30/10/2025
የፕሮዳክሽን ስራዎችን ጥራት በማሳደግና አዳዲስ ሀሳቦችን በመጨመር የመረጃ ተደራሽነትን ለማስፋት ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ።
*******
ጥቅምት 20/2018 ዓ.ም
በዛሬው እለትም ለዚሁ ስራ ግብአት ይሆን ዘንድ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት የተገነባውንና ሙሉ ግብአት የተሟላለትን ዘመናዊ የብሮድካስት ስቱዲዮ በቦታው በመገኘት የፅህፈት ቤቱ የዘርፉ ባለሙያዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በዘርፉ ከሚገኙ ተቋማት ጋር የጉብኝትና የልምድ ልውውጥ ማድረግ ለተቋም ስራዎች ውጤታማነት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የገለፀው ተሞክሮ ወሳጁ ጽህፈት ቤት በልምድ ልውውጡ የስቱዲዮ ግንባታ ፕሮጀክት ስራና ተያያዥ ስራዎችን ምልከታና የልምድ ልውውጥ እንደተደረገ ገልጿል፡፡
የጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽ/ቤት ሀላፊ ወ/ሮ ሠርካለም ተፈሪ እንደተናገሩት አቻ ተቋማት የልምድ ልውውጥ በማድረግ አንዱ ላይ ያለውን የተሻለ ስራ ለሌላው በማካፈል ለነዋሪው ማህበረሰብ ጥራት ያለው መረጃ በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተቋሙን አላማ ከግብ ማድረስ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ቂርቆስ ክፍለ ከተማ የከተማዋ እምብርት ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ያንን የሚመጥን ዘመናዊ ሁለገብ ስቱዲዮ እንዲኖራትና ጥራት ያለው አጫጭር ፕሮግራሞችን፣ ቶክ ሾዎችን፣ የገፅ ለገፅ ውይይቶችን፣ የክፍለ ከተማውን እለታዊ ዘገባዎችን፣ የፕሮዳክሽን ዜናዎችን፣ በጥራት ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው፤ ያንን ወደ ተግባር ለመለወጥ የሚረዳ ሀሳብና መሬት የነካ፤ ዘመኑን የዋጀ የፕሮዳክሽን መተግበሪያ ሁለገብ ብሮድካስት ስቱዲዮ ከነሙሉ ግብአቱ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ተመልክተናል፤ ያንን ተሞክሮ በመውሰድ በክፍለከተማው እንዲኖር ጥረት ይደረጋል ሲሉ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተናግረዋል፡፡