07/06/2020
# ሳትነቃ
እኔ የዋህ አንተ በዳይ ፣
አውቀህ አጥፊ ሁሌ አታላይ፣
እኔ አወጋሽ አንተ ወቃሽ፣
ባመንኩህ ልክ የምትዋሽ፣
እኔ ከፍቶኝ አንተ ሳቂ ፣
ልቅረብህ ስል ደርሶ ራቂ፣
እኔ ፍቅር አንተ ፀብ ፀብ፣
አብሮነትን የምታጠብ••
እኔ መውደድ አንተ መጥላት፣
የሚቀልህ አጉል መኩራት••
እኔ ናፍቆት አንተ ኩርፊያ
ልዩነቶች
አንዱ አንደ ዶፍ ሌላው ካፊያ፣
ሁነን ኗሪ ብንከርምም
እየቻልኩህ እንደምንም
አልገባህ ሲል ሴትነቴ
•• አለቀና ያ ትግስቴ ••
ሳልነግርህ ሄድኩ ይሄው በቃ
እንደተኛህ ሳትነቃ •••