Addis Ababa Government enterprises Admnistration authority

Addis Ababa Government enterprises Admnistration authority we work for the prosperity of our country, Ethiopia

የአዲስ አበባ ከተማ  የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣር በልደታ ክ/ከተማ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ30 አባወራዎች  G+1  የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስተላለፈ።ባለስልጣ...
09/09/2024

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣር በልደታ ክ/ከተማ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ ለ30 አባወራዎች G+1 የመኖሪያ ቤት ገንብቶ አስተላለፈ።

ባለስልጣኑ በስሩ ያሉ የልማት ድርጅቶችን በማስተባበር ለ30 አባወራዎች G+1 የሆኑ መኖሪያ ቤቶችን ሰርቶ በማጠናቀቅ ያስተላለፉት ማለትም ቄራዎች ድርጅት፣ ኤግዚብሽን ማዕከልና ገበያ ልማት፣ ከነማ ፋርማሲ እና የኮንስትራክሽን፣ ዲዛይን ፣ ግንባታና ማማከት ድርጅትን በማስተባበር አዲስ ህንፃ ማስገንባት የቁልፍ ርክክብ መርሀ ግብርም አካሂደዋል ።

የአዲስ አበባ የመንግስት የልማት ድርጀቶች አስተዳደር ባለስልጣን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አባወይ ዮሐንስ ዛሬ ከጳጉሜ ቀናት 4ኛው ቀን የህብር ቀን ነው በዕለቱም አብሮነትና ትብብርን የምናከብርበት መልካም ተግባራትን የምናከናውንበት ኢትዮጵያዊነትን የምናጎላበት ዕለት ነው እንኳን አደረሳችሁ ብለዉ፣ይህ ቦታ ከወራት በፊት ለዕይታም ለመኖሪያም ምቹ አልነበረም ነገር ግን በከተማውና በክፍለ ከተማው አመራሮችና በጎ ፍቃደኛ የህብረተሰብ ክፍሎች ትብብር በፍጥነት ተሰርቶ በማጠናቀቅ ለቤት ባለዕድለኞች ማስረከብ ተችሏል ብለዋል።

ድርጅታችን የነዋሪዎችን ችግር ለማቃለል የሚሰራ ነው ያሉት አቶ አባወይ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ለባዕድለኞች የተረከበው ቤት 40 ሚሊየን ብር የሚገመት ገንዘብ ወጪ በማድረግ ከመኖሪያነት ባለፈ ለንግድ፣ ለዕድር፣ ለካፍቴሪያና ለተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ ክፍሎችን አካቶ ተሰርቷል። በመሆኑም የአካባቢው ነዋሪዎች አዲሱን አመት በአዲስ ቤትና በአዲስ መንፈስ እንዲያከብሩ ከማድረግ ባሻገር ለስራ ዕድል ፈጠራውም ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል ብለው በሌሎች የክፍለ ከተማው አካባቢዎችም ላይ የልማት ስራዎችን በጋራ መስራቱን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አበባ እሸቴ ለቤት እድለኞች እንኳን ደስ አላችሁና ለዘመን መለወጫ እንኳን አደረሳችሁ በማለት ካለፉት 6 አመታት ጀምሮ ለጳጉሜ ቀናት የተለያዩ ስያሜዎች በመስጠት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ሰው ተኮርና የመሰረተ ልማት ስራዎች ሲሰራባቸው ቆይተዋል በዛሬው ዕለትም ጳጉሜ 4 የህብር ቀን በሚል በህብረት በአንድነትና በፍቅር ተሳስበን ብሎም ወገናችን ከችግር ተላቀው በአዲስ መንፈስ ወደ አዲሱ ዘመን እንዲሸጋገሩ የማድረግ ስራን እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።

በመጨረሻም የከተማ፣ የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች የተገነቡ ቤቶችን የጎበኙ ሲሆን ለስራው መቀላጠፍ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል።

10/08/2024
06/08/2024

እንኳን ደስ አለን!

በፈረንሳይ ፓሪስ በመካሄድ ላይ በሚገኘው 33ኛው የኦሎምፒክ ውድድር አትሌት ፅጌ ዱጉማ በተወዳደረችበት የ800 ሜትር በታሪክ ለሀገራችን የመጀመሪያውን የብር ሜዳሊያ አምጥታለች::

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን!

Baga Gammadne!

Dorgommii olompikii 33ffaa Faransaay,Paarisitti geggeefamaa jiru irratti Atileet Tsiggee Dhugumaa meetira 800 irratti dorgomteen seenaa biyya keenyaatti meedaliyaa meetii jalqabaa fiddee jirti.

Irra deebiin baga Gamamdne!

ምሽቱ በአዲስ አበባ ቦሌ!
29/07/2024

ምሽቱ በአዲስ አበባ ቦሌ!

ገዜ ጎፋን አፅናናን ለሞቱት ነብስ ይማር ላሉት መፅናናትን ከመመኘት ውጭ ምን አማራጭ አልነበረንም ,,,,,የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የተመራ የካቢኔ አባላት ቡድ...
26/07/2024

ገዜ ጎፋን አፅናናን ለሞቱት ነብስ ይማር ላሉት መፅናናትን ከመመኘት ውጭ ምን አማራጭ አልነበረንም ,,,,,

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኩቡር አቶ ሞገስ ባልቻ የተመራ የካቢኔ አባላት ቡድን ሆነን ቦታው ተገኝተናል የተፈጠረው ልብ ይሰብራል ምን ይደረጋል የተፈጥሮም ጉዳይ አይደል አዝኖ አይዟቹ ብሎ ከመመለስ ውጭ ምንም ,,,,,,!

