capital market.

At the official licensing ceremony, the Director General Hana Tehelku noted that the entry of a Pan-African institution such as United Capital marks a historic milestone in the development of Ethiopia’s capital market, further indicating that the event demonstrates strong confidence in the credibility of the country’s emerging financial ecosystem and the direction of ongoing reforms.
She noted that such developments reflect growing recognition of Ethiopia’s market potential and institutional progress, and can contribute to strengthening the depth, capacity, and regional integration of the market, while underscoring the importance for licensed service providers to adhere to the highest standards of market conduct, governance, and regulatory compliance.

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ለዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ ሰጠ
**************************************************************
የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን (ባለስልጣኑ) የናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል ግሩፕ ተቀጥላ ኩባንያ (Subsidiary) ለሆነው ዩናይትድ ካፒታል ፋይናንሻል ሰርቪስስ ኃ.የተ.የግ.ማህበር የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪነት ፈቃድ ሰጥቷል።

ይህም ተቋሙን በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጥላ ኩባንያ በማቋቋም እንዲንቀሳቀስ ፈቃድ የተሰጠው የመጀመሪያው የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ያደርገዋል። የተሰጠው ፈቃድ ድርጅቱ በኢንቨስትመንት ባንክ ዘርፍ ስር እንዲሠራ የሚፈቅድ ሲሆን፤ ባለስልጣኑ ከዚህ በተጨማሪ የአምስት (5) የቦርድ ዳይሬክተሮችን ሹመት ያጸደቀ ከመሆኑም በላይ ለአራት (4) ተሿሚ እንደራሴዎችም ፈቃድ ሰጥቷል።

አርብ ግንቦት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተሰጠው ይህ ፈቃድ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉ የተፈቀደላቸው የካፒታል ገበያ አገልግሎት ሰጪዎችን ጠቅላላ ቁጥር ወደ አስራ ስምንት (18)፣ እንዲሁም የኢንቨስትመንት ባንኮችን ቁጥር ወደ ሰባት (7) ከፍ አድርጎታል። ይህም የሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ተግባራዊነት እና ልማት እያሳየ ያለውን ተጨባጭና ቀጣይነት ያለው ዕድገት ያሳያል።

በይፋዊው የፈቃድ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሃና ተኸልቁ እንደገለጹት፣ እንደ ዩናይትድ ካፒታል ያለ የፓን-አፍሪካዊ ተቋም ወደ ገበያው መግባቱ በኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ዕድገት ላይ ታሪካዊ ምዕራፍ እንደሆነ ገልጸው፤ ሁነቱ እያደገ ባለው የሀገሪቱ የፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ተዓማኒነት እና እየተከናወኑ ባሉ የማሻሻያ እርምጃዎች ላይ ጠንካራ እምነት መኖሩን እንደሚያሳይ አመልክተዋል።

ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም፣ እንዲህ ያሉ ዕድገቶች ለኢትዮጵያ የገበያ አቅም እና ለታየው ተቋማዊ መሻሻል የተሰጡ ትልቅ እውቅናዎች መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የገበያውን ጥልቀት፣ አቅም እና ቀጣናዊ ውህደት ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ አመልክተዋል። በተመሳሳይም ፈቃድ የተሰጣቸው አገልግሎት ሰጪዎች ከፍተኛ የገበያ ሥነ-ምግባርን፣ የኮርፖሬት አስተዳደር መርሆዎችን እና የቁጥጥር ማዕቀፎችን ማክበር እንዳለባቸው አፅንዖት ሰጥተው አሳስበዋል::

Address

Flamingo, Minaye Building 16th Floor
Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 05:30
Friday 08:30 - 17:30

Telephone

+251911246658

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Ethiopian Capital Market Authority - የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን:

Share