Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና

Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥነ-ምግባርና ፀረ - ሙስና ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዋጅ ቁጥር 75/2014 የተቋቋመ ነው።
(1)

03/06/2026

የአዲስ አበባ ፀረ ሙስና ኮሚሽን የፖሊሶች ስልጠና

01/06/2026
28/05/2026
በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያኮሚሽኑ ከስር በተጠቀሰው የስራ መደብ ላይ አመልካቾችንን በኮንትራት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ጀ...
21/05/2026

በድጋሚ የወጣ የስራ ማስታወቂያ

ኮሚሽኑ ከስር በተጠቀሰው የስራ መደብ ላይ አመልካቾችንን በኮንትራት አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በመሆኑን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ግንቦት 12/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የስራ ቀናት መመዝገብ ትችላላችሁ።

21/05/2026
08/05/2026

በወንጀል ተፈላጊዎች

እነዚህ በፎቶ ላይ የምትመለከቷቸው ግለሰቦች በከባድ የሙስና ወንጀል ይፈለጋሉ፡፡

ስለሆነም ሕብረተሰቡ ተፈላጊዎቹን የሚመለከት ማንኛውም መረጃ ካለው እንዲያሳውቅ የፌደራል ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡

እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነ...
05/05/2026

እንኳን ለ85ኛው የጀግኖች አርበኞች በዓል አደረሳችሁ

ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች አርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ሙሉ በሙሉ ያስከበሩበት በዓል ነው።

አርበኝነት ማለት ለሀገር ያለ ዋጋ የሚከፈል ከራስ ወዳድነት የነጻ መሥዋዕትነት ነው። ዓላማውም ሀገርንና ሕዝብን ብቻ ማዕከል ያደረገ ነው። ለግል ወይም ለቡድን በተለየ የሚገኝ ነገር የለውም። ለሀገር ከሚገኘው ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ከሚደርስ የዜጋ ድርሻ በቀር።

እናትና አባት አርበኞች ከፋሺስት ጋር የተዋጉት ለሀገር እና ለወገን ብለው ነው። በግል ጥቅም ለማግኘትማ ከአርበኝነት ይልቅ ባንዳነት አቋራጭ ነበር። ግን አላደረጉትም።

የአርበኝነት ትግሉ ከሦስት ጠላቶች ጋር የተደረገ ነበር። ከራስ ፍላጎት፣ ከባንዳና ከወራሪ ፋሺስት ጋር። አርበኝነት የራስን ጥቅም ለሀገር ጥቅም ሲባል መተው ነው። አርበኝነት የግል ክብርን፣ የግል ሥልጣንን እና የግል ጥቅምን መሠዋት ነው። ይሄንን ለመቀበል ከጠላት በፊት ራስን ማሸነፍ ይጠይቃል።

ባንዳዎች ማለት ራሳቸውን ማሸነፍ ያቃታቸው ናቸው። የግል ጥቅምንና ክብርን ማሸነፍ ሲያቅታቸው የሀገራቸውን ክብርና ጥቅም ይሸጣሉ። ባንዳነት ማለት ሀገርን ለራስ ጥቅም በመሸጥ የሚከናነቡት የውርደት ካባ ነው። አርበኞች ከባንዳዎች ጋር ታግለዋል። ባንዳዎች በአንድ በኩል ሀገራችሁን ሽጣችሁ እንደኛ በግል ተጠቀሙ ይሏቸዋል። በሌላ በኩል መንገድ እየመሩ ወራሪውን ያመጡባቸዋል። ያም አልሆን ሲላቸው ሕዝቡን በሐሰተኛ ወሬ ልቡን ይሰልቡባቸዋል።

ዛሬም ሦስቱም ጠላቶች አሉ። መልክና ስም ብቻ ቀይረዋል። በሌላም በኩል ዛሬም በየመስኩ የተሠማሩ ኢትዮጵያውያን አርበኞች አሉ።

የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ብሔራዊ አርበኞችን ይፈልጋል። የራስ ፍላጎትን፣ ባንዳነትን እና ወራሪን እምቢ የሚል አርበኝነት።

የኢንዱስትሪ አርበኞች፣ የግብርና አርበኞች፣ የጸጥታ አርበኞች፣ የፖለቲካ አርበኞች፣ የንግድ አርበኞች፣ የዲፕሎማሲ አርበኞች፣ የመንግሥት አገልጋይ አርበኞች፣ የሕክምና አርበኞች፣ የትምህርት አርበኞች፣ ወዘተ. ያስፈልጉናል።

ይሄንን በዓል የምናከብረው የየራሳችንን የአርበኝነት ደረጃ በመገምገም ነው። ለኢትዮጵያ ምን ያህል አርበኞች ነን?

ዛሬም የግል ፍላጎት የሚያሸንፋቸው ደካሞች አሉ። ሀገርን አፍርሰው የግል ቤት መሥራት የሚመኙ። ትልቁን መርከብ አፍርሰው ትንንሽ ታንኳዎችን ለመሸጥ የሚመኙ። ለቅንጥብጣቢ ነገር ውርደትን ለመሸከም የማይሰቀቁ።

ዛሬም ወራሪዎች አሉ። በአካል ሀገርን ለመውረር ካሰፈሰፉት በተጨማሪ ድህነት፣ ኋላቀርነትና ሌብነት የሚባሉ እንደ ሰርዶ ሀገርን ወርረው ሽባ የሚያደርጉ ጠላቶች አሉ። ሀገርን ለባዳ ከሚሸጡት ባንዳዎች እኩል፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለግል ጥቅማቸው ሲሉ የሚሸጡ ባንዳዎች አሉ። አገልግሎትንና የሕዝብን ሀብት የሚሸቅጡ ባንዳዎች አሉ።

ብሔራዊ አርበኝነት ማለት እነዚህን ሦስት ጠላቶች ታግሎ ማሸነፍ ማለት ነው። ዛሬ የምናየውን የኢትዮጵያ ለውጥና ዕድገት ማስመዝገብ የተቻለው ብሔራዊ አርበኞች በየአካባቢው በመኖራቸው ነው። ብሔራዊ አርበኞች ሦስቱን ጠላቶች እያሸነፉ ቢሆንም ገና ሙሉ በሙሉ ድልን አልተቀዳጁም።
ድሉ እንደ ሚያዝያ 27 የሚታወጀው ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ተምሳሌትስትሆን ነው። ኢትዮጵያ በዓለም ደረጃ ከሚገኙ ኃያል ሀገሮች አንዷ ስትሆን ነው።

ይሄንን ድል እውን ለማድረግ ኢትዮጵያን የሚወዱ የኢትዮጵያ አርበኞች ሁሉ እንዲነሡ በዚህ አጋጣሚ ጥሪ አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!
ፈጣሪ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿን ይባርክ!
ሚያዝያ 27፣ 2018 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

01/05/2026

Address

Addis Ababa

Telephone

+251948747575

Website

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Contact The Organization

Send a message to Addis Ababa Ethics and Anti-Corruption -ፀረ ሙስና:

Share