Bole Woreda 14 Communication

Call Directions Website Contact the organization

Bole Woreda 14 Communication ይህ በቦሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 14 አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ነው።

23/09/2026
23/09/2026
በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ለወጣቶች የሥራ ዕድልና የችሎታ ማሳደጊያ ሥልጠና ተዘጋጀ።ቦሌ ወረዳ 14 ኮምኒኬሽን-መስከረም 13/2019 ዓ.ም የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮ...
23/09/2026

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ለወጣቶች የሥራ ዕድልና የችሎታ ማሳደጊያ ሥልጠና ተዘጋጀ።

ቦሌ ወረዳ 14 ኮምኒኬሽን-መስከረም 13/2019 ዓ.ም

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቶች ጋር በመተባበር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ለሚኖሩ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 29 ዓመት የሆኑ ወጣቶች የሚሆን የሥራ ልምድና የክህሎት ማሳደጊያ ሥልጠና ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚና የሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተገኝ እንደገለጹት፣ ይህ ሥልጠና ወጣቶችን በክህሎት ለማብቃትና ወደ ሥራ ዓለም እንዲገቡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በቀረበው ማስታወቂያ መሠረት፣ በሥልጠናው ለመሳተፍ ወጣቶች የ12ኛ ክፍል ትምህርት ያጠናቀቁ ወይም በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታቸውን ያቋረጡ መሆን አለባቸው። በተጨማሪም የሥራና ክህሎት መደብ ሥራ አስተዳደር ሥርዓት (LMIS ID)፣ ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) እና የወቅቱ የቀበሌ መታወቂያ ያላቸው፣ በምዝገባ ወቅትም ምንም ዓይነት ቋሚ ሥራ የሌላቸው መሆን እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።
ሥልጠናው በቅድመ-ሥልጠና እና በሥራ ላይ ልምድ መቅሰም በሁለት ዋና ዋና ደረጃዎች የተከፈለ ነው፦
🔑የቅድመ-ሥልጠና ደረጃ፦ ወጣቶች ለ12 ቀናት የሚቆይ የሕይወት ክህሎት (Life Skills) ሥልጠና የሚያገኙ ሲሆን፣ በዚህ ወቅት የትራንስፖርትና የሻይ-ቡና አበል ይከፈላቸዋል። በተጨማሪም በ3 ወር ጊዜ ውስጥ የሚሰጥ የ5 ቀናት መሠረታዊ የኮምፒውተር ሥልጠና ተዘጋጅቷል። ሥልጠናዎቹን ላጠናቀቁ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት (Certificate) ይሰጣቸዋል።
🔑የሥራ ላይ ልምድ እና የገንዘብ ድጋፍ፦ በተመረጡ ድርጅቶች ውስጥ ለ6 ወራት በሙሉ ጊዜ በሚደረግ የሥራ ልምድ ልምምድ ወቅት ለተሳታፊዎች በወር 3,278 ብር አበል ይከፈላል። ዕድሜያቸው 5 ዓመትና ከዚያ በታች የሆኑ ሕፃናት ያሏቸው ሴት ወጣቶች ደግሞ ተጨማሪ 945 ብር የሕፃናት ማቆያ ድጋፍ የሚያገኙ ይሆናል። የ6 ወሩን ልምድ ላጠናቀቁ ወጣቶችም ተጨማሪ የ3 ወር የሥራ ማካካሻ ክፍያ ተጨምሮ በድምሩ የ9 ወራት አበል ክፍያ እንደሚደረግ ተጠቅሷል።
አቶ ተገኝ አክለውም ቀደም ሲል ከልማት ፈንድና ከሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮጀክቶች ተጠቃሚ ያልሆኑ እና መስፈርቱን የሚያሟሉ የክፍለ ከተማው ወጣቶች፣ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎቻቸውን በመያዝ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ሥራና ክህሎት ጽሕፈት ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ እንደሚችሉ ጥሪ አቅርበዋል።

23/09/2026

አዲሱ መንግሥት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም ይመሰረታል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ መጠናቀቅን ተከትሎ መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን አስታውቀዋል፡፡

