Addis Ababa Education Bureau

Addis Ababa Education Bureau የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮን መረጃ በፍጥነትና በጥራት የሚያገኙበት ገፅ ነው።
(1)

The page belongs for Addis Ababa Education Bureau and it works for the transfer of educational information for the public.

04/06/2026

በ2018 የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሰጡ ከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ በትኩረት መስራት ይገባል፡፡

(ግንቦት 27/2018 ዓ.ም)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

04/06/2026

English Grade 4

(ግንቦት 27/2018 ዓ.ም)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

04/06/2026

Barnoota Herregaa kutaa 5ffaa

(ግንቦት 27/2018 ዓ.ም)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

03/06/2026

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸዉ የተገነባዉ የብርሃን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለአፍሪካ ህብረት የሰሩት ሙዚቃ።

(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

ዛሬ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ውይይት አድርገናል።በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV ...
03/06/2026

ዛሬ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ከሆኑት ንስቲያን ክርስተንሰን ጋር ውይይት አድርገናል።

በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) ላይ በጋራ በምንሰራቸው ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ከተማችን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን እናሳካዋለን።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!!

Today, we held discussions with H.E. Stian Christensen, Ambassador of Norway to Ethiopia.

We had a productive exchange with the Ambassador on areas of mutual cooperation in preparation for the upcoming Nordic Africa EV Summit, which will be held in Ethiopia this September.
During our discussion, I emphasized that our city has developed considerable experience and capacity in successfully hosting major continental and international events and is increasingly emerging as a preferred destination for such gatherings. I assured the Ambassador that, in close collaboration with all relevant stakeholders, we will organize this summit with the highest standards of professionalism and excellence.

Royal Norwegian Embassy in Addis Ababa

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

03/06/2026

አዎ !

የኢትዮዽያ ህዝብ በፅናት ራሱን ሆኗል፣ ታሪክ ፅፏል፣ ተምሳሌት የሆነ ህዝብ ሊኮራ ይገባል!

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ቢሮው በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በትግበራና ማጠቃለያ ምዕራፎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን አስታወቀ።(ግንቦት 26/20...
03/06/2026

ቢሮው በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በትግበራና ማጠቃለያ ምዕራፎች ባለድርሻ አካላትን በማስተባበር ባከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆኑን አስታወቀ።

(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2018 ዓ.ም የበጀት አመት በቁልፍና አበይት ተግባራት የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች በተገኙበት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በሚገኘው ፓን- አፍሪካ አዳራሽ ገምግሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በቀጣይ የሚሰጡ ከተማ አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች ስኬታማ ሆነው እንዲጠናቀቁ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው በመጠቆም በተለይም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በሚያስፈትኑ ጣቢያዎች የአይ ሲቲ መሰረተ ልማትን ጨምሮ በቂ ግብአቶችን በማሟላት ለፈተናው ዥግጁ እንዲሆኑ በቂ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ተስፋዬ አበራ በበኩላቸው የዛሬው መርሀግብር በከተማ አስተዳደሩ በ2018ዓ.ም የትምህርት አመት የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በቀጣይ የማጠቃለያ ምዕራፍ ቀሪ ተግባራትን በማከናወን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል የትምህርት አመራሩ ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ የሚያስችል መሆኑን አመላክተዋል።

ቢሮው የበጀት አመቱን እቅድ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በማፅደቅ ወደ ተግባር ከመግባት ባሻገር በየሩብ አመቱ አፈጻጸሙን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫ ሲያስቀምጥ መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ገልጸው በበጀት አመቱ በቁልፍና አበይት ተግባራት የተመዘገበው አፈጻጸም በጣም ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በግምገማ መረጋገጡን አስታውቀዋል።

በመርሀግብሩ ክልል አቀፍን እና ሀገር አቀፉን ፈተና ስኬታማ ለማድረግ እየተከናወኑ የሚገኙ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ተስፋዬ አበራ እንዲሁም የበጀት አመቱ የቁልፍና አበይት ተግባራት ሪፖርት በእቅድና በጀት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር በቀጣይ የርብርብ ማዕከል ሆነው የሚከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ አቅጣጫ ተቀምጧል።

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

በሀገር በቀል እዉቀት ፣ በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት !ከንቲባ አዳነች አቤቤ(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም)ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ! https:/...
03/06/2026

በሀገር በቀል እዉቀት ፣ በህዝብ እና በመንግስት ትብብር የተገኘ ድንቅ ውጤት !

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም)

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ::(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም) የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ::

(ግንቦት 26/2018 ዓ.ም) የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

02/06/2026

እንችላለን !!!

Address

6 Kilo Near Anbesa Gibi
Addis Ababa
1000

Opening Hours

Monday 02:30 - 23:30
Tuesday 02:30 - 23:30
Wednesday 02:30 - 23:30
Thursday 02:30 - 23:30
Friday 02:30 - 23:30

Website

https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Education Bureau posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share