Lideta sub-city land development adminstration office

Lideta sub-city land development adminstration office Welcome to our site

17/05/2023
ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እናመስግናለን!!!የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት
03/11/2022

ለከፈላችሁት መስዋዕትነት እናመስግናለን!!!
የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት

16/10/2022

እንኳን ደስ አላቹህ!!

የልደታ ክ/ከተማ አስተዳደር በ2014 በጀት ዓመት በከተማ አስተዳደሩ በተደረገ ምዘና ከ11ዱ ክ/ከተሞች 3ኛ ሆኗል።

በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና ወቅታዊ ጉዳዮች ውጤታማ እንደነበሩ ከተመዘገበው ውጤት መገንዘብ ይቻላል።

ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ስትተጉ ለነበራቹህ ሁሉ እንኳን ደስ አላቹህ

10/09/2022

ጳጉሜን 5 የአንድነት ቀን!!
ማህጸነ ለምለሟ ኢትዮጵያ ጥንካሬዋ አንድነቷ፤ ውበትዋ ደግሞ ብዝሃነቷ እንደሆነ አያጠያይቅም። እኛ ኢትዮጵያውያን ብዙ ህዝብ የሆንን ግን ደግሞ አንድ ሆነን የምንኖር ህዝቦች ነን፡፡
አንድነትና የባለቤትነት ስሜት የሚንፀባርቅበት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በእምነትም ሆነ በብሄር ያለ አንዳች ልዩነት በእኩልነት ለእናት ሃገር በጽኑ እምነት በልብ ትስስር የቆምን ነን፡፡
ድሎቻችን የአንድነታችን ውጤት ናቸው፡፡ ስለ ኢትዮጵያ እልፍ አእላፋት ደማቸውን አፍስሰው አጥንታቸውን ከስክሰው ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን ማንም ከማይደርሰዉ ማማ ላይ በመስቀል ከዘመን ዘመን እንዲሻገር ያደረጉት ቀደምት አባቶቻቸን ሲሆኑ፤ እኛ ዛሬ ባላደራ ሆነን ለቀጣዩ ትውልድ አንድነታችንን ጠብቀን ማሻገር ሃላፊነትም ግዴታም አለብን፡፡
የተስፋ የልምላሜ የአይበገሬነት እንዲሁም የአሸናፊነትን ፀዳል በማንገብ ፅዋው ከትውልድ ትውልድ እየተወራረሰ ይጓዛል። በአባቶቻችን ተጋድሎ የተገነባች ኢትዮጲያን በጽኑ አንድነት እናስቀጥላለን፡፡

በብዝሃነት የታጀበ አንድነት ለጠንካራ ሀገር ግንባታ መሰረት ነው፡፡
ኢትዮጵያ በአንድነት መከላከያ ውስጥ ትገኛለች ። መከላከያችን የአንድነታችን ምልክት አርማ ነው፡፡ የማሸነፋችን ሚስጢር ደግሞ በአንድነት መቆማችን ነው፡፡ ሁሌም ከመከላከያችን ጎን ነን፡፡በፅኑ አንድነት የኢትዮጵያን ብልፅግና እናረጋግጣለን!

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ጳጉሜ 1 የበጎ ፍቃድ ቀንን አስመልክቶ ቁጥራቸው ከ200 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷልበማዕድ ማጋ...
06/09/2022

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ጳጉሜ 1 የበጎ ፍቃድ ቀንን አስመልክቶ ቁጥራቸው ከ200 በላይ ለሚሆኑ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና ለአቅመ ደካሞች ማዕድ አጋርቷል
በማዕድ ማጋራቱ ላይ የተገኙት የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሀይሉ ሉሌ እንደተናገሩት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ዜጎችን መደገፍና ማገዝ ከሁሉም ዜጋ ይጠበቃል ብለው የዛሬውን ድጋፍ ላደረጉ የመሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት አመራሮች እና ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በበኩላቸው እኛ ኢትዮጲያዊያን የምንታወቅበት በመደጋገፍና በመረዳዳት ባህላችን ነው በማለት ይህን የተቀደሰ በጎ ተግባር የጽ/ቤቱ አመራሮች እና ሰራተኞች ካላቸው ላይ ቀንሰው በማዋጣት ይህን ፕሮግራም እንዳዘጋጁ ገልፀዋል

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኞች እና አመራሮች ጳጉሜ 1 የበጎ ፍቃድ ቀንን ምክኒያት በማድረግ ዛሬ ለ200 የጎዳና ተዳዳሪዎች እና አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ ያ...
06/09/2022

