05/06/2026
ኢትዮጵያ አሸንፋለች በሕዝብ ድምፅ፣ በሰላም ጉዞ !
የኢትዮጵያ ሕዝብ የወደፊት ዕድሉን በገዛ እጁ ለመወሰን፣በሙሉ ነፃነት ወደ ምርጫ ጣቢያዎች በመትመም ታሪካዊ የምርጫ ሂደትን አካሂደዋል። ይህ 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ውድድር ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ የዲሞክራሲ ብስለቱንና ለሀገር ግንባታ ያለውን ጽኑ ፍላጎት ለአለም ያሳየበት ታላቅ መድረክ ሆኗል።
በሀገሪቷ ክፍል ዜጎች በሰላማዊ ሰልፍና በታላቅ ትዕግስት ተሰልፈው የሰጡት ድምፅ የሀገሪቱን የሥልጣን ምንጭ ሕዝብ መሆኑን በይፋ አረጋግጧል።የምርጫው ሂደት የተለያዩ የፖለቲካ ራዕዮች በነፃነት የተንፀባረቁበት፣ የሀሳብ ብዝሃነት የተከበረበት እና ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ የተረጋገጠበት በመሆኑ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ባህልን በሀገሪቱ ላይ ጥሏል።
ሂደቱ ምንም ዓይነት የጸጥታ ስጋት ሳይኖርበት፣ በሰላማዊና በሰለጠነ መንገድ መከናወኑ የሕዝባችንን አርቆ አሳቢነት እና ለሀገራዊ መረጋጋት የሰጠውን ከፍተኛ ዋጋ ያሳያል።
ይህ ምርጫ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብና ዲሞክራሲ በጋራ ያሸነፉበት ታሪካዊ ምዕራፍ ነው። ኢትዮጵያ መርጣለች፤ ምርጫዋም ሰላም፣ ልማት እና የተባበረች ጠንካራ ሀገር መገንባት ነው።
#ምርጫ