ሀገሬ አዝናለች የጎፋ ህዝብ አዝኗል ግን ምን ይደረጋል ለሟች ቤተሰቦች ፈጣሪ መፅናናትን ይስጥልኝ 😭😭

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ"የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አመራርና ሠራተኞች  የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ...
20/07/2024

"የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ"

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር አመራርና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሂደዋል።

“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሣብ እየተከናወነ በሚገኘው በ6ኛው ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በእንጦጦ ፓርክ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል::

የቀድሞ አባቶች ችግኞችን በመትከል የጠበቋትን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መከላከል የቻለች ሀገር የአሁኑ ትውልድም አረንጓዴ አሻራውን በማሳረፍ ለምለም ሀገር ለቀጣዩ ትውልድ ማሻገር አለበት ያሉት አመራርና ሠራተኞቹ ችግኞችን ከመትከል ባሻገር ፀድቀው የለመለመች ሀገር ለማስተላላፍ መንከባከብም እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል።

በመርሀግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ተገኝተው አሻራቸውን አኑረዋል።

"የምትተክል ሀገር ፣ የሚያፀና ትውልድ!"የአዲስ አበባ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን የ2016ዓ.ም 6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ቅድመ ዝግጅት
20/07/2024

"የምትተክል ሀገር ፣ የሚያፀና ትውልድ!"

የአዲስ አበባ የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን የ2016ዓ.ም 6ኛ ዙር የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ቅድመ ዝግጅት

በፈተናዎች የመፅናት አቅማችን የተገለጠበት ውጤት ጎርጎራ!
13/07/2024

በፈተናዎች የመፅናት አቅማችን የተገለጠበት ውጤት ጎርጎራ!

ከመገናኛ ሲኤምሲ የሚደርሰው የኮሪደር ልማት!
12/07/2024

ከመገናኛ ሲኤምሲ የሚደርሰው የኮሪደር ልማት!

“ሁሉም ለሰላም፣ ሰላም ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የጎዳና ላይ ሩጫ ከከተማችን ነዋሪዎች ፣ ከሚኒስትሮች ፣ ከአምባሳደሮችና በከተማች ከሚገኙ የአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁ...
07/07/2024

“ሁሉም ለሰላም፣ ሰላም ለሁሉም!” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀውን የጎዳና ላይ ሩጫ ከከተማችን ነዋሪዎች ፣ ከሚኒስትሮች ፣ ከአምባሳደሮችና በከተማች ከሚገኙ የአለምአቀፍ ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን ሮጠናል::

ሰላማችንን በጋራ እናጸናለን፣ እናስቀጥላለን!
"ሁሉም ለሰላም ፣ ሰላም ለሁሉም!"

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ይባርክ
Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ

የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ:: ለምሳሌ...
05/07/2024

የህዝብን ቅሬታ በመስማት የኢሚግሬሽን ስራ ማስተካከያ የሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በመስጠት እና ተቋማዊ ለውጦችን በማከናወን በጥቂት ወራት ውስጥ ብዙ ማሻሻያዎች እየተተገበሩ ይገኛሉ:: ለምሳሌ ያህል:-

- በቀን 900 ፓስፖርት መስጠት የነበረውን አገልግሎት ወደ 1700 ማድረስ ተችሏል፣
- ቀደም ብለው የተጠራቀሙ ጥያቄዎችን አስተናግዶ ለመጨረስ በተሰራ ስራ 1 ሚሊዬን ፓስፓርት ታትሞ ገብቶ እስከ 87% ተሰራጭቷል፣
- የተከማቹ ቅሬታዎች 100% ተፈትተዋል፣
- በኢትዮዽያ በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ 10,467 ሰዎችን መመዝገብ ተችሏል፣
- ሃሰተኛ ማስረጃ የያዙ 18,000 ሰዎች ቅጣት እንዲከፍሉ ተደርጓል፣
- በ88 ሀገሮች የቪዛ አገልግሎት በመክፈት ለ81,9278 ተስተናጋጆች e-visa ጨምሮ የቪዛ አገልግሎት ተሰጥቷል
- ለ4,276,474 ግለሰቦች በአየርና በየብስ መዳረሻ ጣቢያዎች አገልግሎት ተሰጥቷል

በአሁኑ ወቅትም ተቋሙን የዘመነ እና አገልግሎቱን በጥራት የሚሰጥ ተቋም ለማድረግ ብዙ ስራዎች እየተሰሩ ነው::

ም/ቤቱ ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት...
03/07/2024

ም/ቤቱ ነገ ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር) በተገኙበት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት የፌዴራል መንግስት የ2017 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ሰኔ 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ ይካሂዳል፡፡

በኢፌዲሪ ሕገ-መንግስት አንቀፅ 55 (17) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 81 (3) እና አንቀፅ 92 መሰረት የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደበኛ ስብሰባው በመገኘት በፌዴራል መንግስቱ የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 55 (11) እና በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ደንብ ቁጥር 6/2008 አንቀፅ 76 መሰረትም ምክር ቤቱ የ2017 የፌዴራል መንግስት በጀት ዓመት ረቂቅ በጀትን አስመልክቶ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ የሚያቀርበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ አዳምጦ ረቂቅ በጀቱን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በምክር ቤቱ 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮችና የዓለም አቀፍ ተቋማት ተጠሪዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ የምክር ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

Address

Addis Ababa

Telephone

+251913932499

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Government enterprises Admnistration authority posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share