አፈ-ጉባኤው በመልዕክታቸው 42 የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ 10 ሺህ 438 ዕጩዎች እንዲሁም ከ54 ሚሊዮን በላይ መራጮች የተሳተፉበት 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊና ተዓማኒነት ባለው ሁኔታ በስኬት መጠናቀቁን አብራርተዋል፡፡

በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥልጣን አካል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መሆኑንና ተጠሪነቱም ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሆነ ያስታወሱት አፈ-ጉባኤው፤ የምክር ቤቱ የሥራ ዘመንም በመስከረም ወር የመጨረሻ ሳምንት ሰኞ እንደሚጀምር በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 2 መደንገጉን አንስተዋል፡፡

እንደዚሁም በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 56 መሠረት በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይም ጥምር ድርጅቶች የፌዴራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል እንደሚያደራጅና እንደሚመራ ጠቅሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት መስከረም 25 ቀን የመንግሥት ምሥረታ እና የምክር ቤቱ መክፈቻ ሥነ-ሥርዓት እንደሚከናወን ገልጸዋል፡፡

ለሥነ-ሥርዓቱ አስፈላጊው ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት አፈ-ጉባኤው፤ በሕዝብ የተመረጠው አዲሱ መንግሥት ቀጣዩን አምስት ዓመታት ሀገርና ሕዝብ የመምራት ኃላፊነት እንደሚረከብ አረጋግጠዋል፡፡

መጪው ዘመን የሰላም፣ የጤና፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የብልፅግና እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡

✨ በዓላቶቻችንን በሰላምና በአንድነት እናከብራለን! ✨የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የነጋዴው ማህበረሰብ ለኢሬቻና መስቀል ደመራ በዓላት ዝግጅት የምክክር መድረክ አካሄደ 🌼🕊️ቦሌ 14 ኮሙኒኬ...
20/09/2026

✨ በዓላቶቻችንን በሰላምና በአንድነት እናከብራለን! ✨

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የነጋዴው ማህበረሰብ ለኢሬቻና መስቀል ደመራ በዓላት ዝግጅት የምክክር መድረክ አካሄደ 🌼🕊️
ቦሌ 14 ኮሙኒኬሽን - መስከረም 10/2019

የቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር በመጪዎቹ የኢሬቻና የመስቀል ደመራ በዓላት አከባበር እንዲሁም በበዓላቱ ዝግጅት ላይ የነጋዴው ማህበረሰብ ሚና ምን መሆን እንዳለበት የሚያስረዳ የምክክር መድረክ አካሄደ።

🤝 በውይይቱ ላይ የክፍለ ከተማውና የወረዳው አመራሮች፣ የነጋዴው ማህበረሰብ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች ተገኝተዋል። 👥

በመድረኩ የቀረበው የመወያያ ሰነድ በዓላቱ በሰላም እንዲጠናቀቁና ህብረተሰቡን ባሳተፈ መልኩ እንዲከበሩ ነጋዴው ማህበረሰብ ሊጫወት የሚገባውን የጎላ ሚና በዝርዝር አብራርቷል።

📜 በወቅቱ የተላለፉ መልዕክቶችም በዓላቱ የህዝቦችን አንድነት እና አብሮነት የሚያጠናክሩ በመሆናቸው፣ ነጋዴው ማህበረሰብ የበዓላቱን ሰላማዊነት በመጠበቅ፣ ፍትሐዊ የንግድ አገልግሎት በመስጠት፣ አካባቢን በመንከባከብና እሴቶቻቸውን ለማስቀጠል ግንባር ቀደም መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። 🕊️💚

በተጨማሪም ነጋዴው ማህበረሰብ በበዓላት ወቅት የሚጠበቅበትን ማህበራዊና ህዝባዊ ኃላፊነት በላቀ የባለቤትነት ስሜት መወጣት እንዳለበት የተገለጸ ሲሆን፣ 👏 መድረኩ ነጋዴው ማህበረሰብ ለበዓላቱ ስኬታማ ዝግጅት የበኩሉን የጎላ አስተዋፅኦ እንዲያበረክት ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ በመግለጽ ውይይቱ ተጠናቋል።

Address

Around Gerji Police Station
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Bole Woreda 14 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Bole Woreda 14 Communication:

Shortcuts

Share