Ethiopian Meteorology Institute

Ethiopian Meteorology Institute Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Ethiopian Meteorology Institute, Public & Government Service, Addis Ababa.

By collecting analyzing and studying data of atmospheric air, We provide weather forecast and early warnings on the adverse effects of weather and climate of Ethiopia.

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ//////////በሚቀትሉት የጁን የመጀመሪ...
31/05/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በውሃ ዘርፍ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
//////////
በሚቀትሉት የጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ከቀላል እስከ ከባድ መጠን ያለው የገጸምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። በመሆኑም ከሚጠበቀው የአየር ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የውሃ ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳብ ከወዲሁ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርናው ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ///////////  በሚቀጥ...
31/05/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እስከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ በግብርናው ሥራ እንቅስቃሴ ላይ ሊያሳድር የሚችለው ተፅዕኖ
///////////
በሚቀጥሉት የጁን ወር የመጀመሪያዉ አስር ቀናት ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው እርጥበት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛዉ የመኸር ሰብል አብቃይና የበልግ ሰብል ተጠቃሚ በሆኑት አካባቢዎች ላይ እንደሚያገኙ ይጠበቃል። በመሆኑም የሚኖሩ መልካም አጋጣሚዎችን ለመጠቀምና የሚጠበቁ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመቀነስ ከታች የቀረቡትን ቦታ ተኮር የግብርና ሚቲዎሮሎጂ ምክረ ሀሳብ ከወዲሁ ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

31/05/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 11 እስከ 20/2026 (ሰኔ 4 እስከ ሰኔ 13/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
////////
በመጪዎቹ የጁን ሁለተኛዉ አስር ቀናት ዝናብ ሰጭ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ የዝናብ መጠንና ሥርጭት እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄድ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ ፡፡

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ//////////////////በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር...
31/05/2026

እ.ኤ.አ ከጁን 1 እስከ 10/2026 (ግንቦት 24 እሰከ ሰኔ 3/2018 ዓ.ም) የሚኖረው የአየር ሁኔታ አዝማሚያ
//////////////////
በጁን የመጀመሪያዎቹ አስር ቀናት ለዝናብ መፈጠር አስዋጽኦ የሚያደርጉ የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች በተለይም በምዕራብ አጋማሽ የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ የተሻለ ጥንካሬ እንደሚኖራቸው የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ከዚሁ ጋር በተያያዘም እርጥበታማው የአየር ሁኔታ ከቀን ወደ ቀን በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብና በሰሜን ምዕራብ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በመጠንም ሆነ በሥርጭት እየተስፋፋ ከመሄዱ ጋር ተያይዞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸዉ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡
በሚቀጥሉት ቀናቶች ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ አካባቢዎች እና የደቡብ እና የደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ቦታዎቻቸውን የሚሸፍን ከቀላል እስከ ከባድ (ከ1-30 ሚ.ሜ) መጠን ያለው ዝናብ ያገኛሉ፡፡ በተጨማሪም አልፎ አልፎ በውሃ አካላትና በከባቢ አየር ውስጥ ከሚጠናከሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብ ምዕራብ፣ በምዕራብ እና በመካከለኛወ የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ በ24 ሠዓት ውስጥ ከ30 ሚ.ሜ በላይ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚያገኙ አሃዛዊ የትንበያ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በጁን የመጀመሪያው አስር ቀናት ከሚኖረው ከፍተኛ የፀሐይ ሀይል ጋር በተያያዘ በተለይም የቀኑ ከፍተኛ ሙቀት በአፋር ክልል፣ በሰሜንና በደቡም ምዕራብ የሀገሪቱ ሥፍራዎች ሊይ ከ32 እስከ 40 ዲግሪ ሴልሺየስ በላይ እንደሚሆን አሃዛዊ ትንበያዎች ያመላክታሉ፡፡

30/05/2026
30/05/2026

በሚቀጥሉት ቀናቶች የሚኖረው የአየር ሁኔታ ትንበያ

መልካም በዓል
26/05/2026

መልካም በዓል

Address

Addis Ababa

Opening Hours

Monday 08:30 - 05:30
Tuesday 08:30 - 05:30
Wednesday 08:30 - 05:30
Thursday 08:30 - 05:30
Friday 08:30 - 05:30

Telephone

+251116635191

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian Meteorology Institute posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Share