25/06/2026
ህዝባችን ምንም ያህል ጫና፣ ሐሰተኛ ወሬ ቢናፈስም፥ ይሄን ሁሉ ሳይበግረው ምርጫው፥ ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሐዊ እና ሰላማዊ ኾኖ እንዲያልፍ ደማቅ የታሪክ ዕጥፋት እንዲፃፍ ላበረከተው አስተዋፅኦ ከልብ እናመሰግናለን።
ህብረተሰቡ በምርጫው ዕለት በከፍተኛ የዲሲፕሊንና የሰላም ስሜት ወጥቶ ድምጹን በመስጠት ለፓርቲው የሰጠው አደራ እና አመኔታ፤ በቀጣይ የተጀመሩ የልማትና የብልጽግና ጉዞዎችን ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ አቅምና ስንቅ እንደሚሆን ይሆናል።ፓርቲው ህዝብ የጣለበትን ታላቅ ኃላፊነት መሰረት በማድረግ የመረጠውን ህዝብ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ሌሊትና ቀን እንደሚሰራ በድጋሚ ቃሉን አድሷል።
የከተማችን ኗሪዎች ከሌሊቱ 9:00 ሰዓት እስከ ቀጣዩ ሌሊት 9:00 ሰዓት ሳይታክት ይሆነኛል የሚለውን ፓርቲ መርጧል። የመረጠው ፓርቲም ብልፅግና ኾኗል። ስለኾነም፣ የሰጠንን አደራ ሳንሸራርፍ አልቀን እንደምንፈፅም እየገለፅን ፣ ህዝባችን በድምፁ ያሳየውን የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አስቀጥለን፣ ሰላማችን አፅንተን ከህዝባችን ጋር ኾነን የጀመርነውን ሁለንተናዊ የልማት ጥረት እንደምናስቀጥል እያረጋገጥን፤ ህዝባችን ለሰጠን አደራ እና እምነት ከልብ እናመሰግናለን።
የካ ወረዳ 09 ኮሙኒኬሽን ሰኔ 18/2018