ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office

  • Home
  • Ethiopia
  • Addis Ababa
  • ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office

ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office, Government Organization, Addis Ababa.
(1)

እንኳን ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ በደህና መጡ!

ይህ ገፅ በክፍለ ከተማችን የሚከናወኑ የጽ/ቤቱ ተግበሰራት እና ተያያዥ አገልግሎቶችን በተመለከተ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን ለነዋሪው ተደራሽ ለማድረግ የተዘጋጀ ነው።

12/04/2026
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት  ፕሮጀክት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷ ደግሞ ብቁ የማድረግ ትልቅ ግብ የሰነቀ ነው። የከተማ አ...
04/04/2026

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ፣ ለዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷ ደግሞ ብቁ የማድረግ ትልቅ ግብ የሰነቀ ነው። የከተማ አስተዳደሩ "ልማቱ ሰውን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት" በሚል በያዘው አቋም መሠረት በኮሪደሩ ዳርቻ የፈረሱ የንግድ ቦታዎችን ለመተካት በዘመናዊ መልኩ የተገነቡ ሱቆችን ለተነሺዎች ቅድሚያ በመስጠት የማስተላለፍ ስራ በከፍተኛ ትኩረት እየተከናወነ ይገኛል።የአዲሳ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 13 የተገነቡ በኮሪደር ልማት የለሙ ሱቆችን ለልማት ተነሺዎች በዕጣ የማስተላለፍ መረሃ ግብር አከናዉኗል።

የዛሬውን ወርቃማው ሰኞ ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች መብቱን እና ግዴታውን አውቆ ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው መ...
30/03/2026

የዛሬውን ወርቃማው ሰኞ ምክንያት በማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ የቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የመንግስት ሰራተኞች መብቱን እና ግዴታውን አውቆ ቀልጣፋ የመንግስት አገልግሎት መስጠት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ የልምድ እና አውቀት ሽግግር ተካሄደ።
ይህ የውይይት መድረክ በዋናነት የመንግስት ሰራተኛውን መብትና ግዴታ በዝርዝር ከመረዳት ባለፈ፣ በጽህፈት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋ፣ ግልጽና ለነዋሪው ምቹ ለማድረግ ያለመ ነው።

የአረንጓዴ አሻራን በዘላቂነት ማጽናት፦ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ 12 የእንክብካቤ ስራ አከናዉኗል። የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎች...
28/03/2026

የአረንጓዴ አሻራን በዘላቂነት ማጽናት፦ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት በወረዳ 12 የእንክብካቤ ስራ አከናዉኗል።
የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያዎች በ2017 የክረምት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ በዛሬው ዕለት በወረዳ 12 አካባቢ በስኬት አከናውነዋል። በንቅናቄው ላይ የጽ/ቤቱ የስራ መሪዎችና መላው ሰራተኞች በነቃ ተሳትፎ የተገኙ ሲሆን። በመድረኩ የተገኙ የስራ ኃላፊዎች እንደተናገሩት፡- ችግኝ መትከል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ የተከልነውን አጽድቆ ለትውልድ ማሳለፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብሎዋል። ይህም የከተማዋን ውበት ከመጠበቅ ባለፈ ለነዋሪዎች ምቹ አየር እንዲኖር ለማድረግ የሚደረገው ጥረት አካል መሆኑ ተገልጿል።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር በየሳምንቱ ሰኞ የሚያካሂደው "ወርቃማ ሰኞ" የውይይት መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። የዛሬው የውይይት መሪ ቃል "አገልግሎት እና ስነምግባር" የሚ...
23/03/2026

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር በየሳምንቱ ሰኞ የሚያካሂደው "ወርቃማ ሰኞ" የውይይት መድረክ ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል። የዛሬው የውይይት መሪ ቃል "አገልግሎት እና ስነምግባር" የሚል ሲሆን፣ በጽሕፈት ቤቱ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ የሚያስችሉ ቁልፍ ነጥቦች ላይ የእውቀት ሽግግር ተከናውኗል።

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት የሚከናወነው የ**"ወርቃማ ሰኞ"** መርሐ-ግብር ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።የዛሬው የውይይት ትኩረት "የተግባቦት (...
16/03/2026

በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤት በየሳምንቱ ሰኞ ጠዋት የሚከናወነው የ**"ወርቃማ ሰኞ"** መርሐ-ግብር ዛሬም በደመቀ ሁኔታ ተካሂዷል።

የዛሬው የውይይት ትኩረት "የተግባቦት (Communication) ጽንሰ-ሀሳብና አስፈላጊነት" በሚል ርዕስ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በሥራ አካባቢ ሊኖር ስለሚገባው ጤናማ የመረጃ ልውውጥ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።
የማዳመጥ ጥበብ፦ የደንበኞችን ፍላጎትና ቅሬታ በትዕግሥት ማዳመጥ ለችግሮች ግማሽ መልስ ነው።
የጽሕፈት ቤቱ ሠራተኞች በውይይቱ ላይ ንቁ ተሳትፎ ያደረጉ ሲሆን፣ የተገኘውን ግንዛቤ ወደ ተግባር በመቀየር ለክፍለ ከተማው ነዋሪዎች ግልጽነት የተሞላበትና ፈጣን አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ብሏል።

በቀን 30/06/2018 ዓ.ም "አመለካከት ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው"፦ በሚል ማሪ ቃል በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር የእውቀት ሽግግርና የውይይት መድረክ ተካሄደየቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች...
10/03/2026

በቀን 30/06/2018 ዓ.ም "አመለካከት ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው"፦ በሚል ማሪ ቃል በቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር የእውቀት ሽግግርና የውይይት መድረክ ተካሄደ
የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት የሰራተኞችን ክህሎት ለማሳደግና ተገልጋይን ማእከል ያደረገ አሰራርን ለማጠናከር ዘዎትር ሰኞ የሚካሄደው "ወርቃማ ሰኞ" “Attitude is Everything” (አመለካከት ለሁሉም ነገር ወሳኝ ነው) በሚል መሪ ቃል ውይይትና የእውቀት ሽግግር መርሃ-ግብር ተካሄደ። የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ይህንን "ወርቃማ ሰኞ"ን የመማማሪያ መድረክ በማድረግ፣ ሰራተኛው በዕውቀት ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናም ተዘጋጅቶ ህዝቡን እንዲያገለግል እና መልካም ልምዶቻቸውን በማካፈል የስራ መነቃቃት እና ተነሳሽነት የሚፈጥሩበት ነው፡፡

የስድስት ወር የግምገማ ግብረመልስን መነሻ በማድረግ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች እና በታዩ ጥንካሬዎች እና መስተካከል በሚገባቸው ጉድለቶች ላይ የጋራ...
28/02/2026

የስድስት ወር የግምገማ ግብረመልስን መነሻ በማድረግ የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤት ውይይት ዋና ዋና ነጥቦች እና በታዩ ጥንካሬዎች እና መስተካከል በሚገባቸው ጉድለቶች ላይ የጋራ መግባባት ላይ የተደረሰ እና ውይይቱ የሚያሳየው ካለፉት ስድስት ወራት ክፍተት በመማር፣ ለቀጣዩ ግማሽ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከፍተኛ ተነሳሽነት መኖሩን ነው።

28/11/2025
06/11/2025
02/11/2025

ማስታወቂያ

ከ7ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ
👇👇👇👇👇👇👇

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 17:30
Tuesday 08:30 - 17:30
Wednesday 08:30 - 17:30
Thursday 08:30 - 17:30
Friday 08:30 - 17:30

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when ቦሌ ክ/ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት/Bole Sub City Housing Dev. & Admin Office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share