03/06/2026
የአገልግሎት ጥራትን ለማረጋገጥና ተቋማዊ አሰራርን ለማዘመን የሚረዳ የISO (QMS) ስልጠና ለኮሚሽኑ ዳሬክተሮች፣ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሰጠ።
የአዲስ አበባ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማሳደግና የአሰራር ስርዓቱን ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ያለመ የISO 9001:2015 የጥራት አስተዳደር ስርዓት (Quality Management System - QMS) ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል።
በዚህ ስልጠና ላይ የኮሚሽኑ ዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች እንዲሁም የዘርፉ ባለሙያዎች በንቃት ተሳትፈዋል።
የኮሚሽኑን የዕለት ተዕለት የሥራ እንቅስቃሴዎችና የአደጋ መከላከል/መቆጣጠር ስራዎችን ከዓለም አቀፍ የጥራት መመዘኛዎች (ISO Standards) ጋር ማጣጣም።
የአመራሩን የውሳኔ አሰጣጥ እና የባለሙያዎችን የክህሎት ደረጃ በማሳደግ፣ የህዝብን እርካታ ማረጋገጥ።
ቀጣይነት ያለው መሻሻል (Continual Improvement)፦ በተቋሙ ውስጥ ያሉ የአሰራር ክፍተቶችን በየጊዜው እየገመገሙ ስራዎችን በቴክኖሎጂና በዘመናዊ አሰራር መምራት ያለመ ስልጠና ነው።
ሥልጠናው ለተከታታይ ቀናት በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ የሚሰጥ ሲሆን፣ ይህ የጥራት አስተዳደር ስርዓት (QMS) ትግበራ ኮሚሽኑ ወደ ላቀ ስኬትና ዓለም አቀፋዊ እውቅና ለመሸጋገር ለጀመረው ጉዞ ትልቅ እምርታ እንደሚሆን ይታመናል።