Gullele woreda 3 Communication

Gullele woreda 3 Communication ይህ የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የፌስ ቡክ ገፅ ነው
ፔጃችንን ፎሎው በማድረግ አዳዲስና ትኩስ መረጃዎችን ያግኙ!! ፔጃችንን ላይክ በማድረግ በወረዳችን የሚከናወኑትን አበይት ጉዳዮች መረጃ ያግኙ

04/06/2026
ጉለሌ የእንጦጦ የወንዝ ዳርቻ ልማት  ለቱሪዝም መስህብ የሆነና ዜጎችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ያደረገ ፤ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ፤አስደማሚ የእጅ አሻራዎች የስራ ውጤት የሆነውን የል...
04/06/2026

ጉለሌ የእንጦጦ የወንዝ ዳርቻ ልማት ለቱሪዝም መስህብ የሆነና ዜጎችን በስራ ዕድል ፈጠራ ተጠቃሚ ያደረገ ፤ለነዋሪዎች ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ፤አስደማሚ የእጅ አሻራዎች የስራ ውጤት የሆነውን የልማት ፕሮጀክችት ይጎብኙ!!

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑ...
03/06/2026

የቀድሞ የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እና የስራ ባልደረቦችን በማግኘቴ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። የተከበሩ ኡሁሩ ኬንያታ የሚመሩትና 73 አባላት የያዘውን የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ልዑክ፤ ለዲሞክራሲ ግንባታ ሂደታችን ላበረከቱት አገልግሎትና አስተዋጽኦ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

‎ዲሞክራሲያዊ ሂደቶች ከአኅጉራችን ነባራዊ ሁኔታና ተሞክሮ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ለማድረግ አፍሪካዊ ተቋማት ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ። የምርጫ ሂደታችንን ለመደገፍ በመላው ሀገሪቱ ታዛቢዎችን በማሰማራት የምርጫ ታዛቢ ልዑኩ ላደረገው ያልተቆጠበ ጥረት እውቅና እና አድናቆት እየሰጠን፣ የምልከታውን የተሟላ ውጤት እንጠብቃለን።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ

03/06/2026
የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁየአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡ምርጫውን አ...
03/06/2026

የአውሮፓ ኅብረትና አጋር ሀገራት የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሒደት አደነቁ

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም የተካሄደውን 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አድንቋል፡፡

ምርጫውን አስመልክቶ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ሀገራቱ በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና እንደሚሰጡም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ  ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው! የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ...
02/06/2026

7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሕዝቡ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው!

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ መራጩ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነትና ፍላጎት በተግባር ያረጋገጠበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።

ምክር ቤቱ የ7ኛው ሃገራዊ ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት መጠናቀቁን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ማሩ ጃኔ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፤ ምርጫው ግልጽነት እና ፍትሐዊነት ከመላበሱም ባሻገር በመራጩ የከተማዋ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን በተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቅቡልነት ያሳየ ነው።

ምክር ቤቱ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት ለምርጫው ስኬታማነት መሥራቱን አስታውሰው፤ ይህም ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አብራርተዋል።

የምርጫ ሂደቱም እጅግ የተረጋጋ፣ የሰለጠነ እና የዴምክራሲ ሥርዓት ትግበራ ሂደትን ያጠናከረ ሆኖ ማለፉንም ጠቅሰዋል።

መገናኛ ብዙሃንም ለፓርቲዎች የሰጡት የአየር ሰዓት ፍትሐዊ፣ ግልጽና ለሁሉም ፓርቲዎች እኩል የመወዳደሪያ ሜዳ የሰጠ ነው ያሉት አቶ ማሩ፤ ይህም እያንዳንዱ የፖለቲካ ፓርቲ ያሉትን የፖሊሲ አማራጭ ሀሳቦች ያለምንም ገደብና ጫና ለሕዝቡ የሚያቀርብበት ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል።

የጸጥታ አካላትም ያለምንም ወገኝተኝነት ፍጹም ገለልተኛ በሆነና ሙያዊ አካሄዶችን በተከተለ መንገድ የአዲስ አበባ ምርጫ ጣቢያዎችንና የመራጩን ሕዝብ ደህንነት ሲጠብቁ መዋላቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢው፤ የጸጥታ አካላት ያከናወኑት ተግባር ሊመሰገን የሚገባው ነው ብለዋል።

የድምጽ ቆጠራውና ውጤቱን የማደራጀት ሥራ የሚያከናወነው በሕጉ መሰረት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በመሆኑም ውጤቱ በከተማ ደረጃ በኦፊሴላዊ መልኩ እስኪገለጽ ድረስ በትዕግስት እንዲጠበቅ ምክር ቤቱ ጥሪውን ያቀርባል ነው ያሉት።

ማንኛውም ወገን የምርጫ ውጤቱን በጸጋ የመቀበል ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ እንዳለበት አመልክተው፤ ቅሬታዎች ቢኖሩ እንኳን በሕጋዊ እና በሰላማዊ መንገድ ማቅረብ እንደሚገባ አሳስበዋል።

የአዲስ አበባ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ አቶ ዘሪሁን ኮርሜ በበኩላቸው፤ በምርጫው አረጋዊያን፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ያሳዩት ተሳትፎ እና ቁርጠኝነት ተምሳሌታዊ መሆኑን ተናግረዋል።

ለምርጫው ስኬት አስተዋጽኦ ላደረገው መራጩ ሕዝብ፣ ለምርጫ ቦርድ፣ የከተማዋ የጸጥታ አካላት ጨምሮ አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።

የምርጫ ውጤቱ ምንም ይሁን ምን የሕዝብ ድምጽ ልናከብር ይገባል ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ የሰለጠነና ብስለት የተሞላበት የፖለቲካ አካሄድም ይሄው መንገድ ነው ብለዋል።

!

ዛሬ የተመረቀው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት (በምሥል)
02/06/2026

ዛሬ የተመረቀው ከእንጦጦ እስከ ቀጨኔ መድኃኔዓለም ያለው የመልሶ ማልማት እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክት (በምሥል)

02/06/2026

ማየት ማመን ነው_መጥታቹ እዩ።

Address

Haile Melekot Street
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Gullele woreda 3 Communication posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Gullele woreda 3 Communication:

Share