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት ሰራተኞች እና አመራሮች ጳጉሜ 1 የበጎ ፍቃድ ቀንን ምክኒያት በማድረግ ዛሬ ለ200 የጎዳና ተዳዳሪዎች እና አቅመ ደካሞች የምሳ ግብዣ ያዘጋጀን በመሆኑ እንድትገኙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል

ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ  ቀን ምክኒያት በማድረግ የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት  200 በጎችን በስፖንሰር በማሰብባሰብ ለልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል
04/09/2022

ጳጉሜ 1 የበጎ ፈቃድ ቀን ምክኒያት በማድረግ የልደታ ክ/ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ጽ/ቤት
200 በጎችን በስፖንሰር በማሰብባሰብ ለልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር አስረክቧል

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስትዳደር ጽ/ቤት በ2014 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማት እና ባለሞያዎች እውቅና ሰጠብእውቅና ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙትም የልደታ ክፍለ...
25/08/2022

የልደታ ክፍለ ከተማ መሬት ልማትና አስትዳደር ጽ/ቤት በ2014 በጀት ዓመት ውጤታማ አፈፃፀም ለነበራቸው ተቋማት እና ባለሞያዎች እውቅና ሰጠ
ብእውቅና ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙትም የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አሰግደው ኃ/ ጊዮርጊስ እንደተናገሩት በ2014 በጀት ዓመት በመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የነበረው የሌብነትና ብልሹ አሰራር እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በተሰራው ስራ የተገልጋዮችን ቅሬታ በእጅጉ መቀነስ ተችሏል ብለዋል በበጀት ዓመቱ ለተመዘገበው ውጤት የመሬት ልማትና አስትዳደር ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች የነበራችሁ ሚና የጎላ ነበር ብለዋል ስለሆነም በቀጣይ በጀት ዓመትም የተሻለ ስራ በመስራት ጥሩ ውጤት እንድታመጡ የክፍለ ከተማው አስተዳደር ለጽ/ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል
የጽ/ቤቱ ኃላፊ ወ/ሮ ዚያዳ ሻሚል በበኩላቸው በ2014 በጀት ዓመት የተቋማችን አገልግሎት አሰጣጥ በማሻሻል የተገልጋዮቻችንን እርካታ ማረጋገጥ ችለናል ብለዋል እንዲሁም ሌብነትና ብልሹ አሰራር በመታገል ረገድ ከፍተኛ ስራ መሰራቱንም አክለው ወ/ሮ ዚያዳ ገልፀዋል
በመጨረሻም ውጤታማ የስራ አፈፃፀም ላመጡ ባለሞያዎች እንዲሁም ለተቋሙ ስኬታማነት ልዩ አስተዋዕፆ ላበረከቱ አካላት እውቅና እና ሽልማት ተሰጥቷል

19/08/2022

በክ/ከተማው የሚገኙ ጽ/ቤቶች #የአቻ ሰራተኞች ፎረምን በሳምንት አንድ ጊዜ ማካሄድ እንዳለባቸው የልደታ ክ/ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት ገለፀ።

የጽ/ቤቱ ኃላፊ ዶ/ር ጥበቡ ደጀኔ በሰጡት መግለጫ ከዚህ በፊት ሞርኒግ ብሪፊንግ ተብሎ በየቀኑ በቡድን ይካሄድ የነበረው የሰራተኞች ውይይት ስያሜው፣ አደረጃጀቱና አሰራሩ ተለውጦ የአቻ ሰራተኞች ፎረም በሚል በሳምንት አንድ ቀን ብቻ እንደሚካሄድ ገልፀዋል።

ውይይቱ የሰራተኞችን አቅም በማቀራረብ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማሻሻልና የህ/ሰቡን እርካታ ለማረጋገጥ ያስችላል ያሉት ዶ/ር ጥበቡ ተቋማት ውይይቱን ለአገልግሎት አሰጣጥ ምቹ በሆነ ቀንና ስዓት ችግር ሊፈታና ለውጥ ሊያመጣ በሚች ሁኔታ ማካሄድ ይኖርባቸዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የውይይቱ አጀንዳዎች በየሳምንቱ የተከናወኑ ተግባራት፣ የአገልግሎት አሰጣጥ ፣ ስታንዳርድ፣ ራስን የማብቃት እቅድ አፈፃፀሞችና ሌሎች ከስራ ጋር የሚያያዙ ወቅታዊ ጉዳዮች ይሆናሉ ሲሉ ኃላፊው ገልፀዋል።

ሌሎች የሪፎርም ስራዎች በነበሩበት እንደሚቀጥሉም ተገልጿል።

Address

Around Lideta Ferde Bet
Addis Ababa
1234

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Lideta sub-city land development adminstration office posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share